Tuesday, August 16, 2011

መምህር ዘመድኩን በቀለና እና ዲ/ን ደስታ ጌታሁን በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ

            


ሰበር ዜና ፡ መምህር ዘመድኩን በቀለና እና ዲ/ን ደስታ ጌታሁን በፖሊስ ተይዘው ታሰሩ፡፡ ከክፍለ ከተማቸው ውጭተይዘው መወሰዳቸው ሁሉንም አስገርሟል፡፡ ዛሬ ነሐሴ 9 ቀን 2003 ዓም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የገዳማት አስተዳደር ዋና ጸሐፊ ዲ.ን ደስታ እና መምህር ዘመድኩን በቀለ በመጋቤ ሐዲስ? በጋሻው ደሳለኝ ከሳሽነት ቦሌ... ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው በዋስ መፈታታቸው ተሰማ፡፡ 


        ገንዘብ ካለ… እንደሚባለው ከ 4 ቀን በፊት ወ/ሮ እጅጋየሁ መምህር ዘመድኩን በሚገኝበት አራዳ ክፍለ ከተማ ዘመድኩን እና ዳንኤል ክብረት እንዲታሰሩላት ጠይቃ የነበረ ሲሆን በህጋዊ መንገድ ካልሆነ እንዲህ ያለ አሰራር እንደሌለው የመለሰላት የአራዳ ፖሊስ ጣቢያ የሚመሰገን ነበር፡፡በአንጻሩ የቦሌው ፖሊስ ጣቢያ ደግሞ አራዳ ክፍለ ከተማ የሚኖርን ግለሰብ በህገ ወጥ መንገድ በፖሊስ መኪና ሳይሆን የነበጋሻው አዝማች የሆነው የፊደል ካፌ ባለቤት በሆነው በአቶ ኤፍሬም መኪና ታፍሰው ተወስደው ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊሰ ጣቢያ ሲታሰሩ ከሳሽ በጋሻው ደሳለኝና አቶ ኤፍሬም በወቅቱ መርማሪ ፖሊስ እንጂ ከሳሽ አይመስሉም ነበር፡፡
      በስፍራው ተገኝተው የነበሩት የተከሳሾቹ ዘመዶች በሚያሳዝን ሁኔታ በፖሊስ እየተገፈተሩ ሲወጡ ኤርትራዊ እንደሆነ የሚታማው ኤፍሬምና የአንጾኪያ መዝሙር ባለቤት (በጋሻው አሁን የኑፋቄ ስብከቶቹን እየለቀቀበት ያለ መዝሙር ቤት) አቶ አለማየሁ ገፍታሪዎች ነበሩ፡፡ አሳዛኙ ነገር ፖሊስ መኪና እያለው በግለሰብ መኪና ያለ ክፍለ ከተማው ገብቶ ሰውን እንደ እቃ ግለሰብ መኪና አፍሶ ጭኖ መውሰድ ከተቻለ ዲሞክራሲ ህግ መኖሩ ያጠራጥራል፡፡ 

      ሌላኛው አሳዛኝ ዜና ደግሞ ለነበጋሻው መብት ወረቀት የሚበትነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዲ.ን ደስታን ከቦሌ በግለሰብ መኪና ከስራ ገበታው ላይ ታፍሶ ሲወሰድ ማን ናችሁ ብሎ የሚጠይቅ ሰው መጥፋቱ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ ፖሊሶች የሚመጡት ከማእከላዊ ወይም መስሪያ ቤቱ ከሚገኝበት አራዳ ክፍለ ከተማ ሲሆን እሱንም ቢሆን በቅድሚያ ጥበቃዎችን ባለስልጣናቱን አነጋግሮ እገሌ የሚባል ሰው እንፈልጋለን ብለው ነበር፡፡ ዛሬ ግን በወይዘሮ እጅጋየሁ ሳቅ ታጅቦና በአቶ ኤፍሬም መኪና ታፍሶ ከቦሌ ድረስ በመጡ ፖሊሶች ተይዞ ሲወጣ አገሪቱ መንግስት አለባት ወይ ዲሞክራሲስ አለ ወይ? ያስብላል፡፡ 

       የህግን ነገር ጠንቅቆ የሚያውቀው ዘመድኩን ያለ ክፍለ ከተማችን ቦሌ ድረስ የመጣንበት ምክንያት ለምንድን ነው? የሚል ጥያቄ በማንሳቱ ሲፈለጉ እንዲቀርቡ በሚል ማታ ላይ ሊፈቱ ችለዋል፡፡ እንቁ መጽሔት ላይ ለጥያቄ ሲደወልለት ፊቴን ወደ እግዚአብሔር መልሻለሁ ያለው በጋሻው በፍልሰታ ፋይል ይዞ መታየቱ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ማለቱ ይሆንን? የቦሌው ፖሊስ ጣቢያ የነበጋሻው ምኩራብ ለሆነው የአቶ ኤፍሬም ሆቴል ፊደል ካፌ እና ሎቢያቸው ከሆነው ካልዲስ ካፌ ብዙም የማይርቅ መሆኑ ይታወቃል፡፡  


ዘመድኩን ሊከሰስበት ይችላል የተባለውን ከአንድ መፅሄት ጋር ያደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ ቀጥለን እናወጣዋለን ይጠብቁ

3 comments:

  1. sint neger betenagerebet afu zare lehatiat difret bicha new yemiasfelgew ale?

    ReplyDelete