Friday, November 8, 2013

ሰበር ዜና ፡- ብጹዕ አቡነ ኤፍሬም ለተሀድሶ አቀንቃኙ ለ” አባ” ማርቆስ ብርሃኑ የእግድ ደብዳቤ ጻፉለት(አንድ አድርገን ጥቅምት 30 2006 ዓ.ም)፡- በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስያን አስተዳዳሪ “መልአከ ብርሃናት አባ” ማርቆስ ብርሃኑ ከምዕመኑ እና ከማኅበረ ካህናት በተነሳባቸው አስተዳደራዊ እና  ሃይማኖታዊ ህጸጽ ጥያቄ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትአስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ በ28/02/06  ዓ.ም አባ ማርቆስን ከአስተዳዳሪነት ሥራቸውን ከደመወዝ ጋር አግዷል ፡፡ ጉዳዩም ለመንበረ ፓትያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ ወስኗል፡፡ ደብዳቤውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት

ቁጥር ፡- 367/02/06
ቀን ፡- ጥቅምት 28 2006 ዓ.ም

ለ፡- መልአከ ብርሃናት አባ ማርቆስ ብርሃኑ
ደ/ብርሃን

ጉዳዩ፡- ከሥራ እና ከደመወዝ የታገዱ መሆኑን ስለመግለጽ

    በርእሱ እንደተገለጸው የደብረ አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን  ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የአስተዳደር በደል እና ሌሎች የሃይማኖት ችግር አለባቸው በሚል በቀን 25/02/2006 ዓ.ም አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
       በመሆኑም ሀገረ ስብከቱ ጉዳዩን በማስረጃ አስደግፎ ከመረመረ በኋላ የካህናቱንና የህዝቡን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሕዝቡንና የከተማውን ሠላም ከመጠበቅ አኳያ የወሰደው የመፍትሄ ሀሳብ እርስዎን ከሥራ እና ከደመወዝ ታግደው እንዲቆዩ እና ጉዳዩን ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እንዲቀርብ የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር ጉባኤ በቀን 28/02/2006 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
      ስለዚህ ከጥቅምት 29/02/2006 ዓ.ም ጀምሮ ከሥራ እና ከደመወዝ የታገዱ መሆኑን እየገለጽን ጉዳዮዎ ለዋና መስሪያ ቤት የተላለፈ ስለሆነ በዚያ በኩል እንዲከታተሉ እናስታውቃለን፡፡

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ”
አባ ኤፍሬም
የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ግልባጭ
 • ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
 • ለመንበረ ፓትያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
 • ለደ/ብ/ ቅ/ሥላሴ ሰ/ጉ/ጽ/ቤት
 • ለሰሜን ሸዋ አስተዳደር ጽ/ቤት
 • ለሰሜን ሸዋ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ መምሪያ
 • ለሰሜን ሸዋ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ
 • ለደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
 • ለደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ
 • ለደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት

ደ/ብርሃን

‹‹ኢየሱስ አማላጅ ነው የሚል ምዕመንም ሆነ ካህን በሀገረ ስብከቴ እንዲኖር አልፈቅድም›› የሚል የጸና አቋም የያዙት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤፍሬም ባደረጉት ያላሰለሰ ጥረት ይህን ሃይማኖታዊ የህጸጽ ጉዳዩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግራና ቀኙን ፍጹም ሚዛናዊ በሆነ መልኩ  ምዕመኑን ፤ ካህናቱንና ተከሳሽ መልአከ ብርሃናት አባ” ማርቆስ ብርሃኑ ካደመጡ በኋላ ለዚህ ውሳኔ መብቃት መቻላቸው “አንድ አድርገን” ለሌሎች አህጉረ ስብከቶች በአሁኑ ሰዓት ለቅድስት ቤተክርስቲያን የውስጥ እግር እሳት እየሆኗት የሚገኙትን መናፍቃንን እና ተሀድሶያውያንን በጉያቸው አቅፈው አብረው ለሚኖሩት ትልቅ ትምህርት ነው የሚል እምነት አላት፡፡ 

ከዚህ በተጨማሪ ይህ ውሳኔ እንዳይወሰን የሚፈልጉ የአስተዳዳሪው የመልአከ ብርሃናት አባ” ማርቆስ  ደጋፊዎች እያደረጉት ያለውን የህዝብ ማነሳሳት እና የፊርማ ስብሰባ ጉዳይ ለጉዳዩ እንቅፋት ከመሆንም በተጨማሪ ምዕመኑን ወዳልተፈለገ የብጥብጥ መንገድ እንዳይመራው እና በቤተክርስቲያኒቱም ሆነ በከተማው ውስጥ አላስፈላጊ ነገሮችን ለማስቀረት ያስችለው ዘንድ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ለሰሜን ሸዋ ዞን ጸጥታ ጽ/ቤት እና ለሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት ይህን ደብዳቤ አስቀድመው እንዲህ ብለው ጽፈው ነበር፡፡


ለብጹዕ አባታችን ለአቡነ ኤፍሬም እግዚአብሔር 
ረዥም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን፡፡

3 comments:

 1. Erebakachihu rega tenlo yitena.andandu alut yetebalew kemeten belay teganual.sewuyew yeteshal temhret yalachew ayimeslegnem.ke ewuqet manes yetenagerutn hulu memezgebu teru ayimeslegnem.merejawechem bedenb metayet alebachew.betelacha yetefebereku lihonu yichilalu.yetebalew hulu ewenet kehone,legizewim yetewesedew ermja tekekel new,gen bewushet mereja kehone?

  ReplyDelete
 2. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውNovember 10, 2013 at 6:41 AM

  እገዳው ለዘለቄታውና በአጠቃላይ ከቤተክርስትያኑ መሆን አለበት። ተመስገን እግዚአብሄር ለንደዚህ አይነት ጥሩ ዜናዎች።

  ReplyDelete
 3. merejawin keyet endemitagegnut mawek enichilalen.....betam yafetenchihut ayimeslachihum. sijemir tekesesubet yetebalew neger eko tera were new mimeslew...sew betilacham yimesekiral. ene gin minim alamaregn

  ReplyDelete