Monday, August 29, 2011

ኡራኤል ቤተክርስትያን አጠገብ ለመናፍቃን 2300 ካሬ ቦታ ሊሰጣቸው ነው


 • ካልጠፋ ቦታ ከዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ጋር አጠጋግቶ መስጠቱ ችግር ያስከትላል - የአ.አ. ሀገረ ስብከት
 • ስፍራው ለልማት ከተፈለገ የማልማቱ ቅድሚያ ለእኛ ሊሰጠን ይገባል - ነጋዴዎች
 • የእምነት ተቋማት አድልዎ ሊደረግባቸው አይገባም - የኢትዮጵያ ህይወት ብርሃን ቤ/ክ

ጉዳዩ ውዝግብ አስነስቷል
የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ሊዝ ቦርድ ስፋቱ 2222 ካሬ ሜትር የሆነውን ቦታ፣ በአቶ አርከበ ዕቁባይ የቦርድ ሰብሳቢነት ከሊዝ ነጻ lቤተክርስቲያኒቱ እንዲሰጥ ውሳኔ ተላልፏል፡፡
በዚሁ ውሳኔ መሠረትም ቤተ ክርስቲያኒቱ በስፍራው ለሚገኘው አንድ የኪራይ ቤቶች ቤት 317965.58ሣ. ካሳ በሚያዝያ 4/1998 ዓ.ም. ከፍላለች፡፡ ቦታውን ግን አሁንም አልተረከበችም፡፡ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ባለስልጣን የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ሊዝ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ያልቻለበትን ሁኔታ ሲገል፤ የቦታው አገልግሎት ለቅይጥ አገልግሎት እንጂ ቤተክርስቲያን ያለመሆኑንና ቦታው በዋና መንገድ ላይ የሚገኝና ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚከናወንበት ስለሆነ በተፈለገው ፍጥነት ቦታውን ቤተክርስቲያን ማስረከብ እንዳልቻለ በመግለ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመሬት ልማትና አስተዳደር ባለስልጣን ደብዳቤ ፏል፡፡
በሥፍራው የሚገኙ ነጋዴዎች መስተዳድሩ የነዋሪውን ቅድሚያ የማልማት መብት ሳይጠብቅ ያለአግባብ ከቤታችን እንድንፈናቀል ተወስኗል፤ ይሄ ደግሞ የህግ አግባብ የሌለውና የእኛን መብት የተጋፋ ጉዳይ ነው ሲሉ ቅሬታቸውን ለከተማው መስተዳደርና ለህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አቀረቡ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ /ቤትም ነሐሴ 6/2003 በተፃፈ ደብዳቤ፣ አመልካቾቹ የቅድሚያ ማልማት ጥያቄያቸውን ያቀረቡት ስፍራው lቤተክርስቲያኒቱ ከተሰጠ በኋላ መሆኑን በመግለ ለህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ 

የአካባቢው ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቦርድ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም አቤቱታቸውን በተደጋጋሚ ቢያሰሙም ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውንና ያለአግባብና ያለአንዳች ምትክ ቦታ ሜዳ ላይ ሊጣሉ መሆናቸውን ይገልፃሉ፡፡ ይህንኑ ውዝግብ ተከትሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገር ስብከት ጽ/ቤት፤ ለክቡር አቶ ኩማ ደመቅሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሐምሌ 28 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ፣ ለኢትዮጵያ ህይወት ብርሃንቤተክርስቲያን ሊሰጥ የታቀደው ቦታና የደብረጌ ቅ/ዑራኤልቤተክርስቲያንያለበት ቦታ እጅግ የተቀራረበ በመሆኑ፣ ካልጠፋ ቦታ የተለያዩ እምነት አራማጆችን በዚህ መልኩ ማጠጋጋት yቤተክርስቲያኒቱ ችግር ብቻ ሳይሆን የመንግስት አካላትንም የሚመለከት ስለሆነ መፍትሄ እንዲፈለግ አሳስቧል””የኢትዮጵያ ህይወት ብርሃንቤተክርስቲያን 2222 ካ.ሜትር ከሊዝ ነፃ ቦታ ለአምልኮ ቦታዎች መሥሪያ፣ ለወጣት ማዕከላትና የተለያዩ የስልጠና ማዕከላትን ለመገንባት እንዲያስችላት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቦርድ በ1998 ዓ.ም ቢሰጣትም የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር ቦታውን እስከ አሁን ሊያስረክቧቸው እንዳልቻሉ ፓስተር መብራቴ አያሌው ገልፀዋል፡፡ በህግና በስርዓት የተሰጠንን ህጋዊ ቦታ የተለያዩ ሰበቦችን ፈጥረው እስከዛሬ ድረስ ሊያስረክቡን አለመቻላቸው የበታች ባለስልጣናት እያደረሱብን ያለውን ተእኖ ያመለክታል ብለዋል፡፡ቤተክርስቲያን ሰዎችን ማፈናቀል አትፈልግም፤ የእኛ ዓላማ ህብረተሰቡን በድቅ መንገድ ማገልገል ነው ያሉት ፓስተር መብራቴ፤ እኛ ከዚህ ቦታ ጉዳይ የለንም የከፈልነው ገንዘብ ተስተካክሎ እዚሁ ካሳንቺስ አካባቢ ሌላ ቦታ ቢሰጠን አንቃወምም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የሃይማኖት ነፃነታችን በህገመንግስት የፀደቀልን ነው ያሉት ፓስተር አያሌው፤ የቀድሞ መንግስታት የተለያዩ ችግሮችን እየፈጠሩብን የቆዩ ቢሆንም ካሳንቺስ አካባቢ ለ45 ዓመታት የተለያዩ አገልግሎቶችን ስንሰጥ ቆይተናል ብለዋል፡፡ 

የቀድሞው መንግስትቤተክርስቲያንየቀጠና 3 ኢሰፓ /ቤት በማድረግ በደል እንደፈፀመባቸውም ተናግረዋል፡፡በአካባቢውየሚገኘው የዑራኤል ቤተክርስቲያን የተለያዩ የእምነት ተቋማትን በአንድ አካባቢ ማድረግ ለግጭትና ለአላስፈላጊ ችግሮች ይዳርጋል ሲል ለአዲስ አበባ መስተዳድር የፃፈውን አስመልክተው ሲናገሩም፤ ይህ ፈሞ አግባብነት የሌለውና አገሪቱ የምትታወቅበትን በሃይማኖቶች መካከል ያለ መከባበርና ሰላም ታሪክ የሚያጠፋ ነው ብለዋል፡፡ አያይዘውም ሁሉም የሃይማኖት ተቋም ሥራው ወንጌልንና ሰላምን መስበክ በመሆኑ ልዩነታችን ጥንካሬ ሆኖ በጋራ ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ስለጉዳዩ በመግለጽ የጻፈውንም የሲኖዶስ ሃሳብ ነው ብለን ልንቀበለው አንችልም ብለዋል፡፡በሦስት ወገኖች ውዝግብ በእንጥልጥል ላይ ያለው የዑራኤል አካባቢ ነጋዴዎች ስፍራም ማወዛገቡን ቀጥሏል፡፡

From Addis Admas News Paper ..August 27/2011

4 comments:

 1. Chigir mefeter kesew hasab gar Yediyabilos Eqid sichemer gudatu kefetenga new bemehonum new mefetehe sayetefa Endezih ayenetun chigir yemefeterut.Ere tewu ebakachihu egizabheren firu mizanawim hunu...baltefa bota

  ReplyDelete
 2. ልዩነታችን ጥንካሬ ሆኖ በጋራ ልንሰራ ይገባል ...what does mean it? foolish people!!!

  ReplyDelete
 3. ልዩነታችን ጥንካሬ ሆኖ በጋራ ልንሰራ ይገባል ...what does mean it? foolish people!!!

  ReplyDelete
 4. kifuna temama tiwlid milikitin yishal!!!!!!!!!

  ReplyDelete