(አንድ አድርገን ግንቦት 5 2004 ዓ.ም)፡- የርክበ ካህናት ቅዱስ
ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ፣ ግንቦት 2 ቀን 2004 ዓ.ም ጠዋት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተጀምሯል ፤ ስብሰባው ቀናትን አስቆጥሯል
፤ በመጀመሪያ ቀን ከ20 የማያንሱ አጀንዳዎችን በአርቃቂ ኮሚቴው አማካኝነት ተሰናድቶ ስብሰባው ተጀምሯል ፤ የተያዙትን አጀንዳዎች
በአጽንኦ ለመመልከት ችለን ነበር ፤ በርካታ መልካም የሆኑ እና የቤተክርስትያኒቱን ችግር ያማከሉ አጀንዳዎች ተቀርጸዋል ፤ ውሳኔዎቻቸው
ተግባራዊ ከተደረጉ መሰረታዊ ለውጥ ይመጣል ብለን እናምናለን ፤ ነገር ግን መንግስት ዋልድባ ገዳም ላይ እየሰራ ያለውን የሥኳር
ልማት በሚመለከት ገዳሙ አሁን ያለበትን ሁኔታ መሰረት አድርገው የሚነጋገሩበት አጀንዳ አለመያዙ በሰዎች ዘንድ አግራሞትን ፈጥሯል ፤ ቀጥሎም ስለ አቡነ ጳውሎስ
‹‹እመቤታችን ላይ ጥንተ አብሶ አለባት›› ብለው የጻፉት የመመረቂያ ጽሁፍ እንደ አጀንዳ አለመያዙም እንደዚያው ፡፡ በተራ ቁጥር
19 ላይ ልዩ ልዩ ጉዳዮች በማለት የተያዘ አጀንዳ አለ የዋልድባ
ጉዳይ እዚህ ውስጥ ይነሳል ብለው የሚያስቡ ሰዎችም አሉ ፤ ነገር ግን ዋልድባ ገዳሙንና የገዳሙን አባቶች የሲኖዶስ አባላት በተጣለባቸው
ኃላፊነት መሰረት ተነጋግረው መፍትሄ ባያመጡ እንኳን የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥና ማመላከት ይጠበቅባቸዋል ፤ በተጨማሪም እስከ አሁን
ዝም ያሉት አባቶች አቋማቸውን ያንጸባርቃሉ ተብሎም ይጠበቃል ፤ ይህን ጉዳይ በዋና አጀንዳነት ይዘው መነጋገር ካልቻሉ የእነርሱም
ሰልፍ ከወዴት እንደሆነ ይታወቃል ፤ ይህ ደግሞ ምዕመኑ ከእዚህ በፊት በቋፍ ላይ የነበረውን ለአባቶች ያለውን እይታ እስከ ወዲያኛው
ገደል ሊከት ይችላል ፡፡
አሁን እንዴት በዚህ ወቅት ዋልድባ ገዳም ጉደይ እንደ ዋና አጀንዳ መያዝ
የለበትም? ወይንስ ጉዳዩ ለአጀንዳነት አይመጥንም ? ፤ ይህ የሚያሳየው አንድም መነጋገር አልፈለጉም ፤ አልያም ደግሞ የመንግስት
ተጽህኖ አለ ማለት ነው ፤ ‹‹ቄሱም ዝም መጽሀፉም ዝም›› ማለት መቻል የለበትም ፤ ዛሬ ላይ ሆኖ ይህን ጉዳይ መቃወም ካቃታቸው
ነገ ከተወቃሽነት አይድኑም ፤ ‹‹ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት
ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። . . ." የሐዋሪያት ሥራ ፳ ፥ ፳፰ እስኪ ብዙ ሳንል የጉባኤውን ፍጻሜ እንጠብቅ ፤
በሌላ በኩል የአቡነ ጳውሎስ የመመረቂያ መጽሀፍ ላይ የ‹‹ጥንተ አብሶ››
ጉዳይ ለምን አጀንዳ መሆን እንዳልቻለም በምዕመኑ ዘንድ ጥያቄ አለ ፤ ይህስ ለአጀንዳነት አይመጥንም ? ወይስ ልዩ ልዩ ጉዳዮች
የሚለው ውስጥ ለመነጋገር አስበው ነው ? ይህ ጉዳይ እኮ የቤተክርስትያኒቱን አስተምህሮ የሚጻረር ነው ፓትርያርኩ በህይወት እያሉ
ስህተታቸውን ነገሮ ለሰሩት ስራ ይቅርታ እንዲጠይቁ እና ንስሀ እንዲገቡ ማድረግ ይሻላል ? ወይስ ፓትርያርኩ በህይወት ካለፉ በኋላ
በጉዳዩ ላይ ትክክል አይደሉም ማለት ? የፓትርያርኩ ሀውልት መፍረስ ያለበት የመመረቂያ ጽሁፋው ላይ ያጻፉት ኑፋቄ መገለጥና መገሰጽ
ያለባቸው በህይወት ሳሉ ነው ፤ አሁን እየተደረገ ያለው ነገር ጥቂት
አባቶች ፓትርያርኩን ጨምሮ ጉባኤውን ውዝግብ ውስጥ የሚከትን ጉዳይ በሲኖዶስ ስብሰባ ላይ ላለማንሳት የታሰበ አካሄድ እንደሆነ ያሳየናል
፡፡ ለምን ይህ ጉዳይ እሳቸውን ብቻ ሳይሆን በርካቶችን አብረዋቸው
የቆሙትን ሰዎችን አቋቸውን ስለሚያጋልጥ ነው፡፡
‹‹ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። . . ." የሐዋሪያት ሥራ ፳ ፥ ፳፰ ይህን መልእክት በመጽሀፍ ቅዱስ ሰፍሮ እናገኝዋለን ፤
አሁንም ብጹአን አባቶቻችን ለመንጋውና ለቤተክርስተያን ግድ ሊላቸው ይገባል ፡፡ ለምን ይህ ፈተና መጣ አንልም ‹‹ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ
ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።›› 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10 ፤13 ላይ ሰፍሯል ፤ ነገር ግን
ፈተና ሲመጣ ብቻውን እንደመጣ ብቻውን አያልፍም ፤ ፈተናው አብሮ ይዞ የሚያልፋቸው ነገሮች ይኖራሉ ፤ እኛም ስለ ፈተናችን ልንታገስ
በጾም በጸሎት ልንበረታ ያስፈልጋል ፤ ይህ ፈተና የሚያልፈው አባቶች የአባትነታቸው ተግባር ሲፈጽሙ ምዕመናኑም ሀላፊነታቸውን
አውቀው ስራቸውን በአግባቡ ሲፈጽሙ ብቻ ነው ፡፡ ይህ ፈተና ሰዎችን ከስልጣናቸው ሊያፈናቅል ይችላል ፤ እስር ቤት ሊያስገባቸውም
ይችላል ፤ አካላዊ ጉዳትም ሊያደርስባቸው ይችላል ፤ አባቶችን ከበአታቸው በረው እንዲጠፉ መንገድ ሊከፍት ይችላል ፤ በስተመጨረሻ
የህይወት መስዋእትነትንም ሊጠይቅ ይችላል ፤ ይህን አውቀን ነው ፈተናን በእግዚአብሔር ኃይል ለመጋፈጥ መዘጋጀት ያለብን ፤ ስለዚህ
ይህ ፈተና የመጣው ለዋልድባ መነኮሳት ብቻ አይደለም ፤ ይህ ፈተና የሁላችንም ነው ፤ ቅዱስ ፓትርያርኩና የሲኖዶስ አባላት በጉዳዩ
ላይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም በአሁኑ ሰዓት የተጀመረውጉባኤ ላይ ራሱን ችሎ በአጀንዳነትም አልታየም ፤ ነገሩን መቃወምም አለመቃወምም ሁለቱም አቋም ነው ፤ ነገር ግን ሁኔታው እያዩ
ዝም ማለት ግን እንደ አባት መልካም አይደለም ፤ እነርሱ በዚህ ጉዳይ
ላይ አንድ እርምጃ ተራምደው ለእኛ ቢያሳዩን መልካም ነው ፡፡
guys do not worry about original sin about saint mary . It doesnot matter on her life . Worry about Jesus christ Amen
ReplyDeleteyebesebes zenabe ayeferame newe!!!!menafeqe
DeleteAbune Paulos don't say he believes that Mary is under original sin. He stated the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church believes that Mary was born under the umbrella of original sin.
ReplyDeleteIs there detail written dogmatic issue on this concept? I think there is nothing written in our dogmatic books like haimanot abewu except some books say to Mary "Nitshit Zer". How come we differ on this regard with other oriental orthodox belief.
During my early age in Sunday school and Mk, I learnt that one of the differences between orthodox and catholics is because catholics says that Mary is "haile arayamawi" which is related to original sin. Now this seems that we are also supporting their idea. Is there any one who can tell me the difference between what we belief that Mary is free from original sin and immaculee conception by catholics?
Thank You
ነጭ ዕንቁ በአዳም ገላ ውስጥ መጽሐፍን ያንብቡ እስኪ ወዳጄ!
DeleteAs far as my knowledge goes our church does not believe that Our Mother ST.Mary has any possession of the original sin. They prove this by saying how Jesus is incompatable with anything of sin and if he was born from a mother with the original sin that would mean he would have the curse on him too (due to complete Tewahdo). And hence, he created Mary pure from anything cursed in the heart and soul.
ReplyDeletememihir habtemariam tedla yetsafut metshaf ale. ersun bitimeleket sile saint Mary bizu negeroch tagegnaleh. by the way oriental ortodoxy doesn't believe in the original sin of saint Mary. rather it believes saint Mary is free from original sin. there is some confusion in Coptic orthodoxy. this comes once up on a time when pope tewoflos(i am not sure of his name exactly)was in crown. he had some protestant tehadiso servants like abune paulos. they persuade him to believe that saint Mary is under the original sin. bur you can refer the belief of Copts in their books before this pope that they didn't believe that saint Mary is under the sin of Adam.
ReplyDeleteany ways you can read the book written by memihir habtemariam tedla which says "nech enque be adam gela."
who cares they are sellout anyway!!!!!!!!!!!!!!!! what are you expecting..... all the papas is hodam and eat only, do not care about if people die for religion or not..... if you give them money then they will destroy the church too..... they are not a holly fathers.... how can you say a holly synod if they were not talking about the situation of waldiba.... the government is destroying our church and everybody knows about it but if they do not say anything then i will never go to Ethiopian Synod yalebet church unless they fixed this situation..... they all hodamoch.. hodachew amlakachew yihonal yetebalew benezih tefeseme yasazinal begna gize medresu.... i live in USA and I always went to the Ethiopian orthodox tewahedo church (be Ethiopia synodos yemimerawun) malete new ahun gin i feel like i waste my time there.... may be i will go to (geleltegna) honew egziabhiern yemiameseginu alu ke yilma hailu betekrsitian ehedalehu chigiru eskifeta dires ..... any way they are not a hollyfather but a sellout and hodamoch afer yiblu
ReplyDelete