Wednesday, October 2, 2013

‹‹ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በኋላ ይቅር ማለት ያለበት ሕዝብ ነው›› የሀገር ሽማግሌ አባቶች

(አንድ አድርገን መስከረም 23 2006 ዓ.ም)፡-  ከዓመት በፊት ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ የተያዘው በተሀድሶ ኑፋቄ አስተምህሮ ሲሰሩ የነበሩ ቡድኖች በአሁኑ ሰዓት ከሳምንታት በፊት እርቅ ለማውረድ በሚል እሳቤ ታች ላይ እያሉ ይገኛሉ፡፡ እነዚሁ ወገኖች ከ2 ዓመት በፊት የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም  እና በአካባቢው አብያተክርስቲያናት ላይ ችግሮች በተፈጠሩበት ወቅት ሕዝቡን አንድ በማድረግ እና በማስተባበር ከምዕመኑ ፤ ከአገልጋዮችና ከአሕጉረ ስብከቱ በኩል ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸውን የሀገር ሽማግሌ አባቶች በሊቀጳጳሱ በኩል ለማግኝት እና ይቅርታን ለመጠየቅ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ሊቀጳጳሱ በእርሳቸው በኩል ይቅርታን እንደሚቀበሉት ነገር ግን ጉዳዩ በሲኖዶስ የተያዘ በመሆኑ መልሱን ከላይ እንዲጠብቁ መልስ የሰጧቸው ቢሆንም ጥያቄያቸውን በአህጉረ ስብከቱ እና በምዕመኑ መካከል በመሆን በወቅቱ የተፈጠረውን ችግር በማርገብ ፤ ጉዳዩን ወደ ጠቅላይ ቤተክህነትና ፓትርያርክ ጽ/ቤት ድረስ በርካታ መኪኖችን በመኮናተር ከ300 በላይ ምዕመንን በማስከተል አቤቱታቸውን በሕጋዊ መንገድ እንዲቀርብ ያደረጉትን በህዝቡ ዘንድ አመኔታ ያላቸውን የሀገር ሽማግሌ አባቶችን ይቅርታን ለመጠየቅ ፤ ሰላም ለማውረድና በእነርሱ በኩል ወደ ምዕመኑ ለመድረስ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ እንደ ብዙዎች አስተያየት ይህ አካሄድ ምዕመኑን በቀላሉ ይቅርታውን እንዲቀበል በተጽህኖ ፈጣሪ የህዝብ ተወካዮች አማካኝነት እንደመምጣት ቆጥረውታል ፡፡ ጥያቄው የቀረበላቸው አባቶች ‹‹ በወቅቱ ብዙ ሰዎች የተደበደቡ ፤ የታሰሩ ፤ የተፈነከቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ምዕመናን ስላሉ እኛ በግል ተጠርተን ይቅር የምንለው ነገር አይደለም ፤ ይቅርታም መጠየቅ ካለበት ከቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በኋላ ሲሆን ይቅርም ማለት ያለበት ሕዝብ ነው እንጂ እኛ ተወካዮች አይደለምን ›› በማለት መልስ እንደሰጡ ከቦታው ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ይህን ጉዳይ እስከ ጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ድረስ መልክ በማስያዝ በተሀድሶነት ክስ የቀረበባቸው ቡድኖች በቀጣይ የሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት ጉዳዩ በአጀንዳ መልክ ተይዞ በቅዱስ ሲኖዶስ እንዲታይላቸው ለማቅረብ ሃሳብ እንዳላቸውም ተገልጿል ፡፡  በርካቶችም ‹‹ይቅርታው›› ከላይ ይሁን ከውስጥ አሁንም ጥያቄ እያነሱበት ይገኛሉ፡፡

5 comments:

  1. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውOctober 4, 2013 at 12:49 AM

    ማዕከላዊነት፣ኢትዮጵያዊነት እና ትውፊታዊ ቆፍጣናነት ቤተክርስትያንዋን ያድናታል። ለዚህ ነው ጠላትዎችዋ ሊከፋፍሏት፣የህዝቡንም ሀሳብ ሊበታትኑት የሚፈልጉት። ለዘመናት የውጭ ሃይሎች ከውጭ ሊያፈርስዋት ያልቻሉትን፣ በአሁኑ ዘመናችን - በዘመነ ወያኔ/ዘመነ ዓረብ፤ ውስጥዋ ፈልፍሎ የመግባትና መረባቸውን የመዘርጋት እድል አግኝተው ሲያምስዋት ነበር። ሲኖዶሱ ተሰደድኩ/አልተሰደድኩም ብሎ መዘበራረቁ ራሱ ቤተክርስትያኒቱን ክፉኛ አቁስሏታል። ይኼ ቁስል ተሃድሶ ነኝ ባዮቹን ብዙኛ ጠቅሟል።እንዚ ሰዎች ይቅርታ ከተባሉም፣መደረግ ያለበት በአደባባይ ነው እንጂ በግል ጥቅምና በጓደኝነት በተያያዙ ግለሰቦች እጅ በጓሮ በር መሆን የለበትም።
    የማንም ግለሰብ ማንነትና ዝና ከቤተክርስቲያኒቱ ህልውና እና ክብር ቀድሞ ሊታይና ትኩረት ሊያገኝ አይገባም። ይቅርታ ጠያቂዎቹ በጉባዔ ፊት ራሳቸውን ዝቅ አድርገው፣ተንበርክከው እና ድንጋይ በትካሻቸው ላይ ተሸክመው፤ተሃድሶ የተባሉበትን ነጥቦች ሁሉ በዝርዝር ጥፋተኝነታቸውን አምነውበት ነው ይቅርታ መባል ያለባቸው። ከዛም ከመስበክ ስራቸው ለተወሰኑ ጊዜያት መገለል አለባቸው። ከዚያም በሂደት እየታየ ቀስ በቀስ ወደ ስብከቱ ጎራ ሊቀላቀሉ ይችላሉ። ማዕከላዊነት፣ኢትዮጵያዊነት እና ትውፊታዊ ቆፍጣናነት ቤተክርስትያንዋን ይጠብቃታል። እንደውም ለወደፊቱ ቤተክርስትያኒቱ አንድ ትውፊታዊ የስነ-ጥበብ ማዕከል ቢኖራት፤ ይኼም መዓከል ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የስነ ስዕል፣ የስነ መዝሙር፣ የስነ ፅሁፍ፣ የተግባረ ዕድ ወዘተርፈ መምሪያዎች ቢኖሩት፤ ቢያንስ ቢያንስ በመዝሙር ረገድ
    እንኳን ማንም ህገ ወጥ እየተባባለ እጅ ሊቀሳሰር አይችልም። ምክናያቱም ሁሉም ዘማሪዎች በዚህ መዓከል ስር የሚተዳደሩ ስለሚሆን።

    ReplyDelete
  2. Woooooooooo this thing makes clear
    every thing,are you guys do you have
    bible on your hands,or still you read
    that stereo type books this describes
    You who you guys are?

    ReplyDelete
  3. 10/05/13
    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡
    ሰላም ጤና ይስጥልኝ አንድ አድርገኞች፡፡ የእግዚአብሔር በረከት ይደርባችሁ፡፡ይቅርታ!!! የቤተ ክርስቲያናችን መንገዷ ቢሆንም
    ይሄ የሃይማኖት ዕፀፅ ጉዳይ ነው፡፡ዛሬ የሚሰሟቸውና የሚተማመኑባቸው ባለመኖራቸው ይህቺን ስልት ይዘው ቀርበዋል፡፡ ተነካሁ
    ብሎ ስንት ፍርድ ቤት የተደረሰው በማናለብኝነት የተማመነውን ተማምኖ ነበር ዛሬ ስልት ቅየራ፤በስሩ ስንት ዘማሪያን መንገዳቸውን
    አስቷቸዋል፡፡የቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት በማይፈቅደው ሀውልት አስተክሏል፡፡ዛሬ ቀበሮዋ የበግ ለምድ ለብሳ ስትመጣ ቆዳዋን መግ
    ፈፍ ሲገባ የምን መልፈስፈስ ነው፡፡ለሁሉም ቤተ ክርስቲያናችን አንድ ህግ ነው ያላት ስለዚህ እባካችሁ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ጠይ
    ቃችሁ ወይም የስብከት ማህበር አባላት ፈልጋችሁ የመናፍቃን ይቅርታ ምን እንደሚመስል ብንረዳ ለወደፊትም ዕውቀት ይሆነናል፡፡
    አመሰግናለሁ፡፡

    ReplyDelete
  4. Abatoch Betam Tinkakie Yadirgulin!!!

    ReplyDelete
  5. Sewn tewut esk Egziabiherin firu blogu lay post yaderegew erasu meliso degagmo comment yadergal.Lenegeru Egziabiherin bitifera Besime Abi Wowold Womenfesikidus bleh jemireh kifat ataworaw Amlak lib yistachihu!

    ReplyDelete