(አንድ አድርገን ታህሳስ 3 2005 ዓ.ም)፡- የዛሬዋን ቀን ለማክበር እና ከእመቤታችን በረከት ለመቀበል በታእካ ነገሥት
በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን አቃቢ መንበር ብጹእ አቡነ ናትናኤል
፤ ብጹእ አቡነ አረጋዊ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ ፤ ብጹእ አቡነ ስምኦን የምስራቅ ወለጋ
ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብጹእ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ከአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራ የመጡ በርካታ ዲያቆናት ቀሳውስት መነኮሳት እና ምዕመናን በአሉን ለማክበር በቦታው
ተገኝተዋል፡፡
በግቢው እንደደረስኩኝ አንድ አባት ስለ በአሉ ምንነት ለምን እንደምናከብር በሰፊው ትምህርት ሲሰጡ ደረስኩኝ ፤ በመቀጠልም
እመቤታችንን ተማጽነው እና ለምነው ስለታቸው የደረሰላቸው እምባቸው
የደረቀላቸው ፤ ጸሎታቸው የተሰማላቸው የሶስት ምዕመናንን ስለት ለምዕመኑ ተነገረ ፡፡ አንዲት እህታችን እንዲህ በማለት ምስክርነቷ
ሰጥታለች “የኤች አይቪ ቫይረስ ተይዤ ነበር ፤፡ ከዶክተሮችም መድሃኒቱን እንድትጀምር ተነግሮኝም ነበር ፡፡ ነገር ግን “መድሀኒቴም
ይሁን ሕይወቴ እግዚአብሔር ስለሆነ መድሃኒቱን አልጀምርም በጸሎት በጾምና በስግደት እድናለሁ እፈወስማለሁ” በማለት በርካታ ገዳማት
እየሄድኩኝ ከበሽታው እግዚአብሔር እንዲፈውሰኝ ጸሎት አደረኩኝ ፤ ለልጆቼ እንድኖርላቸው ከዚህ በሽታ አድነኝ ብዬ ተማጸንኩኝ ፤
ሞልቶ ከሚተርፍ ተርፎ ከሚቀር እድሜ አትንፈገኝ በማለት ለመንኩኝ ፤ አንገት የማታስጎነብስ
ልመናን የምትሰማ ወደ እመቤታችን ጸበል በማምራት ጸበሏን ጠጥቼ እና ተጠምቄ ከበሽታዬ ነጻ ልወጣ ችያለሁ” በማለት በአውደ ምህረት
ላይ ምስክርነቷን ሰጥታለች ፡፡
ሁለተኛዋ ምስክር “ከጓደኞቼ ጋር ከስራ በአንድ ላይ ተባረርን ፤ ግራ ገባኝ ጨነቀኝ ፤ የማደርገው ነገር ጠፋኝ፡፡ ከጓኞቼ ጋር ከስራ ስንባረር እነርሱ ጠበቃ ቀጥረው ፍርድ ቤት ክስ መሰረቱ
፤ እኔ ግን ጠበቃዬን እግዚአብሔርን እና እመቤታችንን አድርጌ ወደ ቤተ መቅደሱ መጥቼ እመቤቴን ተማጸንኩኝ ፤ ለእኔ ግን ጠበቃዬ ሰው ሳይሆን እመቤታችን ናት በማለት በጸሎት በቤተመቅደስ በመገኝት ለመንኳት ፤ እባክሽን ጠበቃ ሁኝልኝ
፤ እባክሽን ችግሬን ፍቺልኝ ብዬ ተማጸንኳት ፤ ጓደኞቼ ጠበቃ ቀጥረው እስከ አሁን ድረስ ይከራከራሉ እኔ ግን በእናቴ ጠበቃነት
ችግሬ ተፈትቶልኛል ፤ በዚህ ጉዳይ ያልተከፈለኝን የ5 ወር ደመወዝ ከእነ ጥቅማ ጥቅሙ በእሷ
አማላጅነት ተከፍሎኛል ፡፡ እኔን የተለመነች እናት እናንተንም ትለመናችሁ፡፡”
በማለት የተደረገላትን ነገር በአውደ ምህረት መስክራለች፡፡
በመቀጠልም አንድ ወልደ
ማርያም የሚባል ወንድማችን ” በስራዬ ላይ ከባድ ጥፋት ደርሶብኝ ነበረ ፤ በእመቤቴ በእለተ ቀኗ በቤተክርስትያን በመገኝት አልቅሼ
ነገርኳት ፤ የለመንኩት ነገር አንዳች ሳይጓደል ስራዬ እንደ ቀድሞ ተመልሶልኛል ፤ ለክብሯ መግለጫ 5ሺህ ብር ይዤ መጥቻለሁ በማለት
ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ ጸሎታቸው የተሰማላቸውን ሰዎች ምስክርነት
ቢጻፍ ብዙ ሰዎች ይማሩበታል የደከመም ይበረታበታል ብሎ በማሰብ በማሰብ እናንተ ዘንድ እንዲህ አድርሰናል፡፡
መልካም በዓል ይሁንላችሁ
እነርሱን የተለመነች እመቤታችን እኛንም ትለመነን .. አሜን
Kale hiewt yasemalegn Endezi ayenet negeroch betame asefelagi selehonu please bertu
ReplyDeleteEgeziabhere Aserat Adergo Lemebetachen ysetaten Ethiopian Yetebkate
Amen tilemenen. Melkam Ye Emebetachin Beal yihunilin.
ReplyDeleteEthiopia - የእመቤታችን አስራት.
ReplyDeleteAMEN
ReplyDeleteGood job. God bless your work!
ReplyDeleteእነርሱን የተለመነች እመቤታችን እኛንም ትለመነን - አሜን
ReplyDeleteእመቤታችን እኛንም ትለመነን።
ReplyDeleteከልጅዋ ከወዳጅዋ ታማልደን።
አሜን።
lenesu yetelemench Emamilake Egnanem telemenen Amine
ReplyDeleteEgziabher yekber yemesgen yezare wore gedema bekbad chenk west neberkuj enam amleji beyamldechej cenki tefta yene yamaldech enantem tlemenachu.
ReplyDeleteአሜን እናታችን ትለመነን እግዚአብሄር ይባርካችሁ
DeleteDear bloggers and readers, I have no experience of writing on blogs but usually I read from them. I dare to write today mainly to thank MK and this blog writers. I saw what has been written in anti- orthodox blog such as Aba selama. They are showing "ejig mern yelekeke tilacha" and effort to change our church to protestant. I didn't know a lot about those "tehadiso" group and why they were condemned and got ride from the church. Now it is very clear for me and I ask all other to help MK and fight these groups. All the trash that they are writing is a copy of protestant ideology, so they just want to use the name orthodox and write their trash against our church. Shortly, I am writing this to express my appreciation and show support to MK who are struggling to protect our chruch from this "hod aders". I know now with who your are struggling and whom you are defeating by exposing them one by one with evidences. The next step should be getting ride of so called Abune Markos; he is doing same job like aba selama bloggers that is why they are showing him his support. Down to those kehadis and dil for MK. Your sister Lulit.
ReplyDelete