Saturday, December 22, 2012

ማኅበረቅዱሳን ቅዱስ ሲኖዶስ ፮ኛውን ፓትርያርያክ ለመምረጥ የወሰነውን ውሳኔ በድጋሜ እንዲያጤነው ጠየቀ





  •   ቤተክርስቲያን ስድስት ቦታ ብትከፈል አያገባኝም።” አቡነ ቀሌምንጦስ
  •  “ወነአምን በአሐቲ ቤተክርስቲያን” ማኅበረቅዱሳን
  •  ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላሙ ቅድሚያ የማይሰጥ ከሆነ ራሳችንን እናገላለን” በአሜሪካ የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ምእመናን
  •  ሀራ ተዋህዶ የተሰኘው የጡመራ መድረክ “ማኅበረቅዱሳን አቋሙን ለወጠ።” የሚለው መሰረተ ቢስ ወሬ ግብ ምን እንደሆነ እያነጋገረ ነው።
  •  “መንግሥት በካርድ ነው የሚመርጠው ፣ ስለዚህ መንግሥት ኃጥያተኛ ነው? እኛ ማን ሆነን ነው በዕጣ ካልሆነ የምንለው? ከመንግሥት እኛ እንበልጣለን?” አቡነ ጎርጎርዮስ

(አንድ አድርገን ታህሳስ 13 2005 ዓ.ም)፡- ባለፉት ሃያ ዓመታት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት በማበርከት በቅዱስ ሲኖዶስ እና በምእመናን ዘንድ ታማኚነት ያተረፈው ማኅበረ ቅዱሳን ከአቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ የቤተክርስቲያን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲወያይ ለጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በደብዳቤ ማሳወቁ፣ በህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ልሳኖቹ ማሳወቁ እንዲሁም የማኅበሩ አመራሮች አባቶችንና ምእመናን መደበኛ በሆኑና ባልሆኑ መንገዶች በማወያየት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት መጣራቸው ይታወቃል።

ማኅበሩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በይፋ በጻፈው ደብዳቤ እንደገለጸው ሕገ ቤተክርስቲያን እንዲሻሻል፣ ቋሚ የፖትርያርክ መምረጫ ሕግ እንዲኖር፣ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ማሻሻያ የሚያጠና የቴክኒክ ኮሚቴ በይፋ እንዲቋቋም መጠየቁ ይታወሳል። የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ የወሰነውን ውሳኔ ወደ ጎን በመተው የማኅበሩ የሕግ ባለሙያዎች በፓትርያርክ መምረጫ ሕግ አርቃቂ ኮሚቴ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ከውስጥም ከውጭ የነበሩትን ተጽእኖዎች በመቋቋም በጎ ሚናዎች ለመጫወት ሞክሯል።

አርቃቂ ኮሚቴው የምርጫ ሂደቱን በዕጣ ይሁን የሚለውን ሃሳብ ባለመቀበሉ ማኅበሩ ቤተክርስቲያን ለፓትርያርክ  መምረጫነት ብትጠቀምበት የተሻለ ነው ብሎ የሚያምንበትን ስድስት ገጽ ረቂቅ ሕግ በደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳውቋል። ከዚህ በተጨማሪ ለምልዓተ ጉባኤው ሌሎች የመምሪያ ኃላፊዎች በተገኙበት የማኅበሩን አቋም በሦስት ተወካዮች በኩል አሳውቆአል። ይህም ንግግር  በምልዓተ ጉባኤው ሰፍኖ የነበረውን በድምጽ ብልጫ ይሁን የሚለውን ድባብ ቀይሮታል። ምልዓተ ጉባኤው በዕጣ እንዲሆን ከተስማማ በኋላ ከቅድመ ጵጵስና ጀምሮ የብአዴን አባል የሆኑት አቡነ ቀሌምንጦስ፣ የኦህዴድ አባል የሆኑት አቡነ ሳዊሮስ፣ የሕወኃት አባል አቡነ ጎርጎርዮስ ከፓርቲያቸው ኢህአዴግ የተሰጣቸው ተልዕኮ ውሳኔው እንዲያስቀለብሱ በተደራጀ መልኩ በመፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በመንግስት አጀንዳ እንዲጠለፍ ሆኖአል። ለውሳኔው መቀልበስ የዲያቆን ዓባይነህ ካሴን የቪኦኤ ቃለመጠይቅ የማኅበረ ቅዱሳን አቋም “አቡነ መርቆርዮስን ወደ መንበራቸው መመለስ ነው ፣ አታሎናል” በማለት እንደመስፈንጠሪያ እነዚሁ ሊቃነጳጳሳት ተጠቅመውበታል። መጀሪያውኑ ምልዓተ ጉባኤው በዕጣ ምርጫው ይደረግ ብሎ ሲወስን ማኅበሩን በመተማመን የወሰነ አስመሰሎበታል። ማኅበሩ የዲያቆን ዓባይነህ ካሴን መግለጫ በማኅበሩ መካነ ድር እንዲህ በማለት ገልጾታል በማኅበረ ቅዱሳን ያላቸውን ሓላፊነት በመጥቀስ / ዓባይነህ ካሴ ታህሣሥ 6 ቀን 2005 . ምሽት ላይ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ፕሮግራም ለቃለ ምልልስ ቀርበው በወቅታዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ሓሳብ መስጠታቸው ይታወሳል። ማኅበረ ቅዱሳንን በመወከል ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫም ሆነ ቃለ ምልልስ መስጠት የሚችሉት የማኅበሩ ሰብሳቢ ወይም ዋና ጸሐፊ ወይም የማኅበሩ ሕዝብ ግኑኝነት ሓላፊ ናቸው፡፡ ስለዚህ / ዓባይነህ ካሴ በቃለ ምልልሳቸው የሰጡት አስተያየት የግል አስተያየታቸው መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።”

የማኅበሩ አባላት በአሜሪካ የተጀመረውን እርቀ ሰላም በማመቻቸት፣ የፓል ቶክና የስልክ ውይይቶች በማዘጋጀት ምእመናን ሃሳባቸውን እንዲገልጹ በማድረግ የበኩሉን ተወጥቷል።  የሥራ አመራር ጉባኤ አደረገ በተባለው ስብሰባ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔው ደግሞ እንዲያጤነው ጠይቆአል። ለዚህም የማኅበሩ አመራር በተናጥልና በጋራ አባቶችን የማግባበት ሥራ እንደሠሩ ምንጮቻችን ዘግበዋል።

ከዚህ  ጋር በተያያዘ ዜና ትናንት ማምሻውን ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ተገኝቶ የፓርቲውን ተልዕኮ በታማኝነት እየተወጡ የሚገኙ  ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ቀሌምንጦስ፣ አቡነ ጎርጎርዮስና አቡነ ሳዊሮስ ጋር የፓትሪያሪክ ምርጫው በአስቸኳይ ስለሚጀመርበት ሁኔታ መምከራቸው ታውቋል። በውይይቱ ወቅት አቡነ ቀሌምንጦስ “መንግስት ማኅበረ ቅዱሳንን ያስታግስልን፣ አባቶችን የሚከፋፍላቸው እርሱ ነው።” ማለታቸው ተሰምቶአል። ማኅበረ ቅዱሳንን አባ ሰላን የመሰሉ የተሃድሶ መናፍቃን ብሎጎች የሚወሩትን የፈጠራ ወሬዎች በማሰባሰብ ባለው የመንግሥት ሓላፊነት ተጠቅሞ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲከስ የቆየው ሚኒስትሩ ሃሳቡን የሚጋሩት ጳጳሳት በማግኝቱ የልብ ልብ ተሰምቶት ዛሬ ጠዋት የሃይማኖት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዻይሬክተር አቶ ትእዛዙ በመላክ ለማስፈራራት መሞከራቸው ተሰምቷል።

ማኅበሩን በመንግሥት ፈርጣማ ክንድ ለማስመታት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን የማኅበሩን አመራር አባላትም ለማስፈራራትና ተጽእኖ ለማሳደር የደህንነት ባለስልጣናት ጥረት  እያደረጉ ሲሆን የማኅበሩ አመራር አባላት ቅዱስ ሲኖዶስ ለእርቀ ሰላሙ ቅድሚያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል ።  ማኅበሩ ይህንን አቋም በድረ ገጹ ላይ “አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ”  /ማቴ. 524/ በሚል ርእስ ባስነበበው ጽሁፍ ላይ “ ……. ስለዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ለሰላሙ መስፈን አስፈላጊ የሆነ ዋጋ እንዲከፈል ግፊት በማድረግ ሊረባረቡ ይገባል፡፡ ምእመናንም ከካህናት አባቶች ጋር በጸሎት በመትጋት ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሔ እግዚአብሔር እንዲሰጠን መማጸን ይገባናል፡፡ የተጀመሩትን ሒደቶች ሁሉ በእውነተኛነትና በሚዛናዊነት እየተከታተሉ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያሳለፈችው ያለፉት ዓመታት ኣሳዘኝ ሁኔታዎች እንዳይቀጥሉ ዛሬ ላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባን ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ለዚህም ይሠራል።”

የማኅበሩ አቋም ይህ ሆኖ እያለ  በቅርቡ ጡመራን የጀመረው  “ሐራ ተዋህዶ” የተሰኘው የጡመራ መድረክ “ማኅበረቅዱሳን አቋሙን ለወጠ።” በሚል ያቀረበው ዜና የመረጃ ምንጭ ችግር እንዳለበት ተነግሮአል። ከተሳሳተ የመረጃ ምንጭ ያገኘውን ዜና እንደወረደ ማቅረቡ ከጡመራ መድረኩ አዲስነት የተነሳ በልምድ ማጣት የተከሰተ ከሆነ በሂደት እንደሚስተካከል እናምናለን። በዓላማ ማኅበሩ ቅድስት ቤተክርስቲያን የተጋረጠባትን አደጋ ለማስወገድ እየከፈለው ያለውን ዋጋ መና ለማስቀረት፣ የማኀበሩን አባላት ለመከፋፈል ያለመ ከሆነ “አንድ አድርገን” በጽኑ ትቃወማለች። የማኅበረ ቅዱሳን አመራር አባላት በጳጳሳቱ ዘንድ “አስፈሪ ግርማው” ርደተ ህሊና የሚፈጥረውን  መንግሥት እያሳደረበት ያለውን ተጽእኖ በመቋቋም እያደረገ ያለው ተጋድሎ ታደንቃለች። የቤተክርስቲያንን ልዕልና ለማረጋገጥ ከሚሰሩ አካላት ጎን ትቆማለች። “ሐራ ተዋህዶ” የጡምራ መድረክ ዓላማዋ በዚህ ሰዓት የቤተክርስቲያንን አንድነት ማስጠበቅ ከሆነ የጡምራ መድረኳ ጦማሪዎች ለግለሰቦች ያላቸውን አመለካከትና እይታ ማዕከል አድርገው ከመጻፍ እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ እንወዳለን። ስለ ግለሰቦች ሳይሆን አንድ የምታደርገን ቤተክርስቲያ የቆመችበትን ቦታ አጢነን መረጃዎችን ብናስተላልፍ መልካም ነው ትላለች፡፡ እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ቤተክርስቲያን የቆመችበት መስቀለኛ መንገድ ተገንዝበው፣ ቤተክርስቲያናችን ወደ ተሻለ ልዕልና ከፍ ለማድረግ የሚደረጉ ሁለንተናዊ ትግል በተቀናጀ መልኩ በመፈጸምና ልዩነት የሚፈጥሩ ጥቃቅን ጉዳዮች በመተው በአንድነት እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋልን።

ቸር ወሬ ያሰማን!

19 comments:

  1. egziabher yebarkachihu amien cher werie yaseman egziabher deg abat yesten

    ReplyDelete
  2. Replies
    1. hey guys ur talking about individual bishops before what they do and publish in ur blogs. now u get angry because they write what u do? first all u have ur group member have been nominated the next patriach that u don't agree with the system of election "eta". sorry guys u should work to unite the church not stand against it.

      Delete
  3. ማሕበረ ቅዱሳን ባለቀ ሰአት ነው ስለ እርቅ የሚያወራው እጅግ ያሳዝናል ለመሆኑ ማንን ልታታልሉ ነው የፓትርያርክ ምርጫ ደንብ ስታዘጋጁ ከርማችሁ አሁን ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱ ትዝብት ላይ ነው የወደቃችሁ ለማንኛውም ጊዜ ገቢር ለእግዚብሔር ነውና አምላክ ይፍረድ

    ReplyDelete
  4. ከቅድመ ጵጵስና ጀምሮ የብአዴን አባል የሆኑት አቡነ ቀሌምንጦስ፣ የኦህዴድ አባል የሆኑት አቡነ ሳዊሮስ፣ የሕወኃት አባል አቡነ ጎርጎርዮስ ከፓርቲያቸው ኢህአዴግ የተሰጣቸው ተልዕኮ ውሳኔው እንዲያስቀለብሱ በተደራጀ መልኩ በመፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በመንግስት አጀንዳ እንዲጠለፍ ሆኖአል።

    ReplyDelete
  5. ቤተ ክርስቲያኒቱ የወንበዴዎች ዋሻ፣ ንስሐ የማይገቡ ሌቦች መሸሺያ ሆናለች!!

    ReplyDelete
  6. +++
    Yemayazenebil hilinan siten enbel!!!
    Egziabhere yistlin. Yekidusan amlak agelglotachihun yibarklachihu.Leharatewahidon yetesetew asteyayet bego new. Rasun lemayet yetezegage sew kale yimarbetal kelelem chel yilewal. Yih geeze beandinet komen egzeabheren seleand neger yeminleminibet seat new...kegudau wusibsibnet anstar lehulum wogen leabatichim lemahiberat meriwochim lemeamnanm egziabhere yemayazenebil nistuh hilinan yiset zend yeminileminibet lihon yigebal.Yih kehone egziabhere Menfeskidus ewunetun yastemirenal yimeranal.yehulum wogen Abatoch yemayazenebil hilina kemenfeskidus ketesetachew betebeat kifwun yikuakuamalu tiru wusane yiwosinalu bewusanew meemenan dsyilachewal. Yih sayhon biker gin hulum wodeyegeza mignotunafilagotu-wode alwyan negestat, wode zerhareg, woy wodekefa woy wode aplos - kazenebele,menfeskidus yileyal.wusaneum egziabhereninm, sewunm, nege tewat wosagnochinm gotgwach aswosagnochinim ayasdesitim!! Begizew Tagashu gin Kenaew amlak betun liyasteda yinesal!Selebegochum silecher eregnochum chuhet yigedewal!! zim aylim!!Zare new mefthew ersum "YEMAAYAZENEBIL HILINAN SITEN" bilo atkuro astnito melemen new. Beewunet yihin yemilemin yigegn yihon? Enlemin, belimenachin aktacha yemitebekibinin tiret enadrig(ensra), begown mels enkebelalen.YEMAYAZENEBIL HILINAN SITEN AMEN.

    ReplyDelete
  7. Ethiopia tekebira Yenorechiw Ye Kirisitina Hager silehonech New Ahun Gin Begirgir Le Eisilam temchew mebetsabetsi Meleyayet Yemitsekimew Lemanew
    Anid Adirgen Papasatun Mekawemina Bedelega Madireg Min Yitsekimal Abune Kelementsosin Enawkachewalen Menfesaw -Balemoya -Yewah Papas Nachew Abba Sereken betekawemu Gize Enantem Tawdisachew Nebere Ahun Gin Mahibere kidusann Sile Tekawemu Simachewn Matsifat tejemere Malet new Yasazinal Tew fetena -Mekisefit- Yagegachihal Egiziabher Yikotsachihal

    ReplyDelete
  8. enhe "abune kentesew" yemblut selam yelachew wey weys lela teleko alachew? we neeed one church !

    ReplyDelete
  9. ራሄል ስለ ልጆቿ መጽናናትን አልቻለችም 'ሀሎኑ በዝ ሰማይ '
    ' አምላከ አዶናይ'

    ReplyDelete
  10. ስለዚህም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ለሰላሙ መስፈን አስፈላጊ የሆነ ዋጋ እንዲከፈል ግፊት በማድረግ ሊረባረቡ ይገባል፡፡ ምእመናንም ከካህናት አባቶች ጋር በጸሎት በመትጋት ለዚህ ችግር ዘላቂ መፍትሔ እግዚአብሔር እንዲሰጠን መማጸን ይገባናል፡፡ የተጀመሩትን ሒደቶች ሁሉ በእውነተኛነትና በሚዛናዊነት እየተከታተሉ በጎ ተጽዕኖ ማሳደር ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ያሳለፈችው ያለፉት ዓመታት ኣሳዘኝ ሁኔታዎች እንዳይቀጥሉ ዛሬ ላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ እንደሚገባን ማኅበረ ቅዱሳን ያምናል፡፡ ለዚህም ይሠራል።”

    ReplyDelete
  11. እግዚአብሔር ይስጣችሁ
    እዉነት ነዉ 'እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ቤተክርስቲያን የቆመችበት መስቀለኛ መንገድ ተገንዝበው፣ ቤተክርስቲያናችን ወደ ተሻለ ልዕልና ከፍ ለማድረግ የሚደረጉ ሁለንተናዊ ትግል በተቀናጀ መልኩ በመፈጸምና ልዩነት የሚፈጥሩ ጥቃቅን ጉዳዮች በመተው በአንድነት እንድንቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋልን።' ይህን አቅማችሁን እደግፋለሁ

    ReplyDelete
  12. ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካህናትና ምእመናን በሙሉ።

    ባለፉት ሃያ አመታት ቤተክርስቲያን የተከፈለችው ሃገር ውስጥ ባሉና ፈረንጅ አገር ባሉ ብቻ አይደለም። ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያና የኤርትራ ተብላም ተከፍላለች። ስለዚህ አሁን በሚደረገው የእርቀሰላም ውይይት ውስጥ አሥመራ የሚገኙ ካህናትም እንዲካፈሉ በትህትና አሳስባለሁ።

    ሙሉጌታ


    ReplyDelete
  13. God knows who is who.we shall see in a few days THAT enemy of tewahido will be
    punished by almighty.WAIT AND SEE.

    ReplyDelete
  14. Egziabher yetbkachehu ,Bertu sele ewnet metsafachehun atakuartu
    Yedengle Mariam lej ersu Sele ewnet Ykomuten Abatoch Yabertachew
    Tebarku

    ReplyDelete
  15. <><><><><><><> ከእርቁ በኋላስ ? <><><><><><><><>
    ==========================================
    ከእርቁ በኋላ የኦርቶዶክስ ሃይማኖታችን በአስኳይ ልታተኩርባቸው የሚገባ አሥር ነጥቦች፦
    1ኛ ተሃድሶን በንስሃና አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ በውግዘት ማጽዳት፣
    2ኛ ሙስናን ከሁሉም አባቶች እጅ ላይ ማጠብ፣
    3ኛ ዘረኝነትን ከቤተክርሰቲያንና አልፎም ከኢትዮጵያ ከርሰ ምድር ማጥፋት፣
    4ኛ መነኮሳት በምድር ላይ የሚያካብቱትን ሃብት ለቤተክርስቲያ አስረክበው የሰማዩን ሃብት እንዲያካብቱ ማድረግ፣
    5ኛ አባቶች የመኮብለያ ዜግነት ሳይሆን ሃዋርያዊ የሆነ የዓለም ዜግንትን እንዲያገኙ ማድረግ፣
    6ኛ ቤተክርስቲያን በአንድ ፓትርያርክ በአንድ ጊዜ እንድትመራ ማድረግ፤ ቢቻል ደግሞ “ፓትርያርክ በሕይወት እያለ ሌላ ፓትርያርክ አይሶምም የሚለውን ቀኖና በማሻሻል፤ አንድ ፓትርያርክ በሞት እስካልተለየ ድረስ ለአምስት ወይም አሥር አመት ብቻ በፓትርያርክነት እንዲያገለግል መወሰን፣
    7ኛ እግዚአብሔር መንገስታትን ይገዛል እንጂ መንገስት የእግዚአብሔርን መንግሥት አይገዛም። ስለዚህ የመንግስትን በቤተክርስቲያን ጣልቃ ገብነት ማስቆም፤
    8ኛ የቤተክርስቲያን መተዳደሪያ ደንብ (ቃለ አዋዲ) በዓለም ላይ ላሉ አጥቢያ ቤተክርስቲያናት ባሉብት አገር ቋንቋ ተተርጉሞ ማዳረስ፤
    9ኛ ቤተክርስቲያኒቱ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን እንድትችል ቀኖናዋን ማሻሻል፤
    10ኛ ባለንበት ዘመን በጣም ብዙ የቤተክስቲያኗ ሴት ልጆች ቤተክርስቲያንን በጤና ጥበቃና ትምህርት ዘርፎች ለማገልገል ብቁና ፍቃደኛ ናቸው፤ ይሁን እነጂ የቤተክስቲያኗ ቀኖና ስለሚከለክላቸው ችሎታቸው በቴተክርሰቲያን ውስጥ እንደተቀመጠ ጋን ውስጥ እንደሚብራ ጧፍ ሆኗል። ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘውን የሴት ልጆች ተሳትፎ የበለጠ ለቤተክርቲያን ጥቅም እንዲውል ቀኖናውን ማሻሻል፤

    አብ የፈጠራትን፤ ወልድ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ የሰራትን፤ መንፈስ ቅዱስ የሚጠብቃትን ቤተክርስቲያን ሰይጣን እንዳያፈርስብን አጥብቀን እንጸልይ። በሩን በጸና ፀሎት እናንኳኳ፤ እግዚአብሔርን በጸና የልብ ፀሎት እንሻው፤ እርሱም ቃሉን ጠባቂ አምላክ ነውና ይሰጠናል።

    የወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የጻድቃንና ሰማዕታት ፀሎት ከእኛ አይለየን፤ አሜን።

    ከብርሐኑ መልአኩ

    ReplyDelete
  16. Yekidusan amlak Egziabher yirdan.

    ReplyDelete