Saturday, May 12, 2012

ቅ/ሲኖዶስ ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ጉባኤውን ለመቀጠል ወሰነ


 • የሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል፤
 • ለምልአተ ጉባኤው ሐሳብ ተገዥ ባልኾነው የፓትርያርኩ አቋም ስብሰባው እግዳት ውስጥ ገብቷል፤
 • ከእርስዎ ጋራ ንትርክ ሰልችቶናል፤ ሦስተኛ አካል (መንግሥት) ጣልቃ ይግባ” (አንድ አባት)፤
 • ሦስተኛ አካል ጣልቃ አይገባም፤ በተለይም የሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ሳናጠራ እርስዎያነሷቸውን አጀንዳዎች አናይም፤ ሲኖዶሱ በራሱ ወስኖ ኹኔታውን ለሚዲያና ለሕዝቡ ይፋያደርጋል” (ሌላ አባት)፤


(ደጀ ሰላም፤ ግንቦት 4/2004 ዓ.ም፤ May 12/ 2012 READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ንት ዐርብ፣ግንቦት 3 ቀን 2004 . ጠዋት በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ መነጋገርያ አጀንዳዎች ላይ የተጀመረው ውዝግብ ከቀትር በኋላም ቀጥሎ የዋለ ሲኾን ዛሬ፣ ግንቦት 4 ቀን 2004 . ከቀትር በፊትበነበረው የምልአተ ጉባኤው ውሎም እንደቀጠለ መኾኑ ተሰምቷል፡፡

በዛሬ ጠዋቱ ስብሰባ “የእርስዎ ዕውቀት ይህ ስብሰባ የገጠመውን ችግር እንደምን መፍታት ይሳነዋል” በሚል ተማኅፅኖ ሳይቀር በብፁዓን አባቶች እየተለመኑ ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ “የእኔን አጀንዳ ካልተቀበላችኹ የእናንተንም አልቀበለም” እስከ ማለት መድረሳቸው ተገልጧል፡፡ ይልቁንም በሰሜን አሜሪካው ዕርቀ ሰላም ሂደት ቀጣይነት፣ በተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመትና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻ አጀንዳዎች መካተት ላይ የያዙትን አቋም እያከረሩና አልፎ አልፎም እያለሳለሱ የስብሰባን ሂደት እግዳት ውስጥ አስገብተውታል፤ እያደር በሚታየው አሰላለፍም ፓትርያርኩ በአንድ ወገን የተቀሩት የምልአተ ጉባኤ አባላት በሌላ ወገን ጎራ ለይተው መቆማቸው ነው እየተነገረ ያለው፡፡

ዛሬ ቀትር ላይ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው÷ ከፓትርያርኩ በቀር ብዙኀኑ የምልአተ ጉባኤው አባላት ሌላ ሰብሳቢ በመምረጥ መደበኛ ስብሰባውን ከቀትር በኋላ ለመቀጠል ወስነው ለምሳ ዕረፍት ተነሥተው ነበር፡፡ ምልአተ ጉባኤው እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ከዚህ ቀደም መንግሥት ወይም ሌላ ሦስተኛ ወገን ጣልቃ እንዲገባ የቀረበውን ሐሳብ የሚያስታውሱ አስተያየቶች ተነሥተው እንደነበር የጉባኤው ምንጮች ተናግረዋል፤ ከእርስዎ ጋራ መነጋገር አልቻልንም፤ ወደ አጀንዳ ሳንገባ በየቀኑ ከእርስዎ ጋራ ንትርክ ሰልችቶናል፤ ሦስተኛ አካል ይግባ፤ ከዚህ በፊትም መንግሥት ይግባ ብለናል ብለዋል አንድ በፓትርያርኩ ግትርነት የተማረሩ አንድ አባት፡፡ ይኹንና ሐሳቡ ወዲያው ነበር ተቃውሞ የገጠመው፡፡

አሁን ጎራ ለይቷል፤ በአንድ በኩል ቅዱስነትዎ  በኩል የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ፤ ስለዚህ የቀረቡትን አጀንዳዎች ለተቀበሉት አብዛኛው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ድም ተገዥ እየኾኑአይደለም፤ ያሉት ሌላ ብፁዕ አባት ሦስተኛ ወገን የሚባል አካል አይገባም፤ አያስፈልገንም፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጭ፣ ሕግ ተርጓሚ፣ ሕግ አስፈጻሚ ነው፤ ስለዚህ አጀንዳዎቹን አጽድቆ መወያየቱን መቀጠል ይኖርበታል፤” በማለት አንገብጋቢ የኾኑ አጀንዳዎችን በመለየት ዘርዝረዋል፡፡ በእኚህ ብፁዕ አባትሐሳብ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶሱ ይህን ማድረግ ካልቻለ ግን ሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ሀገረ ስብከት አላቸው፤ በአባትነት የሚመሩት ምእመን አላቸው፤ ስብሰባውን አቋርጠን ወደየ አህጉረ ስብከታችን ተመልሰን የእርስዎን እንቢታ እናስረዳለን፤” በማለት አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል፡፡ ከዚህ ሐሳብ ጋራ የሚጣጣምተጨማሪ አስተያየት የሰጡ ሌላ አባ ስብሰባውን ማቋረጥ ብቻ ሳይኾን ይህ ምልአተ ጉባኤ የሚለያየው ስለ ኹኔታው ለሚዲያ መግለጫ በመስጠት ጭምር ነው ማለታቸው ተዘግቧል፡፡

የስብሰባው ምንጮች እንደሚያስረዱት ፓትርያርኩ የኋላ ኋላ በአቡነ ፋኑኤል በድጋሚ መጠቀሱ የተነገረውንሦስተኛ ወገን (የመንግሥት አካልጣልቃ ገብቶ ያነጋግረን የሚለውን ሐሳብ የተቀበሉ ቢኾንም ከዚህ በፊት ተደብድበን ምን የመጣ ነገር አለ፤ በሃይማኖት፣ በአስተዳደር ጉዳይ ሲኖዶሱ የመወሰን ሙሉ ሥልጣን አለው፤በሚል ተቃውሞ ሐሳቡ ተቀባይነት ገኝ ቀርቷል፡፡ በመጨረሻም ከፓትርያርኩ በቀር የምልአተ ጉባኤው አባላት “ስብሰባውን አናቋርጥም፤ ወደ የሀገረ ስብከታችንም አንሄድም፤ ሌላ ሰብሳቢ መርጠን እንቀጥላለን” በሚል ውሳኔ ከቀትር በኋላ ለመገናኘት ቆርጠው መነሣታቸው ተመልክቷል፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ በየጊዜው በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የሚቀርቡትን አጀንዳዎች የማጽደቅና እንደ አስፈላጊነቱም የማሻሻል፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ላይ ሁሉ የመወሰን ሥልጣን እንዳለው ተደንግጓል፡፡

ፓትርያርኩ በብቸኝነት ከሚሟገቱላቸው ሦስቱ አጀንዳዎች ይልቅ ለስብሰባው ከተቀረጹት መነጋገርያ አጀንዳዎች መካከል በተ. (2) ስለ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ዓመታዊ ሪፖርት፣ በተ. (6) ማእከልን ጠብቆ አለመሥራት ስላስከተለው ችግር፣ በተ. (10) ስለ ልማት እና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን፣ በተ. (13) ስለሃይማኖት ሕጸጽ በኮሚቴው የሚቀርበውን ሪፖርት መስማትና መወሰን፣ በተ. (18) በሰሜን አሜሪካው ዕርቅጉዳይ ሪፖርት ስለ መስማት የሚሉት አጀንዳዎች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጧቸው እንደ ኾኑ ብዙኀኑ ብፁዓንሊቃነ ጳጳሳት ከሚያንጸባርቋቸው አቋሞች ለመረዳት ተችሏል፡፡ ከእኒህም ሁሉ በላይና በፊት ደግሞ በዛሬውየቀትር በፊት የስብሰባው ውሎ ስለ ሃይማኖት ሕጸጽ የተጠናቀረው ሪፖርት አጀንዳ አንገብጋቢ እንደኾነ በብዙዎቹ የስብሰባው ተሳታፊዎች አጽንዖት የተሰጠበት ጉዳይ ነው ተብሏል፡፡

ይልቁንም በሃይማኖት ሕጸጽ ጉዳይ ማስረጃ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በሊቃውንት ጉባኤና በብፁዓን ሊቃነጳጳሳት ኮሚቴ ከታየ በኋላ ሪፖርቱ ገና ወደ ምልዓተ ጉባኤው ቀርቦ ውሳኔ ሳይሰጠበት የተወሰኑ ግለሰቦችከሕጸጽ ነጻ መኾናቸው እንደተረጋገጠ በመፍቀሬ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች የተነዛው አሉባልታብዙዎቹን አባቶች ክፉኛ አስቆጥቷ የሚቀርበውን ሪፖርት በጥንቃቄ እንዲመለከቱትም ከወዲሁ አነቃቅቷቸዋል፡፡ አሉባልታውን ከሚያናፍሱት ብሎጎች የአንዳንዶቹ ጸሐፊዎች ሃይማኖታቸው እንዲመረመር ውሳኔ ከተላለፈባቸው ግለሰቦች መካከል እንደሚገኙበት ጉዳዩን በቅርበት ከሚከታተለው የፀረ -ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መርበብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስለ ቅዱሳን ሲኖዶስ ቀጣይ ውይይቶች እና የዛሬ ፍጻሜ የምናዘጋጀውን ሪፖርታዥ እንተጠናቀቀልን እናቀርባለን፤ ተከታተሉን።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን


5 comments:

 1. this is the best idea!

  ReplyDelete
 2. especially if it is possible to decide on the patriarch our church will get relief and best solution will come soon!

  ReplyDelete
 3. ውድ መላው የኢትዮጵያ ህዝበ ክርስቲያን በሙሉ ነገሩን ሁላችንም በጥንቃቄ እንድንከታተልና ከአባቶች ጎን በንቃት እንድንቆም አሳስባለሁ:: ከዚህ በፊት በአባቶች ላይ የደረሰውን ድብደባና ማስፈራራት በማስታውስ አባቶቻችንን ሊያሸማቅቋቸው ይችላሉ:: ይህ ደግሞ የነፍሳችን ጉዳይ ስለሆነ ሁላችንም ለማንኛውም መስዋእትነት ዝግጁ በመሆን ከአባቶች ጎን እንሁን:: የአንድ አድርገን ሪፖርት አዘጋጆችና መላው ክርስቲያኖች እባካችሁ እንደዚህ አይነቱን መልእክት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በማዳረስ ሃላፊነታችንን እነወጣ:: በኛ ዘመን ቤተክርስቲያንን ለመናፍቃን አሳልፈን አንሰጥም:: በህይወት እያለን ተሃድሶ የሆነው አባ ጳውሎስ በቤተክርስቲያን ላይ የሚጫወትባት እዚህ ላይ መቆም አለበት:: ለዚህ ደግሞ ሁሉም ክርስቲያን ነፍሳችንን እስከመስጠት ለሚያደርስ መስዋእትነት ዝግጁ እንሁን:: ከዚህ በኋላ አባቶቻችንን በማስፈራራት እንኳን ቢበታትኗቸው መላው ህዝበ ክርስቲያን ግን በአንድነት ለፍጹም መስዋእትነት ዝግጁ እንድንሆን አሳስባለሁ:: እባካችሁ ሁላችሁም በምትችሉበት መንገድ ሁሉ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እናሳስብ:: ሁሉ ግን እናዳባቶቻችን በስርአት ይሁን:: ኢትዮጵያ በስርአት የሚንቀሳቀስ እንደሚደበደብና እንደሚገደል እናውቃለን ቢሆንም ግን እኛ እስከወዲያኛው ድረስ ስርአት በጠበቀ መንገድ የቤተክርስቲያናችንን ስርአት የማስከበር መንፈሳዊና ሃገራዊ ግዴታ አላብን:: እነሱ እንደለመዱት ይደብድቡን ይግደሉን:: እኛ ግን ነስፍንና ስጋን ጭምር ሊገድል የሚችለውን እንጂ ስጋን ቢቻ ሊገድል የሚችልን ማንኛውንም ወገን አንፈራም ዮሐ. ራእይ 2:10...ለህግ ግን መቼም መች ሁሌም ተገዢዎች ነን::

  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
  H/Mariam

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር ይስጥልን ሀ/ማርያም የተቀደሰ ሃሳብ ነው:: እኔም ይህን ነው የምለው:: ሃማኖታችንን እንዲጠብቅልን እግዚአብሄርን በፀሎት እንለምን ::
  የጻርቃን የሰማዕታት የቅዱሳን ረድኤትና በረከት አይለየን!!! ቸር ወሬ ያሰማን ::
  ገ/ስላሴ From HARAMAYA UNIVERSITY

  ReplyDelete
 5. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete