Monday, November 4, 2013

ንግሥተ ሳባን በDNA ምርመራ

  
/ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ/

‹‹በግእዝ አቆጣጠር›› በያዝነው 2005 .. ከኅትመት ጽንሱ ተቋርጦ በኢንተርኔት የተወለደውን የደራሲተስፋዬ ገብረአብንየስደተኛው ማስታወሻሳነበው ሰነበትኩ፡፡ ሰቅዞ በሚይዝ ማራኪ አቀራረብ ይህ ጸሐፊከማስታወሻነትወደማስረሻነትየሚያዘነብሉ በተለይ የእኛ ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ላይ እና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ላይ መራር ጥላቻን የሚያሳዩ ምዕራፎችንም አስፍሮአል፡፡ ጸሐፊነቱ ለድርሰት ዓለም እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ባለመሆኑ በእሱ አጠራር እንደነአቡነ አርዮስሊቁ ሳተ ብለን አንደነቅበትም ነገር ግን እንደተጀመረው እኛን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ግን በየዘርፉ ምላሽ መሠጠቱ የሚጠቅም ነው፡፡ /http://www.danielkibret.com/2013/10/blog-post_5157.html/ በዚህ መጽሐፉ የንግሥተ ሳባን ታሪክ Fairy tale ከመሆን ውጪ ፋይዳ የለውም በሚል ጠቅሶታል፡ ስለዚህች ንግሥት ከሰሎሞን የሚበልጠው ጌታችንበዚህ ትውልድ ተነሥታ ትፈርድበታለችማለቱ ብቻ ለእኛ ከተረት ያለፈ ትኩረት እንድንሠጣት ያደርገናል፡፡

ስለዚህ እያሰብኩ ባለሁበት ቅጽበት DNA clues to Queenof Sheba tale የሚል ጽሑፍ St. Jhon በሚል መጽሔት ላይ ድንገት አየሁ፡፡ ጽሑፉ የቢቢሲ ኒውስዋ Helen Briggs ሲሆን 2012 የወጣ ነበር፡፡ ሳይንቲስቶች የንግሥት ሳባ አፈ ታሪክ ምንጩ ምን እንደሆነ የሚያስረዱ ፍንጮች በጥቂት አፍሪካውያን DNA ውጤት ላይ ተጽፎ ተገኘ እያሉ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ከግብፃውያን ከሶርያውያን እና ከእስራኤላውያን ጋር መዛመዳቸውን የዘረመል ጥናት /Genetic research/ እያረጋገጠ ነው፡፡ ይህ ክፍለ ዘመን ደግሞ በታላላቅ ሃይማኖታዊ የጽሑፍ ሥራዎች ላይ የተጠቀሰችው ይህች ንግሥት የሳባን ግዛት ያስተዳደረችበት ጊዜ ነበር፡፡ በአሜሪካ የሰው ልጅ ዘረመል ጥናታዊ መጽሔት /The American Journal of Human Genetics/ ላይ የታተመው ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ ከስድሳ ሺህ ዓመታት በፊት የሰው ልጅ ከአፍሪካ ስላደረገው ፍልሰትም ብልጭታን አሳይቶአል፡፡

ንግሥተ ሳባ
 ይህች ንግሥት በመጽሐፍ ቅዱስ በቁርአን እና በኢትዮጵያው ክብረ ነገሥት ላይ ተጠቅሳለች፡፡ የሳባ ምድር በኢየሩሳሌም እና በሮማውያን ግዛቶች ውስጥ በሚዘልቅ ንግድ የበለጸገ ከዛሬዋ ኢትዮጵያ እስከ የመን የሚደርስ ትልቅ ግዛት ነበር፡፡ ንግሥቲቱም ለንጉሥ ሰሎሞን የወርቅ ሥጦታን ይዛ ኢየሩሳሌምን መጎብኘትዋ ይነገራል፡፡ በርከት ያሉ ጽሑፎች ንግሥቲቱ ከንጉሥ ሰሎሞን ልጅ ስለመውለድዋ የሚያሳዩ ቅሬተ አካላዊ ማስረጃዎች እንዳሉና የሰው ልጆች ታሪክም ከየትም ዓለም ይልቅ ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመልስ መዝግበዋል፡፡ ሆኖም ስለ ኢትዮጵያውያን ዘረመል ግን እስካሁን ድረስ የተነገረው በጣም ትንሽ ነገር ነበር፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ምርምር በማድረግ ላይ የሚገኙት Wellcome Trust SangerInstitute in Cambridge, UK, የሚያስተምሩትፕሮፌሰር ክሪስ ታይለር ስሚዝ ግን BBC News ‹‹የዘረመል ጥናት ታሪካዊ ክስተቶችን ሊናገር ይችላል›› ብለዋል ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያውያንን ዘረመል እና ሌሎች አካባቢዎችን ዘረመል በማጥናት ምናልባትም ከሌዋውያን ሊሆን የሚችል ከየዘርመል ፍልሰት /gene flow/ ከሦስት ሺህዓመታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተደርጓል፡፡ ይህ ጊዜ ደግሞ ከንግሥተ ሳባ ታሪክ ጋር በትክክል የተስማማ ነው፡፡›› ሲሉም ያብራራሉ፡፡ ‹‹ይህ ጥናታዊ ጽሑፍ በሰው ልጅ የፍልሰት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ሚና በተጫወተውናእጅግ አጓጊ በሆነው የዚህ አካባቢ ሕዝብ ታሪክ ላይ የተገኘ ብልጭታ ነው›› ያሉት University of Cambridge and the Wellcome Trust Sanger Institute ዋና ተመራማሪ የሆኑት ሉካ ፓጋኒ ደግሞ ‹‹በዘረመል ጥናት የተገኘው ማስረጃ የንግሥተ ሳባን አፈ ታሪክ የሚደግፍ ሆኖአል፡፡›› ብለዋል፡፡

በዚህ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተሠራ በዓይነቱ እጅግ ሰፊ ሊባል የሚችል የዘረመል ምርመራ ላይ ከዐሥር የኢትዮጵያ አካባቢዎች እና ከሁለት የጎረቤት አፍሪካዊ ሀገራት የተውጣጡ ሁለት መቶ የሚሆኑ ግለሰቦች ዘረመል ምርምር ተካሒዶበታል፡፡ በእያንዳንዱ ዘረመል ላይ እስከ አንድ ሚልየን የሚደርሱ genetic letters ተጠንተዋል፡፡ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ላይ የተደረጉ የዘረመል ጥናቶች በትንንሽ የሰው ልጅ ዘረመል እና በእናት በኩል ያለው የዘረመል መስመር ላይ ብቻ በሚያተኩረው mitochondrial DNA ዙሪያ የተገደበ ነበር፡፡ በፔኒሲልቫኒያ ዩኒቨርሲቲ በጄኔቲክስና ባዮሎጂ ዲፓርትመንት መምህርት የሆኑት / ሳራ ቲሽኮፍ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ ‹‹ኢትዮጵያ በባሕልና ከሥነ ልሳን ዘርፍ አንጻር እጅግ ልዩ ሕብር ያለባት ሀገር ናት፡፡ ከአሁን በኋላ ግን በዚህ አካባቢ ስላለው የዘረመል ሕብርም በጥቂቱም ቢሆን ተረድተናል፡፡›› ብለዋል፡፡

ሳይንቲስቶቹ ዘመኑን በተመለተ ጥርጥሮች እንዳሉአቸው እና ከሦስት ሺህ ዓመታት የጥቂት መቶ ዓመታት ልዩነት ሊኖር እንደሚችልም አልሸሸጉም፡፡ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ዘረመል ላይ ባሉት በሦስት ቢሊየን genetic letters of DNA ላይ ተጨማሪ ጥናት የማድረግ ዕቅድም ይዘዋል፡፡ ጽሑፉ ይኼ ነው እሱ እንደ መግቢያ የተጠቀመበት ግጥም ቁጥር 2 ቨርዥን እነሆ ትውልዷ ነው ቢባል - ከወደ አሜሪካ ከአውሮፓ ከላቲን - ወይ ከኮስታሪካ ስምዋ ባይጠራ- በሐበሻ ሰፈር የሳባዋን ንግሥትታሪክሽ ተረት ነውመች እንላት ነበር!!  /. ./

1 comment:

  1. በርግጠኝነት የዲያቆን ዳንኤል ደቀ መዘሙር መሆን ይቅርና በየግዚው በተለያየ መልኩ የሚያወጣቸውን ተከታትሎ አንቦ ለመረዳት የጠለቀ የቤተከረስቴያን ልጅነት የሚያስፈልግበት ወቅት ይታያል። ሆኖም ለእንደናንተ አይነቱ ብዙም ከባድ ስለማይሆን ጠንክሮ ለቤተክርስቴያናችን እና ለምእሙኑ የሚበጅ የዘመኑን ወጀብ የሚመክት ጽሑፍ ለማቅረብ የምትጀምሩት ያለ ጅምር የድንግል ማርያም ልጅ እኛም አንበን እምነታችንን እንድናጏለምስበት እናንተም ዘላቄ ፍሬየ የምታፈሩ አድትሆኑ ያድርግልን ።በርቱ !

    ReplyDelete