ከኃይለሚካኤል፥
ኅዳር ፱ ቀን ፪፲፻፮ ዓ. ም.
ከእስልምና እምነት መምጣት በፊት ዐረቦች የሚኖሩት መካ፣ ያትሪብ፣ መዲና
ወዘተ ተብለው ይጠሩ በነበሩ ሠፈሮች አካባቢ ነበር። ዐረቦች የአስተዳደር ሥርዓት ፣ የህግ ሥርዓት ወይም የእደ ጥበብ ስምሪት አልነበራቸውም። መንግሥትና መንግሥታዊ
አስተዳደር የሚባል ነገርም አያውቁም ነበር።[1]
ቁሬሺ፣ ባኑ ሃሺም፣ ባኑ ኡማያ ወዘተ በሚባሉ ጎሳዎች ተለያይተው ግን ይጣሉ ነበር።[2]
ጣዖት አምላኪዎችም ነበሩ። ካባ የተባለ ድንጋይም ያመልኩ ነበር።
እስከ አራት መቶ ዓ.ም. አካባቢ ዐረቦች ለሚናገሩት ቋንቋ መፃፊያ ፊደል አልነበራቸውም። ከእስልምና መምጣት አስቀድሞ በንግግር
ግጥም መፎካከር የዐረቦች ባህል ነበር።[3]
እጅግ በጣም ግጥም የሚገጥመውን ሰው መጅኑን እያሉ ይጠሩት ነበር። ዐረቦች ከእስልምና በፊት የነበረውን ዘመን ጃሂሊያ ወይም
የድንቁርና ዘመን ብለው ይጠሩታል።
በዚህ
ጊዜ ነበረ አንድ ሙሀመድ የሚባል ዐረብ መካ አጠገብ በሚገኜው የሂራ ኮረብታ
ላይ ሳለሁ ጅብሪል ነገረኝ ብሎ አዲስ እምነት በአቅራቢያው ላሉ ሰዎችና ለዘመዶቹ የሰበከው። በልዩ ልዩ የምዕራባዊ
ትረካዎች
እንደሚነገረው ሙሀመድ በሂራ ኮረብታ ላይ ጅብሪል ነገረኝ ካለበት ጊዜ በፊት እሱ በሚኖርበት አካባቢ ክርስትናን
ለማስፋፋት
ክርስቲያኖች ብቅ ይሉ እንደነበረ ይነገራል። ከነዚህም ውስጥ ዋናዎቹ ኢትዮጵያውያን ነበሩ። ከኢትዮጵያውያንም መካከል
የሂመራ
(የየመን) ንጉሥ አብርሃ ዐረቦች ወደ ሰንዓ መጥተው በሰንዓ የተገነባውን ትልቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ
ክርስቲያን ተደብቀው በመጸዳዳት ባረከሱ ጊዜ ዐረቦቹን ለመቅጣትና የመካን የካባ ጣዖት ለማፍረስ ሥንቅ በዝሆኖች
ጭኖ ያደረገው ዘመቻ ይታወሳል።[4]
ሙሀመድ ይዞት ለተነሳው እምነት መሠረተ ሃሳቡን ያገኘው ክርስትናን ለማስፋፋት እሱ ወደሚኖርበት አካባቢ ከሄዱ ኢትዮጵያውያን
የወንጌል አስተማሪዎች መሆኑን በእስልምና እምነት በተለይም
በቁርአን ውስጥ ያሉ ጭብጦች ያመለክታሉ።
የእስልምና እምነት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ “ኢሳ” የሚባል ስም ነው የተሰጠው።
በሌሎች አገሮች የነበሩ ወንጌላውያን ኢየሱስ ክርስቶስን፥ “የሽዋ” ወይም “ሄሱስ” ወይም “ጀሽዋ” ወይም “ጂሰስ” ወይም
“አየሱስ” እያሉ ነበር የሚጠሩት። በእስልምና ውስጥ ላለው “ኢሳ” ለሚለው ቃል በጣም የሚቀርበው የግዕዙ “ኢየሱስ” ሲሆን
ቀጥሎም የግሪኩ “አየሱስ” ነው። ሙሀመድ ቃሉን ከግዕዙ ወይም
ከግሪኩ መውሰዱን ለመለየት ቀላሉ ማነጻጸሪያ ሙሀመድ “ማርያም” የሚለውን ቃል ከየት እንዳገኘው መለየት ነው። በእስልምና
“ማርያም” የሚለው ቃል ድንግል ማርያምን ለመጥራት የሚጠቀሙበት ሲሆን ቃሉ በግሪክ “ማሪያ” የሚል ሲሆን በግዕዝ ደግሞ
“ማርያም” ነው። ለድምዳሜ በቂ ባይሆኑም ከነዚህ አጠራር በቀላሉ
ሙሀመድ ቃሉን ከግዕዝ ሰዎች እንዳገኘው መንገዱን ያሳያል። እብራይስጥና ግዕዝ ተቀራራቢ በመሆናቸው ምክንያት አጋጣሚውን
በመጥለፍ አንዳንድ ታሪክን ለመሠሪ ዓላማ ለመጠቀም የተነሱ
ምዕራባውያን እና አይሁድ ነን ባዮች ሙሀመድ የእስልምና እምነትን መሠረተ ሃሳብ ያገኘው ከአይሁዶች ነው ለማለት ይቃጣቸዋል።
ነገር ሙሀመድ ሃሳቡን ከአይሁዶች እንዳላገኘው ብዙ ማስረጃወችና አመልካቾች አሉ። በመጀመሪያ አይሁድ በኢየሱስ ክርስቶስ
አያምኑም። ስሙንም አይጠሩም። እንኳን አምላክ ነቢይ ነውም አይሉም። ቅድስት ድንግል ማርያምንም በእምነታቸው አያውቋትም።
በተጨማሪ “ኤልያስ” የሚለውን መጠሪያ እስላሞች የሚጠሩት እንደ
ግዕዙ “ኤልያስ” ብለው እንጂ እንደ እብራይስጡ “ኤልያሁ” ብለው አይደለም። በተለይም ደግሞ የእስላሞች ቁርአን መጠሪያው
“መጽሐፍ” ተብሎ ነው። “መጽሐፍ” የዐረብኛ ቃል አይደለም ከግዕዝ ውጭ በሌላ ቋንቋ ውስጥም አይገኝም። እስልምና ቃሉን የወሰደው ከግዕዝ ነው።
ከሁሉም በላይ ደግሞ አዲሱን እምነቱን እንዳያስፋፋ በመካና በመዲና ተቃውሞ
ሲያጋጥመውና በዳሩል ናድዋ የተሰበሰቡት የቁሬሺ ጎሳ ባላንጣዎቹ ተከታዮቹን ሊገድሉ ሲያሳድዷቸው ፥ ሙሀመድ ለተከታዮቹ፣ “ፍትህን
ሳያጓድል የሚያስተዳድር ደግ ንጉሥ በእውነት ምድር በሐበሻ አገር ይገኛልና ወደ እርሱ ሂዱ። ያስጠጋችኋል።”[5] አላቸው። ተከታዮቹም ወደ አክሱም ተሰደዱ። ንጉሠ ነገሥቱም ተቀብለው
አስትናገዷቸው። እዚህ ላይ ትኩረት የሚያስፈልገው “የሐበሻው” ንጉሥ ደግ መሆናቸውን ማን ነገረው? ፍትሕን ሳያጓድሉ የሚፈርዱ
መሆናቸውንስ እንዴት አወቀ? የሚለው ጥያቄ ነው። ከአይሁድ ወይም ከግሪክ ወይም ከፋርስ ወደ ዐረብ አገር የሚመጡ ሰዎች ስለ
“የሐበሻ” ንጉሥ ደግነት ሊነግሩት አይችሉም። ስለ ኢትዮጵያ ንጉሥ ደግነት ለሙሀመድ ሊነግሩ የሚችሉት ከኢትዮጵያ ወደ ዐረቦች
ሠፈር የሄዱ ኢትዮጵያዊ የክርስትና ተከታዮች ወይም የወንጌል መምህራን ናቸው። እንግዲህ እነዚህ መረጃዎች የሚያሳዩት ሙሀመድ እስልምናን ለወገኖቹ
ለመስበክ መነሻ የሚሆነውን ትምህርት ያገኘው ከኢትዮጵያውያን መሆኑን ነው።
የሙሀመድ
ተከታዮች አክሱም እንደደረሱ መልካም መስተንግዶ እንደተደረገላቸው የዐረብ
ተራኪዎች እራሳቸው ዘወትር ይመሰክራሉ። በተለይም ደግሞ ቁሬሺ የሚባሉት የሙሀመድ ተቃዋሚዎች አክሱም ድረስ ለንጉሠ
ነገሥቱ እጅ
መንሻ ይዘው በመምጣት በሽሽት የመጡት የሙሀመድ ተከታዮች
ወንጀለኞች ናቸውና ስጡን፣ ወደ ዐረብ አገር መልሰን እንውሰዳቸው ብለው ሲጠይቋቸው ንጉሠ ነገሥቱ የሁለቱንም ወገን
ቃል ካዳመጡ
በኋላ ስደተኞቹን አሳልፌ አልሰጥም ማለታቸው እስካሁን ይነገራል። እነዚህ የሙሀመድ ተከታዮች የሆኑ ስደተኞች ወደ
ዐረቦች አገር
ቢመለሱ አደጋ ላይ እንደሚወድቁ ያዩት ነጉሠ ነገሥቱ ስደተኞቹ በሂመራ (የመን) እንዲሠፍሩና እንዲኖሩ ፈቀዱላቸው።
አሁንም
እዚህ ላይ ከላይ የተጠቀሱት ነዳጅ ፈላጊ ሃሰተኛ ምዕራባዊ ተራኪዎችና አይሁድ ነን ባዮች ከእስልምና በፊት የመንን
ፋርሶች
አጥቅተው ይዘዋት ነበር የሚል ሃሰት ይተርካሉ። ከነሱ የሃሰት ትረካ ሌላ እነሱ ለሚሉት ነገር ጭብጥ ማስረጃ የለም።
የመን
የኢትዮጵያውያን ምድር እንደነበርችና በውስጧም ከኢትዮጵያውያን በቀር ዐረብ የሚባል ጎሳ እንዳልነበረባት፣ ዐረብኛ
ቋንቋም እንዳልተነገረባት ይልቁንስ የሂመራ ሰዎች የሚናገሩት ቋንቋ፣ የሚጽፉትም ጽሁፍ ግዕዝ እንደነበረ፣ ባህላቸውም
“የሐበሻ” እንደነበረ የሚያረጋግጡ በጣም በርካታ ማስረጃዎች አሉ።
የሙሀመድ ተከታዮች በኢትዮጵያ ከተሰደዱ በኋላ ጊዜው ሲረጋጋ አንዳንዶቹ እየተመለሱ እስልምናን አስፋፉ። ከሞት አፋፍ
ላይ ደርሶ
የነበረው እስልምና በኢትዮጵያው ንጉሥ ደግነት ምክንያት እንደገና አንሰራራ።
እንግዲህ ይህን የመሰለ መስተንግዶ የተደረገላቸው ዐረቦች ግን እስልምናቸውን
ሲያስፋፉም ሆነ ሲገድሉ፣ በመሬት ንጥቂያም ላይ ሲሰማሩ ርኅራኄ ያደረገችላቸውን ኢትዮጵያ በርኅራኄ አይን አይተዋት አያውቁም።
ብዙ ዐረቦች “ኢትዮጵያ ስላስጠጋቻችሁ እሷን አትንኩ” ብሎ ሙሀመድ ተናግሯል ሲሉ ይደመጣሉ። ይሁንና ከእስልምና በኋላ ዐረቦች
ኢትዮጵያን ሳይነኩ የሰነበቱበት ዘመን የለም። ከእስልምና ማንሰራራት በኋላ
ኢትዮጵያ በእስልምና የደረሰባትን ውድቀት ሲመለከቱ ንጉሠ ነገሥቱ ለነዛ ለተሰደዱ ዐረቦች ያደረጉላቸው መስተንግዶ
ከደግነትም አልፎ የየዋህነት እንደነበር አዙሮ ለሚያይ ሁሉ ግልጽ ሆኖ ይታያል። ንጉሠ ነገሥቱ እጃቸውን ዘርግተው ዐረቦቹን
መቀበላቸው ለኢትዮጵያ ተናዳፊ እባብን እጅ ዘርግቶ እንደመቀበል ነው የሆነባት።
የመንን ወሰዱ። ኢትዮጵያውያንን አረዱ። የቀሩትንም መንገድ ላይ ጣሏቸው።
ከተደረገላቸው ከዚህ ሁሉ ቸርነት በኋላ ዐረቦች እስላምናን ለማስፋፋትና
የሌሎችን መሬቶች ለመንጠቅ ሲሰማሩ የመጀመሪያ ሰለባ ያደረጉት የኢትዮጵያን አውራጃ ሂመራን (የመንን) መውረርና የራሳቸው
ማድረግ ነበር። ዐረቦች በሂመራ በኢትዮጵያውያን ላይ የሠሩት ግፍ
ምዕራባውያን አፍሪካውያንን በባርነት ቀንበር ከገዙበት ግፍ ቢበልጥ እንጂ አያንስም። ዓረቦች ሂመራን (የመንን)
ሲወሩ መጀመሪያ በሰንዓ የሚገኘውን እጅግ የተዋበውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ነበር ያፈረሱት። ክርስቲያኖችንም አረዱ።
የቀሩትን ኢትዮጵያውያን አስገድደው አሰለሟቸው። በባርነትም ገዟቸው። የመንንም አጥለቀለቋት። እጅግ የሚዘገንኑ ግፎችንም
በኢትዮጵያውያን ላይ ፈጸሙባቸው። ልጆቻቸው ታሪካቸውን እንዳያውቁ አደነቆሯቸው። የሚበሉት፣ የሚጠጡትና የሚለብሱትም
አሳጧቸው። አክሃዳም (ጠራጊወች) የሚል ስምም አወጡላቸው።
አክሃዳሞች ከሽንት መጥረግና ከጫማ ማጽዳት ውጭ ሌላ ሥራ
አይፈቀድላቸውም፡፤ ልጆቻቸውም አይማሩም። ዐረቦች “እቃህን ውሻ ቢነካው እጠበው፤ አክሃዳም ከነካው ግን ጣለው” የሚል ፈሊጥ
አውጡ። ዐረቦች አክሃዳም እያሉ የሚጠሯቸውን ሥራና ትምህርት ብቻ ሳይሆን የከለከሏቸው ሰው መሆንን ጭምር ነው።
ከየመን ወረራ በኋላ ዐረቦች እስልምናን በማንገብ የሌሎች ሰዎችን መሬቶች ለመንጠቅ
ወደ ሰሜን አፍሪካ፣ ወደ መካከለኛው ምስራቅና ወደ ፋርስ ዘመቱ። የተከላከሏቸውን በጎራዴ እያረዱ ገደሉ፣ የቀሩትን እስላም
አደረጓቸው፣ መሬታቸውንም ሁሉ ወሰዱ። በተለይ ጥቁሮችን በማጥፋት ከሲሶ በላይ የሚሆነውን የአፍሪካ መልክአ ምድር በንጥቂያ
ወሰዱ። ኢትዮጵያን በዙሪያዋ ከበቧት። በግድም በውድም ብዙ ኢትዮጵያውያንን አሰለሙ። በዳር ድንበርም በማህል አገርም ያሉ
ኢትዮጵያውያንን ካሰለሙም በኋላ የክርስቲያን መንግሥት ስለሆነ ለመካከለኛው መንግሥት አትገዙ፣ ጎጦቻችሁንም ከመካከለኛው
መንግሥት ገንጥሉ የሚሉ ፋትዋዎችን በመደንገግ ሙስሊም የሆኑትን ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ላይ ለጦርነት በማነሳሳት ኢትዮጵያን
በአመጽ ለብዙ መቶ ዓመታት አስጨነቁ። የባህር በሮቿንም ያዙ።
ዐረቦች ቆስጠንጥኒያ ተብሎ የሚጠራውን አገር በንጥቂያ ከወሰዱ በኋላ ኦስማንየ
የሚባል የቱርክ የእስልምና መንግሥት ተቋቁሞ እሱም በመስፋፋትና
እስልምናን በማስፋፋት ብዙ የዓለም ክፍሎችን ይቆጣጠር ጀመር።
ኦስማንየ የተባለው የእስልምና ቀንበር ጫኝ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን መሣሪያ በማስታጠቅ
ኢትዮጵያን ለብዙ አመታት በአመጽና በጦርነት አደቀቁ። በተለይም
አህመድ ግራኝ በመባል የሚታወቀውን ሙስሊም በማስታጠቅ ከምሥራቅ ኢትዮጵያ እስከ ሰሜን ኢትዮጵያ ድረስ በጦርነት አመሷት።
አብያተ ከርስቲያናትን አወደሙ። ቅዱሳን መጻሕፍትን አቃጠሉ። ካህናትን እና ምእመናንን አረዱ። የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የዐረብ ስደተኞችን ካስተናገዱ ጊዜ ጀምሮ
እስከ ዛሬ ድረስ በችግር፣ በጦርነትና በሰላም ማሳጣት ዐረቦች
እንዳመጡት እስልምና ኢትዮጵያን ያዎካት የለም። የዐረቦች
እስልምና አዋኪነቱ በማበጣበጥ ብቻ የተገታ አይደለም። ታሪክንም በመበረዝ ጭምር ነው።
በተለይ ባለፉት ሃምሳ አመታት በዐረባዊው በግብጽ መንግሥትና ካይሮ በሚገኘው
የዓለም ሙስሊሞች እንዲከተሉት የእስልምና መመሪያ ወይም ፋትዋ ማፍለቂያ ማእከል በሆነው በአል አዛር ተቋም አበረታችነት
በኢትዮጵያ የተኪያሄዱት ሁከቶች ኢትዮጵያን ትልቅ አደጋ ላይ የጣሉ ነበሩ። ይህ የዐረቦች የአመጽ ጥንስስ በኢትዮጵያ ብዙ ደም
ካፈሰሰ በኋላ “ኤርትራ” ተብላ የምትጠራውን የኢትዮጵያ አካል ከነነዋሪዎቿ ከኢትዮጵያ ገንጥሏል። በእስልምና ስም የሚመጣው
የዐረቦች የብጥብጥ እርሾ በማሀል አገር፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በሶማሊያ ወዘተ እስካሁን ድረስ ጥፋቱን
እንደቀጠለ ነው።
ዐረቦች እስልምናን ተጠቅመው በሚፈጥሩት ሁከት ምክንያት ኢትዮጵያ በመታመሷና
ድህነትም ላይ በመውደቋ በተለይ ባለፉት አርባ አመታት ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ኢትዮጵያን ትተው በመሰደድ በተለያዩ
የዓለም አገሮች ተበታትነዋል። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ ወደ
ዐረቦች አገር ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ ተሰድደው በዛ እስከ አሁን ይኖራሉ። ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም በታህሳስ ወር ፪፲፻፬
ዓ.ም. ሰላሳ አምስት የሚሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን የክርስቶስን ልደት በቤታቸው ተሰብስበው
ስላከበሩ የሳዑዲ ዐረቢያ መንግሥት እነዚህን ክርስቲያኖች በእሥራትና በድብደባ ካንገላታቸው በኋላ ክሳዑዲ ዐረቢያ አባሯቸዋል።[6]
ዐረቦች የመጀመሪያው ሂጅራ እያሉ በሚያስታውሱት ስደታቸው ከዐረብ አገር ተሰድደው ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢትዮጵያውያን
ላደረጉላቸው አቀባበል፣ የተሰደዱትንም ችግር እንዳያገኛቸው በኢትዮጵያ እንዲኖሩ መልካም መኖሪያ ለሰጧቸው
ኢትዮጵያውያን የከፈሉት ውለታ እነሆ ኢትዮጵያውያን በዐረቢያ
በተሰደዱ ጊዜ ዱላ፣ እሥራትና ካገር ማባረር ሆነ። ዛሬም እንደትናንትናው ዐረቦች ኢትዮጵያውያንን የማጥቃትና የማዋረድ ሥራቸውን
ቀጥለውበታል። በተለይ ሰሞኑን በሳዑዲ ዐረቢያ ኢትዮጵያውያንን
እያሳደዱ በመያዝ እየደበደቡ አጉረዋቸዋል። አንዳንዶችንም ገድለዋቸዋል። ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከቤታቸው እያወጡ አስራ አምስት እና
ሃያ እየሆኑ ሰብአዊነት በሌለው ሰይጣናዊ ሁኔታ ደፍረዋቸዋል።
ከቤታቸውም ከተሰደዱበትም ቦታ እያወጡ ጥለዋቸዋል። የርኅራኄ መስተንግዶ የተደረገላት ቄዳር ግፍን መለሰች። በቄዳር ድንኳኖች ውስጥ
ያላችሁት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ተመልከቱ። ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍስ ብዙ ጌዜ
ኖረች። ኢትዮጵያ ማረፊያ ሰጥታ ሰላምን ለቄዳር ልጆች ሰጠች፣ የቄዳር ልጆች ግን ስላምን ነሷት። መኖርያቸው ለራቀ፣ በቄዳር ድንኳኖች ላደሩ ወዮ፥
እግዚአብሔር ተናግሯልና እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋልና።
እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።
[1] Muller, Herbert J.: The Loom of History, 1958
[2] Grunebaum, G. E.: Classical Islam – A History 600-1258
– 1970
[3] Margoliouth, D.S.: Mohammed and the Rise of Islam, 1931
[4] Discover True Islam: free-minds.org
[5] Safieddine, Shahnaze: Migration to Abyssinia
& Wikipedia, the free encyclopedia
good job
ReplyDeletehmm ye ethiopia hizib le sikay yetefere eskimesil dires zegochachining asekayuachew. gin milashun medhanialem yikifelilin.
ReplyDeleteውድ አንድ አድርገኖች
ReplyDeleteአስተያየቴን እንደምታወጡ በማመን የሚከተለውን ጽፌያለሁ
ታሪኩን በጽሞና አነበብኩት!እስልምና ከ ክርስትና ነው የተኮረጀ የሚል እንድምታ ይዟል።እናንተ ይህን በሉ እንጅ አለም እንደ አንድ ክፍል በሆነበት ጊዜ ይህን ማለቱ ብዙም ደስ አላለኝም።
በጣም የገረመኝ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ እሱ ዘንድ አንድም ሰው የማይበደል ንጉስ መኖሩን ማን ተናገረ?ለሚለው መልሱ ኢትዮጵያኖኦች ናቸው የተናገሩት ማለታችሁ አስቆኛል።የተናገረው አላህ ነው።ስደቱንም የፈቀደው አላህ ነው።
አሁን ያለው ስድተኞች ላይ የሚደርሰውን ግፍ ከ ኢስላም ጋር አያይዛችሁ ኢስላም ጨቋኝ እምነት ነው ለማለትም ደፍራችኋል።ትክክል አይደላችሁም!አረቦች ኢስላምን አይወክሉም።ድሮም ዘላኖች ነበሩ አዎ! የጥንት ታሪካቸው ጣኦት አምላኪዎች በቡድን ተከፋፍለው የሚቧቀሱ ጦረኞች ነበሩ! ይህ ግን ኢስላም ከመጣ በኋላ አክትሟል።ሳኡዲ እየተበደሉ ያሉት ወገኖቻችን ሚዲይያ እንደሚያራግበው ባይሆንም ከፍተኛ በደል መፈጸሙን አንክድም።እስራኤል የተሰደዱ ፈላሻዎች ከዚህ የበለጠ በደል እየደረሰባቸው ነው!ስደት ብዙ መከራ አለው።ግን ኢስላም አይደለም እየበደላቸው ያለ!ሲለዝዚህ እምነቱን እና አረቦችን አንድ አድርጋችሁ አትጨፍልቁ!ኢስላም ከ እንዲህ አይነት ወንጀል ነጻ ነው!!ኢስላም ሰላም ነው።አረቦች ኢስላምን አይወክሉም!