Monday, June 11, 2012

ዝቋላን መልሰን እናልማ

“ይህን ቦታ ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ሃላፊነት አለብን”
(አንድ አድርገን ሰኔ 4 2004 . )- የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መጋቢት 9 2004 . ለቀናት በዘለቀው እና ለማጥፋት አዳጋች የሆነው እሳት ደኑ ላይ ብዙ ጉዳት እንዳደረሰ ይታወቃል በጊዜው እሳቱን ለማጥፋት በርካታ ምዕመናኖች ከአዲስ አበባ ከአዳማ እና ከደብረዘይት ወደ ቦታ አምርተው የተቻላቸውን ሁሉ አድርገው እንደ እግዚአብሔር መልካም ፍቃድ እሳቱን በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል ይህን በእሳት ምክንያት ገዳሙ ያጣውን ደን መልሶ ለማልት ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› መንፈሳዊ ማህበር የመጀመሪያ ዙር የዛፍ ተከላ ፕሮግራም ሰኔ 24 እና ሰኔ 25 ቦታው ድረስ በመሄድ በሺህ የሚቆጠሩ ምዕመናና የሚሳተፉበት የጉድጓድ ቁፋሮ እና ዛፎችን የመትከል መርሀ ግብር አውጥቷል በዚህ የተቀደሰ መንፈሳዊ አገልግሎት ገንዘብ ያላችሁ በገንዘባችሁ ጉልበት ያላችሁ በጉልበታችሁ ትሳተፉ ዘንድ ጥሪያቸውን ያስተላልፋሉ ይህን የዛፍ ተከላ ፕሮግራም ለመርዳት የምትፈልጉ ሰዎች ችግኞችን በመግዛት ብር በማዋጣት እና ቦታው ድረስ በመሄድ የጉልበት አገልግሎት መስጠት ይምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ወደ ገዳሙ የሚደረገው የጉዞ ቀን ቅዳሜ ሰኔ 24 2004 . ሲሆን የመመለሻ ቀን ደግሞ እሁድ ሰኔ 25 ይሆናል ይህን የተቀደሰ አላማ ላይ አሻራዎን ለማሳረፍና ከአባታችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በረከት ለመቀበል የምትፈልጉ ሰዎች የትራንስፖርት ወጪዎትን ብቻ በመሸፈን ማህበሩ ባዘጋጀው የጉዞ መርሀ ግብር ላይ በመገኝት የታሪካዊውን ገዳም ደን መልሶ የማልማት ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ዛፍ የመትከል መርሀ ግብሩ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች ጉድጓድ ለመቆፈር የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን (ገሶ ፤ ዶማ ወይም አካፋ) መያዝ ይጠበቅቦታል ፤

የማይቀርበት ታላቅ የበረከት ስራ….”


ይህን አላማ ለመርዳት ወይም መርሀ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሰዎች  ለበለጠ መረጃ (0911-201649  0911-216440 ፤ 0913-255249 ፤ 0911-015623 ፤ 0924-373474) በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡


7 comments:

  1. Kidanemariam Ze Negelle BoranaJune 11, 2012 at 6:45 AM

    Betam betam girum hasab..neger gin yeden balemuyawochim kedem bilew binegagerubet. ke zaf ayinet mereta eske tekela teknik dires lemabez....

    ReplyDelete
  2. አስተባባሪ እንጂ የጠፋው እኛማ አለን ደሞ ለዝቋል… ዶማዬን አስተካክዬ እጠብቃለሁ

    ReplyDelete
  3. I would love to do.

    ReplyDelete
  4. melekame negere gene genezebe yemisebesebebeten menegede felegu...maletea kemahebere kidusan ga honachehu ende balefewe mk usa online genezebe endesebesebe ahunem online service binore tiru newe keep to update us

    egiziabehere kegna ga yehune

    ReplyDelete
  5. Senne 24 ena 25 ehud kidame kehone endet besenbet gudguad ykoferal endets ytekelal ekidu melkam bihonim kenu yistekakel.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Besenbet melkam sira mesrat aykelekelim. I think so.

      Delete
  6. Melkaminetun zengichew sayhon bealu aysharm woy?Asamagn neger kaleh asiredagn ene mekawome sayhon ke awontawi/kekininet amelekaket new::EGZIABHER yistilign!

    ReplyDelete