Saturday, June 9, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ከ20 በላይ ወጣቶች ታስረዋል


(አንድ አድርገን ግንቦት 2 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የዋልድባ ገዳም ጉዳይ አሁን ወደ ሌላ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል ፤ የመወያያ መድረኮች ውጤት እያመጡ አይደሉም ፤ መንግስት ዘነዘና የዋጠ ይመስል የአቋም ለውጥ ማድረግ ተስኖታል ፤ የሚሰራውን ስራ አሁንም ገዳሙ ላይ ተጽህኖ የለውም ብሎ አምኗል ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ከ3ሺህ የሚበልጥ የአካባቢው ነዋሪ ተቃውሞውን በቦታው ላይ መግለጹን ገልጸን ነበር ፤ ከዚህ ተቃውሞ በኋላ 10 የሚሆኑ የገዳሙ አባቶችን የአካባቢው ባለስልጣናት ሰብስበው አነጋረዋቸው እንደነበረ ለማወቅ ችለናል ፤ በቀጣይ ሰኔ 7 ፤ 2004 ዓ.ም ተጨማሪ የስብሰባ ፕሮግራም መያዛቸውን ጭምር ፤ ከዚህ በፊት የተደረጉት የስብሰባ ውጤቶች መስማት ባንችልም አሁንም ስብሰባዎች እየተደረጉ ናቸው ፤ ከእነዚህ ስብሰባዎች በተጨማሪ ባሳለፍነው ረቡዕ የአካባቢውን ወጣቶች በመሰብሰብ ስለ ግድቡ ለማወያየትም ባለስጣናቱ ሞክረው ነበር ፤ በስብሰባው ላይ የተገኙት በርካታ ወጣቶች ስብሰባውን አድርገው ከጨረሱ በኋላ በያዙት አቋምና ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ አማካኝነት ከየቤታቸው እና በተገኙበት እየተለቀሙ ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመባቸው  ወደ እስር ቤት ገብተዋል  ፤ ለእስር የሚፈለጉ ሰዎች ወሬው እንደደረሳቸው ግማሾቹ ጎንደርና ሌሎች ቦታዎች ሲሸሹ ብዙዎች ደግሞ “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ፥ ወይስ ጭንቀት፥ ወይስ ስደት፥ ወይስ ራብ፥ ወይስ ራቁትነት፥ ወይስ ፍርሃት፥ ወይስ ሰይፍ ነውን?” ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ፤ 35 በማለት መታሰርን መርጠው እዚያው አሳሪዎቻቸው ይጠባበቃሉ ፡፡ ጉዳዩ የእምነትና በእምነት ስለሆነ የሚመጣውን ነገር ሁሉ ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ፤  ወንጌሉ እንዲህ ይላል “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ” ማቴዎስ ወንጌል 10፤28


በቦታው ላይ የሚገኙ የባለስልጣናቱ የስብሰባ መከራከሪያ ነጥብ “ቤተክህነቱ የፈቀደውን እናንተ ምን አገባችሁና ነው የምትቃወሙት” የሚል ነው ፤ እውነታቸውን ነው በቤተክህነቱ  የተላኩት ቡድኖች  ሪፖርት መፍቀዱን በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን አስታውቋል ፤ ስኳር ልማቱ ገዳሙ ላይ የሚያመጣበት ተጽህኖም እንደሌለ አስረግጦ ተናግሯል ፤ የአባቶች የሲኖዶስ ስብሰባ ማጠናቀቂያ  ቀንም ጉዳዩን እንደተነጋገሩበት በማስመሰል የማጠናቀቂያ ሪፖርቱ ላይ ለማገባት ሞክሯል ፤ ይህን የቤተክህነቱን ሪፖርት ግን ምዕመኑ የሚቀበለው አይደለም ፡፡

ባለፉት ሶስት ቀናት የታሰሩት ወጣቶች ቁጥር ከ20 እስከ 30 የሚደርሱ ሲሆን በትላንትናው እለት 3 ወጣቶች ከእስር  ሲፈቱ በእነርሱ ምትክ ከአድርቃይ ወደ ገሪማ 7 ሰዎች በፖሊስ እና በገዳሙ ውስጥ በሚሰለጥኑ የሚኒሻ ሃይሎች ካበት ተይዘው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል ፤ በተጨማሪም ለታሰሩት ወጣቶች ብር ሲሰበስቡ የነበሩ ተጨማሪ ወጣቶችን ወደ እስር አውርደዋቸዋል ፤  አሁን መንግስት ከህዝቡ የሚደርስበትን ተቃውሞ መቋቋም ባለመቻሉ የኃይል እርምጃ መውሰድን የመረጠ ይመስላል ፤ ይህ አካሄድ ለማንም አይበጅም የባለፈው ሳምንት ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን የተፈጠረው ነገር ትምህርት ይሁናችሁ ፤ ከባለፈው ነገር መማር ብልህነት ነው ፤ እንደ መሸነፍ አትቁጠሩት ፤ ምዕመኑ ከቀን ቀን ለእምነቱ የሚያሳየውን ቀናይነት ያለው ጽናት እየጨመ ይገኛል ፤ ባሳለፍንው ማክሰኞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን የተከሰተውን ነገር ማየት ለዚህ በቂ ምክንያት ነው ፤ በሚያሳዝን ሁኔታ የሁለት ሰዎች ነፍስ ቢቀጥፍም ፤ ዛሬ በጉልበት የሚሰራ ስራ ዘላቂነት አይኖረውም ህዝብን ከመንግስት የሚያጋጭ ቂም የሚያስቋጥር ነገር ስለሚፈጠር መንግስት ከያዘው የተሳሳተ መንገድ ይመለስ ፤ ህዝብን ያድምጥ ፤ “ኢህአዴግ የሚናገር አንደበት እንጂ የሚያደምጥ ጆሮ የለውም” ብለው ዶ/ር መራራ ጉዲና ከዓመታት በፊት በተወካዮች ምክር ቤት የተናገሩት እውነት መሆኑን እየተመለከትን እንገኛለን ፤ ከህዝብ ጋር የመወያያ መድረክ በመፍጠር ስብሰባ ጠርቶ መናገር እንጂ ማድመጥ መንግስት የሾማቸው ከትንሹ የስልጣን እርከን ቀበሌ እስከ ከፍተኛው የሚንስትር ደረጃ ድረስ( ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ) ድረስ ያሉ ሰዎች ማድመጥን አልፈጠረባቸውም ፤ ከቀናት በፊት አንድ የዋልድባ ገዳም መነኩሴ በቪኦኤ ሬዲዮ ላይ ሲናገሩ እደሰማነው ፤ ይህ ፕሮጀክት የተቀረጸው ከ12 ዓመት በፊት እንደነበር ተናግረዋል ፤ በጊዜው ስራውን እንዳይጀምሩ ያስፈራቸው ጉዳይ እና እስከ አሁን የቆየበትን ሁኔታ ሲገልጹ  በፊት በትግል ላይ እያሉ ገዳሙ ውስጥ የማይገባ ነገር በማድረጋቸው የደረሰባቸው መቅሰፍትን እንደምክንያት አቅርበዋል ፡፡ “በተዘረጋች እጅና በብርቱ ክንድ፥ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ።” ትንቢተ ኤርምያስ 21 ፤5 ከስራችሁ ባትመለሱ ይህን ቃል እናንተ ላይ ይፈጸማል፡፡ ስለ ቤቱ ሲል መድሀኒአለም ይዋጋችኋል ፤
ፕሮጀክቱን ሲታሰብ አቶ ገብሩ አስራት የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት የነበሩበት ወቅት መሆኑ ነው ፤ በዚህ ጊዜም የወንዝ ቆጠራ ስራዎች ፤ ግድቡ የሚይዘው የውሀ መጠን ፤ የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን የመሬቱን ስፋት ፤ ጠቅላላ ቦታው ድረስ በመሄድ በእጥኚ ኮሚቴ አማካኝነት ስራ ሲሰሩ እንደ ነበር በጊዜው የነበሩ አባት ሲናገሩ ሰምተናል ፤ ይህ ከሆነ 12 ዓመት ሞላው በጊዜው የነበሩት የክልሉ ፕሬዝዳንት እና በኮሚቴው ውስጥ የነበሩት ሰዎች አሁን በቦታው ላይ የሉም ፤ ወንበሩ ሸሽቷቸዋል ፤ 17 ዓመት የታገሉለትም ፓርቲ አባሯቸዋል ፤ አሁንም በዋልድባ ላይ እጃችሁን የጠቆማችሁ ችግሩ ሳይገባችሁ ቀርቶ ሳይሆን መንግስትን ለማስደሰት የምትንቀሳቀሱ የመንግስት ባለስልጣናት የተቀመጣችሁበት ወንበር አንድ ቀን ፈቀቅ እንደሚልባችሁ እያወቃችሁ ለህሊናችሁ ስትሉ ስሩ ፤ እናንተ የቻላችሁትን ዳገት ብትወጡ ቁልቁለቱን ብትወርዱ መድሀኒዓለም ካልፈቀደ ምንም እንደማይሆን እምነታችን ነው ፤ ለሚያልፍ ስልጣን የማያልፍ የታሪክ ስህተት አትስሩ ፤ እኛም የፍርሀት ካባችንን አውልቀን ለቤተክርስትያን የመፍትሄ አካል የምንሆንበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡ የተኛችሁ ካላችሁም የእንቅልፍ ዘመን አልፏል ስለ ቤተክርስትያን ንቁ . . . .
እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ ፤

6 comments:

  1. የተኛችሁ ካላችሁም የእንቅልፍ ዘመን አልፏል ስለ ቤተክርስትያን ንቁ .

    ReplyDelete
  2. ፈርኦን ልቡን አደንድኖ እስራኤልን እስከ ባህር መሃል ቢከተልም እግዚአብሔር መሃል እስኪደርስ ጠብቆታል ፍጻሜው ግን ባህር መሃል ከነሰራዊቱ መስጠም ነበር። ኢህአዴግ አልሰማ ብለህ ትግልህን ብታጠነክር የምትዋጋው ከሰው ጋር እንዳይመስልህ በሰከንዶች ሽርፍራፊ አመድ ከሚያደርግ አምላክ ጋር ነው!! እናንተም በርቱ እኛም በእምነት የድርሻችንን እንሰራለን ውጊያውን ትችሉ እንደሆነ በአይን የምናይበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም...

    ReplyDelete
  3. የእኛ መንግስት በሁሉም ሊያኮላሸን በሙሉ ሀይሉ እየሰራ ነው፡፡ በሀይማኖታችን ሙሉ ለሙሉ ገብቶ ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ገብቶ እያመሰን ነው፡፡ሀገራዊ ስሜታችንን ሊያጠፋ የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም፡፡ ከዚህ በላይ የሚያሳዝነው ግን የእኛው አባቶች ቤተክርስቲያናቸውን ለመናፍቃን ሊሰጡ ከሚያደርጉት ጥረት ባሻገር ገንዘብዋን ለስጋዊ ጥቅም ለማዋል ለምንም መንፈሳዊ አዕምሮ እየታገሉ ናቸው፡፡ ታዲያ በነመለስ እንዴት እናዝን፣ ኃይማኖት የላቸው ወይ መንፈሳዊ የሚለው ቅዋንቅዋ ለጆሮዋቸው ምንም አይደለም፡፡
    ቤቱን እና ኢትዮጵያን የማይረሳ ይጠብቀን

    ReplyDelete
  4. lemin shemik wegiya ategemerum? yihen yahel wene kalachu tnsuna semetu. hezbe atacharsu.

    ReplyDelete
  5. enante poletikgegoche. go to you your poletics live our church.

    ReplyDelete
  6. Yesterday I went to Giorgis church. It looks no body is at their side except the Christians around that area and they willy look sad and it looks and they are saying their only hope is God.
    I don't know but in my opinion MK should have done something regards Waldiba and other issues since their goal is to serve the church. Actually I have seen the report but I think it is not enough. They should fight for Waldiba like they fought about the tehadiso. I am sing this because they are the recognized Union and they have the power than we individually do things for our church.
    Anyways above all we expect things from God not from people.

    ReplyDelete