Monday, December 24, 2012

የብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ወቅታዊ ቃለ መጠይቅ



ዕንቁ ፡- ብፁዕ አባታችን ስለ እድገትና ትምህርትዎ በአጠቃላይ ስለ ራስዎ ይንገሩን ?
ብጹእ አቡነ ሕዝቅኤል፡- የቀድሞ ስሜ መልአከ ምህረት አባ መኮንን ሀብተማርያም ይባላል፡፡ከአባቴ መሪጌታ መኮን ኃይሉና ከእናቴ ወ/ሮ አታላይ ደርሰህ ግንቦት 7 ቀን 1948 ዓ.ም በደበቡብ ወሎ አማራ ሳይንት ልዩ ስሙ ደብረ ብርሃን ለንጓጥ ሥላሴ በተባለው ቦታ ተወለድኩ፡፡ ከሙሉጌታ አበበ እሸቴ ከፊደል እስከ ዳዊት በተወለድኩበት ደብር ከተማርኩ በኋላ በዚያው በአማራ ሳይንት ደራው መድኃኒዓለም ከመሪ ጌታ አፈወርቅ ሳህሉ ቁም ዜማ አቋቋም ፤ ቦረና ቅዱስ ቂርቆስ ደብር ከመጋቤ ምስጥር ደስታ ብዙነህ ቅኔ ከነ አገባቡ ተምሬአለሁ፡፡
ከብጹዕ አቡነ ገብርኤል በ1956 ዓ.ም የዲቁና ማዕረግ ተቀብያለሁ፡፡ ከዚያ ጎጃም መርጡ ለማርያም ከየኔታ ኢሳያስ ቅኔ ከነ አገባቡ ፤ ከመምህር ሀብተ ኢየሱስ መጽሐፈ ነገስት ትርጓሜና የቅኔ መንዶችን ፤ ደብረ መድሃኒት መድኃኒዓለም ከየኔታ አስካል የቅኔ መንገዶችን ከነ አገባቡ ፤ ብቸና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከየኔታ ፍሰሐ ወልደሚካኤል ምስጢርና የቅኔ ሙያን አዳብሬያለሁ፡፡ ከየኔታ ፍስሀ ወልደ ሚካኤል በ1969 ዓ.ም በቅኔ መምህርነት ተመርቄአለሁ፡፡

ወደ ሸዋ ክፍለ ሀገር በ1970 ዓ.ም በመምጣት ደብረ ሊባኖስ ገዳም በመምህርነት ገብረ ኢየሱስ ስም  በተቋቋመው አዳሪ ትምህርት ቤት  ከመምህር ብርሀኑ ገ/ሥላሴና ከመምህር ገ/ሕይወት ኢየሱስ መጻህፍት አዲሳትን ከነትርጓሜው ፤ ከመምህር ገ/ሕይወት የነብያትንና የሰለሞንን ትርጓሜ ተምሬአለሁ፡፡
ደብረ ሊባኖስ ገዳም ጳግሜ 3 በ1981 ዓ.ም ሥርዓተ ምንኩስናንና ፈጸምኩ፡፡ ህዳር 12 ቀን 1982 ዓ.ም የቅስና ማዕረግ ከአቡነ ሳዊሮስ ፤ ከብጹዕ አቡነ ቄርሎስ  የቁምስና ማዕረግ ተቀብያለሁ፡፡ ከሰኔ 20 ቀን  በ1987 ዓ.ም እስከ 1990 ዓ.ም በምስራቅ ሐረርጌ  የሐደሬ ጠቆ መካነ ሥላሴ ደብር ፤ ከየካቲት 1990  እስከ 1993 ዓ.ም የድሬደዋ ደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፤ ከሰኔ 1 ቀን 1993 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 1 ቀን 1994 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ ደብረ ምጽላል  እግዚአብሔር አብ ቤተክርስቲያን ፤ ከሐምሌ 1 ቀን  1994 ዓ.ም ጀምሮ ሰሜን ወሎ ላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪ በመሆን ሳገለግል ቆይቻለሁ፡፡
ዕንቁ፡- ጵጵስና መቼ ተቀበሉ ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል፡-  በ1997 ዓ.ም ነው ጵጵስና የተቀበልኩት ፤ ከዚያም የከፋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆንኩኝ ፡፡ በዚያም ላይ  የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሀፊ  ሆኜ ስሰራ ቆይቼ አሁን ደግሞ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ነኝ፡፡
ዕንቁ፡- በነዚያ የአገልግሎት  ዘመን ውስጥ የገጠመዎት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ነበሩ ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል፡-  ኦ..!  ችግሮችማ ያጋጥማሉ ፤ ብዙዎቹን አሳልፈናቸው እዚህ ደርሰናል፡፡ አስቸጋሪ የነበሩት  እነዚህ ናቸው እያልኩ አልዘረዝራቸውም እንጂ በዓለም ውስጥ ማዘንም መደሰትም ይኖራል፡፡ እኛ ብዙ ደስታው ስለማይስማማን አልፈነው እዚህ ደርሰናል፡፡
ዕንቁ፡- ቤተክርስቲያን ከ20 ዓመት በላይ ለሁለት ተከፍላ መቆየቷን እንዴት ይገልጹታል ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል፡-  እንግዲህ ቤተክርስቲያን ተከፍላለች ፤ መከፈል አልነበረባትም፡፡ ጊዜው የሚፈጥረው መለያየት አለ ፡፡ ያንን ወደ አንድ ለማምጣት እየተጣጣርን ነው ያለነው፡፡ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ፤ ምዕመናንም አንድ ናቸው ፤ አምላካችን አንድ ነው፡፡ ከሰላም የበለጠ እግዚአብሔርንም ሰውንም የሚያስደስት ነገር ስለሌለ ምዕመናንን አንድ ለማድረግ የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲመጣ እየታገልን ነው፡፡ አሁንም ሽማግሌ ልከን እንታረቅ ብለን እየተነጋገርን ነው፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ እንዲያ አልነበረም ፤ አሁን ግን ተቀራርበን በመነጋገር ላይ ነን፡፡
ዕንቁ፡- በቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ እያለ መሾም የለበትም የሚል ሕግ አለ ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል፡-  ሕጉ አለ ፡፡ በደርግ አገዛዝ ዘመን አቡነ ቴዎፍሎስ እያሉ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ተሾመዋል፡፡ ሆኖም ፓትርያርክ በዚህ ዓለም እያለ  ሌላ ፓትርያርክ አይሾምም ነበር፡፡ ያኔ በሀገሪቷ ላይ በነበረው ችግር ተደርጓል፡፡  ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ  የእኛ የቤተክርስቲያን አባት ናቸው፡፡ ቤተክርስቲያን አስቀምጣቸዋለች ፤ በጊዜው ባለው ችግር “እኔ አሞኛል” የሚል ነገር ተነሳ፡፡ ታሪክ በመስማት እንጂ በእርግጥ እኔ በጊዜው የለሁም ፤ “ኃላፊነቱን ተቀበሉኝ ብለው ቅዱስ ሲኖዶስን አሳስበዋል” የሚል ነገር ነበር ፤ ይህ አግባብ አልነበረም፡፡
አሳቸውም በወቅቱ ችግሩን ችለው ሀገራቸው ላይ መቀመጥ ነበረባቸው ፤ በዚያ ምክንያት ሌላ ፓትርያርክ ተሹሟል ፡፡ 20 ዓመት ተጉዘን እዚህ ደርሰናል ፡፡ ከ20 ዓመት በኋላ ቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ጳውሎስ እያሉ ሰላም እንዲወርድ ተፈልጎ የእርቀ ሰላም ሂደቱን ጀምረን ነበር፡፡  ቅዱስ ፓትርያርኩ  እያሉ አንድ እናድርግ ሲባል  እኛም ወዲያ ወዲህ ስንል በመሀል ቅዱስነታቸው አረፉ፡፡ ብጹዕ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሀገር ቤት መጥተው  እዚህ ጠቅላይ ቤተክህነትም ሆነ የሚፈልጉት ገዳም አስፈላጊው ነገር እየተደረገላቸው እንዲቀመጡ ነበር እኛ ለእርቁ ሰው የላክነው፡፡ ይህ እርቀ ሰላም የተጀመረው ቅዱስ ፓትርያርኩ በህይወት ባሉበት ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡የተጀመረው ሂደት መቀጠል አለበት ብለን ነው ዛሬም ሰው የላክነው፡፡
ዕንቁ፡- የተጀመረው የእርቀ ሰላም ሂደት እስከምን ድረስ እንዲጓዝ ነው የታቀደው ? አሁን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በሕይወት የሉም ፤ ፓትርያርክ እያለ ፓትርያርክ አይሾምም የሚለው ሕገ ቤተክርስቲያን  እንዲከበር ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ቀደመ ፓትርያርክነታቸው እንዲመጡ በእናንተ በኩል ሃሳቡ አለ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል፡-  እዚህ መጥተው ፓትርያርክ ይሁኑ ማለት አይቻልም፡፡ ታሪክ ይፋለሳል አምስተኛ ፓትርያርክ እያልን ኖረን ከ20 ዓመት በኋላ ወደ ኋላ መመለስ አይቻልም፡፡ ይህ አስቸጋሪ ስለሆነ ቀኖናውንም ታሪኩንም የሚጥስ ስለሆነ ነው እንጂ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ቦታቸው እንዳይመጡ የጠላ ማንም የለም፡፡ ሁሉም ሰላሙን ፈልጓል፡፡ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሃገር መጥተው በፈለጉበት ቦታ መቀመጥ ይችላሉ፡፡ ሰላሙ ተመስርቶ በውጭ የሚገኙ አባቶቻችን አዚህ መጥተው የመምረጥም የመመረጥም ዕድል ይኖራቸዋል፡፡

ዕንቁ፡- በጥቅምቱ ሲኖዶስ ማጠቃለያ ላይ እርስዎ በሰጡት መግለጫ የፓትርያርክነት ጉዳይ አምስት ብሎ ወደ ስድስት  እንጂ አራት የለም ብለዋል፡፡ ይህ መግለጫ ቀኖና ቤተክርስቲያንን የጠበቀ ነበር ? የእርቁ ሁኔታ መቀጠል እየተገባው ይህን መናገርዎ ሂደቱ ላይ አሉታዊ አስተዋጽኦ አይኖረውም ?

ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል፡-   በዚህም ተባለ በዚያ ችግሩን እኛ የፈጠርነው ሳይሆን ተፈጥሮ ያገኝነው ነው፡፡ የእኛም ድርሻ የማስተካከል ነው፡፡ ትኩረታችን በትክክለኛው መንገድ እንዲሄድ ማድረግ ነው፡፡
ዕንቁ፡- ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ እያሉ ሌላ ፓትርያርክ  መሾሙ ቀኖናውን አያፋልስም?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል፡-   ጥለውት ሲሄዱ እኮ ነው አቡነ ጳውሎስ የተሾሙት ፡፡ ያን ጊዜ የነበረው ክፍተት የፈጠረው ነው፡፡
ዕንቁ፡- በቅርቡ ለ3ተኛ ጊዜ የእርቀ ሰላም ሂደቱ እንዲቀጥል ወደ አሜሪካ አባቶች ተልከዋል፡፡ በቀጣዩ ጥር ወር አራተኛው የእርቅ ውይይቱ እስኪደረግ ድረስ በሁለቱም ወገን ምንም ውሳኔ እንዳይሰጥ ተስማምተዋል፡፡ በሀገር ቤት ያለው ሲኖዶስ ግን የቀጣዩን ፓትርያርክ ምርጫ ሕግ እያዘጋጀ ይገኛል፡፡ ይህ በአሜሪካ ከተላለፈው ውሳኔ ጋር አይጋጭም?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ምንም አይጋጭም፡፡ ሕግ ሕግ ነው፡፡ ሕግ መጻፍና ማጽደቅ ሰላምን ያጠነክራል እንጂ ሰላም የሚነሳ አይደለም፡፡ በፊትም ቢሆን የሕግ መላላት ነው እንጂ ሕጉ የጠበቀ ቢሆን እንዲህ ያለ ችግር ባልተፈጠረ ነበር፡፡
ዕንቁ ፡- የሽማግሌዎቹ የጋራ ስምምነት ደብዳቤ ምን እንደሆነ ለማወቅ ይቻላል? የደብዳቤው መንፈስ ምን ይመስላል?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ሽማግሌዎቹ ደብዳቤ ልከዋል ፤ የደብዳቤው መንፈስ ተቀራርበው እንደተነጋገሩና ለጥር 16 2005ዓ.ም ቀጠሮ እንደተያዘ  የሚገልጽ ነው፡፡  ስለዚህ እኛ ከዚያ በፊት ፓትርያርክ አንሾምም፡፡
ዕንቁ ፡ የእርቀ ሰላም ተደራዳሪ አባቶች ተወጋግዘው እንደነበር  ይታወሳል ፤ በዳላስ ቴክሳስ ድርድር በተካሄደበት ሰሞን  ግን አንድ ላይ ኪዳን አድርሰው  በጋራ ቀድሰውና ተመግበው ሲነጋገሩ  ነበር ይህ ሁኔታ ግዝቱን የሚሽር ነው ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- አብሮ መብላታቸውና አብሮ መጠጣታቸው ጥሩ ነው፡፡ አብረው ማስቀደሳቸውን እኛም ሰምተናል ፡፡ ይህም መልካም ነው በዚሁ ሁኔታው መሰረት ይይዛል እርቅ ይፈጸማል የሚል ተስፋ ሠንቀናል፡፡
ዕንቁ  ፡ -ግዝቱ ተነስቷል ማለት ነው?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- እነሱም አውግዘዋል እኛም አውግዘናል እንግዲህ አባቶች ሲገናኙ “እግዚአብሔር ይፍታህ” ከተባባሉ እኛም ስንገናኝ “እግዚአብሔር ይፍታህ” እንባባል ይሆናል
ዕንቁ ፡- ሁለታችሁም ውግዘቱን ያስተላለፋችሁት በሲኖዶስ ደረጃ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ውግዘቱ ሲነሳስ በሲኖዶስ ጉባኤ ተወያይታችሁ መሆን የለበትም ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ስለውግዘቱ አሁን ከእናንተ ሰማን እንጂ በተላከው ደብዳቤ ላይ ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም አልተገለጸልንም፡፡
ዕንቁ ፡- የምርጫ ሕጉ ሰነድ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ከሰሞኑ ደግሞ ረቂቁ እንደ አዲስ እንዲዘጋጅ ተወስኗል የሚባል ነገር ተሰምቷል እውነት ነው?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- እንደ አዲስ የተዘጋጀ ነገር የለም ፤ በቀረበው ረቂቅ ላይ መወያየት ሊኖር ይችላል፡፡ አንድ ደንብ ሲረቀቅ ተወያይቶ መልክ ማስያዝ ያለ ነው፡፡ ስለዚህም ውይይት ተደርጓል ፡፡ ይህኛው በዚያኛው ተሸሽሏል ስለሚባለው ግን ደንቡ በእጄ ሲገባ መናገር እችላለሁ፡፡
ዕንቁ ፡- በረቂቁ ላይ የእድሜና  የዜግነት ጉዳይ ተጠቅሷል ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ፍትሐ ነገስቱ ከ60 እስከ 80 ዓመት ዕድሜ ያለው ፓትርያርክ መሆን ይችላል ነው የሚለው፡፡ አሁን ከ55 ተነስቶ እስከ 80 እስከ 75ትም ሊሆን ይችላል፡፡ የታረመውን ይዞ ለመናገር የተስተካከለው ረቂቅ ተፈራርመንበት እጃችን አልገባም፡፡ እጃችን ሲገባ ስለ እድሜውም ስለ ዜግነቱም ጉዳይ ላስረዳችሁ እችላለሁ፡፡
ዕንቁ፡- የምርጫ ረቂቁ ሕጉ ለውይይት ይቀርባል?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- መምህራኑም ይሳተፋሉ ፤ ሁሉንም ያሳትፋል፡፡
ዕንቁ፡-የምርጫው ዕለት መቼ ይሆናል?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-  ያልተወሰነ ነው ለእናንተ በዚህ ቀን ነው ብዬ የማስተላልፍበት ጉዳይ የለኝም፡፡ ይህ የሲኖዶስ ውሳኔ ጉዳይ ነው፡፡
ዕንቁ ፡- ከሰሞኑ እየተካሄደ ባለው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ እስከ አሁን ምን ውሳኔዎች ተላልፈዋል ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ያስተላለፍነውን ውሳኔ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ እንጂ አሁን መግለጽ አልችልም ክልክል ነው፡፡
ዕንቁ ፡- እርቀ ሰላሙን በተመለከተ ከሰባት በላይ ማህበራት ለሲኖዶስ ጽ/ቤት የላኳው ደብዳቤዎች ለሲኖዶስ እንዳይቀርብ ተደርጓል የሚል አቤቱታ ከተለያዩ ወገኖች ሲሰማ ሠንብቷል ደብዳቤዎቹ ለሲኖዶስ ያልቀረቡት በምን ምክንያት ነው?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ለእኛ የደረሰን ምንም ደብዳቤ የለም ፡፡ ይህንን አሁን ከእናንተ መስማቴ ነው፡ አልደረሰንም፡፡
ዕንቁ፡- “ከፓትርያርኩ ምርጫ በፊት እርቀ ሰላሙ  መቅደም ይገባዋል” የሚሉ አባቶች አሉ በሚባልበት ወቅት ወደ ምርጫ ዝግጅቱ ያዘነበላችሁት በምን ምክንያት ነው?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ሕገ ደንብ መኖር አለበት፡፡ ሕግ መዘጋጀት አለበት ፤ የምርጫ ሕግ ደንብ ረቀቀ ማለት ፓትርያርክ ተመረጠ ማለት አይደለም ፤ ሕገ ደንቡ ይረቅና እንመልከተው አስፈላጊው ሁሉ ከተሟላ በኋላ ቅዱስ ሲኖዶስ ይወያይበታል  ፡፡ ሕገ ደንቡ መዘጋጀቱ ማንንም የሚጎዳ አይደለም፡፡
ዕንቁ ፡- ይህንን ጉዳይ ማንሳት የፈለኩት ረቂቁ የሚጸድቅ ከሆነ የእርቀ ሰላም ሂደቱን አያናጋውም ወይ ለማለት ነው ፤ በረቂቁ የሚሰፍረው መስፈርት  ሁሉንም ወገን ለምርጫ ዕጩነት የማያሳትፍ ቢሆን ችግር አይፈጥርም?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ሁሉንም ያካትታል ፤ ሰላም ከተፈጠረ ሁሉም የመምረጥም የመመረጥም እድል ይኖረዋል ብለን እናምናለን፡፡
ዕንቁ ፡- በውጭ የሚገኙ አባቶች መሀል ባልተወያዩበት የምርጫ ሕግ መቀበል የማይፈልጉ ቢኖሩስ ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-  ይምጡና እንወያያለን ያን ጊዜ የኛ ሕግ አንዱን የሚጎዳ  ሌላውን የሚያርቅ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ ለሰላም መሳካት ይምጡ እንጂ የሚጎዳ ነገር የለውም፡፡
ዕንቁ ፡- በእናንተ በኩል በውጭ የሚኖሩትን አባቶች በምርጫ ለማሳተፍ ዝግጁ ናችሁ ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- እንዴ ይምጡ እንጂ ደስ ነው የሚለን ሀገሪቷ ሰፊ ስለሆነች ለሁላችን ትበቃለች፤ አይደለም ለእኛ ለሌላም ትተርፋለች፡፡
ዕንቁ፡- የአቡነ መርቆርዮስ እንዳይመጡና እርቀ ሰላሙ እንዳይሳካ በአባቶች ላይ ከመንግስት ጫና እየደረሰ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ ፤ እውን ጫናው አለ ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-  በእኛ ላይ በፍጹም ምንም ጫና አልተደረገም፡፡
ዕንቁ፡- በቅርቡ ፕሬዝዳንት ግርማ ብጹ አቡነ መርቆርዮስ ከነሙሉ ክብራቸው መጥተው መንበራቸው ላይ ይቀመጡ የሚል ደብዳቤ ጽው ነበር፡፡ በማግስቱ ደብዳቤውን ሽረውታል ፤ በቀጣዩ ቀን ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡት የፕሬዝዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ “በውጭ የሚገኙ መጥተው በምርጫ ተወዳድረው ካሸነፉ ቦታው ላይ መቀመጥ ይችላሉ ብለዋል ፤ ይህ መሰሉ አስተያየት እንደ ጫና ሊታይ አይችልም ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-  እንደ እናንተ እኔም ሰምቻለሁ ደብዳቤውን ማየት ግን አልቻልኩም ፡፡ ደብዳቤው ለብጹእ አቡነ ናትናኤል ደርሷል፡፡ አቡነ ናትናኤል በማግስት መልስ ሰጡ ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ የሰጡት መልስ ምን እንደሆነ ግን አልሰማሁም፡፡
ዕንቁ፡- ስለዚህ ምንም ጫና የለም ነው የሚሉት  ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-  በመሰረቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላሙን ፈልጎታል ፤ እርቁን የሚያግደው ፤ ሰላሙን የሚገታው እስከሌለ ድረስ ሁላችንም ባለንበት ተጽናንተን  አምላካችንን በጸሎት እየጠየቅን ነው፡፡ አምላካችን የእኛን ጸሎት ሰምቶ የሚሰጠንን መልስ ብቻ መጠባበቅ ነው ያለብን፡፡ ሰላሙን ሁሉም ይፈልገዋል፡፡ ለሰላሙ ሁሉም ዝግጁ እየሆነ እየተጠባበቀ ነው ያለው ፡፡ ሰላማዊ አምላክ ሰላምን እንዲያወርድልን እንጠይቀዋለን፡፡ ከሰላም የበለጠ እግዚአብሔርን የሚያስደስት ሰውንም የሚጠቅም ነገር የለምና፡፡ ምዕመናንን ባሉበት ሆነው ሰላሙን እንዲጠባበቁ ካህናቱም በጸሎታቸው እግዚአብሐየርን እንዲጠይቁ እያልን መልእክታችንን ለህዝባችን ማስተላለፍ እንወዳለን፡፡
ዕንቁ ፡- ከጥር 16-18 ቀን 2005 ዓ.ም 4ተኛ ዙር የሰላ ውይይት ይካሄዳል፡፡ በዚህ ውይይት  ውጤት ካልተገኝ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የወደፊት እጣ ፈንታ ምን የሚሆን ይመስሎታል ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-  ሰላም ይገኛል ብለን እናምናለን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሚገጥማት ችግር ይኖራል ብለን የሚያሰጋን ነገር የለም፡፡ ሁላችንም ለሰላሙ ዝግጁ መሆን አለብን፡፡ እዚያም ያሉ አባቶች እዚህም ያለነው አባቶች  ለሰላሙ ቅድሚያ መስጠት ድርሻችን ይሆናል፡፡
ዕንቁ፡- አሁን በሁለቱም ወገን ቅድመ ሁኔታ ተቀምጧል ፤ ውጭ ያሉት አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው ሲሉ ፤ የሀገር ቤት ሲኖዶስ ደግሞ የአቡነ መርቆርዮስን ወደ መንበር መመለስ ሳይሆን ወደ ሀገር ቤት መመለስ ነው የሚቀበለው ? ይህ ቅድመ ሁኔታ ሳይነሳ እንዴት ሰላም ሊመጣ ይችላል     ? መፍትሄ ካልመጣ ምን የሚከሰት ይመስሎታል ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-  ሰላሙን የፈለገ ሰው ይምጣ ፤ ጉዳዩ ፓትርያርክ የመሆንም አይደለም፡፡ በመሰረቱ እኛ መጥተው መቀመጥ አለባቸው የሚለው እናንጸባርቃለን፡፡ ፓትርያርክ ይሁኑ በሚለው ዙሪያ እኔም ሲኖዶሱም ከ20 ዓመት በኋላ ወደ ኋላ መመለስ የለበትም ነው የምንለው፡፡ መምጣታቸውን እንፈልጋለን፡፡ በክብር እናስቀምጣቸዋለን ፤ የሚደረገው ሁሉ ይሟላል ፤ የፓትርያርክነቱን ስልጣን ጉዳይ የሚወስነው ግን በቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ነው የሚሆነው፡፡
ዕንቁ ፡- እርቀ ሰላሙ ቀድሞ አንድ ላይ አንድ ላይ ሆነው በጋራ አይተው ሕጉን ማጽደቅ አይቻልም ነበርን?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-   ይምጡ ይምረጡ ይመረጡ ብለናል፡፡
ዕንቁ፡- እርቀ ሰላሙ ሳይቀድም ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-   ታዲያ ምን ቸገረን ? እርቀ ሰላሙን በጥር ቀጥረናል፡፡ ከተፈለገ ተወያይቶ እርቁ የሚያልቅበት መንገድ ይፈጠራል፡፡
ዕንቁ፡- ጥር ላይ እርቀ ሰላሙ በሰላም ከተፈታ የምርጫ ሕጉ እኛ ባለንበት እንደገና ይረቀቅ የሚሉ ከሆነ ተቀባይነት ይኖረዋል?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-  ይምጡና እንነጋገራለን ይህ አያጣላንም፡፡
ዕንቁ ፡- በተለይ 3ተኛው የቴክሳስ ዳላስ የእርቅ ጉባኤ በምዕመኑ ዘንድ ትልቅ ተስፋ ፈጥሯል፡፡ ለቤተክርስቲያኒቱም ትልቅ ተስፋ ተብሏል ፤ እርቀ ሰላሙ ይሳካል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ?
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-    ይሳካል ብያለሁ እናተም ጸልዩ እኔም እጸልያለሁ
ዕንቁ ፡- ብጹእ አባታችን ስለሰጡን ቃለ ምልልስ በጣም አመሰግናለሁ
ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡-    እኔም አመሰግናለሁ ተባረኩ፡፡

11 comments:

  1. abatachin Kalehiwot yasemaln

    ReplyDelete
  2. ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ፡- ሰላም ይገኛል ብለን እናምናለን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሚገጥማት ችግር ይኖራል ብለን የሚያሰጋን ነገር የለም፡፡ ሁላችንም ለሰላሙ ዝግጁ መሆን አለብን፡፡ እዚያም ያሉ አባቶች እዚህም ያለነው አባቶች ለሰላሙ ቅድሚያ መስጠት ድርሻችን ይሆናል፡፡

    ReplyDelete
  3. አባታችን ስለቁጥር ማስተማር ትተው ፍቅርና ቀኖናንን ለምን አይሰብኩም
    መንፈሳዊነትና ብልጠት አብሮ አይሄድም

    ReplyDelete
    Replies
    1. you are right. I was thinking , they dont have to go back to number four after five, but what if abune Merkorios is called the 6th. if abune merkorios and his followers said he should have the siltan and called the 4th, then that is the problem.

      Delete
    2. የአቡኑ መልስ ሺርውድ የሆኑ የፖለቲካ ሰዎች የሚሰጡት መልስ እንጅ በአንድ ጳጳስ አንደበት የሚሰጥ በሐቅ ላይ የተመሠረተ አይመስልም። በእውነት በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግሥት እጅ የለበትም ብሎ ማን ነው የሚያምነው ? ምን አለ እውነቱን ቢመሰክሩ ? አየ ምን አይነት ዘመን ነው የደረስነው ! ለእውነት መናገር ማን አርዓያ ሊሆንነን ነው ? የማንን ዐሰረ ፍኖት ነው ልንከተል የምንችለው ? እኔን የሚያሳስበኝ እምነቱንና የእምነቱ መርዎች ነን ብለው በተቀመጡት መካከል ያለውን ልዩነት የማይረዱ ምዕመናን ፤ የእምነቱ መሪዎች ችግር ብቻም ሳይሆን የእምነቱ ተቋምም መሠረታዊ ችግር ነው እያሉ ለሚያታልሉት መናፍቃንና ኢአማንያን ስብከት ተጋልጠው ቤተ ክርስቲያኒቱን እየጣሉ እንዳይሄዱ ነው። ለዘመናት ያደረጉት ጥረት በዚህ ሁኔታ ዛሬ እየተሳካላቸው ነው ።

      Delete
  4. ayeee ....
    "Alsheshum zor alu" ale yagere sew ...

    ReplyDelete
  5. Abet ante FETARI sintun chilehal. yhe ===Endayamah tiraw - Endayibela gifaw==== ayinet yenigigr beshita medihanitu min yihon. Lhulum EGZIABHER Yirdan!

    ReplyDelete
  6. abatachine,what are you doing? Mengawen betinachihu lesiltan tirotalachihu...Yasazinal!Lemegist agobededachihu...

    ReplyDelete
  7. Ten karate abat yebetekristianitun ber atenkrew yitebkuln
    Abatachin.

    ReplyDelete
  8. Abune Hizikeil Bereketo Yidiresen yeminagerut Hulu Melkam New Firhat Yelebotim Hakun Asikemtsewtal Bete Kiristiyan Atichegerim Yeminichegerew Egaw Nen Yalut Tikikil New Yibertu Patiriyarik Yimert- Abune Merkorewosim Bekibir Ykemeteu- Selam Yifetser Yetesasatut Neger Zema Bet Neberku Yalutin New Zemawin Enkan Lega Yitewt Yalot Ewket Ybekal Zemenaw Neger Bimaruma Melkam Neber Zema Yigelebitsalu Ayawkum Yemilot Bizu Sew New Esat Radiyo Siteyikot Yemisetsut Melis Gin Yasidesital Wede Hala Ayilum Abune Pawlosin Kemotu Behala Mewkeis Endemayigeba Yastemarun Erso Not Ene Patiriyark Bihonu Ewedalehu

    ReplyDelete
  9. Lelaw zim yibel abatochachin tenegagrew endekow sira hewn yisru

    ReplyDelete