Tuesday, August 16, 2011

ሞት ዘረፈን

እንግዲህ መቃብር ጠንክረህ ተማር
ድጓ ተሸክሞ መጣልህ መምህር

1. ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ (1927 - 2003 .)
  • ‹‹የምናሠለጥናቸው በሌላ ቋንቋ ተናግረው የሌለ ሃይማኖት እንዲያመጡ አይደለም፡፡›› (ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ በ1991 ዓ.ም ከተናገሩት)
  • ብፁዕነታቸው በድንገተኛ ሕመም ማረፋቸው የተሰማው ሐሙስ የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ዘጠኝ ሰዓት ገደማ በመንበረ ፓትርያርኩ ከሚገኘው ማረፊያ ቤታቸው ነው፡፡
  • በቤተ ክርስቲያን የዕለቱን ሥርዓተ ቅዳሴ ተካፍለው በደህና የተመለሱት ብፁዕነታቸው በድንገት ማረፋቸው የታወቀ ሲሆን መንስዔው ከልብ ጋር የተገናኘ ሳይሆን እንደማይቀር ተብሎ በባዶ መላምት አልፏል፡፡
  •  ‹‹ብፁዕነታቸው በመንፈሳዊው ትምህርት የተሟላ ሊቅነት ያላቸው፣ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በኩል እግዚአብሔርን በዝማሬ መላእክት፣ ሕዝበ ምእመናንን በትምህርት፣ በስብከተ ወንጌል እና በጸሎተ ቡራኬያቸው ያገለገሉ ያሬዳዊ ቅርስነበሩ፡፡›› (ዜና ሕይወታቸው)
2. ብፁዕ አቡነ በርናባስ

  •  "የትምህርት መጨረሻው መልካም ሥራ ነው፡፡" (ብፁዕ አቡነ በርናባስ) 
  • ‹‹የሲኖዶሱ አካሄድ ውኃ ወቀጣ ሆኗል፤ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር፣ ከግለሰብ ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን መወገን አይሻልም ወይ?››(ብፁዕ አቡነ በርናባስ) 
  • ግንቦት 21 ቀን 2003 ዓ.ም ከሌሊቱ 10፡00 ግድም በድንገተኛ ሕመም በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ያረፉት የምዕራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ በርናባስ 
  • ግንቦት 16 ቀን ከተፈጸመው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ መጠናቀቅ በኋላ ግንቦት 19 ቀን በሀገረ ስብከታቸው መኪና ወደ ባሕር ዳር ያመሩት ብፁዕነታቸው ደብረ ማርቆስ ከተማ ሲደርሱ ድካም እንደሚሰማቸው በመግለጽ በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት መንበረ ጵጵስና አድረው በበነጋው ጉዟቸውን ቀጥለው እንደ ነበር ተገልጧል፡፡ የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑት ብፁዕነታቸው በባሕር ዳር መንበረ ጵጵስናቸው ቅዳሜ ግንቦት 20፣ ከቀኑ 8፡00 ላይ ከደረሱ በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ላይ ነበር ያረፉት

    • "እንኳንስ ተለያይተን፤ አንድ ሆነንም አንችለውም። ዘመኑ እኩይ ነው ዘመኑ ክፉ ነው ወገኖቼ ..." ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ 
    • በ1951 ዓ.ም ተወለዱ፡ 
    • ጁን 21/2010 በሞት ተለዩ 
    • የከምባታ፣ ሐድያ፣ ጉራጌና ስልጢ አህጉረ ስብከተ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የነበሩት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ  
    • ብፁዕነታቸው በሕይወት በነበሩባቸው ጥቂት ዘመናት የሰሯቸው አያሌ ቁምነገሮች ሰርተዋል 
    4. የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ 
    • ብፁዕነታቸው በዘመናዊው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ይከበሩና ይወደዱ ከነበሩ አባቶች አንዱ የነበሩ ሲሆን በተለይም የቅርብ ጓኛቸውና የሃይማኖት ወንድማቸው የነበሩት ታላቁ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሚያደንቋቸው አባት እንደነበሩ ይታወቃል 
    • ከሀገራቸው በስደት ወጥተው በአሜሪካ ይኖሩ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ እረፍት Feb 13, 2010 
    • ብፁዕነታቸው በቤተ ክህነት ፖለቲካ ተጠልፈው የ”ስደተኛው ደጋፊ” ከመሆናቸው በስተቀር በቤተ ክህነቱ አበው መካከል ለተፈጠረው ልዩነት መፍትሔ ይሆናሉ ተብለው ተስፋ ይጣልባቸው ነበር።

    5. መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ 


    • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያ ሐላፊ ለነበሩት እና ነሐሴ አንድ ቀን 2002 ዓ.ም መንሥኤው ባልታወቀ ድንገተኛ ዕረፍት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ሊቁ መጋቤ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ 
    • መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ በግእዝ ቋንቋ ተተርጉሞ በአንድ ጥራዝ እንዲታተም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት ከኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ጋራ በመሥራት ላይ ነበሩ ፡፡ 
    • መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ሰባክያን፣ መምህራን እና ተመራማሪዎች በሰፊው የሚጠቀሙበትን የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ካዘጋጁት አንዱ በመሆን ታላቅ እና ዘወትር የማይረሳ ተግባር አከናውነዋል 
    • ‹‹የብሉይ ኪዳን ማስተማሪያ›› መጽሐፍ አዘጋጅተው በማቅረባቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት “መጋቤ ብሉይ” የሚለውን የማዕርግ ስም የካቲት 14 ቀን 1977 ዓ.ም ሰጥተዋቸዋል፡፡ አሁን ከመሬት አንስተው መጋቢ ሀዲስ ስም መሰጠት ተጀምሯል 
    • የሰማኒያ አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስ ከግእዝ እና ከሰባ ሊቃናት ትርጉም ጋራ ተገናዝቦ በአማርኛ ሲዘጋጅ የመተርጉማኑ ቡድን ሰብሳቢ የነበሩት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ፣ 
    • የሰይፈ ሞትቅጅ እና ምትክ የሌለው መጽሐፍ እንደ መቃጠል ይቆጠራል”

    6. ብፁዕ አቡነ ሚካኤል

    • የሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሽሬ እንዳሥላሴ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
    • በ1942 ዓ.ም ተወለዱ፡፡
    • ነሐሴ 8 ቀን 2003 ዓ.ም አርፈዋል
    • በውጪ አገር እንግሊዝ ለንደን ሴንት ኤድዋርድስ ኮሌጅ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ለአንድ ዓመት፣ ግሪክ አገር በአቴንስ ዩኒቨርስቲ ለስድስት ዓመታት ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት በመማር በቲኦሎጂ ማስትሬት ዲግሪ፣ በአሜሪካ ሆሊ ክሮስ በተባለው የግሪክ ሴሚናሪ ከሲስተማቲክ ቲኦሎጂ ዲፕሎማ፣ በቦስተን ዩኒቨርስቲ የኤስ.ቲኤም ወይም በፓስተራል ካውንስሊንግ /ሳይኮሎጂ/ በማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል
    • የሐሞት ጠጠር ሕመም የነበረባቸው ብፁዕነታቸው የቀዶ ጥገና ሕክምናቸውን በቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በመከታተል ላይ የነበሩ ሲሆን በመካከል ከሰመመናቸው መንቃት ሳይችሉ እንደቀሩ ታውቋል። 
    7. መልአከ ገነት ገብረ ሥላሴ

    • የአራቱ ጉባኤያት አብነት መልአከ ገነት ገብረ ሥላሴ አወቀ በተወለዱ በአንድ መቶ ሁለት ዓመታቸው ግንቦት 28 ቀን 2002 ዓ.ም ለ29 አጥቢያ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል፡ 
    • ጳጉሜ 3 ቀን በ1900 ዓ.ም በ1979 ዓ.ም ከወርኃ ኅዳር እስከ ግንቦት 4 ቀን 2002 ዓ.ም ድረስ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ ለ24 ዓመታት ደከመኝ ስለቸኝ ሳይሉ እስከ መጨረሻ የእስትንፋስ ሕቅታ ድረስ ቃለ እግዚአብሔር በመናገር በልማደ ሰብእ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል
    ‹‹የብፁዕ አባቶቻችንን ነፍስ አምላካችን ከደጋጎቹ ወገን ያኑርልን።››





    2 comments: