(አንድ አድርገን ጥቅምት 21
2006 ዓ.ም)፡- THE ETHIOPIAN HERALD TUESDAY 29 OCTOBER 2013 ዕትም ገጽ 7 ላይ ይህን ነገር ይዞ ወጥቷል ፡፡
Notice
“KIDUS ATNATEWOS YEWENGEL AGELEGELOT” has applied use this name as a religious institution. Any individual or organization opposing the name is here by requested to report to the Ministry of Federal Affairs and Religious Organization and Association Registration directorate, Office on November 11/2013 at 9:00 AM
Ministry of Federal Affairs
Notice
“KIDUS ATNATEWOS YEWENGEL AGELEGELOT” has applied use the under indicated symbol.
(ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎትየሚል መስቀል ያለው ክብ ምልክት)
Any individual or organization opposing the symbol is here by requested to report to the Ministry of Federal Affairs and Religious Organization and Association Registration directorate, Office on November 11/2013 at 9:00 AM Ministry of Federal Affairs
በጋዜጣው
ላይ በእለቱ ከወጡ አዲስ ለመመስረት መንገድ ላይ ያሉ ስድስት የእምነት ተቋማት ውስጥ አንዱ ‹‹ ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎት›› የሚል ነው፡፡ በዚህ ስምም ሆነ የእምነት መጠቀሚያ ምልክት ላይ ተቃውሞ ያለው አካል ካለ ሰኞ ህዳር 2 2006 ዓ.ም (November
11/2013 at 9:00 AM) ላይ እንዲቀርብ ያሳስባል፡፡
እስከ
2004 ዓ.ም መጨረሻ የፌደራል ጉዳዮች ለመንግሥት ተጠሪ ያቀረበው ሪፖርት ላይ 1164(አንድ ሺህ አንድ መቶ ስድሳ አራት) በላይ
የእምነት ተቋማት ለሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ጥያቄ እንዳቀረቡ ሲያስረዳ ከነዚህ ውስጥ 178 ያህሉ ዝቅተኛውን መስፈርት ስላሟሉ የእምነት
ተቋም እንዲያቋቁሙ ፍቃድ መስጠቱን ያስረዳል፡፡(የ2005 ዓ.ም መረጃ አልደረሰንም) የሀገሪቱ ሕገ መንግስት የእምነት ነጻነትን
ለሁሉም የሰጠ ቢሆንም የሃይኖት ማቋቋሚያ መስፈርቱን ተከትለው የሃይማት ተቋማት እየተቋቋሙ ቢሆንም ቅሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ቅዱስ ተብለው ጽላት ተቀርጾላቸው ፤ ገድል ተጽፎላቸው ቀን ተወስኖላቸው በሚገኙ ቅዱሳን ፤ ጻድቃንና ሰማዕታት ስም
የእምነት ተቋም ለማቋቋም ጥያቄ ማቅረብ ተገቢ ነው የሚል እምነት የለንም ፡፡ ቤተክርስቲያኗም ተቃውሞዋን በተባለው ቀን በፌደራል
ጉዳዮች በመቅረብ ታሰማለች ብለን እንገምታለን ፡፡ ያለበለዚያ ዛሬ በቅዱስ አትናቴዎስ ስም የሚቋቋመውን የእምነት ተቋም ያለ ተቃውሞ
ዝም ብለን የምናሳልፍ ከሆነ ከወራት አልያ ከአመታት በኋላ በተክለሃይማኖት ፤ በቅድስት አርሴማ ፤ በአቡነ አረጋዊ ስም ቤተክርስቲያን
እንደማይቋቋም እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፡፡ አይደለም የእምነትን ተቋም ያህል የንግድ ድርጅት አርማ እንኳን አምታች እና
የቀድሞውን ስሙንና አርማውን ተጠቃሚ ተቋም ስምና ዝና ጋር ተመሳሳይነት ካለው አዲስ ሊቋቋም የታሰበው ድርጅት የስም ወይም የአርማ
ለውጥ እንደሚያደርግ ሕጉ ያስገድደዋል፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢሆን ‹‹
ቅዱስ አትናቴዎስ የወንጌል አገልግሎት›› ተብሎ
ለመቋቋም በሂደት ላይ ያለውን የእምነት ድርጅት የእምነቱ መጠሪያ ስም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቀኖናዋ አስቀምጣ
ታቦት የተቀረጸለት ፤ ገድል የተጻፈለት ፤ ቤተክርስቲያን አንፃ በስሙ የምትሰይምበት ፤ ጳጳሳት የምትሾምበት ፤ ቀን ቆርጣ
የምታስበውን ቅዱስና የታላቅ አባትን ስም ለአዲስ ሃይማኖት ስም መጠቀማቸውን በግልጽ የተቃውሞ ድምጽ በሚሰማበት ቀን የእመነቱ
ተከታዮች ስሙን የሚቃወሙበትን መሰረታዊ ነጥቦችን በመያዝ አልያም ቤተክርስቲያኒቱ በተወካዮቿ አማካኝነት በግልጽ ልትቃወም ይገባታል፡፡
ቤተክርስቲያን በምታከብራቸው የእምነቷ አካል አድርጋ በምትዘክራቸው ቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕታት ስም ሌላ
የእምነት ተቋም ሊመሰረትበት አይችልም ፤ ‹‹አንድ አድርገን›› ከፌደራል ጉዳዮች የውስጥ ሰው ባገኝችው መረጃ
መሰረት ይህን ስም በመጠቀም የእመነት ተቋም ለማቋቋም ያሰቡት መቼም የማይተኙላት የተሃድሶ አራማጆች መሆናቸውን የደረሳት መረጃ
ያመለክታል፡፡ ፕሮቴስታንቶች ‹‹ነጻነት›› ፤ ‹‹Embassy of Heaven›› ፤ ‹‹7000 ሺህ ምርጥ አማኞች›› እና መሰል ስሞችን ለሚያቋቁሙስ
እምነት ስም ሲጠቀሙ ተመልክተናል እንጂ በጻድቃን በሰማዕታት እና በቅዱሳን ስም የእምነት ተቋም ሲመሰርቱ አልተመለከትንም፡፡ አሁን
ግን ተሃድሶያውያን ሌላ ስም መጠቀም እየቻሉ ምዕመኑን እና ቤተክርስቲያኒቱን ለማመስ እና ተመሳስሎ ከመቅረብ በተጨማሪ የቤተክርስቲያኗን
ቀኖና እና ዶግማ ቀስ እያሉ የመሸርሸር የእኛን ስሞች በመውሰድ ሊጠቀሙ እየሞከሩ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስያን አጥቢያ ቤተክርስቲያን በምትሰይምበት
ተመሳሳይ ስሞች ሌላው ተቋም መጠቀም አይችልም ሕጉም አይፈቅድለትም ፤ ለምሳሌ ‹‹ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን›› ፤ ‹‹
ቅዱስ አትናቴዎስ ቤተክርስቲያን›› እያሉ በቤተክርስቲያኒቱ ስር ያሉትን ስሞች መጠቀም ከበስተጀርባ የያዘው አለማ ምን ሊሆን እንደሚችል
ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ቅዱስ
አትናቴዎስ ሐዋርያዊው ከ295-373 ዓ.ም በሕይወት የኖረ ታላቅ ሐዋሪያ አባት ነው ፤ አባ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ፤ በቅዱስ
ማርቆስ መንበር 20ኛ ፓትርያርክ በመሆን ከ326 ዓ.ም. ጀምሮ ለ43 ዓመት አገልግሏል ፡፡ አባ አትናቴዎስ 2ኛ፤ 28ኛ ፓትርያርክ በመሆን
ከ489 ዓ.ም.ጀምሮ 6 ዓመት ከ10 ወር ያህል ቤተክርስቲያንን አገልግለዋል ፡፡ አባ አትናቴዎስ 3ኛ 76ኛ ፓትርያርክ በመሆን ከ1250 ዓ.ም.ጀምሮ 11 ዓመት ከ1 ወር ያህል አገልግለዋል፡፡
ቅዱስ አትናቴዎስ ቀዳማዊ ከታላቁ ርዕሰ ገዳማውያን ከአባ እንጦንስ ዘንድ ሥርዓተ ምንኵስናን
ተምሮ ፈጽሟል፡፡ የአባ እንጦንስን የሕይወት ታሪክ (ገድል) የጻፈውም እርሱ ነው፡፡ አርዮሳውያን በቅዱስ አትናቴዎስ ላይ በግፍ
በተነሡበት ጊዜ ወደ ሮም በመሰደድ ከ339-346 ዓ.ም. ተቀምጧል፡፡ እርሱም በቆየባቸው ሰባት ዓመታት ከአባ እንጦንስ የተማረውን የመነኰሳት
ሕግና አኗኗር አስተምሯቸዋል፡፡ በሮማ ምድርም ሥርዓተ ምንኩስናን ለማስፋፋት የመጀመሪያው አባት አትናቴዎስ ሐዋርያዊ አባታችን
ነበር፡፡
ሁላችን ልንቃወመው የሚገባ ….
ቸር ሰንብቱ
መናፍቃን ገና ሁሉ ነገራችን የኛ ነው ሳይሉን ይቀራሉ ? ቤተክህነቱ እንደው ገና ከ እንቅልፍ እየነቃ ነው
ReplyDeleteThis is one of the great challenges against our church from "Tehadeso". So, Never we allow or keep quite when they are trying to use our forefathers Holy name for their satanic mission. Lets disseminate the information to all and discuss about and get ready to react legally.
ReplyDeleteAmelake Kidusan Betechrestainachinen yetebekelen. Amen