- “እረኞች ሆይ ፦ የበጎቻችሁን ምክር ስሙ”
(አንድ አድርገን ታህሳስ 12 2004 ዓ.ም)፡-በአሁኑ ሰዓት ፓትርያርክ ለመሾም የሚደረገውን ጥድፊያ “አንድ አድርገን”
አጥብቃ ትቃወማለች ፤ለ20 ዓመት የቆየውን መከፋፈል ወደ ሌላ ደረጃ የሚያሻግር ስራ መስራት ከታሪክ ተወቃሽነት አያድንም ፤ ህዝቡ
መጀመሪያ እርቀ ሰላሙን ይቅደም የቤተክርስቲያኒቱን አንድነት ይመለስ ከዚያ የፓትርያርክ ምርጫው ይደረስበታል የሚል አቋም በያዘበት
በአሁኑ ወቅት አባቶች የምርጫ ህጉን እንደዚህ አጣድፈው የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለመሰየም የሚያደርጉት ጉዞ አንድም ለራሳቸው ሁለተኛም
ለቤተክርስቲያን ሶስተኛም ለምዕመኑ ጥሩ አካሄድ አለመሆኑን አውቀው የያዙትን አቋም ቢያንስ እስከ እርቀ ሰላሙ ፍጻሜ ድረስ ቢያቆዩት
መልካም ነው የሚል አስተያየት አለን ፡፡ ይህን አካሄድ ለመቃወም ፌስቡክ እና ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች በቂዎች ናቸው ብለን
አናስብም ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ከ500ሺህ ባልዘለለበት ሁኔታ ነገሩን በድህረ-ገጾች እና በፌስቡክ ላይ
ተደራሽ ከማድረግ በተጨማሪ ምዕመኑ ሁኔታው አውቆ እና ተረድቶ በግልጽ በአካል የሚቃወምበት ሃሳቡን የሚገልጽበት መንገድ ራሱን በማደራጀት
ማመቻቸት መቻል አለበት ፡፡ ኢንተርኔት ኢትዮጵያ ውስጥ 2 በመቶ ተደራሽ አለመሆኑን ልናውቅ ይገባል ፤ ይህ ጉዳይ ከምናወራውና
ከምናስበው በላይ ከባድ የሆነ ችግር ይዞብን እንደሚመጣ መገመት መቻል አለብን ፡፡ ባለፈው 20 ዓመት እሮሮ ሳይበቃ ወደ አዲስ
እሮሮ መሸጋገር መቻል የለብንም ፤ ሌላ የገማ እንቁላል ሲወረወር መመልከት መቻል የለብንም ፤ ቤተክርስቲያን አሁን የሚያስፈልጋት
ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት አንድነቷ ነው ፡፡ ባለፉት 16 መቶ ክፍለ ዘመናት ከግብጽ በመቶ አስራ አንድ አባቶች አንድነቷ አደጋ
ላይ ሳይወድቅ መመራት ችላለች ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት በንጉሰ ነገስቱ እና በወቅቱ በነበሩ አባቶቻችን የጳጳስነት እና የፓትርያርክነት ስልጣን ወደ ኢትዮጵያውያን ከተመለሰ በኋላ
በአንድነት የማያስቀጥላት ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡
አሁን ያሉት አባቶች ይህን እድል ሳይጠቀሙበት ቀርተው ቀጣይ ፓትርያርክ ምርጫ እንዲከናወን ከፈቀዱና አስመራጭ ኮሚቴ
ካለጊዜው ከሰየሙ ከባለፉት አቡነ መርቆርዮስን መንግስትን በመፍራት እና አቋም በማጣት ያደረጉትን ከፍተኛ ስህተት እየደገሙት መሆኑን
ይረዱ ፤ በየአህጉረ ስብከታቸው ከቤተክርስቲያኒቱ አንድነት በፊት
ራሳቸውን ለወንበር ለማብቃት ውስጥ ውስጡን ብዙ ገንዘብ አፍስሰው እና ሰዎችን ቀጥረው እግዚአብሔር እንደሚመርጥ ፍጹም ዘንግተው
የቅስቀሳ ስራ እየሰሩ ያሉ አባቶችም ቢሆኑ ከዚህ ስራቸው ወደ ኋላ ካላሉ ስራቸውን አደባባይ ከማውጣት ወደ ኋላ አንልም ፡፡ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የሚገኙ ስለ ቤተክርስቲያን ግድ የሚላቸው ምዕመናን
ይህን መልካም አጋጣሚ በከፍተኛ ሃላፊነት ይገባኛል ብሎ ለብጹአን
አባቶች ከምርጫው ይልቅ ሰላሙን አስቀድሙ ብሎ ጥያቄውን ማቅረብ ካልቻለ ነገ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ለሚፈጠሩት አለመግባባቶች እና
ወደ ሌላ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ያለውን ልዩነት የራሱን አስተዋጽኦ ማድረጉን መረዳት መቻል አለበት ፡፡ ይች ቤተክርስቲያን የጳጳጳሳት
ብቻ አይደለችም ፤ የመነኮሳት ብቻ አይደለችም ፤ የቀሳውስም ብቻ አይደለችም ፤ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች ብቻም አይደለችም
፤ የምዕመኑም ብቻ አይደለችም ፤ ቤተክርስቲያን የሁላችን ናት ፤ በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ሁላችን እንደ ደረጃችን እኩል ያገባናል
፤ የባለፈውን ስህተት ዳግም ሲሰራ እያየን ዝም ማለት መቻል የለብንም ፤ ምዕመኑ በየአህጉረ ስብከቱ ከታች እስከ ላይ ያለውን ምዕመን
በማስተባበር በግልጽ ድምጹን የሚያሰማበት መንገድ ሊያመቻች ይችላል ፤ ነገሩ “ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ” እንዳይሆን አሁን ስለ ቤተክርስቲያን
ብለን አቋም ሊኖረን ይገባል ፤ ዝምታችን ገደብ ሊኖረው ይገባል ፤ ይህን ጉዳይ ከፌስቡክ እና ከድረ-ገጽ ዘገባነት በማውረድ በተግባር
ስራ የምንሰራበት ድምጻችንን የምናሰማበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡
የቤተክርስቲያን ጉዳዩ ሁላችንንም ያገባናን
demsachinin masemat enjemir!!!!!
ReplyDeleteአባት እና ልጅ
ReplyDelete=========
ልጅ አባቱን ቢክደው እንቢ አሻፈረኝ ቢለው ፤
አባት ነው ልጅ ? እኮ ማነው የሚጐዳው ።
አባት በልጅ ቢያዝን ፣ ልጅም ቢያዝን ባባት፤
ከቶ በማን ፣ ለማን ይደርሳል ጉዳት ።
እንዲያው ፣ መለኪያ ቢኖረው ለሃዘን ፤
የየትኛ ትካዜ ይበልጥ ይሆን ቢመዘን ።
ልጅ አባቱን ባይሰማ ፣ አባት ልጁን ቢቆጣ ፤
ልጅም ባባቱ ቢያዝንና ቤቱን ለቆ ቢወጣ ።
ልጅ ስብርብር ቢል ቢሆን ቆማጣ ፤
ማን ነው ጥፋተኛ ለሚመጣው ጣጣ ።
የአባት ፍቅሩ አይሎ ፣ ና በእኔ ዳን ልጄ ብሎ ፤
ይኸው ስጋየን ብላ ደሜን ጠጣ ብሎ አባብሎ ።
ልጅ እንቢ መዳን አልፈልግም ካለው ፤
አባት ወይስ ልጅ ? ለዚህ ቂመኛ ማነው ።
አባት ደግሶ ሊድር ልጁን ፤
እልፍኝ አስጥሎ አጽድቶ ደጁን ።
ካልታረቀው ልጅ አባቱን ፤
ማን ሊመርቅ ነው ዘሩን ፤
በምድር የዘራውን ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር።
ከብርሃኑ መልአኩ
So powerful poem. Egziabhere yagezen eski.
DeleteThis is a good way.
DeleteGod Bless you Andadrgen .you did good job as usuall
ReplyDeletewe have to unite to our religion unity .This is the best time
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ReplyDeleteውድ የአንድ አደርገን ድረገጽ አዘጋጆች ለምታደርጉት ጥረት እግዚአብሔር እርሱ ባወቀ ብድሩን ይክፈላችሁ። ባዜናችሁ ላይ እናንተ ባላችሁ መረጃ መሰረት አንዳንድ ጳጳሳት የእግዚአብሔርን ታላቅነትና ታጋሽነት ዘንግተው ራሳቸውን ለሕገወጥ ፓትርያርከነት እንዳጩ በደፈናው እየነገራችሁን ነው።
ለምሳሌ “በየአህጉረ ስብከታቸው ከቤተክርስቲያኒቱ አንድነት በፊት ራሳቸውን ለወንበር ለማብቃት ውስጥ ውስጡን ብዙ ገንዘብ አፍስሰው እና ሰዎችን ቀጥረው እግዚአብሔር እንደሚመርጥ ፍጹም ዘንግተው የቅስቀሳ ስራ እየሰሩ ያሉ አባቶችም ቢሆኑ ከዚህ ስራቸው ወደ ኋላ ካላሉ ስራቸውን አደባባይ ከማውጣት ወደ ኋላ አንልም”
እንደ ሚዲያና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይነታችሁ የናንተ ተግባር እነዚህን ፀረ-ቤተክርስቲያን ስማቸውን ከነሙሉ ምግባራቸው አሁኑኑ ለምእመናን በማሳወቅ የእምነቱ ተከታይ የሆነው ምእመን ቤተክርስቲያኑን እንዲጠበቅ ማድረግ ነው እንጂ ዛሬ የተድበሰበሰ መረጃ ማውጣት ብቻውን ምእመኑን የበለጠ ውዥንብር ውስጥ ሊከተው ይችላል። ለነኚሕ የቤተክርስቲያን ፀሮችም ስማቸውና ምግባራቸው አሁን እስካልተገለጸ ደረስ የልብ ልብ ይሰማቸዋል።
እናንተ የድርሻችሁን ስትወጡ ፈጣሪያችን ደግሞ ከተናቁት ምእመናን መካከል ለቤቱ ጠባቂ ራሱ ያስነሳል።
ፍሬሰንበት!!
We have to know the name of those govt supported papasat we should protest them not just only on the coming sunday it should be every sunday so tell us their name please.do not Hide them they should know that we know them.include their picture if possible.
ReplyDeletespecialy those of who are working now in the electoral committe.
ውድ ኢት/ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች በሙሉ በሀገር ቤት ያሉት አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያኒቱን የአንድነት እና የሰላምጉዳይ ክድጡ ወደማጡ እየወሰዱት ይገኛሉ። የሰላም ልኡካኑ የተስማሙባቸውን ጉዳዮች አለማጠበቃቸው በጣም የሚገርም ነገር ነው። ከእንዲህ አይነት ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደባሰ ችግር የሚወስድ ምርጫ እነዚህ አባቶች ምን ሊያተርፉበት ነው ።
ReplyDeleteበጣም አላበዙትም እንዴ ከእንግዲህ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ የነሱ ብቻ መሆኑ ማብቃት አለበት እላለሁ። ሁላችንም የሰላም እና የአንድነት ጉባኤው ያቀረብልልን ሀሳብ ተግባራዊ በማድገር የድርሻችንን እንወጣ።
በጸሎትም በርትተን ስለቤተ ክርስቲያናችን ሰላም እንጸልይ።
Asking questions are really nice thing if you are
ReplyDeletenot understanding anything totally, except this post presents good understanding
even.
Feel free to visit my blog post GFI Norte