Friday, June 22, 2012

የ“አዲስ ራዕይ” አመለካከት (ክፍል 2) ….



ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ

  •  ዋህቢያ ይሁን ከማህበረ ቅዱሳን ወይም ከሌላው እምነት ውስጥ ጽንፈኝነት አይመለከተኝም የሚለው በግላጭ ወጥቶ እንዲያወግዝ እድል ሊኖረው ይገባል
  •  ኢህአዴግ የቄሱም የሼሁም ድርጅት ነው ፡፡ ከአባልነት አንጻር የየትኛውም እምነት ተከታይ መሆን ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ፡፡ የአንድ እምነት ሰባኪ  የሆነ ሰው ኢህአዴግ አባል መሆን ይችላል  የኢህአዴግ አመራር መሆንን ግን አይፈቀድም
  • ደርግ ግለሰቦችን በተናጠል  ሲገድል እናንተ ደግሞ ገዳማትን በማፍረስ በጅምላ እምነትንና አማኞችን  የመግደል ምግባር ላይ ተሰማርታችኋል
  • በርካታ አባላት ማህበረ ቅዱሳን እንደሆኑት ሁሉ በርካታ አባላትም የወሃቢያ ወይ  የሌላ የእስልምና ፈለግ ተከታዮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ችግሩ የትኛውም እምነት ይከተሉ የሚለው አይደለም ፡፡ ችግሩ ያለው..............................

(አንድ አድርገን ሰኔ 15 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ከትላንት በስተያ በወፍ በረር በመቃኝት “አዲስ ራዕይ” መጽሄትን በጥቂቱ ለማስዳሰስ ሞክረን ነበረ ፤ አሁን ደግሞ  ምን አይነት ነጥቦች እንዳካተተ ፤ በየነጥቦቹ ስር ምን ዓይነት ሀሳቦችን እንደሚያነሳ ለማሳየት እንሞክራለን ፤ የአጻጻፍ ይዘት እና የጽሁፉን ፍሰት አብረን እንቃኛለን፡፡ የራሳችንንም ሃሳብ ጣል በማድረግም እናያለን ፤ ፅሁፉ ሲጀምር “በሰላምና ህገ-መንግስቱ ዙሪያ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር የዜጎችና የመንግስት መብትም ግዴታም ነው” በማለት  ይጀምራል፡፡

1  የጽሁፉ መግቢያ…. 
የሀገራችን ህዝቦች ለዘመናት እምነትና ማንነት ሳይገድባቸው ተጋግዘውና ተከባብረው ኖረዋል፡፡ የገዥዎቻቸው ይሁን በስማቸው ሲነግዱ የነበሩ የተለያዩ ኃይሎች ባህሪይ ሳይጫናቸው ይህን መግባባትና አብሮነት ይዘው ዘልቀዋል ፡፡ በአሁኑ ወቅት የህዝቦች ትስስርና መከባበር ህገ መንግስታዊ ዋስትና በማግኝቱ ይበልጥ በመጠናከር ላይ በመሆኑ የጋራ ጠላታቸው የሆነውን ድህነትና ኋላ ቀርነት እየተዋጉ በእድገት ጎዳና መረማመድ ጀምረዋል ፡፡ በዚሁ በተቃራኒ ደግሞ ለዜጎች የጋራና የተናጠል መብቶች ተደረገውን ጥበቃና የእምነትን እኩልነትና ነጻነት ለማረጋገጥ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም አብሮነቱን ለማንኳሰስ የሚፈልጉ ኃይሎችም ከሁሉም አቅጣጫ ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም ጥፋታቸውን ከወዲሁ በጉልህ በሚታይ ደረጃ ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል፡፡ እነዚህ ኃይሎች በተለያየ ጊዜ የህዝቡን የንቃተ ህሊና ደረጃ ግምት ውስጥ ያስገባ የማደናገሪያ እና ስሜት መቀስቀሻ አጋጣሚዎችን በመጠቀም በተሳሳተ አቋማቸው ለማስፋፋት በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜም የብዙሀን የልብ ትርታ የሚነኩ የሚመስሉ አጀንዳዎች ውስጥ የመደበቅ ስልት ይጠቀማሉ ፡፡ ችግሩ በአንድ እምነት በአንድ አይነት የፖለቲካ አተያይ የታጠረ አይደለም ፤ ስለዚህ የተወሰኑትን ማየት ተገቢ ይሆናል፡፡” በማለት መግቢያውን ይጀምራል ፡፡ እውነት ነው ለዘመናት ህዝቦች እምነት እና ብሔር ሳይገድባቸው ተከባብረውና አንተ ትብስ አንቺ ትብስ ተባብለው መኖር ችለዋል ፤ እየኖሩም ናቸው ፡፡ የገዥዎቻቸው ጫና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በውስጣቸው የነበረውን ግንኙነት መበጠስ ባይችልም ማላላት ግን ችሎ ነበር ፤ አንዱ እምነት በአንዱ ላይ እምነት እንዳይኖረው ሙስሊም ክርስትያኑን ፤ ክርስትያ ሙስሊሙን በተለያየ አይን እንዲተያዩ በማድረግ ደረጃ ከእምነቱ አማኞች በተለየ መልኩ ትልቁን ሚና ሲጫወት የነበረው መንግስት ነው ፤ በየጊዜ በእምነት ላይ ጥቂት የሚባሉ ብዙሀኑን የማይወክሉ ሰዎች የሚያደርጉትን የእምነት ነጻነትን መጋፋት አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ የሚያልፈው መንግስት ነገሮች የተለየ መንገድ እንዲይዙ መፍትሄም እንዳይገኝ ከማድረግ አኳያ የራሱን ሚና በየጊዜው እየተጫወተ ይገኛል፡፡ 

 መግቢያው የህዝቦች ነጻነት ህገ መንግስታዊ ዋስትና እንደተሰጠው ያትታል ፤ እኛ ይህን ዲስኩር መሬት ወርዶ መመልከት አልቻልንም ፤ በቅርቡ ከደቡብ ክልል የተፈናቀሉት የአካባቢው አርሶ አደሮች ላይ የደረሰው በደል ይህን አባባል ገደል የሚከት ሆኖ አግኝተነዋል ፤  ማንኛውም የእምነት ተከታይም ሆነ የትኛውም ብሔረሰብ በመላ ሀገሪቱ ተዘዋውሮ መስራት እንደሚችል ፤ መኖር እንደሚችል ህገ መንግስቱ ያስቀምጣል ፤ ይህ ግን ሲሆን እየተመለከትን አይደለም፡፡ ቀጥሎም የጋራ ጠላት የተባለው ኢቲቪ ላይ Screen saver መሆን የቀረውን ‘ድህነት’ና ኋላ ቀርነት ላይ ዜጎች እየተዋጉ መሆኑን ያስቀምጣል ፤ እኛን የገረመን 21 ድፍን ዓመታት ሙሉ “ድህነት” የሚለው ቃል እንዴት እንደማይሰለቻቸው ነው ፤ ማህበረሰቡ የነጣ ደሀ ነው ፤  በቴሌቪዥንና በኤፍ.ኤም ጣቢያዎች ከቀበሌ ባለስልጣናት እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ የዲስኩሮቻቸው ማጠንጠኛው “ድህነት” ነው ፡፡ ይገርማል!! የተፈጠረውን የእምነት ነጻነት ለማንኳሰስ የሚሯሯጡ ሃይሎች መኖራቸውንም ያስቀምጣል ፤ ሰው ስለ እምነቱ ለምን ብሎ መጠየቅ ከቻለ በተለየ አይን የሚታይበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ፤ ዋልድባልን ለምን ? ስንል ሌላ መነጽር ውስጥ ያስገቡናል ፤ ሙስሊሞችም መጅሊስ ለምን ? ሲሉ እንደዚያው ፤ ስለዚህ ህዝብ ጥያቄውን በተለያየ መልኩ ሊያቀርብ ይችላል ጥያቄውንም ከምንም ጋር ባለማያያዝ ተገቢ መልስ መስጠት ያለበት መንግስት ሆኖ ሳለ ጥያቄዎቻችን ከመመለስ ይልቅ የተለየ ስም በመስጠት የጥያቄውን መሰረት ወደ ሌላ የማዞር ስራ ይሰራል ፤ ኪራይ ሰብሳቢ ፤ ጸረ ዲሞክራሲ ፤ የልማት ጠር ፤ አሸባሪ ፤ እምነትን መከታ በማድረግ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኝት የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች ፤ በማለት ታፔላ ይለጥፋል   ፤  

በስተመጨረሻም “በየደረጃው በአመራሩ እና አባላት ዘንድ የውይይት መድረኮች ከፍተን መግባባት በመፍጠር ህዝቡን ከብዥታዎች አስወጥተን አክራሪዎችን በማጋለጥ ተባብሮ መንቀሳቀስ ይቻል ዘንድ በፈጸምነው እና ልንፈጽመው በሚገባን በተናፈሰው እና በእውነታው ….”ዙሪያ ስራ መሰራት እንዳለበት ያስገነዝባል ፤ ማህበረሰቡን መሰብሰቡ እና ሁኔታውን ማስረዳቱ መመካከር መቻሉ በጣም የሚደገፍ እና የሚበረታታ ጉዳይ ቢሆንም መንግስትን የሚወክሉ አካላት የማይላወስ የማይታጠፍ አምባገነናዊ አመለካከት ይዘው ስብሰባ ላይ ስለሚገቡ ውጤቱን መመልከት አልቻልንም ፤ ስብሰባው ሁላ ገለባ ሆኖብን ተቸግረናል ፍሬ ልናይበት አልቻልንም ፤ ለምሳሌ በአሁኑ ሰዓት ዋድባት በተመለከት ሲጀመር ጀምሮ በጣም በርካታ ስብሰባዎች ተደርገዋል ነገር ግን አንዱም ፍሬ የለውም ፤ ለምን ቢባል እነርሱ ከስብሰባው በፊት ስብሰባው እንዲህ መሆን አለበት ፤ እንዲህም መጠናቀቅ አለበት ብለው ሂሳቡን ቀድመው አስልተው ስለሚገቡ ውጤቱ መንግስትንና ህዝብን የሚያስማማ ሆኖም መመልከት አልቻልንም ፤ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ የስኳር ዳይሬክተሩ ባሉበት ከስብሰባው በፊት የስብሰባው ባለ ስድስት ነጥብ ዋልድባን በሚመለከት የአቋም መግለጫ አልቆ ተጽፎ ነበር ፤ ታዲያ ይህ ምኑ ነው ስብሰባ የሚያስብለው ? ከዚያ በኋላ ለሚስኪን ተሰብሳቢ ባለ ስድስት ነጥብ የአቋም መግለጫ  ሲነበብለት ሞቅ አድርጎ አጨብጭቦ ስብሰባው ይጠናቀቃል፡፡  

2 . “የበርካታ ዘመናት አድሎና ጨለማ ተገፎ ላለፉት 20 ዓመታት የእኩልነት ብርሀን አይተናል”  በማለት ከመግቢያው ቀጥሎ ጸሀፊው ሀሳቡን ይቀጥላል ፡፡ እፎይታ መጽሄት በገበያ በነበረችበት ጊዜ አንዱ ጋዜጠኛ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ወደ ደቡብ ያመራና ፤ አንድን የዶርዜ ብሔረሰብ አዛውንት “ከእፎይታ መጽሄት” ነው የመጣሁት እና እርስዎን ቃለ መጠይቅ ማድረግ እፈልጋለሁ ይላቸዋል ፤ እርሳቸውም ቀበል አድርገው ማን አልከኝ ? “እፎይታ” የማን እፎይታ ነው? የህዝቡ ነው የእናንተ ? ፤ ባይሆን እናንተ እፎይ ብላችሁ ሊሆን ይችላል ፤ ህዝቡ ግን አሁንም እፎይ አላለም ፤ ባይሆን የመጽሄቷን ስም “የእኛ እፎይታ” ብላችሁ ስሟ ብትቀይሯን መልካ ነው ብለውት ነበር ፤ እኛም አሁን የጨለማ ጊዜው ለማን እንደተገፈፈ እርግጠኛ ሆነን መናገር አንችልም ፤ እኛ ግን አሁንም ጨለማ ውስጥ ነን ፤ በደርግ ዘመነ መንግስት ቤተክርስትያን ላይ ያለ ህግ ያደረሰው አደጋ አሁን ደግሞ ህግን ከለላ አድርጎ እየተከናወነ ነው ፤ የቤተክርስትያን ቦታዎችን ያለ አግባብ የመቀነስ እና የመንጠቅ ስራን ተያይዛችሁታል ፤ በደርግ ዘመነ መንግስት ቤተክርስትያ የተወረሰባትን ህንጻዎችን እና ይዞታዎቿ አሁንም ስልጣን ከያዛችሁ ከ21 ዓመታት በኋ ስትመልሱ አልተመለከትንም ፤ ደርግ ግለሰቦችን በተናጠል  ሲገድል እናንተ ደግሞ  ገዳማትን በማፍረስ በጅምላ እምነትንና አማኞችን የመግደል ምግባር ላይ ተሰማርታችኋል ፤   

ፅሁፉ እንዲህ ይላል “ሀገራችን ለበርካታ ዓመታት  ዜጎች በሚከተሉት እምነት ብቻ ሳይሆን በደማቸውም ዝቅና ከፍ ተደርገው የሚታዩባት ነበረች፡፡ በየዘመኑ የነበሩ ነገስታት እና የበላይ መሪዎች አንዱን ሃይማኖት ከሌላው በማበላለጥ መንግስታዊ  ሃይማት እንዲኖር በህገ መንግስቱ በመደንገግ ሃይማኖትና ትምህርትን በማዋሃድ መሪዎቹ የሚፈልጉት ሃይማኖት በህግ ልዕልና እንዲያገኝ በማድረግ የሌሎች እምነቶችን ተከታዮች የሚያሸማቅቁበትን ስርዓት በመፍጠር ለበርካታ ዘመናት ህገ-መንስታዊ ጥበቃ እየተደረገለትና እውቅና የነበረው መድሎ አስፍነው ቆይተዋል፡፡” ይላል ፤ ይህን ማለት የሚችለው ለህዝቦች ሙሉ ነጻነት የሰጠ የመጻፍና የመናገር ሀሳብን ማንሸራሸርን ጉዳይ የሚቀበል ፤ ህዝቦችን በእኩል አይን በመመልከት በሚዛን የማይበድል ፤ ከባለፈው ትምህርት ወስዶ የተሻለች ኢትዮጵን ለመፍጠር የሚታትር ፤ በእምነቶች መካከል ያለውን ክፍተት በማጥበብ ህዝቡ በሰላም በመቻቻል እንዲኖር ስራ የሚሰራ መንግስት ነው ፤ እናንተ ግን ይህው 21 ዓመታችሁ የሞኝ ዘፈን ይመስል አንድ ነገር ትደጋግሙልናላችሁ ፤ በዘመናት የነበሩ ነገስታት የራሳቸውን አስተዋጽዎ ትልቅ አሻራ ጥለው አልፈዋል ፤ እናንተ ግን የእነሱን ችግር ክፍተት ለህዝብ በማሳየት ሳትሻሉ ተሽለናል በማለት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኝት ቀኑን ሙሉ ስትታትሩ ትታያለችሁ ፤ በወሬ የሚመጣ ለውጥ የለም ፤ በምታወሩበት እና ይህን ጽሁፍ በምትሰሩበት ወቅት መሬት የወረደ ስራ ብትሰሩ መልካም ተግባራችሁን ባትጽፉትም ያስተምር ነበር ፤ ይህ ግን አልሆነም ፤ 

በቅርቡ ከ50 ዓመት በፊት በአማርኛ የታተመ የቁርአን መጽሀፍ ላይ የመጀመሪያ የመግቢያ ገጽ የሚገርም ጽሁፍ ተመልክተናል ፤ በዘመኑ የነበሩት ሙስሊሞች ቀዳማዊ ኃይለስላሴን በወቅቱ ስለሰጧቸው የእምነት ነጻነት ቁርአኑን ታትሞ አስኪጨረስ ድረስ የቅርብ ክትትል በማድረግ ፤ ሙስሊሙን ከሚወክሉ ኢማሞች ጋር በመሆን ስራውን ከጫፍ ከማድረስ አኳያ ያደረጉትን አስተዋጽኦ በእምነት መጻህፍታቸው የመጀመሪያ ገጽ ላይ አመስግነው ሲጽፉ ስንመለከት በጣም ነው የገረመን ፤ በጊዜው የነበሩ አማኞች ሳይመቻቸው ተመችቶናል ፤ ሳይበሉ ጠግበናል ፤ ሳይጥጠጡ ረክተናል የሚሉ አይመስለኝም ፤ አሁን ግን እናንተ እየሰራችሁ ያላችሁት ስራ ሙስሊሞችን “በነገስታት ተበድላችኋል” እያላችሁ የመንገር ስራ ነው እየሰራችሁ የምትገኙት ፤ ሁሉም በዘመኑ መልካምም ይሁን ጥሩ ያልሆነ ነገር ሰርቶ ሊያልፍ ይችላል ፤ ዋናው ነገር ግን ቀጣዩ መንግስት ይህ ትምህርት ሆኖት የተሻለ ነገር ለመፍጠር መስራት ይገባዋል እንጂ ግንቦት 20 በመጣ ቁጥር ስለ እምነት ነጻነት መደስኮር “ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ” ስለሆነ አካሄዳችሁን አጢኑ ፤ ልቦና ካላችሁ ማስተዋሉን ካደላችሁ ኳሷ እግራችሁ ስር ናት፡፡    

ጽሁፉ ይቀጥላል “ሀገራችን የራሳቸውን ሃይማኖት ህገ መንግስታዊ ሽፋን ሰጥተው ይፋ የሀገሪቱ ሃይማኖት አድርገው የሌላውን ያረከሱ ስርአቶች የነበሩባት ያህል ጸረ-ሁሉም አይነት ሃይማኖቶች የነበረው የደርግ ስርአት ውስጥም አልፋለች፡፡…” በማለት ይቀጥላል ፤ ይህ ጽሁፍ “ለቀባሪው አረዱት” የሚመስል ነው ፤ እኛ ያለፍንበት አማኞች እያለን እናንተ ደግሞ የደርግን ስርዓት ለመንገር ትጥራላችሁ ፤ ደርግ ሙስሊም ክርስትያ ሳይል በርካታ መከራዎችን አድርሷል ፤ አቡነ ቴዎፍሎስን በግፍ በሲባጎ እንጦጦ አካባቢ በአንድ ቤት ውስጥ ገድሏል ፤ ይህ ቢያልፍም ታሪክ ነው ፤ እና ምን ይሁን ? ፤ አሁን እናንተ ከእርሱ የማትሻሉበትን ስራ እየሰራችሁ መሆኑን ተረዱ ፤ ደርግ 17 ዓመታትን ሲቆይ ዋልድባ ላይ ሄዶ ገዳሙን ለማጥፋት አልተነሳም ፤ የናንተ ምግባር ግን ከደርግም የባሰ ነው ፤ ሰውን መግደልና ሃይማኖትን መግደል ልዩነት አለው ፤ ደርግ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ገድሏል  ፤ እናንተ ደግሞ 40 ሚሊየን የሚቆጠር ኦርቶዶክሳውያን የመግደል ስራ እየሰራችሁ መሆኑን ማን ይንገራችሁ ? ፤ 1600 ዓመት ሙሉ ማንም ያልተደፈረውን እየደፈራችሁ መሆኑንስ ? ዋልድባ የመነኮሳት የጳጳሳት የፓትርያርኮች መውጫ መሆኑን ማን ይንገራችሁ? ምንጩን የማድረቅ ስራ እየሰራችሁ መሆኑንስ ማን ያስረዳችሁ? አስኪ በእምነት ደረጃ ከደርግ የምትለዩበትን ነገር ንገሩን ?  እነዚህን አጠፋችሁ ማለት በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ እምነቱን አጠፋችሁ ስርዓቱን አናጋችሁ ማለት ነው ፤ ዛሬ  ዋልድባ ላይ የሚማር የሚመመንን መነኩሴ ሳይኖረን ነገ ላይ ጳጳሳት ከየት የሚመጡ ይመስላችኋል ? ለኦርቶዶክስ ህልውና ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ገዳም መሆኑንስ ተገንዝባችኋል ? ስለዚህ መጀመሪያ ደርግን ለመውቀስ ከደርግ ተሸሎ መገኝት ግድ የሚል ይመስለናል፡፡ ጽሁፉ እንዲህ እያለ ዘወትር ጆሯችን የሰለቸውን የቴሌቪዥን ዲስኩር ላይ መሰረት በማድረግ ይቀጥላል

3 . በዚህ ውስጥ “የሀገራችን ሁኔታ ከአለም አቀፋዊ የሃይል ሚዛኑ ግብግብ ተነጥሎ አይታይም” የሚል ዋና አርዕስትን መሰረት አድርጎ ይጀምራል ፤ ቀጥሎም “ሀገራችንን ከየትኛውም ወገን ከሚመጣ የአለም አቀፍ የሃይልና የሃይማኖት ፉክክር ግንባርነት መከላከል የግድ ይላል” የሚል መፈክር ጽሁፉን ይጀምራል፡፡ “በፖለቲካዊ የሃይል ሚዛን ይሁን እስልምናንና ክርስትናን በምስራቅ ኢትዮጵያ በኩል ወደ ተቀሩት የአፍሪካ ሀገሮች ለማስፋፋት ኢትዮጵያን እንደ አንድ ግንባር የመጠቀም ፍላጎት ያለው ኃይል በርካታ ነው፡፡ የጂኦ ፖለቲካዊ የሃይል ሚዛን ላይ የተመሰረቱ የሃይል ፍላጎቶች በእምነት ተስታከው ሚቀርቡበት ሁኔታም አንዳንድ ጊዜም መሳ ለመሳ ሌላ ጊዜ ግንባር ፈጥረው የሚታዩባቸው አጋጣሚዎች ሰፋ ብለው ይታያሉ” በማለት በአሁኑ ሰዓት ከእምነት ጋር የተፈጠሩት ችግሮችን ፖለቲካዊ ይዘት እንዳላቸው በማመሳሰል ፖለቲካዊ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይሰጣል ፡፡ ቀጥሎም ባለፈው ዓመት በግብጽ ውስጥ ስለተከናወነው ዓመጽ ሙስሊሞች 90 በመቶ እንደሚሆኑ ከነዚህ ውስጥ 95 በመቶ የሚሆነው የሱኒ ቀሪው 5 በመቶ ደግሞ የሺአ እስልምና እምነት ተከታይ እንደሆኑ ፤ ክርስትያኖች ደግሞ ከ10 በመቶ እንደሚሆኑ ፤ ሁለቱም በአንድ ላይ ሁነው ስርዓቱን እንዳስወገዱ ያትታል፡፡ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የእስልምና ተከታዮች ሱኒ ፤ ሺአ ፤ ውሀቢያ ፤ እና በሌሎች ስሞች በመከፋፈል በመንግስ ላይ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበሪዊ ስራዎች ላይ ዘልቀው በመግባት መንግስት እንደመንግስት ያልቆመባቸውን ሀገሮች ከህዝባቸው ቁጥር ከቀደምት ታሪካቸው በመነሳት ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ይሰጣል ፤ በመቀጠልም “የችግሩን ስፋት እኛ ሀገር  ውስጥ ከሚኖረው ውስን መገለጫው ይልቅ አለም ዓቀፋዊ ፤ ፖለቲካዊና ጂኦ ፖለቲካዊ ይዘቱንም በመቃኝት ነው ልንረዳ የምንችለው እና የሚገባን” በማለት አሁን እየተፈጠረ ያለው ነገር ዓለማቀፋዊ ችግርን መነሻ በማድረግ አንባቢያን (የኢህአዴግ አባላት) በዚህ መልኩ እዲመለከቱት የነብይነት ስራውን እየሰራ ይታያል፡፡  በመጨረሻም “እያንዳንዳችን(አመራሮችን ይመለከታል) የመሰለንን እምነት ይዘን የራሳችንን የመያዝ መብታችን እንዲከበር የምንታገለውን ያህል የሌላውም መከበሩን መቀበል ፤ እንዲከበርም መስራት አለብን የምንለው ለዚህ ነው ፤ መንግስት በምንም አይነት መልኩ በሀይማኖት ጣልቃ አይገባም የምንለው ለዚህ ነው፤ መንግስታዊ ሃይማኖት ሊኖር አይችልም ፤ ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል ናቸው የምንለው ለዚህ ነው ፤ከድህነት በፍጥነት እንውጣ ፤ ዲሞክራሲን በፍጥነት እንገንባ ፤ ከእድገታችንም ሁሉም በጥረቱ ልክ የሚጠቀምበትን ሁኔታ እንፍጠር የምንለው ለዚህ ነው ፤ በእስልምና ይሁን በክርስትና የሚመጣን ጽንፈኝነት እንመክት የምንለው ለዚሀ ነው ፤ በነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ሀገራዊ መግባባትን ፈጥረን ረዥም ዓመት ከተጓዘን ድንቁርና ፤ ጸረ-ዲሞክራሲና ድህነት ከሚፈጥሩት ተጋላጭነት በፍጥነት በመላቀቅ ከውስጣችን ይሁን ከውጭ ሃይሎች ፍላጎቶች የሚመጣብንን አደጋ መመከት እንችላለን” በማለት ይቋጫል ፡፡ ይህ አባላቶች ሁኔታውን እንዴት መመልከት እና መመዘን እንዳለባቸው የሚያመላክት አንቀጽ ነው ፤

4. “አክራሪነትና አፈራረጁ ከልማትና ዴሞክራሲያችን አንጻር እና ከሃይማኖት መሪዎችና አባላት አንጻር” የሚል አርእስን ተጠቅሟል ቀጥሎም “ከየትኛውም ወገን በየትኛውም ሽፋን የሚከሰትን ጽንፈኝነት(አክራሪነት) ማጋለጥና ስለ ሰላም ማስተማር የእምነት ነጻነታችን እንዳይሸራረፍ መጠበቅ እንጂ የማንንም እምነት መጋፋት አይደለም” ብሎ ይጀምራል፡፡ “የችግሩን ምንጭ ስፋትና መገለጫ በማጤን በህብረተሰባችን ውስጥ በተገኝው አጋጣሚ ሁሉ መግባባት እንዲፈጠርበት ማስተማር ፤ የመታገያ አግባቦቹ ላይ ግልጽነትን መፍጠር የመንግስትና ሁሉም ሰላም ወዳድ ዜጎች ሃላፊነትም ግዴታም ነው፡፡  ችግሩ ከአንድ ሃይማኖት ጋር የተሳሰረ ባለመሆኑ በሚዲያዎች በትምህር ተቋማት ፤ በማንኛውም በርካታ ህዝብ በተገኝበት አጋጣሚ ሁሉ ስለ ህገ መንግስታችንና ሰላም ማስተማር የማንንም እምነት ማጉደፍ ፤ ወይም ማሞካሸት ሊሆን አይችልም ፤ በመሰረቱ በዓለማችን የሚታወቁ ትላልቅ ሃይማኖቶች ሁሉ ስለ ፍቅርና ሰላም ስለመቻቻል አብሮ መኖር የሚሰብኩ ናቸውና፡፡ በአንጻሩ ደግሞ በዓለማችን በአህጉራችን አፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በአገራችን አንዳንድ ሃይማኖቶች ጥቂት ተከታዮች  ዘንድ እምነቶቹን በሽፋንንነት ተጠቅሞም ይሁን በፖለቲካዊ ተለውሶ ከመሰረታዊና ነባራዊ የሃይማኖቶቹ አስተምህሮ ፈንጠር ብለው የሚንጸባረቁ መገለጫዎች አሉ ፡፡ እነዚህ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ነገር ግን ከሃይማኖቱ መሰረታዊ መመሪያዎች(ቁርአንና መጽሀፍ ቅዱስ) ያፈነገጡ ሆነው ሳለ በሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞችን ማጋለጥ ለሁሉም የእምነት ተከታዮች በአጠቃላይ ለዜጎች የማመን ብቻ ሳይሆን ያለማመን መብታቸውም ጭምር ተከብሮ በሰላም የሚኖሩበትን ሁኔታ መፍጠር እንጂ የትኛውንም ሃይማት መንካት አግባብ  አይሆንም ፡፡ መነሻችንና መድረሻን ህገ-መንግስታችንን የሚንዱ አደጋዎችን መከላከል በመሆኑ…” ይህኛው አንቀፅ ጨፍልቆ  የሚያስቀምጣቸው ነገሮች አሉ ፤ በተጨማሪ ማህበረሰቡና አመራሮች ጽንፈኞችን እንዲያጋልጥ ይመክራል ፤ እንዲህ እያለ የሚከተሉትን ነጥቦች ለመዳሰስ ይሞክራል፡፡
·        የሰሞኑ የነባሩ የኢትዮጵያ እስልምና አስተምህሮ ስልጠና እና ተያይዞ የተፈጠረው መደናገር
·        የመንግስትን ሚና በተመለከተ (የከወናቸወን ነጥቦች  የስልጠና ስፍራዎችን የማመቻቸት ጉዳይ ፤ የጸጥታና ጥበቃ አገልግሎት ጉዳይ ፤ የመንግስት ግዴታ የሆነው የህገ መንግስት ትምህርት በየስልጠናዎቹ ለአመራሮች የመስጠት ጉዳይ)
·        አህባሽ የሚባል አዲስ አስልምና በመንግስት ድጋፍ መጅሊስ አምጥቷ የሚል ተረተ
·        ቅርብ ጊዜ ወዲህ ከአወሊያ ጋር ተያይዞ የተፈጠረው ሁኔታ እና ይህን ተከትሎ በተወሰኑ ቡድኖች ተነስተው በርካታዎችን ያሳሳቱ የተሳሳቱ አቋሞች ..በማለት እስከ ሃያዎቹ መጀመሪያ ገጾች እነዚህን ሁኔታዎች ያስቀምጣል ነገር ግን እዚህ ጋር የተነሱት ሃሳቦች ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ባይመለከተንም በየቦታው ለጽሁፉ ማጣፈጫነት ሲጠቀመን መመልከት ይቻላል ፤ አሁን ይህ ሁሉ ነገር በየአዳራሾቻቸው ከታች እስከ ላይ ያሉ አካላት በመነጋገር አቋም የሚይዙባቸው ሆነው እናገኛቸዋለን ፤ ለማንኛው መንግስት በየወቅቱ የሚይዘውን አቋም ማወቅ ለአካሄድ መልካም ነው ፤
በስተመጨረሻ ፅሁፉ ለአባላት “ቀጣይ የትግል አግባባችን ምን ይሁን?” በሚል  ነጥብ ላይ ይህን ሰፍሮ እናገኝዋለን “ኢህአዴግ የቄሱም የሼሁም ድርጅት ነው ፡፡ ከአባልነት አንጻር የየትኛውም እምነት ተከታይ መሆን ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ፡፡ የአንድ እምነት ሰባኪ  የሆነ ሰው ኢህአዴግ አባል መሆን ይቻላል ፡፡ የኢህአዴግ አመራር መሆን ግን አይፈቀድም ፡፡ አልፎ አልፎ በአንዳንድ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ አባላችንና አመራራችን ዘንድ የመንግስትና የድርጅት አመራር ፤ የእምነት ተቋማት ሰባኪም ለመሆን የሚቃጣቸው እንደሆነ ይታያል ፡፡ ይህ ሁኔታ በማኛውም ወቅት ከተከሰተ በትግል መታረም አለበት ፤ አመራነት አንድ መደበኛ ስራ ነው ፡፡ ሰባኪነት ሌላ መደበኛ ስራ ነው ፡፡ ሁለቱን እያምታ የሚሄድ አመራ ሊኖረን አይችልም ፡፡ ከዚህ በመጠኑ የተሻሉት ደግሞ የሚያጠፉት አብረው ጥፋት ሳይፈጽሙ ፤ የሚያጠፋውንም  ታግለው ሳያስተካክሉ አጥር ጥግ ቆመው የሚመለከቱ ናቸው፡፡ ከድርጅታችን መርህ አንጻር ከታየ ሁለቱም ስህተቶች ናቸው፡፡ አብሮ ማጥፋትና ሌላው ሲያጠፋ እያዩ እንዳላዩ ማለፍም ስህተት ነው ፤ ዞሮ ዞሮ በሁለቱም መንገድ ጥፋቶቹ ከመፈጸም የሚገቱበት ሁኔታ አይኖርም፡፡
ሙስሊም ይሁን ክርስትያን አባላት ይህን ተከተሉ ያንን አትከተሉ የሚባሉበት ሁኔታ የለም ፡፡ በርካታ አባላት ማህበረ ቅዱሳን እንደሆኑት ሁሉ በርካታ አባላትም የወሃቢያ ወይን የሌላ የእስልምና ፈለግ ተከታዮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ችግሩ የትኛውም እምነት ይከተሉ የሚለው አይደለም ፡፡ ችግሩ ያለው ከሚከተሉት እምነት ወይም ሴክት ውስጥ መቻቻልን ፤ ህገ መንግስትን ሴኩላሪዝምን የሚሸረሽሩ ዝንባሌዎች ከራሳቸው ይን ከሌላ እምነት በተንጸባረቀ ጊዜ ሁሉ ከሚታገሉለት ድርጅት መርህ እና ከሀገሪቱ ህ መንግስት መንፈስ አንጻር  በጥብቅ ዲሲፒሊን የማይታገሉ መሆናቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው እምነታችንን በመከተልና የኢህአዴግ አባል ሆኖ በመታገል መካከል ቅራኔ የለም የምንለው ፡፡ በዚህ መንፈስ ነው አባላችን የሚጠበቅበትን ሚዛናዊነት ይዞ ህገ መንግስቱ እንዳይሸራረፍ እንዲታገል መጠየቅ እምነቱን እንዲሸረሽር መገደድ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባው፡፡” በማለት ይቀጥላል…..

በሌላ ነጥብ ውስጥ እንዲህ የሚል ነገር ያገኛሉ “ጅምላ ፍረጃ ማስወገዳችን አንድ ነገር ሆኖ በየደረጃው የሰከነ ውይይት እንዲካሄድ ማድረግ ይገባል፡፡ በሚዲያ የተጀመረው ውይይትም ህዝቡ ባጠቃላይ ስዕሉና በዝርዝር ክስተቶች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲገነዘብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለዘብተኛ አቋም ያላቸው ጽንፈኞቹም የሚዲያ አክሰስ አግኝተው ሀሳባቸውን ቢገልጹ ህዝቡ ተጨማሪመረጃ ያገኛል፡፡ የተሸለ ግልጽነት ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች በተለያዩ አማራጮች ሰፊው ህዝብ እውነታው ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዝ ማድረግ አለባቸው፡፡ ከዋህቢያ ይሁን ከማህበረ ቅዱሳን ወይም ከሌላው እምነት ውስጥ ጽንፈኝነት አይመለከተኝም የሚለው በግላጭ ወጥቶ እንዲያወግዝ እድል ሊኖረው ይገባል፡፡ በዚሁ አግባብም ልናደፋፍረውና ጽንፈኛው ተነጥሎ እንዲጋለጥ የሚያደርግ አካሄድ ሊኖረን ይገባል፡፡” ይላል ፤ 

ለእኛ ይህ ማለት መጀመሪያ “ጽንፈኛ ነህ”  ብሎ ካበቃ በኋላ ለመፍትሄው “አይደለሁም” ብለህ ራስህን ለህዝብ ግለጽ አድርግ እንደማለት ነው ፤ ይች አካሄድ በምስራቅ ሀረርጌ ልዩ ስሙ በበደኖ አካባቢ  የበርካታ ሰዎች ደም ያለበት በቀጥታ ትእዛዝ ያስጨፈጨፈ ሰውን ትዝ አስብሎናል አቶ ታምራት ላይኔ ፤ ሰውየው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሳለ ሊመታ ስለተፈለገ በቴሌቪዥን እንዲህ በልና ነጻ ትወጣለህ ያለበለዚያ ግን… ብለው ካባበሉት በኋላ ያችን እነርሱ የሚፈልጓትን ነጥብ አንስቶላቸው ሲያበቃ ቃሊቲ ወረወሩት ፤ አሁንም ጽንፈኝነትን መወገዝ ካለበት በአባቶች ዘንድ እንጂ አንተኛው ማህበር እንዲህ በልና አውግዝ አንተኛው ደግሞ እንዲህ በል ከተባለ በኋላ ይች ውግዘት ይዛ የምትመጣው ነገር አይታወቅም ፤ ዛሬ የምትሰጠውን የማውገዝ እድልን ብቻ አለመመልከት ነው ፤ ይዛ ይምትመጣውንም መዘዝ ማሰብ መልካም ነው፡፡        

ቸር ሰንብቱ 

8 comments:

  1. It's really a good analysis. Good job!

    ReplyDelete
  2. መንገዱን ዘግቶብን ቆሟል መኪናው:
    ወይ አዲስ አልገዛን በሽታ የሌለው:
    ተበላሽቶ ቆየ መተላለፊያው፡
    እባካችሁ ግፉ እናስወግደው።

    ReplyDelete
  3. The bloger, who are writing on this blog, is a christian, What is your problem whatever it has been talked by anyone? If I were you I don't care about the report of the "Addis Raey". In some extent it has a protection for the church whether you believe or not. Don't judge simply. If you have a problem say something. Government as a government has a responsibility for each and everything. Radicalism is the cancer for this country. It should be stopped. What is your problem when the government says this? Preach Gospel, go ahead, what is your problem then? Have you been beaten while you are preaching the Gospel? I don't think.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Ante buchi! Wusha! Yemimeleketinin eninageralen! Mahbere Kidusan yebete kirstian akal new. Addis Raey Metsihet yeminagerew yemimeleketenin new. Degmo menfesawi sew ye hager guday ayagebawum yale man new? Abune Petros be Italy Fascist yetegedelut Hagerin bilew ayidelem? Ante engidiyawus endet yigebahal.
      Gary endtechane bekilo adn akitacha bicha new yemitayih. Yehonewunim yalhonewunim wore bemamelales ena hassetegna report bemazegajet siltan mekonatet.
      To be EPRDF member for a long time, it needs some kind of stupidity!!! That is why EPRDF is full of stupids who thinks using Meles's Mind only. Meles may be clever how to protect his power for long. He may have some intelligence to reason and judge. But he never has access to full information to decide the right. You bow for him and he get more proud and proud till he loose to think the right.
      EPRDF is following after the Derg regime not only with time Chronology but also in actions and freedom.
      Please wash your eyes so that your vision gets more clear. Meditate with yourselves to evaluate your daily activities and interactions. How many times do you lie? How many times do you force people to do what do not want? How many times do ignore the service requests of the kind people that deserve your service? How many times do you insult people?
      Answer this questions for your selves!!! It will be useful for you!!!

      Delete
    2. menfesawi sew be'betekereseteayn zuria becha tatero mekemet yelebetem.... bezuria yalewen neger mekagnet asefelagi new...mengeste gudeguade eyekofere mehonune tenageru enji men aderegu enesu..egna gen masetewale aleben....

      Delete
    3. I totally agree with the involvement of the Spiritual men into the political works. However, the context of the addis raey is not as you said. The danger of Radicalism is the center at the end of the day for every problem. That is the context.

      Delete
  4. Every one can access every of your link by using
    1. www.sslbrowser.com
    2. www.proxfree.com
    this sites are very smart to unblock any blocked links sites so u can advertise this sites. I can access Dejeselam and Andadirgen(www.andadirgen.blogspot.com)so advertise this sites and every body can access any site via this sites.

    ReplyDelete
  5. It will take them only a day to block this site again. Please sort out other options so that we can follow you without difficulty.

    ReplyDelete