Saturday, October 12, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመገኝት ጸሎት አደረጉ

(አንድ አድርገኝ ጥቅምት 2 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ነገ ጥቅምት 3 2006 ዓ.ም ከናይጄሪያ  ጋር ላለባቸው ወሳኝ ጨዋታ ትላንትና አርብ አመሻሹ ላይ ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በመሄድ አምላክ ድሉን እንዲያጎናጽፋቸው ጸሎት አድርገው ወደ ማረፊያቸው ኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ተመልሰዋል ፡፡ ከሳምንት በፊት ዴቪድ ማርክ የተባሉ የናይጄሪያ ሴናተር መላው ናይጄርያዊ ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገውን ጨዋታ ለማሸነፍ እንዲያበረታታ በካቶሊክ አማኞች ለ9 ቀናት የሚዘልቅ የፀሎት ስነስርዓት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ በአሁኑ ሰዓት በርካቶች በአዲስ አበባ እና በበርካታ ክልል ከተማዎች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ማሊያ ስካርፍ እና እጅ ላይ የሚደረጉ ማጌጫዎችን በመግዛት ቡድኑን ለመደገፍ ከፍተኛ ዝግጅቶችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ባሳለፍነው የአፍሪካ ዋንጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንዲት ጎልን ብቻ አግብቶ ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጎሏ መገኛ የቅዱስ ገብርኤል ወዳጅ 19 ቁጥር በመልበስ የሚጫወተው አዳነ ግርማ መሆኑ አይረሳም፡፡ 

የኢትዮጵያ አምላክ ይርዳችሁ 

2 comments:

  1. ቀድሞውንም ሁላቸንም ወደአምላካቸን ወደመድሃኒታችን እየሱስ ከርስቶስ ወደናታቸን ወደ ቅደስትድንገል ማርያም ፀሎታቸን አቅርበን ቢሆን ኖሮ የት በድረሰን ነበር አሁንም መልካም አና ደስ የሚል ነው የሚሻለውን የመርጣቹህት ቀደሞውንም ቢሆን አንኩአኩ የከፍትላችሁአል ፍልጉ ይስጣቹአል ተብለን ነበር ነገር ግን ጆሮችንን አልከፍት አልን አሁንም ዓለመሸም ድካማውን የሚያነሳ አምላክ ክንዱ ከናንተጋር ይሁን ጎልያድን በትንሽ ደንጋይ የጣለ የዳዊት አምላክ ከናንተ ጋር ይሁን አሜን

    ReplyDelete
  2. ባለፈውም ለአንድ ጎል አሁንም ለአንድ ጎል ነው የፀለዮት

    ReplyDelete