Thursday, May 17, 2012

ዝምታም ያስጨንቅ ኖሯል?


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበበብ ይህን ሊንክ ይጠቀሙ
ለ:- ማህበረ ቅዱሳን ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ :- የማህበሩ ሚዲያ ክፍልን በተመለከተ ይሆናል
በዋልድባ አካባቢ መንግስት ያቀደውን ግዙፍ የስኳር ፋብሪካን በማስመልከት በዋልድባ ይዞታ ላይ ያደረሰውን ተጽህኖ መኖር አለመኖር የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሁሉ ተፈላጊውን የማጣራት ስራ አከናውኖ መመለሱ ይታወሳል::
ይህንንም መነሻ በማድረግ በቅርቡ ሁሉንም የመገናኛ አውታሮች ያሳተፈ ጋዜጣዊ መግለጫ መሰጠቱንና ይህንንም ጋዜጣዊ መግለጫም የማህበረ ቅዱሳን ጋዜተኞች መከታተላቸውን መሳተፋቸው እና የሚፈልጉትን ጥያቄ ሁሉ በይፋ አቅርበው ምላሽ መሰጠቱ ይታወቃል::
ስለሆነም ማንኛውም ጋዜጠኛ በተለይም ደግሞ የቤተክርስትያኒቱ ልሳን የሆነው የማህበሩ ጋዜጣ እና መጽሄት መረጃ ከወሰደ በኋላ መግለጫውን አለማውጣቱ አግባብነት የሌለው ከመሆኑም በላይ የሚዲያ ስነ ምግባርንም ያልተከተለ ስለሆነ በመምሪያችሁ በኩል ዘገባው የቀረበት ምክንያት በጽሁፍ እንዲገልጹ መመሪያ እንዲተላለፍ እንጠይቃለን፣  በማለት ለህዝብ ግንኙነት መምሪያ በቁጥር 234/2004 በቀን 10/08/04 የተጻፈ ደብዳቤ ለመምሪያችን ቀርቦ ተመልክተነዋል::
ስለዚህም ምንም እንኳ ከላይ የተጠቀሰው ሁሉ ሲከናወን ማደራጃ መምሪያው የሚያውቀው ባይሆንም ቅሉ እንደተባለው ጋዜጣዊ መግለጫውን በሚዲያ ለማውጣት ተስማምታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ ከወሰናችሁ በኋላ ዘገባው የቀረበትም ምክንያት በጽሁፍ ለማደራጃ መምሪያው እየገለጽን ከጠቅላይ ቤተክህነት የህዝብ ግንኙነት መምሪያ የተጻፈውን አንድ ገጽ ማስታወሻ አያይዘን ልከናል፡፡

ግልባጭ
 የሚመለከታቸው • ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
 • ለብጹእ ቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
 • ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
 • ለህዝብ ግንኙነት መምሪያ
 • ለህግ አገልግሎት መምሪያ

ü  የማይመለከታቸው መስሪያ ቤቶች
o   ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር
o   ለብሔራዊ ደህንነት አገልግሎት
o   ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

(አንድ አድርገን ግንቦት 9 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ይህ ደብዳቤ በጣሙን አስገርሞናል ፤ ለምን ስለ ዋልድባ አልዘገባችሁም ተብሎ እንዴት ደብዳቤ ይጻፋል ? ደብዳቤው ተገቢ ነው የሚል እምነት የለንም ፤ መጀመሪያ ቤተክህነቱን የምንጠይቀው ጥያቄ አለን ፤ ለምን ዋልድባ ሲታረስ ተመልክታችሁ አልታረሰም የሚል መግለጫ ለመገናኛ ብዙሀን ሰጣችሁ ? ዓለም የተቃወመውን ስራ እናንተ ብቻ በመደገፋችሁ አፍረንባችኋል ፤ እናንተ ከመንግስት ጎን ብትቆሙ ብዙም አይገርመንም ፤ ግን ገዳሙ ላይ የሚሰራውን ስራ መቃወም ቢያቅታችሁ እንኳን ደጋፊ ባትሆኑ መልካም ነበር ፤ መጀመሪያ መቃወም ያለባችሁ እናንተ ሆናችሁ ሳለ ፤ ለምን ስለዋልድባ አልዘገባችሁም?  ማለታችሁ ለሰሚም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ፤ እንዴት አንድ ማህበር  አልዘገብክም ተብሎ ደብዳቤ ይጻፍለታል ፤ በቅርቡ በስራ ላይ የዋለው ህግ ጋዜጠኞችን ለምን ጻፋችሁ እያለ ነበር ዘብጥያ የሚያወርዳቸው ፤ በብእር አማካኝነት ሽብርተኛ የሚባልበት ዘመን ላይ ደርሰናል ፤  አሁን ደግሞ መልኳን ቀይራ መጣች መሰል ፤ ዝምታም ይህን ያህል ያስጨንቃቸው ኖሯል ? ሰው ለምን ተናገርክ ማለት ይቻላል ለምን አልተናገርክም ? ለምንስ አቋምህን አልገለጽክም ? ብሎ ደብዳቤ ሲጻፍ ዘንድሮ አየን ፤ ይህ 2004 ዓ.ም ገና ብዙ ነገሮች ያሳየናል ፤ ከአሁን አሁን ማህበሩ በዋልድባ ገዳም ጉዳይ ላይ አቋሙን እንደ ማህበር እስከ አሁን ባይገልጽም ይቃወማል ብለው የገመቱ ይመስላሉ ፤ ለካ ዝምታም ያስፈራል ? እኔ ጩህት ብቻ ይመስለኝ ነበር ::

ይህ ሀሳብ ከቤተክህነቱ ብቻ የመጣ ሀሳብ ነው ብሎ የሚያስብ ካለ ተሳስቷል ፤ ይህ አቋም የቤተክህነቱ ብቻ ቢሆን ኖሮ ግልባጭ ለማይመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ባልተላከ ነበር ፤ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ፤ ለብሔራዊ ደህንነት አገልግሎትና ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቤተክህነቱ እና ማህበሩ ማህል የሚደረግን የደብዳቤ ልውውጥ የቱ ጋር የቆሙ ተቋማት ናቸው ? አሁን አሁንማ ሰዎቹ ጤነኞች መሆናቸውን እስከመጠራጠር ደርሰናል ፤ እንዴት ይህን የመሰለ ይዘት ያለው ሀሳብ ከቤተክህነቱ ይወጣል?  ለነገሩ አቡነ ጳውሎስ በወንበሩ እስካሉ ድረስ ከዚህም የባሰ እንደማይወጣ እርግጠኛ ሆነን መናገር አንችልም ፤ የሚያስቀምጥ እግዚአብሔር የሚነቅልም እርሱ ፤ ጽዋው እስኪሞላ መጠበቅ ብቻ ነው ፡፡ የእኛ የመከራ ጽዋ  ሞልቷል ነው የሚባለው ገንፍሏል? መንግስትም ሆነ የቤተክህነቱ ሰዎች ዝምታን ተቃውሞ አድርገው ወስደውታል ፤ ቢገባቸው መቃወም ራሱ መብት ነው ፤ ሀገሩ ኢትዮጵያ ሆነ እንጂ ፤ ህገመንግስቱ ሀሳብን የመግለጽ መብት ብሎ ያስቀመጠው አንቀጽ አለ ፤ አዚህኛው ውስጥ ግን ያለመናገርም መብት እንዳለ ዘነጋችሁት ፤  

የተጻፈው ደብዳቤ ላይ ‹‹የሚዲያ ስነ ምግባር ›› የሚል ቃል አለው ፤ ይህ ደግሞ ስነ ምግባሩን ያላወቁት ወይንም እያወቁ ‹‹በዜና ቤተክርስትያን›› የጣሱትና ያጣሱት ሰዎች አጠገባቸው እያሉላቸው ዘለው ስለ ስነ ምግባር ሊያስረዱ ይሞክራሉ ፤ እኔ ጥያቄ አለኝ ፤ የሚዲያ ስነምግባር ማለት ምን ማለት ነው ?  እናንተ ስለ ሚዲያ ስነምግባር ለማውራት እውቀቱም ሆነ ብቃቱ የላችሁም ፤ የቤተክርስትያኒቱን  ድምጽ የሆነችውን ‹‹ዜና ቤተክርስትያን ›› ላይ ያወጣችሁት ከስነምግባር ውጪ የሆነ ጽሁፍ ስነምግባር ካለው ሰው እና ስለ ‹‹ሚዲያ ስነምግባር›› ማስረዳት ከሚችል ተቋም የሚጠበቅ አይደለም፡፡  እኛ ግን እንላለን ማህበሩ ቦታው ላይ በላካቸው ልኡካን ቡድኖች አማካኝነት ያጠናውን ጥናት ትክክለኛ ሪፖርት በትእግስት እንጠብቃለን፡፡

ይህን ደብዳቤ እንደዚህው አይተን የምናልፈው መሆን መቻል የለበትም ፤ ቤተክህነቱ ውስጥ ያለውን የነቀዘን አሰራር የሚቃወመው ማህበረ ቅዱሳን  እነርሱ ሊቋቋሙት ስላልቻሉ ከተራራ ጋር ሊያላትሙት መንገድ ጠራጊ ሆነው በአንዲት ደብዳቤ ብቅ ብለዋል ፤  የዚህን ደብዳቤ መልስ ግን ማስተዋል ያሻዋል ፤ ለምን ? ብሎ መጠየቅም ይገባል እንላለን፡፡


‹‹ኢያሪኮም ከእስራኤል ልጆች የተነሣ ፈጽማ ተዘግታ ነበር ወደ እርስዋ የሚገባ ከእርስዋም የሚወጣ ማንም አልነበረም። እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው። ተመልከት፥ ኢያሪኮንና ንጉሥዋን ጽኑዓን ኃያላንዋንም በእጅህ ሰጥቼአለሁ። ሰልፈኞቻችሁ ሁሉ ከተማይቱን አንድ ጊዜ ይዙሩአት እንዲሁም ስድስት ቀን አድርጉ።ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በታቦቱ ፊት ይሸከሙ በሰባተኛውም ቀን ከተማይቱን ሰባት ጊዜ ዙሩ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ይንፉ።ቀንደ መለከቱም ባለማቋረጥ ሲነፋ፥ የመለከቱንም ድምፅ ስትሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ የከተማይቱም ቅጥር ይወድቃል፥ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ አቅንቶ ይገባባታል። ›› መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 6፤  1-6

በዚህኛው ታሪክ እንደምንረዳው እግዚአብሔር እያሱን ተናገረው ቃሉ የማይታጠፍ አምላክ የከተማይቱን ቅጥር በጩህት እንዲፈርስ አደረገ ፤ አሁን እናንተ በማይገባችሁ ቦታ ላይ ተቀምጣችሁ ህዝበ ክርስትያኒን እና ቤተክርስትያኒቱን ወላጅ እንደሌለው ልጅ የምትጫወቱባል እግዚአብሄር ሲናገር የተቀመጣችሁበት ወንበር ይሸሻል መግቢያ ቀዳዳም ታጣላችሁ ፤ በዝምታ ብቻ ይጥላችኋል ፤ እናንተ ጩሁ እኛ ግን ዝም እንላለን ፤ ዝምታን የሚሰማ አምላክ ሁሌም ከጎናችን ነው ፤ እያሪኮ በጩህት ነው የፈለሰችው የእናንተን ደግሞ በዝምታ እግዚአብሔር እስከወዲያኛው ያፈርሳችኋል ፤ እስኪ ዝምታችን እንቅልፍ እንዲነሳቸው በርትተን ስለ ዋልድባ እንጸልይ  ፤ ‹‹አንደበትህ ዝም ይበል ልብህ እንዲናገር ፤ ልብህም ዝም ይበል እግዚአብሔር ይናገር ›› ይላሉ አባቶቻችን ፤ እስኪ ዝም ብለን ወደ ላይ  እናመልክት እርሱ ይናገራቸው ፡፡

23 comments:

 1. ሳታመካኝ ብላኝ አያ ጅቦ
  አቶ እንቁ ባህርይ ምን ነካህ ይህን ያህል ጅል ነህ የሚዲያ ሥነ ምግባርም አታውቅም።

  ReplyDelete
 2. ere bemariam yebtkenet sewoch betchristianchen atsedbu.Amlak lebona yestachehu.

  ReplyDelete
 3. እግዚያብሄርን የማይፈራ የኃይማኖት አባት ሊኖር እንዴት እንደቻለ አምላክ ይወቀዉ፡፡ እነዚህ ሰዎች መዋለጃቸዉ እየደረሰ ነዉ፡፡ ድሮ ድሮ የኃይማኖት አባቶች ሲከፋቸዉና ሰይጣል ሲጠናወታቸዉ ወደ ገዳም ይሄዱ ነበር ያሁኖቹ ደግሞ የገዳማዊያኑን መመነኛ ገዳም እያሳረሱ ከአለቆቻቸዉ ምንዳ ይቀበላሉ፡፡ እንደ ጌታቸዉ ዶኒ፡፡ ኸረ ለምንድን ነዉ ያበደ ዉሻ የሁኑት አባ ጳዉሎስ ልብ ይስጥህ ወደ መቃብር ሳትሄድ በፉት ለንሳሃ ልብህን ይመልስልህ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና አምላክ በሆነ ተሸከመህ

  ReplyDelete
 4. እግዚያብሄርን የማይፈራ የኃይማኖት አባት ሊኖር እንዴት እንደቻለ አምላክ ይወቀዉ፡፡ እነዚህ ሰዎች መዋለጃቸዉ እየደረሰ ነዉ፡፡ ድሮ ድሮ የኃይማኖት አባቶች ሲከፋቸዉና ሰይጣል ሲጠናወታቸዉ ወደ ገዳም ይሄዱ ነበር ያሁኖቹ ደግሞ የገዳማዊያኑን መመነኛ ገዳም እያሳረሱ ከአለቆቻቸዉ ምንዳ ይቀበላሉ፡፡ እንደ ጌታቸዉ ዶኒ፡፡ ኸረ ለምንድን ነዉ ያበደ ዉሻ የሁኑት አባ ጳዉሎስ ልብ ይስጥህ ወደ መቃብር ሳትሄድ በፉት ለንሳሃ ልብህን ይመልስልህ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና አምላክ በሆነ ተሸከመህ

  ReplyDelete
 5. Ahun Mastewal Alebin Behulum Mesimer Yalenew Hulu Tikikil Aydelenm Sinodosu-Bete Kihinetu -Likawnt Gubaew-Sira Asikiyaju-Memiriyaw-Gazetsegaw -Sebakiw-Mahibere Kidusan -Menkusew- Papasu -Patiryariku Zemariw -Negerochin Mastewal Alebin Yemin Gedel sinad Mog Yiskal Bilih Gin Yaleksal YiBalal Hulunm Sedebnew -Manew Dehina -Abba Sereken -Leke Kahinat Getachew Donin -D Begashawin Ato Malet Yegemernew Sile Tselanachew New Siltsanachew Gin Ale Ega Kihinetin Lemeyaz Min Mebit Alen ? Dr Kesis Mesifin Kinetachew Meyaz Yelbetim Yeminilewm Kihinet Yale Agibab Menekat silelelebet new Degimom ega yehayimanot sewoch kehonin Abatochin Sedibo Lesedabi Mestsetu Melkam aidelem Negeru Hulu yetesfafaw Beye Biloogu Abune Ekele Endih Aderegu -Abba Ekele Endihi Seru -Sebaki Ekele Endih Sera -Zemar Ekele Hatsatega bemalet beyemedirekuna beye biloogu sinmezegib bemewalachin new Ahun Asiteyayet yesetsut Ahunim Meregagat Alebin Balebet yelelew Hayimanot Asimeselachihut Betely Abba Selama -Awde Mihiret- Deje Birhan Yetebalu Yemenafikan Biloogoch egir beegir eyeteketatelu Lenegeru hilu Afirash mels eyesetu new Ahunim Ebakachihu Mewegagezu Kerto Menegager yinur Gindachinn Ansiten Gudif Mayet yishalal Degimom Yaltewgezen Sew Ega Siletselanew Bicha Ato Malet Yikum yastezazibal Mr Enkobahiriy Ato Aydelum Ene lemin yesinodosun & yepapasun siltsan eninekalen

  ReplyDelete
 6. የሚጠበቅ ነው ግን ህዝበክርስቲያን አንድ ነገር ሊያድርግ ይገበዋል

  ReplyDelete
 7. ሳታመካኝ ብላኝ አያ ጅቦ
  አቶ እንቁ ባህርይ ምን ነካህ ይህን ያህል ጅል ነህ የሚዲያ ሥነ ምግባርም አታውቅም።

  ReplyDelete
 8. ሳታመካኝ ብላኝ አያ ጅቦ
  አቶ እንቁ ባህርይ ምን ነካህ ይህን ያህል ጅል ነህ የሚዲያ ሥነ ምግባርም አታውቅም።
  ሳታመካኝ ብላኝ አያ ጅቦ
  አቶ እንቁ ባህርይ ምን ነካህ ይህን ያህል ጅል ነህ የሚዲያ ሥነ ምግባርም አታውቅም።
  ሳታመካኝ ብላኝ አያ ጅቦ
  አቶ እንቁ ባህርይ ምን ነካህ ይህን ያህል ጅል ነህ የሚዲያ ሥነ ምግባርም አታውቅም።
  ሳታመካኝ ብላኝ አያ ጅቦ
  አቶ እንቁ ባህርይ ምን ነካህ ይህን ያህል ጅል ነህ የሚዲያ ሥነ ምግባርም አታውቅም።
  ሳታመካኝ ብላኝ አያ ጅቦ
  አቶ እንቁ ባህርይ ምን ነካህ ይህን ያህል ጅል ነህ የሚዲያ ሥነ ምግባርም አታውቅም።

  dedebe menafeqe enqubahiri...erkuse bahiri

  ReplyDelete
 9. እስኪ ፍረዱ መቼም ለመክሰስ የፈጠኑ ሁነው ነው እንጅ፣ የሰ/ትም/ቤቶች መ/መምሪያም እኮ የቤተ ክህነቱን መግለጫ በማ/መምሪያው ድህረ ገፁ ላይ አልዘገበውም ፣ ማ/መምሪያውስ ለምን በድህረ ገፁ ላይ እንዳልዘገበው ሊገልፅልን ይችላል፡፡ ነው ድህረ ገፁ የማህበሩን ስም ለማጥፋት ብቻ ነው የሚውለው?

  ReplyDelete
 10. Even The Government wants this information. The Government Fears that its project will not be implemented properly if Orthodox Society is against it. This guy may want to get some additional problems in MK that will enable him to link to the Government.

  Keep Silent MK

  ReplyDelete
 11. አይ መ/ር እንቁ ባህርይ መጀመሪያ እንተ እመራዋለሁ በምትለው የማ/መምሪያው ድህረ ገፅ ላይ እንዳልወጣ ታውቃለህ?

  ReplyDelete
 12. የእኔም አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ
  በጭንቅላታቸው እያሰቡ ፣ በራሳቸውና በቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ ብቻ የሚንቀሳቀሱ ኃየሎች አይመስሉኝም ፡፡ የዚህኛውን ደብዳቤ መንፈስ እንደተረዳሁት ሌላ ኃይል ከጀርባ ሆኖ የሚያሰራቸው ይመስላል ፤ ያውም መንግሥት ፡፡ ምክንያቱም የዋልድባ የስኳር ልማት ግንባታ ለመንግሥት ነው እንጅ ፣ ለቤተ ክርስቲያን ልጣጭ እንኳን አይደርሳትም ፡፡ ጀሌዎቹ አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለመፈጸም በመሞከራቸው ደግሞ ገና ለእኛ ስህተት የሚመስለን ፣ ነገር ግን ባለጉዳዮች ማኀበሩን ህገ ወጥ ብሎ ለመዝጋት ሊጓዙበት የፈለጉት መንገድ ቅያሽ ነው ፡፡ ምክንያቶችን ለመደርደር ካልሆነ ፣ ሌሎች የዘገቡት አልበቃ ብሏቸው ፣ ጥያቄ ባላነሱም ነበር ፡፡
  ቀበሮ ከታች ፣ በግ ደግሞ ከላይ ሆና ከወራጅ ውሃ ይጠጡ ነበር ፡፡ ቀበሮ በጓን የሚበላበትን ምክንያት ፈልጐ ፣ ውሃውን እንዳልጠጣ አደፈረስሽብኝ ብሎ አምባ ጓሮ አነሳ የሚሉት ተረትና ምሳሌ አነጋገር ነበር ፡፡ ገና ሌሎችም ህልውናውን ለመፈታተኛ የሚቀርቡ ጉዳዮች ይኖራሉ ፡፡ ለማንኛውም ጠንቀቅ ማለት አይከፋም ፤ አግባብ ያለው መልስ እየሰጡ ማለፍም አንዱ ስልት ይመስለኛል ፡፡

  ReplyDelete
 13. Debdabew Ayasgerimm Negeru Giltsi new lemi Alakerbum Menor felgu Mahibere Kidusan Lieukan melakun enawkalen Beye Bilogu kemezerzer siewnet Begitsi memesker neberebet Ahunim Yetetseyekew Yederesebetin Huneta endiyakerb new enj yalamenebetn endiyakerb ayidelem

  ReplyDelete
  Replies
  1. ayeeeee, negeru yegebah atimeslem. Bejet kefelew yelakuachew meseleh? It is already reported by their people that the sugar factory will not touch the monastery. Do you think they are asking MK's report because it is trustworthy? I don't think so, more than MK's report, the monastery's monks already complained about the problem. They should listen the monks more than MK's report. Because they are the one who are living at the place. Just like you, I want to hear MK's report, but I will wait forever, until they are ready to do it. So don't be fool by this letter...

   Delete
 14. ከመንግስት ጋር ለማላተም እና ማህበሩን ለማዘጋት፣ መቼም አይሳካም፣መሰረቱ ከሰው አይደለምና፣.....ማህበሩን ይጠብቅልን!!!!!!

  አቤቱ ይቅር በለን!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 15. It's true that MK should say something about it. As we can understand from their recent activity they are fighting 'tehadiso'. So in my opinion if they willy are care about Ethiopian Orthodox church it is must that they should say something about Waldiba Monastery. And if they are up to the truth trust me a lot of Ethiopian Orthodox church believers will be in their side. But if they hesitate to do so they are the same with everybody sucking the churches blood.
  I always taught that MK are the right but I doubt their loyalty to the church if they are going to be silent about this case.
  I am still waiting for their say in this regard and be sure MK your report is in favour of God which means the truth.

  ReplyDelete
 16. የእኔም አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ
  በጭንቅላታቸው እያሰቡ ፣ በራሳቸውና በቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ ብቻ የሚንቀሳቀሱ ኃየሎች አይመስሉኝም ፡፡ የዚህኛውን ደብዳቤ መንፈስ እንደተረዳሁት ሌላ ኃይል ከጀርባ ሆኖ የሚያሰራቸው ይመስላል ፤ ያውም መንግሥት ፡፡ ምክንያቱም የዋልድባ የስኳር ልማት ግንባታ ለመንግሥት ነው እንጅ ፣ ለቤተ ክርስቲያን ልጣጭ እንኳን አይደርሳትም ፡፡ ጀሌዎቹ አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለመፈጸም በመሞከራቸው ደግሞ ገና ለእኛ ስህተት የሚመስለን ፣ ነገር ግን ባለጉዳዮች ማኀበሩን ህገ ወጥ ብሎ ለመዝጋት ሊጓዙበት የፈለጉት መንገድ ቅያሽ ነው ፡፡ ምክንያቶችን ለመደርደር ካልሆነ ፣ ሌሎች የዘገቡት አልበቃ ብሏቸው ፣ ጥያቄ ባላነሱም ነበር ፡፡
  ቀበሮ ከታች ፣ በግ ደግሞ ከላይ ሆና ከወራጅ ውሃ ይጠጡ ነበር ፡፡ ቀበሮ በጓን የሚበላበትን ምክንያት ፈልጐ ፣ ውሃውን እንዳልጠጣ አደፈረስሽብኝ ብሎ አምባ ጓሮ አነሳ የሚሉት ተረትና ምሳሌ አነጋገር ነበር ፡፡ ገና ሌሎችም ህልውናውን ለመፈታተኛ የሚቀርቡ ጉዳዮች ይኖራሉ ፡፡ ለማንኛውም ጠንቀቅ ማለት አይከፋም ፤ አግባብ ያለው መልስ እየሰጡ ማለፍም አንዱ ስልት ይመስለኛል ፡፡
  100% agree

  ReplyDelete
 17. አሁን ትክክለኛ ጥያቄ ነው ማህበሩ የተጠየቀው፡፡ማህበሩ በዋልድባ ገዳም ስለሚሰራዉ ግድብ ጉዳይ ለማስጠናት ባለሙያዎችን እንዴላከ በተለያዩ ብሎጎች አንብበናል፡፡የጥናቱ ዉጤት ምን ይመስላል?ችግር ካለው ችግሩን መናገር፤ችግር ከሌለዉም የለዉም ብሎ መናገር ከአንድ ከእዉነተኛ ማህበር የሚጠበቅ ይመስለኛል፡፡ቀድሞዉኑ ማህበሩ ከመነሳቱ በፊት ይህን ማድረግ የነበረባት ቤተክህነት ነች፡፡እርሷ ተኛች፤ለነገሩ ምን እርሷ ትተኛለች በውስጧ ያሉት ጆቢራዎች ተኙ እንጂ፡፡ስለሆነም ማህበሩ ስራ መስራት ነበረበት እና ስራዉን እንደጀመረ ሁሉ ዉጤቱንም ሊነግረን ይገባል፡፡በቃ ከመንግስት ጋር ለማጣላት ምናምን ምናምን የሚባለው ነገር እንደ ግለሰብ ለእኔ አይዋጥልኝም፡፡ከመንግስት ጋር ከእነንትና ጋር ያጣላል እያሉ እዉነትን መደበቅ ተገቢ አይደለም፡፡በቃ እዉነቱን እዉነት ሃሰቱን ሃሰት ብሎ መናገር ተገቢ ነው፡፡የመንግስት ጉዳይ ሲሆን ላለመጣላት፤የግለሰብ ጉዳይ ሲሆን ነገሩን ማራገብ ተገቢ አይደለም፡፡ማህበሩ ልክ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን ለምሳሌ የተሃዲሶ አራማጆችን እያሳደደ እንዳለ ሁሉ በቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚመጣ አካልንም ተው ረጋ በል ሊል ይገባል፡፡
  እዚህ ላይ ግን ትጉረት ሊደረግባቸው የሚገበቡ ጉዳዮች፤
  በዋልድባ በሚሰራው ግድብ የቤተክህነት አቋም ምን እነደሆነ ምዕመኑ መጀመሪያ እንዲጠይቅ ቢደረግ
  ማህበሩ አለኝ የሚለው ሪፖርት ግድቡ በዋልድባ ላይ ጉዳት የሚያመጣ ከሆነ መፍትሄዉንም ለመንግስት የሚያመላክት ቢሆን
  ማህበሩ ያንን ሲያደርግ መንግስትን በመጥላት፤ልማትን በመቃወም ሳይሆን ከቤተክርስቲያን ህልዉና በመነሳት ብቻ እንደሆነ ቢጠቅስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. "ማህበሩ ያንን ሲያደርግ መንግስትን በመጥላት፤ልማትን በመቃወም ሳይሆን ከቤተክርስቲያን ህልዉና በመነሳት ብቻ እንደሆነ ቢጠቅስ"
   Do you think it will avoid anything at all? Because even the monks said they don't have any problem with the development or sugar factory anywhere in Ethiopia. They said just leave our place for us. So if Mahibere Kidusan gave out its report it will be the same thing which is, "this sugar factory is going to hurt the monastery. We have no problem with the factory but the place should be somewhere." But some poeple just want something to acuse the mahiber and find a way to say this mahiber is against mengist. So I would say lets be patient and wait for their own time to report it. If you really have a question that you need an answer to, you can ask personally the monks or people near the monastery (ye Gonder memenan). Peace to EOTC.

   Delete
 18. የእኔም አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ
  በጭንቅላታቸው እያሰቡ ፣ በራሳቸውና በቤተ ክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ ብቻ የሚንቀሳቀሱ ኃየሎች አይመስሉኝም ፡፡ የዚህኛውን ደብዳቤ መንፈስ እንደተረዳሁት ሌላ ኃይል ከጀርባ ሆኖ የሚያሰራቸው ይመስላል ፤ ያውም መንግሥት ፡፡ ምክንያቱም የዋልድባ የስኳር ልማት ግንባታ ለመንግሥት ነው እንጅ ፣ ለቤተ ክርስቲያን ልጣጭ እንኳን አይደርሳትም ፡፡ ጀሌዎቹ አድርጉ የተባሉትን ሁሉ ለመፈጸም በመሞከራቸው ደግሞ ገና ለእኛ ስህተት የሚመስለን ፣ ነገር ግን ባለጉዳዮች ማኀበሩን ህገ ወጥ ብሎ ለመዝጋት ሊጓዙበት የፈለጉት መንገድ ቅያሽ ነው ፡፡ ምክንያቶችን ለመደርደር ካልሆነ ፣ ሌሎች የዘገቡት አልበቃ ብሏቸው ፣ ጥያቄ ባላነሱም ነበር ፡፡
  ቀበሮ ከታች ፣ በግ ደግሞ ከላይ ሆና ከወራጅ ውሃ ይጠጡ ነበር ፡፡ ቀበሮ በጓን የሚበላበትን ምክንያት ፈልጐ ፣ ውሃውን እንዳልጠጣ አደፈረስሽብኝ ብሎ አምባ ጓሮ አነሳ የሚሉት ተረትና ምሳሌ አነጋገር ነበር ፡፡ ገና ሌሎችም ህልውናውን ለመፈታተኛ የሚቀርቡ ጉዳዮች ይኖራሉ ፡፡ ለማንኛውም ጠንቀቅ ማለት አይከፋም ፤ አግባብ ያለው መልስ እየሰጡ ማለፍም አንዱ ስልት ይመስለኛል ፡፡

  ReplyDelete
 19. I am sorry to see such type of argument.The so called "Betchnet is one part of EPRDF wing so what?

  ReplyDelete
 20. wendme ke 2tu asteyayet sechi befit yestehwn hasb edegfalehu m/kdusan reportun tkmun ena gudatun lablatochu liyasawk ygebawal ymimetawnm neger abren megafet new

  ReplyDelete