Tuesday, June 26, 2012

የቁጥር ነገር


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ

(አንድ አድርገን ሰኔ 19 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በርካታ ጊዜያት መንግስት እና አለማቀፋዊ ተቋማት የቁጥር ነገር አያስማማቸውም ፤ IMF ወይንም World Bank የሀገሪቱ እድገት በዚህኛው ዓመት 6 ከመቶ አይበልጥም ብሎ ሲተነብይ መንግስት ደግሞ “አይሆንም እኛ ለተከታታይ 6 ዓመታት 11.2 በመቶ ነው ያደግነው” በማለት ዓመታዊ ያልተሰላ ሂሳብ ያቀርባል እና በየዓመቱ ሰኔ አልፎ ሀምሌ ሲመጣ የቁጥር ነገር ዋናው የመከራከሪያ ያለመስማሚያ ነጥብ ሆኖ መመልከት የዘወትር ተግባራችን ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ አሁን እኛ አነሳሳችን ስለ እንደዚህ ዓይነት ነገር ለመናገር አይደለም  ፤ ባይሆን ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ይህ “የቁጥር ነገር” በሙስሊም ወንድሞቻን ዘንድ እንዴት እየቀረበ መሆኑን ለማስገንዘብ እና ለማሳየት በማሰብ ነው “የቁጥር ነገር” በማለት የተነሳነው፡፡


ከጥቂት ቀናት በፊት የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ላይ “እስልምና በኢትዮጵያ” የሚል የእስልምና በኢትዮጵያ አመሰራረት ከስነ መሰረቱ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ያለውን አመለካከት በምሁራን አንደበት ሰፊ ትንታኔ በመስጠት ሰዎች እንዲያውቁ የማድረግ ፕሮግራም በመስራት ላይ ይገኛል ፤ ተጋባዥ እንግዶች በእምነቱ ውስጥ የተለያየ የስልጣን ተዋረድ ላይ ከሚገኙ የሃይማኖት ሰዎች በተጨማሪ በእስልምና እምነት ላይ የዶክትሬት ወረቀታቸውን የሰሩ ሰዎች ይገኙበታል፤ በዚህ ወቅት በእውቀት ደረጃ ያወቅናቸውንና የታዘብናቸውን ነገሮች አሁን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማመሳጠር ለማቅረብ አንወዳለን ፤ የመጀመሪያው ሙስሊም ወንድሞቻችን “ኢትዮጵያ ውስጥ የነገሠ የእስልምና ሃይማኖትን የሚከተል ንጉስ” እንደነበር ዘወትር በመገናኛ ብዙሃን ፊት በመቅረብ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነገር ሆኗል ፤ ነገር ግን በዚህ የውይይት መድረክ ላይ እንደተገነዘብኩትኝ ኢትዮጵያ ውስጥ የእስልምናን እምነት ተከታይ የነበረ ንጉስ እንዳልነበረ  ፤ ይህን ንጉስ አለ ብለው የሚሉ ሰዎች ካሉ መሰረታቸው አፈ-ታሪክ እንጂ የሚጨበጥ ማስረጃ እንዳልተገኝለት ጭምር ነው ፤ ነገሠ የተባለበት ዘመን ትንሽ ራቅ ስለሚል በዚያን ጊዜ የነበረ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ጸሀፊዎች የተጻፉ መዛግብት ማግኝት አልተቻለም ፤ ይህ ንጉስ ነገሰ በተባለበት ዘመን አነጋገሡን ፤ ማንን እንዳገባ ፤ ምን ያህል ልጆች እንደወለደ ፤ ልጆቹ የእርሱን ንግስና ለምን እንዳልተቀበሉ እና ለትውልድ ለምን እንዳላስተላለፉ የሚገልጥ ይህ ነው የሚባል ማስረጃ ማግኝት አዳጋች መሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ አሁን የማንንም ታሪክ ለመደምሰስ ወይም እንዳልተደረገ ሆኖ ለማቅረብ ሳይሆን ያልተደረገን እና በዘመኑ ያልተከናወነን ነገር ከ15 ክፍለ ዘመን በኋላ በመነሳት እኛም ነገስታት ነበሩን ማለት በታሪክም ተጠያቂ ስለሚያደርግ ይህ ነገር እንደዚህው በቀላሉ መታየት የለበትም የሚል አቋም አለን፡፡

ባለን መረጃ መሰረት በትግራይ አካባቢ የሚገኝው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው መስጂድ እንደሆነ የሚነገርለት አል-ነጃሺ መስኪድን ከላይ ካልነው የፈጠራ ታሪክ ጋር በማመሳጠር የሀገሪቱ እና የዓለም ቅርስ ሆኖ እንደ ላሊበላ አክሱም እና መሰል አድባራት የማስመዝገብ ስራ መጀመሩን ነው፡፡ እኛ ይህ መስጂድ በታሪክነት መመዝገብ የለበትም የሚል ጭፍን አመለካከት የለንም ፤ ነገር ግን መመዝገብ ያለበት በጊዜው የነበረው ታሪክ መነሻ በማድረግ ሳይጨመርና ሳይቀነስ መሆን መቻል አለበት የሚል የጠራ አቋም አለን ፤ ክርስትትያኑ ታሪክ እንዳለው ሁላ ሙስሊሙም የራሱ ታሪክ አለው ፤ ነገር ግን ያልተደረገን ታሪክ ለፉክክር መጨመር ታሪክን ከማጉደፍ በተጨማሪ ወደፊት የሚያመጣው የታሪክ መፋለስ ስለሚኖር መታሰብ ያለበት ጉዳይ መሆን መቻል አለበት፡፡

በመቀጠልም በዚህ “እስልምና በኢትዮጵያ” የሚል ተከታታይ ፕሮግራም ላይ አንድ በአሁኑ ሰዓት የሙስሊሙን ጥያቄ መንግስት ዘንድ እንዲያቀርብ ከተመረጡት ሰዎች ውስጥ ስለ አንዋር መስኪድ ስለተሰበሰበው የአማኝ ብዛት ሲናገር እንዲህ በማለት ነበር “በዛሬው እለት ከግማሽ ሚሊየን በላይ ኢስላም በመርካቶ አንዋር መስኪድ በመሰብሰብ ከስግደት በኋላ ተቃውሞውን ማሰማት ችሏል” በማለት ሲናገር በመስማታችን በጣም ተገርመናል ፤ ሲጀመር አዲስ አበባ ውስጥ በባለፈው ሀገራዊ የህዝብ ቆጠራ ስሌት ከ2.8 ሚሊየን በላይ ሰዎች በከተማይቱ ይኖራሉ ብሎ ያስቀምጣል ፤ ታዲያ ከዚህ ቁጥር ውስጥ 74 በመቶ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አማኝ ሲሆን ፤ 16 በመቶ ደግሞ የእስልምና ሃይማኖት አማኞች መሆናቸውን ያስቀምጣል ፤ እኛ ለሂሳብ እንዲያመቸን የከተማዋ ነዋሪ 3.5 ሚሊየን ብናደርሰው እንኳን ሁሉም ሙስሊም ከቤቱ ወጥቶ አንዋር መስኪድ ቢሰበሰብ 560 ሺህ ህዝብ ነው የሚሆነው ፤ ይህ ደግሞ የማይታሰብ ነው ፤ እንዲው የውስጥን መሻት ከመግለጽ አኳያ ካልሆነ በቀር ያልሆነ እና ያልተደረገን ነገር በመገናኛ ብዙሃን ብዙሀንነትን ለመግለጽ መናገር ራስን ትዝብት ላይ ስለሚጥል ጠንቀቅ ማለቱ የተሻለ ይመስለናል ፡፡


Based on the 2007 Census conducted by the Central Statistical Agency of Ethiopia (CSA), Addis Ababa has a total population of 2,739,551, of whom 1,305,387 are men and 1,434,164 women; ....... The religion with the most believers in Addis Ababa is Ethiopian Orthodox with 74.7% of the population, while 16.2% are Muslim, 7.77% Protestant, and 0.48% Catholic.[17]   

የዛሬ ሁለት ዓመት ‹‹አረፋ›› በዓላቸውን ሲያከብሩ እንደተለመደው በጠዋት አዲስ አበባ ስታዲየም በመሄድ የስግደት ስርአታቸውን እያከናወኑ ነበር ፤ በጊዜውም በቀጥታ በሚደረግ ስርጭት ላይ የኢቲቪ ሙስሊም ዘጋቢ እንዲህ ብሎ ነበር “ በዛሬው እለት ከ1.5 ሚሊየን የሚበልጡ ሙስሊሞች በስታዲየም እና በዙሪያው በሚገኙ ቦታዎች ላይ በመገኝት በአሉን በደማቅ ሁኔታ እያከበሩ ነው” በማለት ሲናገር ፊቱ ላይ የማፈር ወይም የመሸማቀቅ ሁኔታ በፍጹም አይታይበትም ፤ በመሰረቱ ስታዲየሙ ሰዎች የሚቀመጡበት ቦታ ቢሞላ መቀመጫው ብቻ 40 ሺህ ሰው መያዝ አይችልም ፤ ሜዳው ከ10 ሺህ ሰው በላይም መስተናገድ አይችልም ፤ በስታዲየሙ ዙሪያ አስር የስታዲየምን ቦታ የሚያክል ህዝብ መስገድ ቢችል እንኳን ከግማሽ ሚሊየን የማይበልጥ ቁጥር እናገኛለን፤ ይህ ማለት እኛ እጅጉን አጋነነው ነው እንጂ የዚህን ግማሽ ሰው ከወጣ ራሱ ብዙ የሚባል ቁጥር ነው ፤ እየሆነ ያለው ነገር ግን የራስን ቁጥር ከክርስትያኑ ጋር በማስተያየት ለራስ የተሻለ እይታን ለመፍጠር የሚደረግ ነገር መሆኑን ለማወቅ ያችላል ፤

መንግስትም ይህን ለምን ? ብላችሁ ብትጠይቁ “የሃይማኖት እኩልነት” የምትለውን አንቀጽ ከህገ መንግስቱ ላይ በመምዘዝ መልስ ይሰጣል  እንጂ ስለ ተባለው ቁጥር ትክክለኝነት ዘጋቢውን የሚጠይቅበት አግባብ የለውም ፤ ይህ ማለት ከአዲስ አበባ ነዋሪ 50 በመቶ ሙስሊም ነው እያሉን ነው ፤ እርስዎ ይህን ነገር እንዴት ያዩታል ? በመሰረቱ በአዲስ አበባ ውስጥ በመስኪድ ቁጥር ከ100 ካሬ እስከ ከ5ሺህ ካሬ በላይ ስፋት ያላቸው ከ150 በላይ መስኪዶች እንዳሉ እሙን ነው ፤ ከእነዚህ ውስጥም 70 በመቶ የተሰሩት ባሳለፍነው 10ት አመታት ውስጥ ነው ፤ የኦርቶዶክስት ቤተክርስትያን በ1826 ዓ.ም በመጀመሪያ ከተመሰረተው የቀራንዮ መድሃኒአለም ቤተክርስትያን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ያሉት ከ132 አይዘሉም ፤ ይህ አሁን መሬት ላይ ያለ እውነታ ነው ፤ ይህ የአማኝ ቁጥር ግን ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው ፤ የኤፍ ኤም ጣቢያዎቻችን እና ብቸኛው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና መሰል የመገናኛ ጣቢያዎች  በቁጥር ጉዳይ ላይ መጠንቀቅ ይገባቸዋል የሚል እምነት አለን፡፡

ይህ እይታ የ“አንድ አድርገን” ብሎግ አዘጋጆችን ብቻ የሚወክል ነው፡፡ 

4 comments:

  1. እግዚአብሔር ይባርካችሁ አንድ አድርገኖች!ይሄ በግድ እኩል ታሪክ ይኑረን የሚሉት ማጭበርበር መፍትሄ ካልተፈለገለት ወደፊት ታሪካችንን የሚያጨልም የክፋት ስራ ነው። የንጉስ ነጃሺ የድርቅና ታሪክ አደባባይ ውሸትነቱ ስለተረጋገጠ ደስ ብሎኛል! አገልግሎታችሁ ይባረክ

    ReplyDelete
  2. እጥር ምጥን ያለ ተጊ የሆነ መልእክት ነው በጣም ሊታሰብበት የሚገባው ነገር በክርስትናውና በሞስሊሙ መካከል ያለው ፐርሰንት አቀማመጥ በልዬ ልዩ ድህረ ገፆች ላይ እኔ እንዳየሁት ከሆነ ክርስቲያኑ 45 በመቶ ሙስሊሙን 55 በመቶ ነው የሚል ነው ከየት እንደመጣ አይታወቅም "ውሸት እያደር እውነት ይሆናል" የሚባል ፈሊጥ አለ ጥንቃቄ ሊደረግበት አስፈልባል ሌላው እኔ የአካባቢው ተወላጅ ነኝ ለመሆኑ የባቦ ጋያ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የቦታ ይዞ ከምን ደረስ? በጣም እየተከታተልኩ ነበር

    ReplyDelete
  3. And Adirgen Melkam Melekit new yetebalew tikikil new musilimu mewashet Kejemere Koyitowal yemigermew America wisitsi yalu Papasat Kemusilimu Gon Mekom Aleben Eyalu selamaw selif Mewtsatachew new Lemehonu Mesilimu wedefit yemileken yimesilachihal ? Bebeshsha yetaredut-beJima yemigegut -Aris yalut harer yalut kirsityanoch dem yitsaral And adirgen bezih guday sefa yale neger mesirat yasfelgal Abune Melketsedekin-Abune Mekariyosin-Aba Wolide tinsaein erfu belachew

    ReplyDelete
  4. Excellent view
    Good on you guys

    እግዚአብሔር ይባርካችሁ አንድ አድርገኖች!ይሄ በግድ እኩል ታሪክ ይኑረን የሚሉት ማጭበርበር መፍትሄ ካልተፈለገለት ወደፊት ታሪካችንን የሚያጨልም የክፋት ስራ ነው። የንጉስ ነጃሺ የድርቅና ታሪክ አደባባይ ውሸትነቱ ስለተረጋገጠ ደስ ብሎኛል! አገልግሎታችሁ ይባረክ

    ReplyDelete