Saturday, March 19, 2016

አይን ያወጣ ዝርፊያ



source :- Addis Admass



  • ሥራ አስኪያጁ በልጃቸው ሕክምና ስም የሚያሰባስቡት ገንዘብ ተቃውሞ ገጠመው

      በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያበሚል ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ እንዳሉ የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ ከእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ግማሽ ሚሊዮን ብር በርዳታ እንዲሰጣቸው መወሰኑን የተቃወሙት የገዳሙ ሒሳብ ሹም ከሥራና ከደመወዝ መታገዳቸውን ገልጸዋል፡፡


ሥራ አስኪያጁ ሕመምተኛ ልጃቸውን በውጭ ሀገር ለማሳከም ይችሉ ዘንድ፣ ከሀገረ ስብከቱ የገዳማትና አድባራት ሓላፊዎች ተውጣጥተው በክፍላተ ከተማ በተዋቀሩ ኮሚቴዎች 2 . ብር ያላነሰ ገንዘብ መሰብሰቡን የጠቀሱት ምንጮች፤ አገልጋዮች በየግላቸው የገንዘብ ርዳታ እንዲያበረክቱ ከመጠየቅ ውጭ የአብያተ ክርስቲያናቱ ገንዘብ ለድጋፉ ወጪ መደረጉ አግባብነት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡ድጋፉ በሥራ አስኪያጁ ዕውቅና የሚደረግ ከመኾኑ አንጻር ባለው ተጨባጭ ኹኔታ ከተጽዕኖ የጸዳና በበጎ ፈቃድ ብቻ የሚደረግ ነው ለማለት እንቸገራለንያሉት ምንጮቹ፣ በጉዳዩ ላይ ተቃውሞን ማሰማት፣ ከሥራ አላግባብ መታገድንና መዛወርን ጨምሮ በተለያዩ ሰበቦች ሽፋን ለጉዳት ሊዳርገን ይችላል ብለው እንደሚሰጉ ያስረዳሉ፡፡

ለዚህም፣ በእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ሒሳብ ሹም ላይ ባለፈው ሰኞ የተወሰደውን ከሥራና ከደመወዝ የማገድ ርምጃ የጠቀሱት ምንጮች፤ ውሳኔውም በሌላ ሰበብ ሽፋን መተላለፉን ጠቁመዋል፡፡

ሒሳብ ሹሟ እማሆይ ዐጸደ ማርያም ማሞ፣ ቀድሞ ከሚሠሩበት ቤቴል ቅዱስ ሚካኤል ወደ ገዳሙ ተዘዋውረው የመጡት፣ የሀገረ ስብከቱ /ቤት ባለፈው ኅዳር ወር ከደርዘን በሚልቁ የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሠራተኞች ላይ የሥራ ዝውውር ባደረገበት ወቅት ነው፡፡ በወቅቱ ገዳሙ፣ሕገ ደንባችን አይፈቅድምበሚል ምደባቸውን ቢቃወምም ይህንኑ ቅሬታ በውስጡ እንደያዘ ተቀብሏቸው እንደነበር ይገልጻል፡፡ እማሆይ ዐጸደም ላለፉት አራት ወራት የገዳሙ ሒሳብ ሹም ኾነው ሥራቸውን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡ ከመጋቢት 5 ቀን ጀምሮ ግን ከሥራና ከደመወዝ መታገዳቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ባለፈው ሰኞ ከገዳሙ /ቤት ደርሷቸዋል፡፡

ገዳሙ የሒሳብ ሹሟን ምደባ የተቀበለው፣ከበላይ መሥሪያ ቤት ላለመጋጨትና ትእዛዝ ለማክበር ሲባልእንደነበር አስታውሶ፣ ይህም የገዳሙን ማኅበር ዕረፍትና ሰላም ነስቶ ቁጣን እንደቀሰቀሰ የገለፀ ሲሆን፤ እገዳው፥የገዳሙን ሕገ ደንብና ሥርዓት ለመጠበቅና ለማስከበር ሲባልየተላለፈ መኾኑን ከማመልከት በቀር በጽ/ቤቱ የተጠቀሰ አዲስ ምክንያት የለም፡፡ የምደባው ጉዳይ /ቤቱ በሽፋንነት የተጠቀመበት መኾኑን የሚናገሩት ምንጮቹ፤ ለወራት ሥራቸውን ሲያከናወኑ በቆዩት ሒሳብ ሹሟ ላይ የተላለፈው እገዳ ተገቢነት የሌለውና የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ የካቲት 25 ቀን ባካሔደው ስብሰባ ካሳለፈው ውሳኔ ጋር በቀጥታ የተያያዘ እንደኾነ ያረጋግጣሉ፡፡

በተጠቀሰው ቀን የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ በዋና አስተዳዳሪው ሰብሳቢነት ባካሔደው ስብሰባ፤ ለሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ለልጃቸው ማሳከሚያ ገንዘብ ለማሳባሰብ በተዋቀሩ ኮሚቴዎች የቀረበው የድጋፍ ጥያቄ፣ ተገቢነት ያለውና ገዳሙ ከሌሎች ገዳማትና አድባራት ሳይለይና ብዙ ሳይዘገይ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው አስታውቋል፡፡  “ጥያቄው ሰብአዊ ፍጡርን የማዳን ወሳኝ ጉዳይ መኾኑ ታምኖበት፣ ከገዳሙ ገቢ ላይ ብር 500‚000 ወጪ ኾኖ እንዲመደብ፣ ከዚህ ውስጥ 300‚000 ብር በገዳሙ ስም፤ 200‚000 ብር በገዳሙ ሠራተኞች ስም ተሠይሞ በገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ አማካይነት ለክብር ሥራ አስኪያጁ  እንዲደርሳቸውበሚልም ውሳኔ አሳልፏል፡፡

የገዳሙ /ቤት፣ ውሳኔው እንዲፈጸምና ሒሳቡ እንዲወራረድ የካቲት 30 ቀን ለሒሳብ ክፍሉ በጻፈው መሸኛ ትእዛዝ ቢሰጥም፣ ሒሳብ ሹሟ ክፍያውን እንደማይፈጽሙ በመግለጽ ውሳኔውን ተቃውመዋል፤ ይህንኑም ተከትሎ ባለፈው ሰኞ ከሥራና ከደመወዝ መታገዳቸው ታውቋል፡፡ ሒሳብ ሹሟ እገዳውን በመቃወም ለሀገረ ስብከቱ /ቤት አቤቱታ ማቅረባቸው የተጠቆመ ሲኾን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ /ቤቱም ጉዳዩን እንዲያውቀው መደረጉ ተገልጿል፡፡

2 comments:

  1. What do you think you YEMANE may benefit from such immoral act in the name of your poor child? Do you think you may live as long as Matusala lived in this material world? So why are acting in such a way? Do you think you can easily repay for what you doing these days?

    ReplyDelete
  2. It is absolutely shame, to steal the churches' money in such day light.
    This man has been the parasites of the church for quite long time, he has been their because of mutual interest between the high corrupt and racist church leaders like Aba Matheyis.

    ReplyDelete