Tuesday, June 5, 2012

በቤተል ጊዮርጊስ ከይዞታ ጋር ተያይዞ በተነሳ ተቃውሞ ሁለት ሰዎች ሞቱ

(አንድ አድርገን ግንቦት29 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ቦታው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተል ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ሲሆን ይህ ቦታ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት ሰፊ ቦታ ካላቸው አብያተክርስያናት አንዱ ነው ፤ ቦታው ህጋዊ ካርታ ያለው ቢሆንም አጥር ግን የለውም ፤ በዚህ መሀል ባዶ ቦታ ነው በሚል ከቤተክርስትያኒቱ ቦታ ላይ መንግስት በመቁረስ ለሙስሊሞችና  ለተለያዩ መሰረተልማቶች በሊዝ የሸጠ ሲሆን ይህን ያወቁት የአካባቢው ነዋሪዎች በመሰባሰብ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ክፍለ ከተማ ድረስ ሂደው ጉዳዩን መንግስት ላስቀመጣቸው ሃላፊዎች ቢያስረዱም ሰሚ አላገኙም ነበር፤ በዚህ ሰዓት “እናንተም መታችሁ ቦታውን ታጥራላችሁ እኛም ዝም ብለን አንመለከታችሁም” በማለት በቁጣ ሊመለሱ ችለዋል ፤ ይህ ከሆነ በኋላ የቤተክርስያኒቱ ቦታውን ሲታጠር በቦታው በመገኝት የተመለከቱ ክርስትያኖች ባነሱት ተቃውሞ አንድ ወጣትና አንድ ፖሊስ በግጭቱ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል ፤የተፈጠረው ሁኔታ ያልተጠበቀ እና ተቃውሞውም ይበረታል ብሎ ያልጠበቀው መንግስት የክርስትያኖቹን ቁጣ በቀላሉ ለማብረድ ባለመቻል በአከባቢው የነበረው የፖሊስ ኋይል ህዝቡን ለመበተን በቂ ባለመሆኑ ከፌደራል ፖሊስ በርካታ የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች ወደ ቦታው በመምጣት ለተቃውሞ የወጣውን ህዝብ በአስለቃሽ ጭስ በትነዋል ፤ አስለቃሽ ጭሱ ወደ ጊዮርጊስ ቤተክርስያን ግቢ ውስጥ ሲተኩሱ ተስተውሏል ፤ በርካቶችም ለእስር ተዳርገዋል ፤ ይህ ተቃውሞ እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት ድረስ የህዝቡ ተቃውሞ በመቀጠሉ አካባቢው ውጥረት ነግሶበት አምሽቷል ፤ በዚህ ሁኔታ ህዝቡ ክፉኛ የተቆጣ በመሆኑ መንግስት ያለአግባብ የሸጠውን የቤተክርስትያኒቱን ቦታ ካልመለሰ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይፈጠር ያሰጋል ፤ በአሁኑ ሰዓትም የጦር ካምፕ ይመስል ቦታው በከፍተኛ የፖሊስ ሀይል እየተጠበቀ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡



ከዚህ ጋር በተያያዘ ከጊዮርጊስ ወረድ ብሎ የሚገኝው ከ10 ሺህ ካሬ በላይ የሚሆነው "ወይራ ታቦት ማደሪያ" የሚባለው ስፍራ ለጥምቀት ከ5 በላይ ታቦቶች የሚያርፉበትነና ከጥር 20-22 ድረስ በየጊዜው ትልቅ ጉባኤ የሚካሄድበት ቦታ ነው ፤ የዚህ ቦታ ህጋዊ ባለቤት ቤተክርስትያኒቱ ብትሆንም እስከ አሁን ድረስ ሳይታጠር እንዲህው ተቀምጦ ይገኛል ፤ ወደፊት እነዚህን የመሰሉ ቦታዎች የግጭት መነሻ እንዳይሆኑ የሚመለከተው አካል ትኩረት ቢሰጣቸው መልካም ነው፡፡

ከመስከረም 9 1998 ዓ.ም በፊት የተሰሩት በአዲስ አበባ የሚገኙ 120 ገዳማትና አድባራት የጸበል ቦታዎች ፤ የመካነ መቃብር ፤ የበዓለ ጥምቀት ማክበሪያ እና መሰል ስፍራዎች ሙሉ ይዞታቸውን ሳይቀነስ የይዞታ ማረጋገጫ እንደተዘጋጀላቸው ከወራት በፊት ገልጸን ነበር ፤ በዚህ ወቅትም አቡነ ጳውሎስ ከአዲስ አበባ መስተዳደር ተወካይ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መቀበላቸው ይታወሳል ፤ እነዚህ ቦታዎች ህጋዊ ካርታ እስካገኙ ድረስ ቤተክህነቱ እና አብያተክርስትያናቶቹ ቦታቸውን የመከለል ሀላፊነትን መወጣት አለባቸው፤ በከተማዋ ከ152 በላይ የቤተክርስትያኒቱ ገዳማት አድባራት እና የጸበል ቦታዎች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ 31 ገዳማትና አድባራ ቀደም ብሎ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መውሰዳቸው ይታወቃል፡፡



አሁንም መንግስት እጁን ከቤተክርስያናችን ላይ ያንሳ ዋልድባ ድረስ ሄደን የሚሰራውን የስኳር ልማት  መቃወም ቢያቅተን እንኳን እዚህው አጠገባችን ያለውን የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተክርስትያን ቦታ ቆርሶ ሲሸጥ አይተን ዝም የምንልበት አይን ሰምተን የምናልፍበት ጆሮ የለንም ፡፡

11 comments:

  1. This is a typical strategy of the government to give a fighting agenda for both Christians and Muslims.

    It is for diverting the attention of both Muslim and Chrstian community. Very sad!

    ReplyDelete
  2. God help us please!

    ReplyDelete
  3. መንግስት እጁን ከቤተክርስያናችን ላይ ያንሳ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  4. አቤቱ የሆነብንን አስብ!!!!


    ከዚህ በላይ መቀለድ አይቻልም፣ መንግስት አርፎ አልቀመጥ ካለ በራሱ ጊዜውን ያሳጥራል

    ReplyDelete
  5. at Anonymouse (12:02) እኔም በሃሳብህ እስማማለሁ መንግስት መፍትሄ መስጠት ያቃተዉን የሙስሊም ወገኖቻችን ጥያቄ እና የኛዉ የኦርቶዶክስ የዋልድባ ጥያቄም መልስ መስጠት ስላልቻለ ምናልባት ለምን እርስ በእርሳቸዉ ኣናፋጅም ብሎ ከሆነስ ጎበዝ!!! በሌላ መልኩ ደግሞ ክርስያን እና ሙስሊሙ ሲፋጅ ሌሎች የምእራቡርእዮተዓለም ኣራማጆች (ኣብዛኞቹ ኢሃዴጎች)አገሪቱን ለመዉረር ይሆን መጠርጠር ደግ ነዉና ምናለ ሁለታችንም ነቅተን በመከባበር ብናሳፍራቸዉ!!!!!
    ገብረወት ባይከዳኝ

    ReplyDelete
  6. እጅግ በጣም ያሳዝናል! ቦታው ይዞታነቱ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ከተመሰረተ ጀምሮ የደብሩ ሲሆን የደብሩ ምዕመናን በቅርብ ጊዜ የተመረቀውን አዲሱን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በመስራት ከፍተኛ ርብርብ ሲያደርጉ የኖሩ ናቸው:: አሁን ደግሞ አጥር ከማጠር ጀምሮ ያለውን የልማት ሥራ ለመስራት በዝግጅት ላይ ነበሩ:: በመሀሉ በየቦታው (በሀገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጭ) ያለን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች በአንድነት አሁን ያለውን ቅኝ ገዚ የኢሀዲግ መንግስት በቃን ተነቃብህ አንፈልግህ ብለን ስንቃወም ይህንን አንድነት ሰብሮ እድሜውን ለማራዘም ይህ የተረገመ መንግስት የቀየሰው ወንድማማቾችን የማጋጨትና በእነርሱ ደም ዙፋኑን ለዘላለም ዘርግቶ የመኖረ ተንኮል ይህን አይነት አሳዘኝ ሥራ እንዲሰራ አድርጎታል:: ሕዝቡ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሊጠነቀቅ ይገባል ክርሰቲያኖችና ሙስሊም ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ እንያያዝ አደራ በፈጣሪያችን ሥም እማጸናችሁአለሁ! መውደቂያው የደረሰበት ይህ መንግስት በእኛ ደም እድሜውን እንዳያራዝም በአንድነት እንቁም!ለዚህ ታላቅ የሆነ ሃገርንና ቤተክርስቲያንን ከቅኝ ገዚዎች የመታደግ ሥራ ለሰማዕትነት እንነሳ! ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር ህይወቱን የሰጠው ወጣት አስቀናኝ እንድን ከተለው እግዚአብሔር ይፍቀድልን!

    ReplyDelete
  7. ይሄ ወሮ በላ መንግሥት ሰፊ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን በነጻ አስረከበ ዝም አልን! በሚሊዮን ሄክታር የሚቆጠር የኢትዮጵያ ለም መሬት ለሳውዲ ለማሌዚያ ለቻይናና ለህንድ ባለሃብቶች ተሽጦ ገንዘቡን ኪሱ አስገባ ዝም አልን! በርካታ ሄክታር የኦሮሚያ ለምለም ደን በእሳት ተቃጥሎ ተመንጥሮ ለውጭ ኢንቬስተሮች ሻይ ቅጠል መትከያነት ተሽጦ ገንዘቡን ኪሱ አስገባ ዝም አልን! ለምቶ እህል ልንበላበት ከልመና ልንወጣበት የሚያስቸል በርካታ ሄክታር መሬት ለጠገቡ ፈረንጆች አበባ ማብቀያ እንዲሆን ተሽጦ ገንዘቡን ኪሱ አስገባ የአበባው መሬትም ሌላ የእህል ዘር እንዳያበቅል ሆኖ በአሲድ እየተቃጠለ እያየን ዝም አልን! ወደ ዋልድባ ገዳም ሄዶ የእምነት ቦታውን በጉልበቱ ነጥቆ የቅዱሳንን አጽም እየፈነቀለ ሲጥል አቅም የሌላቸው መነኮሳትን እያሳደደ ሲያስር እያየን ዝም አልን! አሁን ደግሞ በሃገሪቱ ያሉ ቤተ ክርስቲያኖችንና መስጊዶችን ቀስ በቀስ ይዞታቸውን እየሸጠ ገንዘቡን ኪሱ መክተት ጀመረ ዝም አልን !በዚህ ጉዳይ ማንም እንዳይቃወመው በቤተክርስቲያን ካድሬዎችን ከዲያቆን እስከ ፓትርያርክ አስቀመጠ በመስጊድ ካድሬዎቹን ከደረሳ እስከ ኢማና የመጅሊስ መሪ ጭምር አስቀመጠ! ደጋፌዎቹ አህባሾችንም ሰገሰገ! ወገኖቼ በሂደት ሃገራችንን እያጣናት እኛም ለባርነት እየተሸጥን ነውና በእግዚአብሔር ወይም በአላህ ሥም ሃገራችንን በአንድነት እንድናድናት እለምናለሁ ሃገራችንን በአንድነት እንድናድናት እለምናለሁ ሃገራችንን በአንድነት እንድናድናት እለምናለሁ !ሃገረ የሌለው የተዋረደ ስደተኛ ሆነን ከምንቀር ሃገር ያለው ለሃገሩ በክብር የሞተ ሰው ብንሆን ይሻለናልና በአንድነት እንቁም!

    ReplyDelete
  8. minew albezam?
    arfo yetekemete yetegnawin bere
    nekaktew qesqisew aderegut awre
    Mengist hoy bedel. fida, siqay, chikaneh beza. Yeterabe hodin hod asbisehewal metekegza bet eyasatahew new. ahunis semaetinetin yedem timatihin begilts eyawejih new. ke'engidih gin ................

    ReplyDelete
  9. Mengist yalemal enji hager yishetal, hizbin yatalilal, tiwlidn yatefal, selamin yinesal endie ?

    ReplyDelete
  10. Amlake semaitu zim atbelen!!!

    ReplyDelete
  11. mengist yemanwedewin poetics west endengeba lemen endemegefafan alakim

    ReplyDelete