Friday, November 22, 2013

የእነ በጋሻው ጉዳይ ወደ እርቅ እያመራ መሆኑ ተገለጸ

(አንድ አድርገን ህዳር 12 2006 ዓ.ም )፡- ከዚህ በፊት በተለያየ ጊዜ በሃዋሳ ፤ ዲላ እና ሌሎች አካባቢዎች ሁከት በማስነሳትና በሃይማኖት ህጸጽ በህዝቡ በተነሳባቸው ጥያቄ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ ደርሶ የነበረው የእነ በጋሻው ደሳለኝ ጉዳይ በጥቅምቱ የሲኖዶስ ጉባኤ ላይ የመጨረሻ እልባት እንዲሰጠው በተወሰነው መሰረት ሶስት ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን ሲያጠና ከቆየ በኋላ በእርቅ ለመቋጨት የሚያስችል ውሳኔ ላይ መድረሱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡
 
ከቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን አጣርተው የመጨረሻ እልባት እንዲያበጁለት የተመረጡት  ብፁዕ አቡነ  እስጢፋኖስ ፤ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘካናዳ እና  ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ለዚህ እርቅ መነሻ የሆነው 21/2/06 በቅዱስ ሲኖዶስ /ቤት አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ ላይ በጋሻው ደሳለኝና ያሬድ አደም በብፁዕ አቡነ ገብርኤል እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ በመጠየቃቸውና አቡነ ገብርኤልም ‹‹ይቅር ማለት የአባት ስርአት ነው›› ብለው ቅርታውን መቀበላቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በእለቱ እርቁን መጠየቅ እንደሚፈልጉና ይቅርታውንም ለመጠየቅ ሶስት በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላቸው ሰዎች ከአዋሳ እንዲጠሩላቸው ስም ጠቅስው በጠየቁት መሰረት የተባሉት ሶስቱ የሀገር ሽማግሌዎች ተጠርተው 27/02/06 .  ይቅርታ የጠየቋቸው ሲሆን ሽማግሌዎችም እንደ ግለሰብ ይቅርታውን ለመቀበል እንደማይቸገሩ ጠቅሰው፤ ነገር ግን አሁን በሕዝብ ተወክለን ስላልመጣን በሕዝብ ስም ይቅርታውን መቀበል እንደማይችሉ በጊዜው ገልጠውላቸው ነበር፡፡

 
ይህም ከሆነ በኋላ ሽማግሌዎቹ ወደ ሀዋሳ ተመልሰው ሕዝቡን ያወዩ ሲሆን ሕዝቡም በውይይቱ ወቅት ያለውን ሀሳብ ከነስጋቱ ጭምር ገልጿል፡፡ ተወያዮቹ እርቁን ከተቀበሉ በኋላ ተወካዮቻቸውን የመረጡ ሲሆን በዚሁ መሰረት እንደገና ከሕዝብ ወገን 7 ሽማግሌዎች ከነ በጋሻው ወገን ደግሞ 5 ሰዎች ተወክለው እንዲቀርቡ በተደረሰው ስምምነት መሰረት 05/03/06 ዓ.ም በሃዋሳ ምእመን የተወከሉ ሰባት ሸማግሌዎች እና ከነበጋሻው ወገን የተወከሉ አምስት ተወካዮች በተገኙበት የእርቅ ውይይት ተካሂዷል፡፡ 
በዚህም መሰረት ተገንጥለው ለብቻ ወጥተው የነበሩት የነበጋሻው ቡድን ወደ እናት ቤተክርስቲያናቸው እንዲመለሱ እና ከሰበካ ውጪ ባሉ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅሮች በሰንበት ትምህርት ቤት አመራርና በልማት ኮሚቴ ውስጥ ሁለት ሁለት ተወካይ እንዲኖራቸውና ከዚህ በኋላ በአንዲት ቤተክርስቲያን ስር በአንድነት ለማገልገልና ለመገልገል በመስማማት የተጠናቀቀ ሲሆን በቋሚ ሲኖዶስ ታይቶ ከጸደቀ በኋላ

በዚህ ወር መጨረሻው ሳምንት በሃዋሳ ቅዱስ ገብርኤል በይፋ ለሕዝቡ ይነገራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ የውስጥ ምንጮቻችን አስታውቀውናል፡፡

አንዳንድ ምዕመናን   ለእርቀ ሰላሙ መነሻ መጀመሪያ ምክንያት የሰዎቹ የእርቅ ጥያቄ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ጫና በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ሁለተኛ ምክንያት ነው ብለውም ያምናሉ ፡፡
አነ በጋሻው አውደ ምህረት ላይ ወጥተው ይቅርታ ይጠቃሉ ወይ? ከሆነስ ምን ብለው ነው ይቅርታ የሚጠይቁት? ምንስ አጥፍተን ነበር ይላሉ ? መድረክ አግኝተው የማስተማራቸው ነገርስ በምን መልኩ ይከናወናል ? የሚሉት ጥያቄዎች መልስ የሚፈልጋቸው ናቸው በማለት ምዕመኑ አሁንም በጥያቄነት እያነሳ ይገኛል፡፡
እስኪ ስለዚህ ጉዳይ የእርስዎን ሀሳብ በብሎጋችን ላይ ያኑሩልን…..
እናመሰግናለን…..

18 comments:

 1. Besmeab Weweld Wemenfes Kidus Ahadu Amlak Amen.mechem erk yemaiwed seitan bicha new enezih sewoch bewnet tetsetstew kehone yikrta madreg tegebi new miknyatum betkristian ke Amkakwa yetemarechew yikrta new. Amlakachin adam yet new yalehew enji yet neberk ayilmna,betekriastiam kemehriwa kebalebetwa keamlakwa new yemtmeraw. yih sil gin yihen. bemenfes kudus yemimeraw kidus sinodos abatoch beyibelt endemiyawkut balemezengat new, lewondimoche yimlew gin ke aryos memeles yadnachu ewnetegna memeles yadrglachu sill kelb enji lekekld aydelehum..

  ReplyDelete
 2. ሰላም አንድ አድርገን እንዴት ናችሁ መቼም እናንተን የሚያህል የቤተክርስቲያንን መረጃ ለህዝብ ለማድረስ የምትጥሩትን ያህል በሌላዉም ቢለመድ መልካም ነዉ ። እነበጋሻዉ በኔ አስተሳሰብ የዋህነት እና ገንዘብ መዉደድ እንዲሁም ቤተክርስቲያናችንን ወደ ምእራቡ አስተሳሰብ መቀላቀል አላማ ያላቸዉ ይመስለኛል ።ያደግም ፈጽሞ አይታሰብም እኔ እንኩ ካገሪ ከወጣሁ ብዙ አመቴ ቢሆነኝም የቤተክርስቲያኔን ድምጽ መለየት አያቅተኝም እናም እነበጋሻዉ ቶሎ መድረክ ይሰጣቸዉ የሚል አመለካከት የለኝም በመድረክ ላይ ጭፈራቸዉን እስኪያቆሙ ድረስ በአባቶች እግር ስር ቁጭ ብለዉ መማር እና ቅኖና ቤተክርስቲያን መሰጠት አለበት ህዝቡን በመከፋፈል እና የልተለመደ ያዘማመር ስርአት ለህዝቡ ስላስተማሩት አካሄዳቸዉን ማስተካከል አለባቸዉ የሚል አሳብ አለኝ

  ReplyDelete
 3. adega nwe. Mene malte endalbenge alawekeme tehdeso ymibalwese ?

  ReplyDelete
 4. megibatun yigibu gin ende mimen enji....wode ageligilote megibate

  ReplyDelete
 5. egziabhier yebetekerestian andenet yetebekelen derown kerestosen kemesbeke wechi menem alatefume neber .mahber kedusan degmo bejemerachu gizie betekerstianenn beteru hunieta magelegelachun balekedeme ahun ahun gen sew abalachu kalehone ena sel kerestose betedegagami kesebeke tehadeso belachu masadede serachen belachu teyayezatuchal. egiziabhier selamun yesten

  ReplyDelete
 6. እርቅን የሚጠላ የማይወድ ሠይጣን ብቻ ነው፡፡ እርቅን እምቢ አንልም፡፡ እርቁ የርስት ንጥቂያ አይደለም የሃይማኖት /ዶግማ/ ችግር እንጂ እርቅ በሃይማኖት አንድ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ደግሞ የእውቀት ማነስ ከሆነ ቁጭ ብለው ይማሩ፡፡ ማደሪያዎቹ ደግሞ በማስመሰል ውስጣቸው ሳያምን ላያቸውን የይቅርታ ሰዎች በማስመሰል ሣይለወጡ ተለውጠናል፣ ሣይጸጸቱ ተጸጽተናል ማለት የተለመደ ቅጥፈት ነው፡፡ አርዮስ በቅዱስ ጴጥሮስ /ተፍጻሜተ ሰማዕት/ ተወግዞ ከህነቱ ተሽሮ ታራ ሰው ሆኖ ከነተከታዮቹ ተወግዞ ሳለ እርሱ በሥጋ ዕረፍት ሲወሰድ ተመልሻለው የእናንተን ሃይማኖት ትምህርት አምናለሁ ብሎ በዘመኑ በሕይወትም በተግባርም መንጋውን የሚታደጉ ጳጳሳትን አሳስቶም ነበር ፡፡ ነገር ግን የአባቱን አደራ/የሃይማኖት ቃል/ የዘነጋ አኪላዎስ ግዝቱን ፈቶ ክህነት ሰጥቶ የአንድ ቤተክርስቲያን አለቃ አድርጎ ቢሾመው በተፍጻሜተ ጴጥሮስ አንደበት ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ የተገዘተውን በመፍታቱ አኪላዎስ ፓትርያርክ በተሾመ በ6ወር ተቀስፎ ሞተ፣ ይላል የቤተክርስቲያን ታሪክ፡፡
  እኔ ግን አልተመቸኝም ጳጳሳት አባቶች እውነተኞቹ እስቲ ከእርቁ በፊት በቀኖና የታዩ ከዚያም እግዚአብሔር መልስ ይስጥ መቀሰፍ እንዳይመጣ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አምላክ እባክህ ከሠይጣን ስውር ጦር፣ተንኮል ጠብቀን፡፡
  አንድ አድርገኖች ዜናውን በየጊዜው ማውጣቱ ጠቃሚ ቢሆንም በቤተክርስቲያን ታሪክ የሚነገሩ እውነተኛ አባቶች ያለፉበት መንገድ ትምህርት ጣፉ፡፡ ይሆ ትውልድ እኮ ከመሠረታዊ ትምህርት ወጥቶ ጥቅስ አሳዳጅ ብቻ ሆኗል፡፡ የቤተክርስቲያን ታሪክ ወንጌል የማይመስላቸው ስንቶች ይሆኑ ታዲያ እነዚሀ ናቸው እኮ ችግሮቻችን አስተምሩን ሦስቱን ጉባዔያት ታሪክ የተሰሩ ሥራዎች እጥር ምጥን አድርጋትሁ አስነብቡን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ewinet newe yihinin guday abatoch yatarulin. i will never trust those guys

   Delete
 7. Egzeabhear yemesgen, sew ketekone sihtet, simetawinet,...be seyf enkuan joro kemekuret belay agelgay liyaderg yechilal..qalu neawna lintebikew gid yelenal. Andande betekrsteanachin wust yetesasatewn sew sihitet mayet eskiaschegir yetilacha menfes, yewegentegninet menfes, yetikim menfes, Fikir yemaytaybet menfes, ye alu alu menfes, sewn yemasdeset menfes, .... Sew aschegari neaw... Ende ene kehone chigiru agelgaun hulu akahedun be agibab yemikotater akal dikmet yechgiru hulu mikneat neaw... Betam yemigermegn gin yetewededachu Egzeabhern yemitagelegilu wegenoche eskemeche new aynina jorowachin tatochachin yetewenu ena temesasaynet, sitebaberu( be agelgilot) yemitaut lay bicha hone??? yeleloch agelgayochn sihitetoch lemin aygola yehon? Yemiadergut hulu.. Yeminagerut hulu, yetezemerew hulu derejawn yetebeke sile hone yehone? Lemin yehon sebakiw be and sibket lay 5 gize "Kirstos" eyale minim yemayseman 3 gize eyedegageme "Eyesus" kale negerachn hulu yemikeyayerew??? Be mezmuratim endihu neaw... Gin hasabachin libachinin yet new yalew? ( wegenoche abatochachin "Getachin ena Amalkachin Eyesus Kiristos" silu min eyalu endehone lemin endinl endazezun gilts new ). Lelaw and sebaki ye agelgilot zemenun hulu weynm bebzat sile Kidist Dingle Mariam sisebk minim yemaybalew sile Kirstos Eyesus abzto yemisebkewn lemin beteleye ayn enayewaln? Agelgilot eko liu liu Tsegawm endihu ke keEgziabhear neaw. Endew and gize and yeteweqesen sebaki quch beye nigigrochun... Lemalet yefelegewn lemeredat simokir ena lela yaltewekese agelgay endihu sitazeb ende ene kehone manim yemiterf endelele ena hasabachin enkiskaseachin yagadele endehone tesemtognal. Minalbat kewch lemigebaw bicha tikuretachinin adirgen abziten Beye awdemihretu lay edil siltegegne ena siram silehone bemimesil menged agibabnet yelelachewn weynm ke eyta wuchi yalutn tehadisoawianin agelgilot yemisetachew yelem elalehu.... Yebetekrsteanm meseretawi chigiroch enesu endehonu amnalehu...enantem andandem bihon sile pente, tehadiso, musina bicha sayhon bizu chigiroch silalu agelgilotachihun be Andinet ena Fikr menfes sile betekrstean bilachu tsafu yebetekrsteanim le teleyau ye haymanot dirjitoch ena alemawinet megabinet megitat yechalalna. Mejemeriam erasachinin enagelgil ketilo betekrsteanin, quanquachinin yemelsln..andim yadirgen Amen

  ReplyDelete
  Replies
  1. besneab wewleld wemenfes kududs ahadu amlak amen. lewendmie lemindinew kristos sibal minm yemaymeslen eyesus sibal negerachin hulu yemikeyayerew silalkew bemejeria endih sitl ewnet betekristianachin tawkataleh way? yasblal ,mikniatum betekrsianachen kemesbek alfa getachin eyesus kristosn elet elet timegebewalech kudus sigaw kubur demun tifettalech. kale eyesus kristos lela man alat . neger gin esun be amlaknetu kudusanu betsegachew kehwariat ende tesetat tamelkewalech enji ende tera sew ayidelem, silezih wondmie orthodox tewahdo be eyesus kirsos meterat attamam mesloh kehone kidasiewa admit ,

   Delete
 8. ይቅር መባባል እንዴት ደስ ይላል ቢሆንም ግን የሃይማኖት ጉዳይ ሰለሆነ ዛሬ በሰው ፊት ስህተተኞች ነን በለው ካመኑ ከኣባቶች እግር ስር ቁጭ ብለው ቀኖና ወስደው ንስሃ ይግቡ... ካልሆነ ግን "ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ ኣይለቅም" እንዳይሆን

  ReplyDelete
 9. I think they should be baned for the time being. They have a link everywhere. Here in london debre tsion by-law form on a facebook, a few of there supporters blaming for the causecand insulting Abune Gebriel in the church compound. We have to be careful this issue does not cooled down easly. By the way if tell us more about what exactly they have done i will post it or share it to members in London my email a/c tewahdo@hotmail.co.uk Thankyou, Godnless you.

  ReplyDelete
 10. እኔ ግን እርቁ የአዞ እንባ ነው እላለሁ።

  ReplyDelete
 11. መናፍቃን ወደ ቤተክርስቲያን መመለሳቸው ሌላ ጥፋት እንዳይሆን እሰጋለሁ ቢቻል ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ጠራርጎ ማስወጣት መልካም ነበረ እዛው አዳራሻቸው ቢዘፈኑ ይሻላቸው ነበር አባቶቻችንን በቀሳጭ ጳጳሳት እውነተኞቹን ጳጳሳት አሳስተው የተለመድ ሸራቸውን ሊሸርቡ እንደሆነ የተረዳ ነው ስለዚህ ዛሬም ቢሆን ምእመናን ቤተክርስቲያናቸውን በንቃትና በትጋት መጠበቅ አለባቸው ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. መናፍቅ ማለት ምን ማለት አንደሆነ የምታውቅ ኣይመሰለኘም ። ከ ሌላ የአምነት ተቅዋም ለቤተክርስቲያናችን ና ለ ክርስቶሰ ምርኮ የሚሆኑ ሰዎች ኣሳምኖ በ ማምጥአት ፈንታ የቤተክርስቲያን ልጆች ማሳደድ ምን ይባላል። ልጆቹን ከቤተክርስቲያን ኣሳደህ ኪረስቶስን ደስ ያሰኝሀው ይመስልሃል? በዚ ከ 20 ኣመት ባልበልበዛ ጊዜ 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ኦርቶዶክስውያን ከቤትከርስቲያናችን ወደ ሌላ አምነት አንደሄዱ ኣታውቅም። አንደኣንተ ሃሳብ ሃይማኖታችንን ዜሮ ለማስቀረት የተነሳህ ነው የሚመስለው።በበኩሌ በአርቁ ደስ ብሎኛል። ጌታ የቤተክርስቲያናችን አድገት ያሳየን።

   Delete
 12. be Abi be Wold be Menfesqidus be Andi AMLAK sim Amen!!! ene erqu bideregi desi yilegnal mikiniyatum seyxan liyafir silehone ........gin gin gin erqu ketederege ene ANDIADIRGEN mini yaworalu minis post yadergalu ...lenegeru ahunis erqu endaykahed ERASACHEW POST ARGEW ERASACHEW -VE COMENT YISEXALU ...degmom melisew yaxalalu ......Tekabe Getachew negn!!!!

  ReplyDelete
 13. diro.diro 1 argen sitilu ewunet yimeslegn neber ......ahun gn simachihun qeyiru LEYAYEN argut kkkkkkkkkkkkkkj

  ReplyDelete
 14. ereku harif new lemeketelewe gene enesu ye 2 year timeherte yasefelegachehuale

  ReplyDelete
 15. ereku harif new lemeketelewe gene enesu ye 2 year timeherte yasefelegachehuale

  ReplyDelete