- በዚህ ዘመንም ከአባታችሁ ከቅዱስ ያሬድ የተቀበላችሁትን ዜማ ትታችሁ ሌላ ያሬዳዊ ያልሆነዜማን እናሰማችሁ ባዩ በዝቷል፡፡
- ከአባቶች ባልተሰጠ ሥርዓት ዓይንን ጨፍኖ እጅን እያወራጩ እስከመዝለልም ተደርሷል፡፡
- “ያሬዳዊ ዜማ ለገበያ_አይመችም” በሚል መፈክር ብዙዎች ገንዘብን ፍለጋ የዜማ ርስታቸውንጥለዋል፡፡
- ያሬዳዊ ዜማን እንከተል እያሉ የናቡቴን ድምጽ የሚያሰሙ ምዕመናንና ካህናትም በቃልምበየመዝሙሮችም ላይ ‹ሜልኮሎች›፣‹ወግ አጥባቂዎች›፣‹ኋላ ቀሮች›፣‹ትምክህተኞች› እየተባሉ ሲወረፉ እንመለከታለን፡፡
(አንድ አድርገን ህዳር 03 2006 ዓ.ም)፡- አባቶቻችን ብዙ መስዋዕትነትን የከፈሉትና ደማቸውን ያፈሰሱት ሥጋቸውን የቆረሱት አጥንታቸውንም የከሰከሱት ግዑዟን ምድር ለማውረስ ብቻ አልነበረም፡፡ ከብዙ መስዋዕትነት ጋር ወደዚህ ትውልድ ያሻገሩት ሌላ ትልቅ ርስት አለ፡፡ይህም ሃይማኖትና ትውፊት ቋንቀዋና ፊደል ዜማና ሥርዓት ነው፡፡
ከአበው ከወረስናቸው በርካታ መንፈሳዊ ርስቶቻችን አንዱ መንፈሳዊው ዜማ ነው፡፡ይህ መንፈሳዊ ዜማ አባቶቻችን ከእግዚአብሔር የተቀበሉትና ከእርሱ ጋር የተገናኙበት እኛም ተግተን ብንጠብቀው ወደ ሰማያዊ ኅብረት የምንነጠቅበት መሰላል ነው፡፡ መንፈሳዊው ዜማ በዓለም ካሉት ሀገራት ይልቅ ለኢትዮጵያ ተለይተው ከተሰጡ ሃብታት አንዱ ነው፡፡ኢትዮጵያ ከታላቁ አባት ከቅዱስ ያሬድ የተቀበለችው የዜማ ርስትም ጣዕሙን ለሚያውቀው በጦር መወጋትን እንኳን ነው፡፡ይህን የዜማ ርስት ግን በዚህ ዘመን አልሰጥም ብሎ እንደናቡቴ የሚጠብቅ አልተገኘም ፤ ንጉሥ አክዓብ ለናቡቴ ያቀረባቸውን ሁለት አማራጮችም በዘመናችን ትውልዱ በደስታ ተቀብሎት ይገኛል፡፡
ለናቡቴ የቀረበው የመጀመሪያው ምርጫ የአባቶችን ርስት ወስጄ ሌላ ርስትን ልስጥህ የሚል ነበር፡፡በዚህ ዘመንም ከአባታችሁ ከቅዱስ ያሬድ የተቀበላችሁትን_ዜማ_ትታችሁ ሌላ ያሬዳዊ ያልሆነ ዜማን እናሰማችሁ ባዩ በዝቷል፡፡ይህንንም ጥሪ ተቀብሎ ያሬዳዊ ያልሆነን ዜማ ማድመጥና ማድነቅ የተለመደ ሆኗል፡፡
ሁለተኛው የናቡቴ ምርጫ ደግሞ ‹ገንዘብ ልስጥህ ርስትህን ስጠኝ› ነበር፡፡ይህን አይነቱንም መንገድ ዛሬ ብዙዎች የቀደመውን የዜማ ርስታችንን ለመጣላችን መንስኤ ነው፡፡‹‹ያሬዳዊ ዜማ ለገበያ አይመችም›› በሚል መፈክር ብዙዎች ገንዘብን ፍለጋ የዜማ ርስታቸውን ጥለዋል፡፡የናቡቴና የእኛ ዘመን ነገር ልዩነቱ ናቡቴ በንጉሥ ተገድዶም እንኳን ርስቱን ሳይሰጥ የሞተ ሲሆን ይህ ትውልድ ደግሞ በራሱ ፍላጎት ርስቱን እየሸጠና እየለወጠ መሆኑ ነው፡፡ ያሬዳዊ ዜማ የአንድ ወገን ባሕል ሳይሆን እግዚአብሔር በቀጥታ ለቤተ ክርስቲያን ዘኢትዮጵያ የሰጠው መንሳዊ ጸጋ ነው፡፡ ያሬዳዊውን ዜማ ማጣጣልና መቃወም ቤተ ክርስቲያኒቱን መቃወም እንጂ የተወሰኑ ግለሰቦችን መቃወም አይደለም፡፡በዘመናችን ያሬዳዊው ዜማ ከቤተ መቅደስ አገልግሎት ውጪ ቦታ እንዳይኖረው የሚያደርግ አካሄድ እየተስተዋለ ነው፡፡ይልቁንም ከመናፍቃን መዝሙሮችና ከተለያዩ ዘፈኖች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የተቀዱ ዜማዎች ቤተ ክርስቲያኒቱን እያጥለቀለቋት ነው፡፡ይህ ወረርሽኝ ከዜማም አልፎ የመናፍቃን ላህይ ያላቸው ግጥሞችን፣ሥጋዊ ኑሮን የሚመለከቱ የኑሮ ውድነትን፣ወቅታዊ ችግሮችን፣ፖለቲካዊ ጉዮችን ሳይቀር የሚመለከቱ የመዝሙር ግጥሞችም መስማት ተጀምሯል፡፡
የጌታችን የባሕርይ አምላክነትና ክብረ ቅዱሳንን እንዘከርበት የነበረውንም መዝሙር ስለ ሥጋዊ ድልና አሸናፊነት፣ስለጠላት የሚያወሩ መልእክቶችን መያዝ ጀመረ፡፡ከዚህም አልፎ በቤተ ክርስቲያን ዓውደ ምሕረት ከአባቶች ባልተሰጠ ሥርዓት ዓይንን ጨፍኖ እጅን እያወራጩ እስከ መዝለልም ተደርሷል፡፡ብዙዎቹን መንፈሳዊ ያልሆኑ ዝማሬዎች መጀመሪያ ለሚሰማቸው የሚያሳቅቁ ቢሆኑም በኋላ ግን እየተለመዱ መጥተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ያሬዳዊ ዜማን እንከተል እያሉ የናቡቴን ድምጽ የሚያሰሙ ምዕመናንና ካህናትም በቃልም በየመዝሙሮችም ላይ ‹ሜልኮሎች›፣‹ወግ አይባቂዎች›፣ ‹ኋላ ቀሮች›፣‹ትምክህተኞች› እየተባሉ ሲወረፉ እንመለከታለን፡፡ሥርዓትን እንከተል፣ እንደ አበው እንዘምር፣ርስታችንን አንልቀቅ፣በስሜት ሳይሆን በመንፈስ እንዘምር የሚሉ ሁሉ ክርስትና እንዳልገባቸው የክርስቶስን ፍቅር ያልገባቸው አድርጎ መፈረጅም እየተለመደ መጥቷል፡፡ይህም እግዚአብሔርን ማክበርና መውደድ የሚገለጠው በእርግጥ ከልክ በላይ በመዝለል፣ሥርዓትን በማቃለል ነውን? በመዝሙር ሥጋ ስትደሰት እና ስትጨፍር ነፍስ የምትሰቀቅና የምታለቅስ መሆን ይገባታል? እውነት የቅዱስ ዳዊት ዝማሬ ሥጋዊ ስሜትን ለማስደሰት የሚደረግ ጭፈራ ነበር? እውነት ቅዱስ ጳውሎስና ሲላስ የእስር ቤቱን መሠረት ያናወጡት በዝላይና ጩኸት ብዛት ነው? የሚሉትን ጥያቄ እንድጠይቅ ያስፈልጋል፡፡
ምዕመናን! መንፈሳዊውን የቅዱስ ያሬድ ዜማ ማጣጣም ያልቻልነው ሥጋዊ ጆሮ ስላለን ነው፡፡ መንፈሳዊ ጆሮ ቢኖረን መንፈሳዊው ባልሆነው ዜማ ምንኛ ባዘንበት ነበር፡፡
‹የአባቶቼን ርስት እሰጥ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቅልኝ› ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሥጋዊ ኑሮን የሚመለከቱ የኑሮ ውድነትን፣ወቅታዊ ችግሮችን፣ፖለቲካዊ ጉዮችን ሳይቀር የሚመለከቱ የመዝሙር ግጥሞችም መስማት ተጀምሯል፡"gin be mezmur yihe hulu chigir endikalel melemen(be mezmur limena makireb misgana makireb)sihitet new?
ReplyDeletediakon henok beewnetu egziabiher yibarikih yihe guday betekiristeyanachinin betam yasasibatal leekawint abew bezemerubet,kinea betekegnubet yetekedese awide mihiret yekelete zefen sezefenibet mayet betam yasazinal megerimew kidus yaredin yemayawiku ymuzika abat eyalu seeteru yemedemetu alu behig amilak lebalu yigebal sile kidus yared leanebu yigebachewal kidus yared yemuzeeka milikitochin ysera sayihon yemelaekitin zimarea yaye esunim beketita lebetekiristean yasitelalefe abat new ya malet leEtiopia bicha yetesete kidisina malet new mikinyatum egizeeabiherin kefitiretochu hulu bande aynet zema yeminameseginew yeEtiopia oritodox tewahido betekirsteanina melaekit neni malet new yih memeret min yidenk masitewal lehulachin yihun amen
ReplyDeleteማዕከላዊነት፣ኢትዮጵያዊነት፣ትውፊታዊ ቆፍጣናነት - ሁሉንም ችግር ይቀርፋል። ይኼ የሚሆነው ደግሞ አንድ ሲኖዶስ፣አንድ አገር፣አንድ ሊቀ ጳጳስ፣ አንድ የቤተ-ክርስትያን ጠላት ያልሆነ መንግስት ሲኖር ነው። አድር-ባይነት ከበዛ ሁሉም ዜሮ ይሆናል።
ReplyDeleteDiakon Henok Egziabhear yasadigh, ende lijinete bizu yasqochegnal..neber.. Gin Yaredawiw ye Betekrstean sitotawoch bicha aydelem..bizuwn atitenal, eyatanim neaw, Zim bilen Yabatochachinin maletu yeBetekrsteanin hilwina aytebikimna Sirachinin bicha linsera ena nege yekeren ena yalewn endanata meyayaz yasfelgal:: Betekrsteanu, Amlalku , Ye Egziabhear Qal terdto endiqom yalazegajut, yaltezegaje hizb teyzo Lemn hone malet yemikebd ena yemaymesl mehonun betesebochachini eskinineteq aytenewal, ,, Ahun enkuan keqirb gize jemro yehn yemesaselu chigiroch silagatemu Bizu sirawoch tesertewal!....silehulum neger.. Behulu neger Egziabhear yemesgen! Fetena yatenekral, yemiasfelgen bisot tesemtot, lalemetfat, lalemanqelafat,....chigir kemebzatu-menfesawnet bemetfatu, qinat tesemtot yerasun astewatso lemadreg yetenesawn.. Yeminesawn bicha eyetemeleketu agul tekelakay kemehon Befikir ena tiegist tebabro lemesrat ena kewch yalewn netaki megabi mehonin masqom yeBetekrstean gideta neaw,.. Sirachinin ensra! Gena bizu yemetal Qidus Siga ena Demun yetereda ena yeminafq tiwld.. Wetat enafra . Yewetatu chinkilat.. Yeseytanim meselten.. Eyaetemeleketin Gizeachin linwaj yegebal enji Yabatochachinin eyalin Sit endemitebk eyanqelafan masnetequn linilemamed, mewenejajelin Bahri ena maninetachin linaderg Aygebam...Yebqan! Yemimar kewdeqew... Ke telatim yemaral... Wetatun, Tiwldu,...Betesebu ..Sembet timhrt bicha amarach lihon aygebam Wede Agelgilot( bebzat
ReplyDeleteEgziabhear yemigelegelibet ena erasun yemiagelegilibet lizegaj yegebal).. Wede Betu LISAB..Ligotet yegebal ,,,minim yemiansen neger yelem.. Biansenm Geta memchawn beHiwot linasib yegebal, YeEthiopia Tewahido Orthodox betekrsteanachinim Egziabhear yesetatin Yehin yemesaselu Tsegana Bereket Lelawm tiwld ena zega litakaflew enji Lijochwa ene bicha eyalu saytekemubet enditegnu aymeslegnm... Yadelachew ena endeterdut chaina hedew yeteredut minim yehun min be Qinat Yesebkalu.. Egna beHagerachin sinawera ena sinbala Betekrstean lemesrat tarik yehonebet zemen dersenal... Sile Hulum neger Egziabhear yemesgen Alama yenorew yehonal:: egna gin wedelibachin temelisen beteley wetat wegenoche agul ye siga qinat enaqum erasachinin enastekakil::
Kale hiwot yasemalen lebawisete simelalse yeneberw neger New letikem bich marote gitimena zema lemisarute sawoch masetewalune yesetachew
ReplyDelete