Friday, August 5, 2011

ለተሐድሶ አቀንቃኞች

ቢሣነው ማየት አጥርቶ፡፡ 
ሲበዛበት ብዥታ 
ሲዛባበት እይታ 
ታየችው እናቱ አርጅታ፡፡
ያደገበት ወግ ሥርዐቷ
ተረሰቶ እሷነቷ
በይ ላድስሽ አላት 
ማፍረሻ ቀስት እያሣያት፡፡
ወገን ዝም አትበሉ 
እውነትን መስክሩ፡፡
ለዚህ ለጡት ነካሽ
አስታውሱት አይርሣ
መታደስ ያለበት 
የእሱ ልብ? ወይስ እሷ?

No comments:

Post a Comment