Friday, June 22, 2012

“አንድ አድርገን” ለሁለተኛ ጊዜ ተዘጋች



ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ www.andadirgen.blogspot.ca ይጠቀሙ
  •  “ጠላት የዘጋውን በር አትመልከት ፤ እግዚአብሔር እጅ ያለውን ቁልፍ ተመልከት”  አቡነ ሺኖዳ

(አንድ አድርገን ሰኔ 15 2004 ዓ.ም)፡-ህገ መንግስታችን አንቀጽ 29 ቁጥር 1 ላይ “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል” ይላል አንቀጽ ቁጥር 2 ደግሞ “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው ፡፡ ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሁፍ ወይም በህትመት በስነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም ማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል” በማለት ያስቀምጣል ፤
ይህን ህገመንግስት መንግስት ከነሀሴ 15 ከ1987 ዓ.ም (የጸደቀበት ቀን) ወዲህ አንብቦት የሚያውቅ አይመስልም ፤ እኛ ሀሳባችንን በብሎጋችን ላይ ማስፈር ሰዎች ዘንድም ማድረስ አልቻልንም ፤ ይህን ያህል የምንጽፈው ነገር የሀገርን ሰላምና የህዝቦችን በሰላም መኖር የሚያናጋ ነውን? ፤ ይህ የዜጎችን በነጻነት ሃሳብን የመግለጽ መብቶችን የሚጋፋ ይመስለናል ፤ “የአመለካከት እና ሀሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ” መብትን የሚጋፋ ድርጊት ነው :: የተለያዩ የመረጃ ምንጮች የሚያናፍሱትን መረጃ ነው እኛም የምንጠቀመው ፤ አልፎ አልፎ ሚስጥራዊ ነገሮች ቢኖሩም ፤ ለምሳሌ ከቀናት በፊት ኢህአዴግ በሃይማኖት አክራሪነት በኩል የጻፈውን ጽሁፍ አንባቢዎች ዘንድ አድርሰናል ፤ ታዲያ እነርሱ ሲጽፉት ምንም ያልመሰላቸው እኛ ሂስ ብንሰጥበት ለምን ያኮርፋሉ ፤ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ከመንግስት እሳቤ ተነስተን ነው ሀሳብ የሰጠነው ፤ ይህን ያህል የምንጽፈው ነገር ብሎግ የሚያዘጋ ነውን ? ለእነርሱ ሊመስላቸው ይችላል ለእኛ ግን የማይዋጥልን እውነት ነው ፤ በእኛ በኩል ካለን መረጃ አኳያ ምንም የጻፍነው ነገር የለም፤ ምንም ለሰዎች ያደረስነውም መረጃ የለም ፤  

“አንድ አድርገን” ከተከፈተች አንድ ዓመት እንኳን በቅጡ አልሞላትም ፤ እኛም አንደኛ ዓመቷን ለማክበር አንዲት ሻማ እንኳን መለኮስ አልቻልንም ፤ በዚች አጭር ጊዜ 3 ሳምንታት ሙሉ ያለመነበብ አደጋ እና ለ2 ጊዜ ያህል የመዘጋት አደጋ አጋጥሟታል ፤ ሁለት ጊዜም ከመዘጋቷ በፊት እንደምትዘጋ መረጃው ደርሶናል ፤ ይህን የመሰለ ነገር ግን ይባስ እንድንጠነክር ጉልበት ይሰጠናል እንጂ ፈጽሞ የመጻፍ ፍላጎታችንን ሊያጠፋ አይቻለውም ፤ ጠላት ዘወትር ጉድጓድ ይምሳል እኛ ግን እንደ እግዚአብሔር ጥበቃ የጠላትን መረብን እየበጣጠስን መረጃዎችን ሰዎች ዘንድ እናደርሳለን ፤ ብሎጋችንን ለመዝጋት ምንም ያህል ቢጥሩ እኛም ይህን አውቀን የእነርሱን ሁለት እጥፍ ስራ ሰርተን እንጠብቃችዋለን ፤ እነርሱ እንዳንነበብ አንድ እርምጃ ቢራመዱ እኛ ደግሞ ሰዎች እንዲያነቡን ሁለት እርምጃ ተራምደን እንጠብቃችዋለን ፤ እነርሱ መዝጋት ካልደከማቸው እኛ መክፈት አይከብደንም ፤ ባለፉት 10 ወራት የተቻለንን ነገር በማድረግ መረጃዎችን ሰዎች ዘንድ የማድረስ ስራ ሰርተናል ፤ ይህ ሊገርማቸው አይገባም ፤ የ10 ወሩ ሲገርማቸው እኛ ግን እንደ አምላክ መልካም ፍቃድ ለሚቀጥሉት አስርት ዓመታት የመረጃ ምንጭ ሆነን እንቀጥላለን ፤ አባታችን አቡነ ሺኖዳ አንድ ወቅት “ጠላት የዘጋውን በር አትመልከት ፤ እግዚአብሔር እጅ ያለውን ቁልፍ ተመልከት” ብለው ነበር ፤  እኛም ጠላት የዘጋውን በር አንመለከትም ::

በአሁኑ ሰዓት “አንድ አድርገን” አንድ ሚሊየን ጊዜ የምትጎበኝበት ጊዜ በመቅረቡ እና አንድ ዓመቷን በማሰብ የሰራናቸውን ስራዎች ወደ ኋላ ዞር ብለን በማየት ለመገምገም እና ወደፊትስ እንዴት መቀጠል አለብን ብለን የተሻለ ስራ ለመስራት የተዘጋጀንበት ወቅት ነበር ፤  በመሀል ይህ የመዘጋት አደጋ አጋጠመን እንጂ ፤ ይህን በመሰለ ፈተና አንድ ሚሊየን ጊዜ መጎብኝት ማለት ቀላል የሚባል አይደለም ፤ ከዚህ በፊት ያሉት www.andadirgen.blogspot.com and www.andadirgen.blogspot.in ሊንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ በኮምፒዩተር አማካኝነት ኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ሰዎች መጠቀምና መረጃውን ማንበብ አይችሉም፡፡ እነዚህ ሁለቱ ሊንኮች ቢዘጉትም ለሶስተኛ ጊዜ www.andadirgen.blogspot.ca አድራሻ በማዘጋጀት አገልግሎታችንን መቀጠል ችለናል ፤ በመጨረሻም ተጠቃሚዎች ይህን ሊንክ  ተጠቅመው መረጃዎችን በቀጥታ ማግኝት እንደሚችሉ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

“እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ” 

11 comments:

  1. As to me the best solution is to advertise to people to subscribe to your blogs. So when ever you have new post (article) send to all of us we then read it from there. I will prefer as email message not as PDF, but if it is difficult, you can send us the PDF.

    ReplyDelete
  2. Include email subscription gadget. Then everybody will subscribe and the feedburner will automatically send your articles to the subscribers. But most of the time, people may not subscribe.
    But those who do want it can get the access through email.
    Bertu teberatu enilalen.

    ReplyDelete
  3. look ! truth can not be hidden. which blog is criminal , aba selama/awdemihret or andadirgen? I think the government is apperently involved to weaken the church along with abune poulos and other enemies.

    ReplyDelete
  4. why not you make it in the form of facebook subscription?like deje selam?

    ReplyDelete
    Replies
    1. It's a good idea, but arrange both options. I mean both email and fb subscription.

      So far, you guys did a good job. pls keep it up. May God be with you!

      Delete
  5. በርቱ !!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  6. Please do it with Facebook too, like dejeselam!! That will increase your accessibility.

    ReplyDelete
  7. ካለኝ ገጠመኝ ችግሩ የሚጀምረው ከስማችሁ ነው ፡፡ መንግሥት አንድ የሚባል ቁጥር አይወድም ፡፡ እናንተ ደግሞ ይባስ ብላችሁ አድርገንንም ጨምራችሁበታል ፣ መነጣጠልንና መከፋፈልን መመሪያው ያደረገ መንግሥትን ፣ ባታደርጉትም የምትቃወሙት ይመስለዋል ፡፡ ከዚህ ቀደም አንድነት ዳቦ ቤት የሚል ከፍቼ ሥሰራ የምን አንድነት ነው የምትለው በማለት ያለፍላጐቴ በቡችሎቹ ክትትል ብዛት ለመቀየር ተገድጃለሁ ፡፡ እናንተም ምናልባት ለየት ያለ መንፈሳዊ መልዕክት በሚያስተላልፍ መታወቂያ ብትጀምሩ ትኩረቱና ክትትሉ ሊቀንስ ይችል ይሆናል የሚል ግምት አለኝ ፡፡

    ReplyDelete
  8. Please take all the above advise. This is the best site which have been giving us update information. I also would like to thank you for your effort.
    Please be strong and continue with your effort.

    ReplyDelete
  9. bertu bertue gzabhear yebarkachu

    ReplyDelete