Wednesday, October 9, 2013

ጆሮ የለመደው ዜና ‹‹የአብያተ ክርስቲያናት ቃጠሎ››


ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ  ባወጣው መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 . ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት መውደሙን ጠቅሷል።ፓርቲው እንዳለው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ ታውቆ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሠድ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ ጆሮ አላገኙም፡፡
ጉዳዩንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረትም አለመሳካቱን አትቷል፡፡በአንድ አካባቢ በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ በቤተክርስትያን ላይ የማውደም ተግባር ስምንት ጊዜ ሲፈፀም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አንድም ቀን አለመገለፁና በመንግስት በኩል መፍትሔ አለመስጠቱ ፓርቲውን እንዳሳሰበውም ተገልጿል፡፡

አንጋጫ ኪ/ምህረት ፣ ዳገት ሚካኤል ፣ የደርበን ሚካኤል ፣ ዋሻ መድሀኒዓለም ፣  መንክር ማሪያም ፣ ቀዝቀዝ ገብርኤል ፣ ደማም   ኢየሱስ  እና ምስለ  ዋሻ  ጊዮርጊስ  ሙሉ  በሙሉ  እና  በከፊል  መውደማቸውን  ከፓርቲው መግለጫ  ለመረዳት  ተችሎአል።
ሰማያዊ ፓርቲ በመንግስት በኩል ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት የቃጠሎው ምክንያት ተጣርቶ ድርጊቱን የፈፀመው አካል በህግ ተጠያቂ እንዲሆንና ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገለፅ እንዲሁም በሕዝብ አመኔታ የሚጣልባቸው ተቋማትን የማውደም ተግባር ወደፊትም እንዳይደገም በመንግስት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ በአፅንኦት ጠይቋል።
ጉዳዩን በማስመልከት ለምስራቅ ጎጃም የባህልና ቱሪዝም አንድ ሰራተኛ በመደወል ያነጋገርናቸው ሲሆን እሳቸውም አብያተ ቤተክርስቲያናቱ መቃጠላቸውን አረጋግጠውልናል። ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉት እኝህ ሰራተኛ፣ በቃጠሎው የተነሳ በህዝቡና በመንግስት በኩል እንዲሁም በህዝቡና በቱሪዝም ኮሚሽን በኩል ውዝግብ ተነስቷል።
መንግስት ድርጊቱን የፈጸሙት የሙስሊም አክራሪ አባላት ናቸው ብሏል፣  የባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤትም የችግሩ መነሻ በውል ባይታወቅም በአክራሪዎች ምክንያት እንዳልሆ በውል እንደሚያምን አክለው ገልጸዋል። የመንግስት አካሄድ ትክክል አይደለም ያሉት ሰራተኛው፣ ህዝቡ መንግስትን አናምንም ባይል ኖሮ ችግሮች ሊፈጠሩ ይችሉ ነበር ብለዋል።አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ጉልላታቸው አካባቢ እንደተቃጠለ፣ ታሪካው ቅርሶች ሳይወድሙ በህዝቡ ጥረት እንደተረፉ እኝሁ ሰራተኛ በዝርዝር አስረድተዋል።
የ‹‹አንድ አድርገን›› ሃሳብ
(አንድ አድርገን መስከረም 30 2006 ዓ.ም)፡- በአሁኑ ሰዓት ከጊዜ ወደ ጊዜ ባልተለመደ ሁኔታ ቁጥሩ እየጨመ የመጣው የአብያተክርስቲያናት የቃጠሎ ዜና ነው፡፡ ጥያቄውን ቤተክርስቲያን ማንሳት ሲገባት ከጉዳዩ ርቀው የሚገኙ ወገኖች ጥያቄውን እያነሱልን ይገኛሉ፡፡ ከ1997 ዓ.ም ወዲህ ባሉት 9 ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ15 የሚበልጡ አብያተክርስቲያናት የእሳት ቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸዋል ፤ ነገር ግን ከሁለት ያላነሱ ቃጠሎዎች ብቻ በማን አማካኝነት እንደደረሰ የሕግ መስመሩን ተከትሎ ውሳኔ ሲሰጥባቸው አብዛኞቹ እንደተዳፈኑ ቀርተዋል ፤ ምዕመኑ ቤተክርስቲያን ሲቃጠል አልቅሶ ብር ከማዋጣት ይልቅ በማን እንደተቃጠለ ለማወቅ የሚያነሳው ጥያቄ አለመኖሩ ነገሩን ተደጋጋሚ እንዲከሰት እያደረገው ይገኛል፡፡
ጥቅምት 14 2005 ዓ.ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተለየ ስሙ አጉስታ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በጠራራ ጸሀይ እንደ ጧፍ ተንቦግቡጋ ስታበቃ የደብሩ አስተዳደር ፤ ሃገረ ስብከቱ እና ጠቅላይ ቤተክህነት ጉዳዩን ወደ ፖሊስ ይዘው አለመሄዳቸው ፤ ምርመራ እና ማጣራት እንዲደረግ ከማድረግ ይልቅ የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ላይ ብቻ መሰማራታቸው በርካታ ምዕመናንን ቅር አሰኝቷል ፤ ዘግይቶም ቢሆን ጥያቄ ቢነሳ መልስ ያላገኝ የውሃ ሽታ ሆኖ ቀርቷል ፤ በወቅቱ በሳምንት ጊዜ ውስጥ 700 ሺህ ብር መሰብሰብ የቻሉ ቢሆንም ቆይቶም ቢሆን ከተሰበሰበው ብር ውስጥ 193 ሺህ ብር መባከኑን የሰንበት ተማሪዎች እና የአካባቢው ወጣቶች ለክስ ወደ ሃገረ ስብከቱ ባቀረቡት መረጃ ለማወቅ ተችሏል ፤ ይህም ቢሆን መልስ የሌለው እንዲጣራ ያልተፈለገ ጉዳይ ሆኖ አልፏል ፡፡
 በርካታ ምዕመናን ቤተክርስቲያናቱን ከበው በሚገኙበት ቦታ ላይም አብያተ ክርስቲያናት ይቃጠላሉ ፤ ምንም ምዕመን የሌለበት ቦታ ላይም አብያ ክርስቲያናት ይቃጠላሉ ፤ ከነዚህ ቃጠሎዎች ጀርባ እነማን እንዳሉ ለማወቅ ቤተክርቲያኒቱ ከሕግ አካላት ጋር ተባብራ መስራት ስውር ሴራዎችንም ቀድማ ማክሸፍ ይጠበቅባታል ፤ የቤተክርስቲያን ቃጠሎ ዜና ጆሯችን እንዲለምደው እኛም መፍቀድ መቻል የለብንም ፤ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ ቀድሞ መደረግ ሲገባው ፤ ሆኖ ከተገኝም አስፈላጊው መጣራት መደረግ መቻል አለበት የሚል እምነት አለን፡፡
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን

4 comments:

  1. where is synod ? where is the diocese bishop ? I think they already left their responsibility. I do not beleive Ethiopian bishops are take care their church. Most of them are under government political game. They are not standing for justice , peace. They are talking but their are not practicing it. Now a days other secular people are standing for justice and they are in jail where as, Ethiopian orthodox bishops are a afraid talking and practicing a bout justice peace and truth. I d o not trust that you call it bishops . They are standing for only mederawe kebere

    ReplyDelete
  2. What are you talking about it?first thing
    is first,do you known the orthodox church how
    Many members they turn their face to
    Other religion.if you don't know it
    More than 7,000,000 .if you keep doing what you doing for the next 5-10
    Years you goon loose closest to 8-10,
    000,000.you can guess who it looks like within 20-30 years the church building it goon be for rent to do something odd stuff.or it goon turn to
    museum's.take my word it is not far it's,
    near future.whose fault is that?that you
    Guys fault,you know where you go in,
    but you dragging a lot of people to heel.

    ReplyDelete
  3. muselyemn bcha anmelket lezeh dergit kerstyan nene yemiilute semea kerstiyan heymmanotochm kete tyaqinet yeraqu aymeselenem.

    ReplyDelete
  4. Are you a true orthodoxy?if you are why you don't post on my comments
    I posted a week ago?you known what
    I am token about.show your self to the
    world.I want you to post on your blog
    If not I goon post it on my way.

    ReplyDelete