Sunday, August 7, 2011

ለሱባኤተኞች በሙሉ




«የምንፈለገውን ብቻ ሳይሆን የሚያስፈልገንንም ነገሮች ለመቀበል መዘጋጀት አለብን ይህን ለማድርግ ደግሞ ደጋግመን የአምላክን ለእኛ ያለውን አላማ ልንረዳው እና ልናውቅ ይገባል። እርሱም የሕይወት ትንሳኤያችን ነው፡ የድንግል ማርያም ምልጃ እና ልመና ሁሉ በእኛ ሕይወት ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለውና እኛም የድንግልን ትንሳኤ ማየት እየናፈቅን በጽሞና እንተጋለን »

ሐዋርያት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የድንግል ማርያምን ትንሳኤ ለማየት በማሰባቸው ሱባኤ ገብተዋል። ምክናያቱም የጌታ እናት ተነስታ ማረጉዋን ከሐዋርያው ቶማስ ሰምተዋል እና ይህን ለማየት የቶማስን ማስረጃ እና ምስክርነት ተቀብለው አምላካቸውን ተማጽነው የተመኙትን አይተዋል። እኛም ሱባኤያችን ከልምድ ወይም ደግሞ በአመት የሆነ ነገር ነው በማለት አልያም ደግሞ ልክ እንደ ዓመቱ በጀት መዝጊያ አድርገን ብቻ ሳይሆን ያጠፈነውን አርመን የበደልነውን ክሰን የተጣላነውን ታርቀን የቀማነውን መልሰን በአዲስ ልብ እና በአዲስ መንፈስ ተሰርተን ቀጣዩን ዓመት ልንቀበለው ይገባል። ሐዋርያት የድንግልን ትንሳኤ አይተው ስጋውን እና ደሙን ተቀብለው አምላካቸውን እያከበሩ ወደ ዓለም ሁሉ ተበታትነዋል። እኛም የድንግል ምልጃና ልመና ረድቶን በሕይወት ተለውጠን ስጋው እና ደሙን ተቀብለን ታድሰን እንድንገናኝ ፈጣሪ ጊዜያችንን ይባርክ።

እርግጥ ይህ ወቅት እና ይህ ጊዜ ለልመና ምቹ ነው ምክኒያቱም ተማሪውም ከትምህርቱ ሰራተኛውም የዓመት ረፍቱን ወስዶ እራሱን ለእግዚአብሔር የሚያስገዛበት እና የእግዚአብሔርንም ድንቅ ነገር የሚያይበት ወቅት ነው ከዚያም ባሻገር በዘመናችን ለረጅም ቀናት ከቤተ ክርስትያን ቅጥር ከገዳማት ክልል ሳንወጣ ዓለምን ሁሉ ረስተን ምኞቱንም ሁሉ ሰቅለን ከሰማያውያኑ ጋራ ይህን ታላቅ ምስጢር ሌሊት በስዓታት ንዒ…..ንዒ …….ንዒ…….እያልን ከአባቶቻችን ጎን ጎመን ምስጋናዋን እየሰማን በዚህም ሰማያዊ ስርዓት ልባችን እየተነካ ነፍሳችን ደግሞ ከዚህ ማዕድ የተመገበች ከሌላው ጊዜ ሁሉ ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን መልካም ምስጢር እና ያልተዛባ እና ያልተቀየጠ ስርዓት እና አስተምሮ እያየን ከቤቱ በረከት የምንጠግብበት ያለ ዋጋም የሕወትን ውኃ የምንጠጣበት ታላቅ ግብዢያ ነው እና ሁላችንም በዚህ ግብዣ ላይ እራሳችንን እያየን የፍቅሩን ማእድ ታጥበንና ንስሐ ገብተን ተመግበን የዘላለምን ሕይወት እንድናገኝ ይርዳን።

ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባኤ በአንድነት በመንፈስ
ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያለው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት

ሞትማ በሞት ተሸንፏል
በአንቺ ላይ ምን ስላጣን ያገኛል

እቡዋት ዘምስሌኪ ለሰብ ይከሰቱ ይቤላ ለማርያም ይዜኔ ምርሄኔ አብ ዘይሄሪ እስመ ይሴኒ..
መልካም የጽሞና ጊዜ እና የለውጥ ወቅት ይሁንላችሁ ድንግል ማርያም ከእናንተ ጋራ ትሁን አሜን፩!!!!!!!!

No comments:

Post a Comment