Thursday, August 18, 2011

“ተሐድሶ የለም” ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ



መቀመጫው በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በዕለተ ረቡዕ 06/02/2011 በሰርክ ጉባኤ በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መድረክ ላይ ተሐድሶ የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የለም በማለት አስተማረ:: እንዲሁም ደግሞ ጸረ ተሐድሶ እንቅስቃሴ እያካሄዱ የሚገኙት ማኅበራት እና ግለሰዎች ላይ ተስፋዬ መቆያ የወቀሳ እና የተቃውሞ ድምጹን አሰምቶዋል:: ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ “ተሐድሶ የለም” ብሎ መናገር መብቱ ቢሆንም፤ ነገር ግን የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ የሚታገሉ ወገኖችን መወንጀል አይገባውም ነበር::


ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የተሐድሶ መናፍቃን እንቅስቃሴ መኖሩን ለምን እንደተቃወመው ለጊዜው የሚታወቅ ነገር የለም:: እንዲሁም ደግሞ በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ እውን‹‹ተሐድሶ›› የለምን? በሚል ርዕስ ተሐድሶን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሑፍ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ ተቃውሞታል:: 

 የተዋሕዶ ልጆች የቤተ ክርስቲያናችን የውስጥ መናፍቃንን ለማጋለጥ በአንድነት በተረባረቡበት በዚህ ወቅት “ተሐድሶ የለም” ብሎ መቃወም የሰባኪው ማንነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል:: 



ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ እንደዚህ አይነት ተቃውሞ ሲያቀርብ ይህ የመጀመሪያ አይደለም፤ የዛሬ ዓመት አካባቢ ቨርጂኒያ ውድ ብሪጅ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ በግለሰዎች ስም እና በቀሳውስቱ ስያሜ ተሰጥቶት ኢየሱስ ወብስራተ ገብሬል በሚል በዚህ ሀገር ቋንቋ ቤተ ክርስቲያን “ተከፍቶ” ነበር:: ይህንን ድርጊት ያበሳጫቸው የቤተ ክርስቲያን ልጆች ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጥቢያ አመሠራረት በተመለከተ ፍትሐ ነገሥትን መሰረት ያደረገ ጽሑፍ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ለምዕመናን አሰራጭተው ነበር:: በዚህም ግዜ የዛኔው ዲ/ን የአሁኑ ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ “ወንጌል ይሰበክ እንጂ ቤተ ክርስቲያን ያለ ጳጳስ መባረክ ይቻላል” በማለት አስተምሮ ነበረ:: እንዲሁም ደግሞ ቀኖና ይጠበቅ በማለት ጽሑፉን ያሰራጩ ወገኖች ተስፋዬ መቆያ “የወንጌል ጠላቶች” በማለት ተቃውሟቸውም ነበረ::

እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

3 comments:

  1. የተሰወረ የተከደነ ነገር በምድር ላይ ባለመኖሩ የሰወሩት እውነታ እግዚያብሔር በረቂቅ ጥበቡ ያጋልጥና ልÐቹን ይጠብቃ፡፡ ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡

    ReplyDelete
  2. Tehadiso is not a new problem for our church it was well known poison. So, first of all as Ethiopian Preach it shouldn't be said "TEHADISO YELEM" but they have to preach how the peoples keep themselves from tehadiso. Actually now in order to be known by peoples the best strategy became "TALKING ABOUT (NOT PREACHING) TEHADISO".
    NOW THE SAINTS AND LIKAWINTE BETEKIRISTIAN ARE HIDING THEMSELVES AND I THINK THEY ARE PARAYING LIKE ETHIOPIAWIW ABEMELEK "YE'ETHIOPIAN METFAT ATASAYEGN!"
    Egziabher YeEthiopian Metfat Ayasayen. (Ethiopia is Orthodox Tewahido)

    ReplyDelete
  3. wey gued yhen tsufe aychew alwekem nebre gien yemkew ngre selnbre temlsleng!

    ""EGZIABHER Sew Alew"" YemIlew Yedakon Daniel Kebret Sibket Wey Gude Ewintem
    EGZIABHER Sew Alew Ehmmmmmmmmmmmmm

    ReplyDelete