- "እርሶ እኛን አይወክሉንም እና ልንሰማዎትም ሆነ ቡራኬዎትን አንቀበልም" ከመነኩሳት ወገን ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
- "በዋልድባ ገዳም ምንም ድርድር አናደርግም" የአካባቢው ነዋሪ
- በርካታ ወጣቶችም በመንግሥት ታጣቂዎች ታፍሰው ተወስደዋል
ባለፈው ቅዳሜ በዓዲርቃይ ከተማ ላይ በዋልድባ አካባቢ ሊሰራ በታቀደው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ የአካቢው ነዋሪዎችን፣ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤልሳዕ በተገኙበት፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች በተገኙበት እንዲሁም ከቤተክህነት ተወካዮች በተገኙበት የማስፈራራቱ እና በግድ የማሳመኑ ስራ እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን በደረሱን መረጃ መሰረት መንግስት ለልማቱ እፈልጋቸዋለው ከሚላቸው የዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ የሚፈርሱን መካናት የሚከተሉት ናቸው፡
- ከአበረንታት
- ማርገፅ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
- ድል ሰቆቃ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
- እጣኑ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተክርስቲያን
- ሙሉ ቤት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
- ከአባ ነፃ
- ዲዋር ግዛ ቅዱስ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን
- ማይ ሸረፋ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
- አዲ ፈረጅ አብዮ እግዚ ቤተክርስቲያን
- ማይ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
- ታች እጣኖ ቅዱስተ ማርያም ቤተክርስቲያን
- ላይ ኩርማ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
- ጎድጓድ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን
- ቃሊማ አቡነ ሳሙኤል ቤተክርስቲያን
- ቃሊማ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
- ቃሊማ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን
- ማይ ዓርቃይ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እና ሌሎችም ስማቸው ያልተገለጸ አብያተ ክርስቲያናት እንደሚነሱ ዘገባው ደርሶናል።
ለዚህም ነው የገዳሙ መነኩሳት ይልቁንም በሰቋር ኪዳነ ምሕረት የሚገኙት መነኩሳይት (አነስት) ታላቅ ተጋድሎ እያደረጉ የሚገኙት፡፡ እንደ መነኩሳይቱ አነጋገር “በመጀመሪያ እኛን ገድላችሁ መሬቱን ማረስ ትችላላችሁ አለበለዚያ ግን እኛ በሕይወት ቆመን ቅዱሳን አባቶቻችን በደማቸው እና በአጥንታቸው ያስከበሩት ገዳም በኛ በልጆቻቸው በአረማውያን ሊወሰድ አይችልም” በማለት በታላቅ ተጋድሎ ላይ ይገኛሉ። ". . .የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ. . ." መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ ፳ ፥ ፫ የናቡቴ ቃል ዛሬም በእነዚህ መነኩሳይት አድሮ ለእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ያስተጋባል የአባቶቻችን ርስት እንሰጥ ዘንድ ከእኛ ያርቅ በማለት።
እንደመረጃ ምንጫችን ከሆነ በስብሰባው ዕለት የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በቦታው ተገኝተው ቡራኬ ለማድረግ ሲነሱ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል "እርሶ እኛን አይወክሉንም" በማለት ተሰብሰባዊ ገዳማውያኑ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ በከፍተኛ ደረጃ በቦታቸው ያልተገኙትን አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ ኮንነዋቸዋል፣ በተያያዘ ዜና በስብሰባው እለት የቤተክህነቱም ተወካዮች በቦታው ተገኝተው ገዳማውያኑን እና የአካባቢውን ነዋሪ ለማሳመን ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ እንደነበር እና በመጨረሻ የመንግሥት ተወካዮች ቦታው እንደውም "የአማራ ክልል አይደለም" ይህንን በቀጥታ የሚመለከተው "የክልል ትግራይ" ነዋሪ ነው በማለት የስብሰባውን መንፈስ ወደ ዘር እና ጎሳ ሲለውጡት ተመልክተዋል። እነዚሁ የመንግሥት ተወካዮችም በግድም ይሁን በውድ ልማቱን መቀበል አለባችሁ የሃገራችን የሥራ አጥ ቁጥሩን በ50000 ይቀንሳል በማለት ዲስኩራቸውን መስማት ለሰለቸው ተሰብሳቢ ሲያሰሙ ውለዋል።
በመጨረሻ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ ተሰብሳቢው የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች “ከዚህ በኃላ ስብሰባ አትጥሩን አቋማችን የታወቀ እና አንድ ነው የአባቶቻችንን ርስት አትንኩብን፣ አጽመ ቅዱሳኑን አታፍልሱ፣ ካልጠፋ መሬት ለምን ወደ ገዳማን መጣችሁብን፣ እኛ ጉልበታችን መድኅኒዓለም ነው ያሻችሁን ማድረግ ትችላላችሁ መሬቱንም ስታርሱ እኛንም ገድላችሁ መሆን አለበት” በማለት ከፍተኛ የሆነ ሁካታ ተነስቶ በስብሰባው ከተሳተፉትም አንሰበሰብም በማለት በውጭ ቁጭ ብለው ከነበሩ በተለይ ወጣቶችን የመንግሥት ታጣቂዎች በርካታዎችን ጭነው ለእስር ዳርገዋቸዋል በርካቶችም ሸሸተው ወደ ጫካ እንደገቡ ከአካባቢው ምንጮቻችን ገልጸውልናል። ማኅበረ መነኩሳቱም ምሬት በተሞላበት መልኩ ነዋሪዎችን "መጥታችሁ ቅርሶቻችሁን ተረከቡን" ሲሉ መሰማታቸውንም እነዚሁ ምንጮቻችን ገልጸውናል።
መንግሥትም በማናለብኝነት አብያተ ክርስቲያኑን እንደሚያፈርስ ሲገልጽ፣ የቤተክህነቱም ተወካዮች ተባባሪ ሆነው ለአብያተ ክርስቲያኑ መፍረስ አይነተኛ ተሳትፎ ሲያደርጉ በሌላ በኩል የዋልድባ ገዳም ማኅበረ መነኩሳቱ፣ የአካባቢዊ ነዋሪ በተለይ ደባቅ፣ ዛሬማ፣ ዓዲርቃይ፣ እና አካባቢው ላይ ያሉ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነት እየከፈሉ በሚገኙበት በዚህ ሰዓት እኛ እንደክርስቲያን አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል። በማንኛውም በጸሎትም በገንዘብም በማንኛውም መንገድ ልንተባበራቸው እና ቅዱሱን ገዳማችንን የሊቃውንት መፍለቂያ እንዲሁም የበረካታ ዓይናማ መምህራንና የቤተክርስቲያን ሊቃውንት መገኛ የሆነውን ገዳም ልንታደግ ይገባል እንላለን።
እግዚአብሔር ቤተክርስትያን ይጠብቅ
ከSave Waldba የተወሰደ
ገዳማውያኑን አባቶች እግዚአብሔር ያታደጋቸው! ቤተ ክርስቲያናችን በአጠቃላይ መሪ የላት መሪዋ መድኃኔዓለም ነው የእሱ ሰራዊተ መላእክት አሉ እውነት ልንገራችሁ! አባ ጳውሎስና ግብረ በላዎቹ ቤተ ክርስቲያንችን ምንም አልቀረም እያጠፏት ነው ሐብቷን ንብረቷን እየዘረፉ እያዘረፉ ናቸው የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይፍረድባቸው! መለስ ዜናዊን ጀነራል ውንጌት አብረን ነው የተማርነው በጣም ክፉ አረመኔ እግዚአብሔርን የማያውቅ እግዚአብሔርን የሚሳደብ ነው ዓይነ ስውራንን እንዴት እንደሚያገላታ ጠቅላላ ተማሪዎችና አስተማሪዎችን የሚያዝኑበት ሰው ነው ከዲያብሎስ ጋር በእድሜ ነው እንጂ የሚበላለጡት ተግባራቸው አንድ ናቸው መለስ ሳይበልጥ አይቀርም እሱ ኢትዮጵያዊ ስላልሆነ ለኢትዮጵያውያን ግድ የለውም ጨካኝ ሰው ነው ወደ ልቡ ቢመለስና አማኝ ቢሆን መልካም ነው ወደ ፊት ብዙ የምለው ነገር አለኝ በመለስ እምነት ዙርያ በቅርብ ጓደኛዬ ስለነበር ምን እንደሚል አወራለሁ የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረድበት ታያላችሁ በቅርብ ቀን እግዚአብሔር በቤተ መንግሥትም በቤተ ክህነትም ፍርድ ያመታል ... ይቀጥላል
ReplyDeletePlease let us know about him(Meles) in this blog. We don't know our leader help us by writing something in this blog. Thanks.
Deleteተዉ ገዳማቱን መዳፈር ይቅርባችሁ
ReplyDeleteበነሱ ፀሎት ነውና እዚህ መድሳችሁ
እባካችሁ ገዳማቱን መዳፈር ይቅርባችሁ
ሰለፊያ ስትሉን በአደባባይ ዝም አልናችሁ
ለአምላካችን እርሱ ይየው አልናችሁ
እርሱም የበቀል አምላክ ነውና መለሰው በአደባባይ
ያውም አድርጎ ለዓለም እንዲታይ
አሁን ተዉን አትንኩ ገዳማችንን ዋልድባን
አትንኩብን አባቶቻችንን ቅዱሳን
ለእኛም ለእናንተም ብሎም ለዓለም የሚፀልዩትን
በረከታቸው ለሁላችን የሚደርስልንን
እባካችሁ ዋልድባ እንኩዋን ፖለቲካ አይነገርበትም ወሬ
መናኞቹ የሚኖሩ ናቸውና በመንፈስ ፍሬ
አሁንም እንላለን አትንኩብን ገዳማችንን
ለመኖራችሁ ምንም የላችሁም ተገን
መጨረሻችሁ ይሆናል ማዘን
ሳትባሉ ማኔ ቴቄል ፋሬስ
የእውነት አምላክ በልባችሁ ይንገስ!!!
benatiwo tolo tsafu selzihe nfese bela aremene sewe yeaba paulose buchila, Egziabhere be Abebe Gelawe awredotale gena yeketililetale ayekerlete ke amilakachine eyemetabete endehone alaweke
ReplyDeleteተዉ ገዳማቱን መዳፈር ይቅርባችሁ
ReplyDeleteበነሱ ፀሎት ነውና እዚህ መድረሳችሁ
እባካችሁ ገዳማቱን መዳፈር ይቅርባችሁ
ሰለፊያ ስትሉን በአደባባይ ዝም አልናችሁ
ለአምላካችን እርሱ ይየው አልናችሁ
እርሱም የበቀል አምላክ ነውና መለሰው በአደባባይ
ያውም አድርጎ ለዓለም እንዲታይ
አሁን ተዉን አትንኩ ገዳማችንን ዋልድባን
አትንኩብን አባቶቻችንን ቅዱሳን
ለእኛም ለእናንተም ብሎም ለዓለም የሚፀልዩትን
በረከታቸው ለሁላችን የሚደርስልንን
እባካችሁ ዋልድባ እንኩዋን ፖለቲካ አይነገርበትም ወሬ
መናኞቹ የሚኖሩ ናቸውና በመንፈስ ፍሬ
አሁንም እንላለን አትንኩብን ገዳማችንን
ለመኖራችሁ ምንም የላችሁም ተገን
መጨረሻችሁ ይሆናል ማዘን
ሳትባሉ ማኔ ቴቄል ፋሬስ
የእውነት አምላክ በልባችሁ ይንገስ!!!