Tuesday, May 8, 2012

የመቀሌ ኪዳነምህረት ጸበል መንገድ ሊወጣባት ነው



እንኳን አደረሳችሁ
(አንድ አድርገን ግንቦት ልደታ ፤ 2004ዓ.ም)፡- በመቀሌ ከተማ የምትገኝው የኪዳነምህረትን ጸበል መንገድ ሊሄድባት እንደሆነ ሰምተናል ፤ መንገድ ከወጣባት መንፈሳዊ አገልግሎቱን ለመስጠትም መንገዱ ችግር ይፈጥራል ፤ ቦታዋ በርካታ የመቀሌ ህዝብ ፈውስ ያገኝባት ከመሆኗም በተጨማሪ በርካታ ምዕመን ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በመምጣት ጸበሏን በመጠመቅ እና በመጠጣት በርካታ ፈውስ የሚገኝባት መሆኗንም ለማወቅ ችለናል ፤ በቀን ቢያንስ 1000 ሰዎች አገልግሎቱን የሚያገኙ ሲሆን አሁን ግን መንግስት ለመስራት ያሰበው ድልድይ የጸበሉን የቦታ ህልውና አደጋ ላይ እንደሚጥለው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል ፤ በቦታው ላይ ከመጠመቂያ ቦታው በተጨማሪ ህሙማን ማሳረፊያ ያለው ሲሆን እሱም ከጸበሉ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ አደጋ አጥልቶበታል ፤ እዚህ ቦታ ላይ ከኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከመላው አውሮፓ እና ከአሜሪካ በርካቶች መድሀኒት በሌለው በሽታ የተጠቁ ክርስትያች እና ክርስትያን ያልሆኑ ወገኖቻችን ፈውስ እንዳገኙበት ለማወቅ ችለናል ፡፡ ይህን ቦታ ሊሰራ የታሰበው መንገድ ዲዛይን እንዲቀየር በአካባቢው የሚገኙ ሰዎች አቤቱታቸውን ለአካባቢው መስተዳደር ያሳወቁ ሲሆን መስተዳድሩም በሁለት ቀናት ውስጥ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋር የመፍትሄ ሀሳብ እንደሚያስቀምጥ ቃል ገብቷል ፡፡


በተያያዘ ዜና ከጥቂት  ከቀናት በፊት የደረሰን መረጃ እንደሚያስረዳው በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ካራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ‹‹የካራ ቅድስት አርሴማ›› ቤተክርስቲያን የፀበል ቦታ ህጋዊ ይዞታነት በህብረተሰቡ እና በወረዳው አስተዳደር መካከል ውዝግብ መነሳቱንና  ፤ ወረዳው ‹‹የቤተክርስቲያኒቱ ይዞታ ህጋዊ አይደለም›› እና ‹‹ያለ አግባብ ቦታውን አስፋፍተው ይዘዋል›› በማለት  ወደ ስፍራው የአፍራሽ ግበረ ሃይል ልኮ የፀበል ቦታው እንዲፈርስ አድርጓ ፤ በአካባቢው ከነበረው የእምነቱ ተከታይ ጋር  መጋጨቱን ለማወቅ ችለናል ፤ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች ወደ ስፍራው በማምራት ህጋዊውን ቦታ ህገወጥ በማስባል የማፍረስ ስራቸውን አከናውነዋል ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ቤተክህነቱ የተነፈሰው ነገር አለመኖሩ ነገሩን ገራሚ አድርጎታል ፤ ዋልድባ ሲታረስ ዝም ፤ ባቦጋያ መድሀኒአለም ቦታው ሲሸጥ ዝም ፤ መቀሌ ኪዳነምህረት የጸበል ቦታ መንገድ ሊያወጡበት ሲሉ ዝም ፤ ታዲያ መቼ ነው መንግስት እያደረገ ያለው ነገር በመቃወም ከቤተክርስትያኒቱ ጎን የሚቆሙት? እሱን ቀን ማየት ፤ ለችግሮች የመፍትሄ አካል ሲሆኑ ማየት ብንመኝም ለማየት አልታደልንም፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ የወረዳውን አስተዳደር፣ የየካ /ከተማ  ከህብረተሰቡ ውስጥ ከተወጣጡ ጊዜያዊ ኮሚቴዎች ጋር በመነጋገር ‹‹ያለ አግባብ ተይዟል›› የተባለው ቦታ በኮሚቴው አማካኝነት  እንዲለቀቅ ማግባባት ቢያደርግም ‹‹የጸበል ቦታችን ህገ ወጥ አይደለም ህጋዊ መሰረት ያለው ነው በዚህ ላይ አንደራደርም›› ባለው  ማህበረሰብ  ዘንድ ተቀባይነትን አላገኘም ነበር።  በመሰረቱ ብናየው ይህ ጉዳይ መጀመሪያ ሊያስብበት የሚገባው ቤተክህነቱ ነበር ፤ ጉዳዩ በአሁኑ ሰዓት እልባት አላገኝም ፤

እኛ እንዲህ አድርግገን ጠርጥረናል
መንግስት በሚሰራው ፕሮጀክት በምን አይነት ሰዎች እንደሚያሰራ ጥርጣሬ አለን ፤ እንደ በሬው ታሪክ ለመንግስት ሳሩን እያሳዩት ገደሉን ግን እንዳያይ እያደረጉት አለመሆኑንስ በምን እንመን ? ፤ ለምሳሌ ማነው በግለሰብ ደረጃ የዋልድባን የስኳር ልማት ፕሮፖዛል የሰራው? እነማንስ አብረው በፕሮፖዛሉ ስራ ላይ አብረው ተካፍለዋል ? ማንስ ነው የመቀሌን መንገድ በጸበሉ ላይ የቀየሰው ? ፤ ማንስ ነው የባቦጋያ መድሀኒዓለምን ቦታ ለሪዞርት ማስፋፊያ እንዲሰጥ ሀሳብ ያቀረበው ? ፤ ነገሮች ተከናውነው ብናያቸውም መነሻቸው ግን የአንድ ወይም የጥቂት ሰዎች ሀሳብ መሆናቸውን አንርሳ ፤ ታዲያ እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው?  ቤተክርስትያኒቱን ለማፈራረስ እና ሰላሟን ለመንሳት የቆሙ ሰዎች እንደማይሰሩት ምን ማረጋገጫ አለን? ፤ መንገዱ ሲሰራ ቤተክርስትያንን አጥርም ሆነ ቦታዋን ቆርሶ የሚወስድ ፤ የማስፋፊያ ሪዞርት ሲታሰብ 10ሺህ ካሬ ቦታ ከቦታዋ ላይ ቆርሶ የሚወስድ ፤ ስኳር ልማቱ ሲሰራ የገዳሙን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ፤ 18 ቤተክርስያናትን ነበሩ የሚያስብል ስራ እየተከናወነ እየሆነ እያየንና እየተመለከትን እንዴት አድርገን ከኋላ ያሉትን ሰዎች እንመን ? ፤ ፕሮጀክቱን የሚቀርጹትን ሰዎች አውቀው ይሁን ሳያውቁ ይስሩን በምን እንመናቸው ፤ የነዚህን ሰዎች ጀርባቸውን በምን እናረጋግጥ ?

የእስከ አሁኑ ፈተና እንዳለ ነው ፤ጊዜ ፈራጅ ስለሆነ ጊዜ መፍትሄ ይሰጠዋል ፤ ከአሁን በኋላስ ያሉትን አብያተክርስትያኖች የመንገድ ሲሳይ አለመሆናቸውን በምን እናረጋግጥ ? ፤ እኛ ግን እነዚህ ሰዎች ላይ ስጋት አለን  ፤ ይህ ሆን ተብሎ እንደማይደረግ እስካላመንን ድረስ አጋጣሚ ነው ለማለት ይከብደናል ፤ በደሴ የዛሬ ዓመት ገደማ የተከናወነውን የሰው ህይወትም ያለፈበት ጉዳይን ማስታወስ ይበቃል ፤  ጀርባቸውን  ባናውቅ እንኳን ማንነታቸውን ብንረዳ ሌላውን ለማወቅ ቀላል ይሆንልን ነበር ፤ አሁን የወደፊት የትኩረት አቅጣጫችን ይህን የመሰለ ፕሮጀክት እየቀረጹ መንግስትን ከህዝብ የሚያላትሙትን ሰዎች ላይ ለማድረግም አስበናል ፤ ከፈለግን የማንደርስበት ነጥብ እንደሌለም እምነታችን ነው ፤ ለማንኛውም ችግሩ ላይ ብቻ ማመልከት ተገቢ መስሎ አይታየንም ፤ የሁኔታው መነሻውን ያለበትንና  እና መድረሻ ነጥቡን ማወቅ መልካም ነው ፤ አሁን ግን እየሆነ ባለው ነገር የእኛ እይታ ከችግሩ ይልቅ እነዚህ ሰዎች ላይ አነጣጥሯል ፡፡ መጠርጠር መልካም ነው ፤ ማን ያውቃል ይህ ነገር እየተፈጸመ ያለው ከእኛ በተቃራኒ  በቆሙ ሰዎች አለመሆኑን ?

5 comments:

  1. tikikele derome eko yemitebeqe newe gene mane defero yenagere merejame megegnete selalebete

    ReplyDelete
  2. It may be, please follow properly and inform for as as soon as possible. Bedelu beza, minew amlak hoy bedelachine yihon?

    ReplyDelete
  3. tikikele ebakachu merejawen adersun

    ReplyDelete
  4. ብዕሩ ዘ-አትላንታMay 9, 2012 at 6:31 AM

    ትክክለኛ አስተያየት ነዉ። ከችግር በኋላ ለመፍትሄ እየሮጥን አቤቱታ እና ልቅሶ ነዉ ያተረፍነዉ። አሁን መሠራት ያለበት ምንጩ ላይ መሆኑ የተደረሰ ይመስለናል። ለመረጃዉ እኛም ከጎናችሁ ነን በርቱ።

    ReplyDelete
  5. It is realy hard to say the people causing the problem are those who created the proposal. What if this proffesionals are already instructed by this devil government to do it in such a way that it affects our church and belief negatively?

    I see one and only one solution. Remove Paulos. AND WOND ORTHODOX TEWAHIDO WIST BINOR YASTEBABIREN!! Look at what our muslim brothers and sisters are doing. What is wrong with u?????????????????????????????????????

    ReplyDelete