Wednesday, June 27, 2012

1061 የሃይማኖት ድርጅቶች የመቋቋሚያ ፍቃድ ጠይቀዋል


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ


(አንድ አድርገን ሰኔ 20 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የፌደራል ጉዳዮች  ሪፖርት በቅርቡ አንድ ሰው አምጥቶልን ማንበብ ችለን ነበር  ፤ ሪፖርቱ ከሃይማኖት ጽንፈኝነት ፤በሀገሪቱ ላይ በሃይማኖቶች መካከል የተከሰተውን ችግርን እንዴት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ እንደፈታው የሚያትት ጉዳይ ይገኝበታል ፤ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግቢ ተማሪዎች ሃይማኖታዊ በዓል ለማክበር በጠየቁበት ጊዜ ያቀረቡት ጥያቄ አግባብ አለመሆኑን ከሚመለከታቸው የሃይማኖት አባቶች ጋር በመወያየት የበዓል አከባባሩ ከግቢ ውጪ መሆን እንዳለበትና በጊዜው በዓሉን በዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳልተከበረ ያስቀምጣል ፤ በመቀጠልም በጅማ አካባቢ የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች በርካታ ስልጠናዎችን እንደሰጠ እና ከ7000 በላይ ጽሁፎችን ከበርካታ ለማህበረሰቡ እንዳሰራጨ ይናገራል ፤ በአሁኑ ሰዓት ከየሃይማኖት ተቋማቱ በማሰባሰብ የሃይማኖት አንድነት ጉባኤ በየጊዜው መደረጉ በአሁኑ ሰዓት የሚታዩ ችግሮችን ከመፍታትና መስመር ከማስያዝ አኳያ መስሪያ ቤቱ በዚህ ላይ ትልቅ ስራ እንደሰራ አስፍሯል፤ በተጨማሪም በጥምቀት በዓል ወቅት የሃይማኖትን እኩልነት በሚጻረር መልኩ አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኞች በቲሸርቶቻቸው ላይ ያሰፈሯቸው ጽሁፎች እንደ አንድ ችግር በማንሳት በዚህ ላይ የሚመለከተው አካል ሁሉ ህገ መንግስቱን ከማስከበር እና የሃይማኖት እኩልነትን ከማረጋገጥ አኳያ አብሮ መስራት እንዳለበት ያትታል፡፡

ከላይ የተጻፉት ሀሳቦች ሁላ በአንድ በሌላም መልኩ ከተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች የምንሰማቸው በመሆናቸው ብዙም ትንግርት አልፈጠሩብንም ፤ በጣም የገረመን ነገር ከበጎ አድራጎት እና ማህበራዊ ኤጀንሲ በኩል የመጣለት ሪፖርት  ላይ እንዲህ የሚል ነገር በመስፈሩ ነው “……. ተቋሙ በአዋጅ የሃይማኖት ምዝገባ እና ፍቃድ መስጠት እንዲተገበር በተሰጠው ተግባርና ሃላፊነት መሰረት ከበጎ አድራጎት ማህበራዊ ኤጀንሲ የ1061 የሃይማኖት ድርጅቶች ፋይል የተረከበ ሲሆን በተጨማሪ እድሳት ከጠየቁት ባለጉዳዮች ውስጥ መስፈርቱን ያሟሉት 178 የሃይማኖት ተቋማት ፍቃድና እድሳት እንዲያገኙ ተደርጓል ፤ ለ12 የውጭ ዜጎች የስራ ፍቃድ ፤ ለ16 የሃይማኖት ተቋማት የባንክ ሂሳብ እንዲከፈትላቸው የትብብር ደብዳቤ ተጽፎላቸዋል….” የሚለው አንቀጽ ነው ፡፡ ባሳለፍነው ጥቂጥ ዓመታት ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ከተቋቋመ በኋላ የራሳቸውን ሃይማኖት ለማቋቋም ከ1000 በላይ ተቋማት ጥያቄያቸውን አቅርበዋል ፤ ይህ ጥያቄ የሚቀርበው በጎ አድራጎትና ማህበራዊ ኤጀንሲ ሲሆን ኤጀንሲው ያስቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ በርካታ የእምነት ድርጅቶች ፍቃድ አግኝተዋል ፤ 178 ያህሉ ደግሞ ፍቃዳቸውን ማሳደስ ችለዋል ፤ ይህ የሚያሳየን ነገር ከአመታት በኋላ በሺህ የሚቆጠሩ የእምነት ተቋማት ተቋቁመው ለመመልከት ብዙ ጊዜ እንደማይወስድብን ነው ፤ በዓለም ላይ ከ20ሺህ በላይ የእምነት ተቋማት ይገኛሉ ፤ ከእነዚህ ውስጥም ብዙውን ቁጥር የሚይዙት ሩቅ ምስራቅና አውሮፓ ላይ የሚገኙ የእምነት ተቋማት ናቸው ፤ ከጥቂት አመታት በኋላም ኢትዮጵያ ከእነዚህ ሀገራት ያላነሰ የእምነት ተቋማት ይኖራታል የሚል ግምት አለን ፤ ይህን ለማለት የደፈርነው በአሁኑ ሰዓት በጥቂት ዓመታት ውስጥ ከ1000 በላይ የእምነት ተቋማት የመመስረቻ ፍቃድ እንዲሰጣቸው ፍቃድ መጠየቃቸው አንዱ ማሳያ ይሆናል በማለት ነው ፤ እነዚህ የሚቋቋሙት ወይም ለመቋቋም ማመልከቻ ያስገቡ ተቋማትን በተመለከተ ምንም ማለት ባንፈልግ እንኳን በሚቀጥሉት ዓመታት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፤ በተለያዩ የስልጣን ደረጃ ላይ የሚገኙ የቤተክርስትያኒቱ አባቶች ፤ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ቤተክርስትያኒቱ እውቅና የተሰጠቻቸው ማህበራት ምዕመናንን ከተኩላዎች ለመጠበቅ ምን እየሰሩ ይገኛሉ ? ብለን መጠየቅ አስገድዶናል ፤ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ ብቻ ቤተክርስትያኒቱ በመተኛቷ በርካታ ነፍሳት በተኩላ ተነጥቀዋል ፤ ከ10 ሚሊየን ያላነሰ ምዕመን ቤተክርስትያኒቱ አጥታለች ፤ የእስከ አሁኑ ቁስል እንዳለ ሆኖ በአሁኑ ሰዓት ፍቃድ የጠየቁት የእምነት ተቋማት ውስጥ ባለማወቅ የሚሄዱት ነፍሳትን ቀድሞ በማሰብ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡  

በአንድ ቀን ስንት የእምነት ተቋም ይቋቋማል ?
ስናነብ ካገኝነው( አዲስ ዘመን ዓርብ ግንቦት 13 ቀን 2002 ዓ.ም ገፅ 8)

የውስጥ ችግሮች እንዳሉ ሆነው የውጭ ችግሮች ላይ የወደፊት ተግዳሮቶች ላይ አተኩረን ስራ መስራት ይገባናል ፤ በ1987 ዓ.ም በነበረው ቆጠራ 50.6 በመቶ የአማኝ ቁጥር ነበረን ፤ በ1999 በተደረገው ቆጠራ ደግሞ 43.5 በመቶ ደርሰናል ፤ በ2011 በሚደረገው ቆጠራ 23 በመቶ እንዳንደርስ ስጋት አለን ፤ በርካታ ጊዜያት ከኦርቶዶክስ አማኝነት ሰዎች ሲሄዱ ወደ ፕሮቴስታንቶች እንጂ ወደ ሙስሊሞች ሲሄዱ አይታይም ፤ በዚህ ምክንያት የኛ አብያተክርስትያናት በአማኞች ቁጥር ሲቀንስ የፕሮቴስታንቶቹ አዳራሽ እየሞላ እየተመለከትን ነው ፤ ስፍር ቁጥር የሌላቸው አዳራሾች ከእድር ቤት እኩል በየሰፈሮቻችን እየተከፈቱ ይገኛሉ ፤ እነዚህ አዳራሾች ነገ ከነገ ወዲያ አምስት ስድስት እጥፍ በልጠው ሲሰሩ የሚኖረው ተጽህኖ በማስላት ቀድመን እንዘጋጅ ፤ መንግስታችን የሃይማኖት እኩልነት የሚል አቋም ስላለው አሁን እነዚህ ተቋማት ፍቃድ ባይሰጣቸው አንኳን እያደር እየተፈቀደላቸው እንደሚሄዱ መዘንጋት የለብንም ፤ የጠላትን አሰላለፍ ማወቅ ለጥንቃቄ መልካም ነው የሚል እምነት አለን፡፡
 ሐገር አቀፍ የህዝብ ብዛት በሃይማኖት

  
ኦርቶዶክስ በ1987 ዓ.ም   …….   50.6 %
               ኦርቶዶክስ በ1999  ዓ.ም ………   43.5 %
               ኦርቶዶክስ በ2011  ዓ.ም  ……….   ?
 እውነታው ይሄ ነው፡፡ የመፍትሔ ሰው እንሁን፡፡


አቡነ ጳውሎስም ቤተክርስትያኒቱን ለማፈራረስና ሁለት ቦታ ለመሰንጠቅ በእነ ኀይለ ጊዮርጊስ አስተባባሪነት በማቋቋም ላይ የሚገኙትን ጉባኤ አርድእት የተሰኘ ቡድን ከማደራጀት ይቆጠቡ ፤ ይህን በመቋቋም ላይ ያለን ማህበር እንደ 25 ግለሰቦች ጥርቅም ወይም እንደ አንድ ተራ ማህበር የሚመለከተው ሰው ካለ ተሳስቷል ፤ ወደ ፊት የሚያሳድረው ተጽህኖ አሁን ላይ ሆነን መመልከት አንችል ይሆናል ፤ መመስረቱ እውን ከሆነ ግን ቤተክርስትያኒቱ ላይ የሚያሳድረው ክርን ካለው የሃይል ሚዛን ጋር ተዳምሮ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዳይመራት ስጋት አለን ፤ ይህ የአንድ ማህበር የመመስረትና ያለመመስረት ጉዳይ አይደለም ፤ ይህ ጉዳይ የነገይቱ ቤተክርስትያን ለሁለት የመከፈልና አንድ ሆና የመቀጠል ያለመቀጠል ጉዳይ ነው ፤ እስከ አሁን ከግለሰቦች ጋር ስለቤተክርስትያን ብለን ያደረግነው ትግል ይበቃናል ፤ የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ላለፈችበት ሁኔታ ለእኛ ትምህርት ይሁነን ፤ ነገን ተመልክተን ዘመኑን እንዋጅ ፤ ይህ ከላይ የገለጽነው የውስጥ ችግራችን ሲሆን የውጩንም የምንመለከትበትን መነጽራችንን እናስተካክል ፤ ለማንኛውም ወደ ፊት ፍቃዳቸው የታደሰላቸውንና  ፍቃድ የጠየቁትን ተቋማት አስፈላጊ ከሆነ ለመረጃ ያህል ብሎጋችን ላይ እናወጣቸዋለን ……

ቸር ሰንብቱ  

8 comments:

  1. Dear Andadrgen may GOD bless u all given us such info.

    It is so saaaad , Please GOD LET LISTEN OUR PRAYER AND LOOK AFTER OUR BELOVED TEWAHEDO

    አቡነ ጳውሎስም ቤተክርስትያኒቱን ለማፈራረስና ሁለት ቦታ ለመሰንጠቅ በእነ ኀይለ ጊዮርጊስ አስተባባሪነት በማቋቋም ላይ የሚገኙትን “ጉባኤ አርድእት” የተሰኘ ቡድን ከማደራጀት ይቆጠቡ ፤ ይህን በመቋቋም ላይ ያለን ማህበር እንደ 25 ግለሰቦች ጥርቅም ወይም እንደ አንድ ተራ ማህበር የሚመለከተው ሰው ካለ ተሳስቷል ፤


    የሃይል ሚዛን ጋር ተዳምሮ ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዳይመራት ስጋት አለን ፤ ይህ የአንድ ማህበር የመመስረትና ያለመመስረት ጉዳይ አይደለም ፤ ይህ ጉዳይ የነገይቱ ቤተክርስትያን ለሁለት የመከፈልና አንድ ሆና የመቀጠል ያለመቀጠል ጉዳይ ነው ፤ እስከ አሁን ከግለሰቦች ጋር ስለቤተክርስትያን ብለን ያደረግነው ትግል ይበቃናል ፤ የህንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ላለፈችበት ሁኔታ ለእኛ ትምህርት ይሁነን ፤

    ReplyDelete
  2. የዓለም መጨረሻዋ ካልሆነ በስተቀር ፣ ይኸ ሁሉ ግርግር አይገባኝም ፡፡ እንዲያው ግን የፖለቲካ ቁማርተኞት ለዕድሜ ማራዘሚያ የሚፈጥሩልን የቤት ሥራ እንዳይሆን እፈራለሁ ፡፡ ብቻ ከምን የተነሳ እንደሁ መመለስ በማልችለው መልኩ ፣ ከራሴና ከቤተሰቤ ጀምሮ ሰው ሁሉ ሃይማኖቱን ትኩረት ሰጥቶት ለማወቅ በየፊናው ብዙ እየታገለ ነው ፡፡ አሁን የናንተን ሳነበው ደግሞ ጭራሽ ልቤ ፈራ ፡፡

    ይኸ ባህላዊ የሚባለው የሃይማኖት ዓይነት ደግሞ ምንድር ነው ? ጭቅጭቅና ብግነት የሌለበት ባህላዊ እሴቶችን /ዕደ ጥበባትን ፣ ባህልንና ወግን / መንከባከብ ከሆነ ዓላማው ፣ በሃይማኖትነቱ ባይሆን እንኳን ፣ በሃገር አዳኝነቱና አለኝታነቱ እንድቀላቀለውና የድርሻዬን እንዳግዝ የምታውቁት ሰፋ አድርጉና ጻፉልን፡፡

    በተረፈ ምናልባት የቤተ ክርስቲያን ችግሩ ከመሪዎቻችን ጋር የተቆራኘ ከሆነ ፣ ዕድሜያቸው በሰው ዕድሜ ልክ የተገደበ /ግፋ ቢል 12ዐ/ ስለሆነ ፣ ሲያበቁ ያበቃል /ከትንቢተ ብልጣ ብልጥ አባባል/ ፡፡ በተረፈ የምናየው ከእግዚአብሔር ከሆነ ማንም በትግል ሊያቆመው አይችልም ፤ ከዚያ ውጭ ከሆነ ደግሞ እንኳንስ በሺህና በሚሊዮን በቢሊዮንም ቢቆጠር የትም አይደርስም ፡፡ እንደ አፍሮና ቤል ሱሪ የጊዜያው ፋሽን ሆኖ ያልፋል ፡፡ በምንም አትናወጡ ፤ ባላችሁበት ጸንታችሁ ቁሙ ፡፡ ይህን ስል ደግሞ ዝም ብሎ እንደ ሃውልት ምንም ሳይሠሩ መገተር መፍትሄ አይሆንም ፡፡ ባላችሁ ዕድልና መድረክ ሃይማኖትን ለማስተማርና ለመግለጥ ተጠቀሙበት ፤ ብዙ ያስተምራል ፤ ብዙውን ያጸናል ፤ ሌላውንም ይመልሳል ፡፡

    ጊዜው ተቀይሯል ፡፡ ወላጆቻችን ስለተነገራቸው ወይም ስለተሰበከላቸው ብቻ አምነው በሃይማኖት ጸንተው ፣ እልል እያሉ መስማማታቸውን ሲገልጡ ኑረዋል ፡፡ ይኸኛው ቀለም ቆጣሪ ትውልድ ግን በተነገረው ብቻ አይቆምም ፡፡ አለፍ ብሎም መጽሐፍን ለመረዳትና ግንዛቤ ለማስፋት በንባብ ይደክማል ፡፡ እዚህ ትውልድ ላይ ነው ትኩረት ሰጥቶ ፣ መጽሐፉን እንዴት እንደሚረዳው ማገዝ የሚያስፈልገው ፡፡ የተዋሕዶ እምነታችን ትክክል ናት የሚባልበትን ምክንያት በየርዕሱ ገልጣችሁ ካላስተማራችሁ ፤ ለሃይማኖት ደናግል ለሆኑት የቃልና የወረቀት ተማሪዎች ለሚቀርብላቸውና በራሳቸውም ለሚፈጥሩት ጥያቄ መልስ ሲያጡ ፣ በቀላል ውትወታ ብቻ መኰብለል ይጀምራሉ ፡፡ ያ እንዳይሆን ቤተ ክርስቲያናችን የምታምነውንና የምታስተምረውን ወንጌል ከነመግለጫው አብሮ በማቅረብ ብዙዎችን ከኩብለላ መጠበቅ ይቻላል ፡፡ ዝም ብሎ እሮሮ ፣ ብሶትንና ጭንከትን ማካፈል ለችግሩ መፍትሄ አያመጣም ፣ ወንዝም አያሻግርምና አስቡበት ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. I agree with you.

      Delete
    2. ግን ማን ይስራዉ?

      Delete
    3. ማን ይስራው ላልከው ሰው ፣ መልሱ ሃይማኖትን የተማራትና የሚያውቃት ሊቅ ነው ፡፡ እኔም አንተም /አንቺም ትንሽ ከተማርን ያንኑ ያህል መግለጽ ይጠበቅናል ፡፡ እኔ ባልማርም ትክክል የመሰለኝንና የተረዳሁትን አስረዳለሁ ፡፡ አንተ /አንቺ ምን እያደረግህ/ሽ ነው

      Delete
  3. zareame metasebe yalebete gudaye ga newe


    betekirstiyanene egiziabehere yetebeqelene

    ReplyDelete
  4. "...እስከ አሁን ከግለሰቦች ጋር ስለቤተክርስትያን ብለን ያደረግነው ትግል ይበቃናል ..."
    It's to late to say that.
    You pushed many fathers and preachers and then they have benn gothered behind you unless your pridiction. It's 5.00 pm and everybody has known you.

    ReplyDelete
    Replies
    1. አይ አንተ መናፍቃን ስለታወቀባቸዉና ማንንነታቸዉ ስለተጋለጠ ነዉ? የተገፉ የመሰለህ

      ዛሬ ላይ እኮ ትናንት ለቤተክርስቲያን ደንታ ስለሌላቸዉና የመጀመሪያ ገለልተኛ ቤተክርስቲያን ያቋቋሙ ሰዉ የቤተክርስቲያን መሪ ወይም ፓትሪያርክ ሆነዋል

      መናፍቃን ቤቤተክርስቲያን ዉስጥ እተሾሙ እየተሸለሙና ቤተክርስቲያንን ዉስጥ እንዳሻቸዉ እያደረጉ ባለበት ሰዓት እነዚህን ሰዎች ማጋለጥና ማንነታቸዉን ማሳወቅ መግፋት አይደለም

      እዉነት አርነት ያወጣል በቃችሁ ሊባሉም ይገባል
      ሁላችንም የቤተክርስቲያን ነገር ያገባናል
      እናም አንድአድርጎች በርቱ እዉነቱን እዉነት ሐሰቱን ሐሰት ወይም
      መናፍቁን መናፍቅ ሌባን ሌባ ማለታችሁ ክፋት የለዉም
      የአምላክም ትዕዛዝ ነዉ

      ሰላም ሁኑ

      Delete