Tuesday, October 22, 2013

በእናቴ ጠባሳ አላፍርም!



ከአባ ዮሐንስ


የእናቴ ጠባሳም ይሁን ማድያት አያሳፍረኝም ውለታዋን ቢያስታውሰኝ እንጂ!!

(አንድ አድርገን ጥቅምት 13 2006 ዓ.ም)፡- ቤተ ክርስቲያን የመከራን ጽዋ መጨለጥ አዲስ ባይሆንባትም የሚያስገርመው በውስጥ ሰው ምቹ ጊዜ ተፈልጎ የላምና የጊደር መስዋእት አቅራቢዎች ለነበሩት የአይሁድ ሊቃነ ካህናት ተላልፎ መሰጠቱ ነው። ከአምስት ገበያ ህዝብ መካከል የአንድ ገበያ ህዝብ ያህሉ የመልኩን ደም ግባት ለመመልከት የሚመላለስ እንደነበረ ታላቁ መጽሓፍ ያወሳል በአንጻሩም የቤተክርስቲያን መስራች የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ምን ያህል ደም ግባቱ ያማረ መሆኑንም ያስጨብጣል።


ምቹ ጊዜ ጠብቆ ሊያስገድለው ይዝት የነበረው ይሁዳ በመካከል ተቀምጦ ከጌታው የቀረበት ነገር አልነበረም ዓሳ እና እንጀራ አበርክቶ ለህዝብ በበረከት ባጠገበ ጊዜ ይሁዳም ሆዱን ሞልቶ ነበር ተአምራትንም በመመልከት ያደንቅ ይገረምም ነበር ሌሎቹም ሐዋርያት ከጌታ ጋር በመሆናቸው መንፈሳዊ ኩራት ይሰማቸው አለኝታቸው በመሆኑም ይወዱት ፍቅራቸውንም በተለያየ መንገድ ይገልጹለት ነበር። ለምሳሌ ‹‹የሰው ልጅ ለሊቃነ ካህናት ተላልፎ ይሰጣል ይሰቀላል ይሞታል›› ባላቸው ጊዜ ይህስ አይሁንብህ ጌታ ሆይ ከማለት አልፈው በተያዘ ጊዜም ሰይፍ ለመምዘዝ አልተመለሱም ይሁን እንጂ ነገሩ እየገፋ በመምጣቱ የሰውን ልጅ ለማክበር በአደባባይ ሲያንገላቱት ልብሱን ገፈው ሲያራቁቱት በጅራፍ የሚያምረውን ደም ግባቱን ሲያደበዝዙት ከከዋክብተ ሰማይ በላይ መቁጠር እስኪሳን ድረስ ሰንበሮች በደም ግባቱ ላይ ሲጋደሙ ያኔ እንወድሀለን ሲሉ የነበሩ ሆዳቸው ስለሞላ እናንግስህ እባክህንማለት ሲማጸኑ የነበሩ ሁሉ በአካባቢው አልተገኙም ነበር ፡፡ ከሐዋርያትም ወገን ይህን መከራ ባዩ ጊዜ 3 ዓመታት በላይ ጌታ ሲሉት የኖሩት ‹‹ሰውየ›› በሚል ተክተው ‹‹የምትይውን ሰውየ አላውቀውም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ደም ግባት ሲኖረው ከእርሱ ጋር ለመኖር መፍቀድ አበርክቶ ሲያበላ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ማለት ደም ግባቱ በመከራ ሲጠፋ በእርሱ ማፈር መሸማቀቅ አላውቀውም ማለትን ስናስብ የዛሬይቱን ቤተ ክርስቲያንን ያስታውሰናል ፡፡ በይበልጥ ውሉደ ክህነት አባቶች ቀሳውስት ዲያቆናትሰንበት ት/ቤትን ሶሻሊስቶች ባደረሱባት እንግልት ቤተ ክርስቲያናችን ጎስቁላና ደምግባቷ ደብዝዞ ስለታየ ሙስናዘረኝነትፖለቲካዊ አመለካከት ተገምደው እያሳረፉባት ካለው የማዳከም ጅራፍ የተነሳ ጠባሳ ቢበዛባትም እናታችን መሆኗን ልንክደ አይደለም ልንዘነጋ አይገባም፡፡ በዚህ ጊዜ በዚህ ሰዓት ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ልንናገር ልንጸልይ ልንመሰክር አልፎም መስዋእትነትን ልንከፍልላት ይገባል እንጂ ፌስ ቡክ መጠቀሚያ አካውንት ከፍቶ ምን እየተባለ ነው? ምን እየተሰራ ነው? እያየን እየሰማን ጠባሳ ያለባት ቤተክርስቲያን እናቴ አይደለችምከችግሯ ተላቃ ከህመሟ አገግማ ደም ግባቷ ባማረ ጊዜ እናቴ ትሆናለች ብሎ ማሰብና ዝምታን መምረጥ አባትም አማኝም አያሰኝም ፡፡ መከራ የሌለባት ቤተ ክርስቲያን መስቀልን የማትሸከም ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ መመስረቷ ያጠያይቃል

የቤተክርስቲያን ልጅ ነኝ ለማለት ምቹ ጊዜ አትጠበቅም ፤ የይሁዳነት ጠባይ ነውበደስታውም በሓዘኑም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን እናታችን ናትበዮዲት ጉዲት ዘመን በግራኝ መሐመድ ዘመን  ሶሻሊቶችም ዘመን ያለችም የመከራ ጸዋ ጨላጯ ባለ ጠባሳዋ ቤተ ክርስቲያን እናታችን ናትግርፋቱ ለእኛ ነውሞቱ ለሕይወታችን ነውትንሳኤው ለትንሳኤያችን ነውከክርስቶስ ጋር ካልሞትን በትንሳኤም መተባበር አንችልምበችግሯ ጊዜ በቤተክርስቲያን ጋር ካልተጠበስን መከራዋን ጌጣችን ካላደርግን የይሁዳ እንጂ የክርስቶስ የክርስትና ልጆች አይደለንም

በእናቴ ጠባሳ አላፍርም !


1 comment:

  1. This is absolutely correct that each Christian has to know and practice. Or else we can not be the follower of Christ and the children of our beloved mother Church.
    Let the Mercy and Blessing of Jesus Christ be with us to really hold His Cross and protect our Church.

    ReplyDelete