Wednesday, August 31, 2011

የብሎገሮች ቀን



በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያውያ ውስጥ ያለው የብሎገር ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ በቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡  በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ ኑሮ፣ በእምነት፣ በኪነ ጥበብ ወዘተ ላይ የሚያተኩሩ ብሎጎች ብቅ በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ እኛም ይችን ብሎግ ይዘን የሚቀጥለውን አላማ አድርን ተነስተናል:: 

አንድ አድርገን

አንድ አድርገን
አንዲት  ቅድስት  ቤተ  ክርስቲያንን  በሚመለከት  ዕለት  በዕለት  የሚታየዉ፦ የውስጥና  የውጭ  ችግር ፡ - አደጋና  የወደፊት ስጋት ምን እንደኾነ ኹሉም የእናት ቤተክርስቲያን ልጆች  እንዲያውቁት ፤ የበኩላቸውንም  መፍትሔ  እንዲፈልጉ ፤  ሐሳብ እንዲሰጡ ፤ በክርስትናቸው  የሚጠበቅባቸውን  ሓላፊነት  እንዲወጡ  የክርስቶስን  መስቀል  ለመሸከም  የማይሰቀቅ  ክሣደ  ኅሊና  ኖሯቸው  ለስብከተ  ወንጌልና  ሐዋርያዊ  ተልእኮዋ  መሳካት  ለህልውናዋ  መጠበቅና  ለፍጹም  አንድነቷ  እንዲነሡ  የምታተጋ  ዐውደ  ምጽሓፍ  ወመስተሳትፍ  ናት ። 

አንድ አድርገን ከተመሰረተች የአንደ ወር ያልበለጠ እድሜ ሲኖራት ባለን የዳታቤዝ መረጃ መሰረት በቀን ቢያንስ 2000 ሰዎች እንደሚጎበኙን ለማወቅ ችለናል ፡፡ይህ ደግሞ እኛ በርትተን እንድንሰራ እና ሚዛናዊ ነገር ይዘን እንድናቀርብ እንደ ማበረታቻ ሽልማት አይተነዋል፡፡ወደፊት ብሎጉን ወደ ድህረ ገፅ ለማሳደግ እቅድ የያዝን ሲሆን ስብከቶችን(በድምፅ፤ በምስል፤በፅሁፍ)ወቅታዊ መረጃዎችን(ከጋዜጣ፤ከመፅሄት፤ከዌብሳይት)በዓላትን፤ ነገረ ቅዱሳንን ፤ ገዳማት ፤ ሌሎች ብዙ ክፍሎችን የያዘና በርካታ አምደኞች ያሉት ገፅ ለመክፈት ስራ በመስራ ላይ እንገኛለን፡፡ 

ይህች ብሎግ የተለያዩ ሰዎችን ሐሳብ የምታስተናግድ ሲሆን በፁሁፉ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ የተገኝበትን አድራሻ ትጠቅሳለች የራሷ ከሆነ ከአንድ አድርገን ብለን የምናወጣ ሲሆን ጥቂት ብሎጎች ወይም ድህረገፆች ግን ከአንድ አድርገን ብሎግ ላይ በመውሰድ የራሳቸው አስመስለው ሙሉ ስማቸውን ፅፈው እያወጡ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ 

አንድን ፅሁፍ ለመፃፍ ከብዕር እና ከወረቀት ባሻገር ብዙ መረጃዎችን በስልክ ፤ በጽሁፍ ፤ በድምፅ ፤ በምስልና አስፈላጊም ከሆነ ቦታው ድረስ ሄደን አረጋግጠን ሚዛናዊነቱን ጠብቀን የምናወጣ ሲሆን ይህ ሁሉ ልፋትና ድካም የራስ አስመስሎ በኮፒ ፔስት ማውጣት ተገቢ ስላልሆነ የብሎገሮች እና የዌብሳይቶች ባለቤቶች አትኩሮት ተሰጥቶት የማተካከያ እርምጃ ቢወሰድ ጥሩ ነው እንላለን፡፡ 

ሁላችንም የቆምነው መልእክት የምናስተላልፈው ስለ አንዲት ቤተክርስትያን ከሆነ መረጃውን ብዙ ሰዎች ጋር ተደራሲ መሆኑ ጥሩ ጎን መሆኑ እያለ ትናንሽ ስህተቶች እያረምን አብሮ የመስራት ፍላጎታችንን እያሳደግን መረጃን በቀላሉ ለማያገኙት ወገኖቻችን ለማድረስ ጠንክረን ብንሰራ ጥሩ ነው የሚል አስተያየት አለን፡፡ 

እንኳን ለብሎገሮች ቀን አደረሳችሁ

1 comment: