በመልካሙ ተክሌ
(አዲስ
አድማስ ጥቅምት 16 2006 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን “መጽሐፈ ቅዳሴ” ወደ
ኦሮምኛ ቋንቋ ተተረጎመ፡፡ ለብዙ ዘመናት “መጽሐፈ ቅዳሴ”ን በግእዝ እና በአማርኛ ስትጠቀምበት የቆየችው
ቤተክርስትያኗ፤መፅሃፉን በኦሮምኛ ማስተርጎም የጀመረችው በ1999 ዓ.ም እንደሆነ ታውቋል፡፡ የመጽሐፉ መተርጎም በኦሮሚያ ክልል
ላሉ አብያተ ክርስትያናት በኦሮምኛ ለመቀደስ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡ የቤተክርስትያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እያካሄደ ባለው የጥቅምት
ምልዐተ ጉባዔው ትኩረት ከሰጣቸው ዋና አጀንዳዎቹ አንዱ ስብከተ ወንጌልን ማዳረስ እንደሆነ የገለፁት ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ
አቡነ ማትያስ፤ የመጽሐፉ ሕትመት እንዲቀላጠፍ ትዕዛዝ እንዳስተላለፉም ለማወቅ ተችሏል፡፡ “መጫፈ ቂዳሴ”
በሚል ርዕስ የተተረጎመው የኦሮምኛ መጽሐፉ፤በቅርቡ ዝግጅቱን የተቀላቀሉትን ብፁዕ አቡነ ዮሴፍን ጨምሮ፣ በርካታ ጳጳሳት ተሳትፈውበታል፡፡
መጽሐፉ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት እየታተመ ሲሆን በዚህ ሳምንት ከተጠናቀቀ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ መዝጊያ ላይ ሊመረቅ
እንደሚችል ታውቋል፡፡
ይኼን ጊዜኮ በላቲን ቃላት ይሆናልኮ የተፃፈው ? አይደል ? ይኼ ቤተክርስትያንዋንና አገሪቱን የሚያኩራራ ሳይሆን ወደ በለጠ ግርግርና ልዩነት የሚሰድ ነው። የውጭ ፖሊስ
ReplyDeleteየሚከተለው መንግስት የሚጠቀምበት ዘዴ ነው።አማርኛ የአማራ ብቻ ቋንቋ ነው/ነበር የሚለውን ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ኦርቶዶክስ ሃሳብ የሚያራግቡ ቡድኖች የነደፉት ዕቅድ ነው።
Jaalattes Jibbites Oromoon Siibiita !!!
DeleteI am very Happy. Thanks God.
ReplyDeleteThis comment has been removed by the author.
ReplyDeleteDes yemil zena new! Egziabher yetemesegene yihun. Wede lelochim kuankua bekirbu endemiteregom tesfa adergalehu!
ReplyDelete