Saturday, November 16, 2013

ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው

  • ‹‹ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ›› መዝሙረ ዳዊት 82 ፤ 3


(አንድ አድርገን ህዳር 08 2006 ዓ.ም)፡- መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ ከ300 በላይ በየጎዳናው ወድቀው የነበሩና የተረሱ የአዕምሮ ህሙማንና አረጋውያንን በተለይ የአልጋ ቁራኛ የሆኑትን አረጋውያንን ከወደቁበት ጎዳና ፤ ከተረሱበት ቦታ በማንሳት በአዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት አጠገብ  መጠለያ አዘጋጅቶ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸው ድረስ ለመንከባከብ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል  ተጨማሪ አረጋውያንን ከጎዳና ለማንሳትና ቀሪ ዘመናቸውን በተመቻቸ ሁኔታ ያሳልፉ ዘንድ በግሎባል ሆቴል እሁድ ታህሳስ 13 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ እርስዎም ለዚህ ለተቀደሰ ጉባኤ ተሳታፊ ይኑ ዘንድ አንድ ቲኬት በ200 ብር በመግዛት  አንድም በየቦታው የወደቁትን ወገኖቻችንን ሲረዱ በሌላም የዜግነት ግዴታዎን በመወጣት ማዕከሉ ለቆመለት አላማ መሳካት የበኩልዎች የዜግነትዎን ኃፊነት ይወጡ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
አንድ የመግቢያ ቲኬት በመቄዶኒያ ለሚረዱ አንድ አረጋዊ ለ10 ቀን ሙሉ የምግብ እና የህክምና ወጪ ይሸፍናል ፤ ይህንን ፕሮግራም የሚደረገው ግሎባል ሆቴል በነጻ በፈቀደው አዳራሽ መሰረት ነው፡፡
 
ቲኬቱ የሚገኝበት ቦታ፡-  በመቄዶኒያ ፤ በሴፍዌይ ሱፐር ማርኬት የሺ ቡና እና በልዩ ሙያ ምግብ ቤት ይገኛል፡፡
በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የምትኖሩ  ማዕከሉን ለመርዳት የምትፈልጉ ሰዎች ካላችሁ በስልክ ቁጥር 0923 97 66 08 ወይም 0920 28 92 73 በመደወል  ስለ መቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል  መረጃ ማግኝት የምትችሉ መሆኑን ‹‹አንድ አድርገን›› ለመግለጽ ትወዳለች፡፡
ይህን መረጃ share በማድረግ ሰዎች ዘንድ ተደራሽ እንዲሆን ያድርጉ፡፡

No comments:

Post a Comment