Wednesday, December 5, 2012

ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ ደብዳቤ ጻፉ


  •  “የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ለሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ” ደብዳቤውን እንዲያውቁት የተባሉት መስሪያ ቤቶች
  •  ከስልጣኔ ውጪ ነው ያደረኩት ፤ በችኮላ የተጻፈ ደብዳቤ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ፤ በስሜትና በችኮላ የሆነ ነገር ነው ፤ ስለ ሰራሁት ስህተት አቡነ ናትናኤል ይቅርታ አድርጌልሃለሁ ብለውኛል” ፕሬዝዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ
  •  “ይህ የእናንተ ጉዳይ አይደለም አያገባችሁም” አቃቢ መንበር አቡነ ናትናኤል

(አንድ አድርገን ህዳር 27 2005 ዓ.ም)፡-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አራተኛ ፓትርያርክ ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ ከነሙሉ ክብራቸውና ማዕረጋቸው ወደቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ የሚጋብዝ ከኢትዮጵያው ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ደብዳቤ መጻፉ ተሰማ፡፡ 


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አባቶች መካከል ቀኖና ተጣሰ በሚል ምክንያት በሁለቱ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት በሰሜን አሜሪካው የሰላም ኮሚቴው አስተባባሪነት ሶስተኛውን የእርቀ ሰላም ድርድር ረቡዕ ህዳር 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ዳላስ ውስጥ መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ለዚህው እርቀ ሰላም ጉባኤ ከአዲስ አበባው  ፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ ገሪማ የልዑካኑ መሪ፣ ፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ አባል፣ ፫ኛ/ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ አባል ፬ኛ/ ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ በጸሐፊነት  የተወከሉ ሲሆን ከአሜሪካው ሲኖዶስ ፩ኛ/ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የልዑካኑ መሪ፣ ፪ኛ/ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ አባል፣ ፫ኛ/ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ አባል ፬ኛ/ ሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ በጸሐፊነት ተወክለዋል፡፡ የዳላሱ ጉባኤ ከመጀመሪያው የዋሽንግተን ጉባኤ ለየት የሚያደርገው አባቶች አብረው ጸልየውና አብረው ማዕድ ቀርበው የጀመሩት ጉባኤ በመሆኑ  ተስፋ ሰጪ ነው ተብሏል፡፡ “ውግዘት” የሚለው አልፈው አብረው በአንድ ማዕድ መቀመጣቸው እና አንድ ላይ ጸሎት ማድረጋቸው በዋነኛነት ሁለቱም ወገኖች ለሰላሙ መሳካት ፍላጎት እንዳላቸው ፤ ቀጥሎም የሰላምና የአንድነት ጉባኤውን ጥረት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ትላንት ህዳር 26  የተጀመረው የሰላም ጉባኤ አባቶች የሚነጋገሩበት ጉዳይ እና የሚደርሱበት የስምምነት ሃሳብ ምዕመኑ በከፍተኛ ተስፋ የሚጠብቀው ጉዳይ ሆኗል ፡፡ ይህ ደግሞ በዛሬ እና በነገ የሚታይ ውጤት ይሆናል፡፡
 የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን አባቶች የእርቀ ሰላም ውይይት በሰሜን አሜሪካ ዳላስ ቴክሳስ

ይህ በእንዲህ እያለ ማክሰኞ ህዳር 25/03/2005 ዓ.ም በፕሬዝዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ስምና ፊርማ ከቤተመንግስት የሚቀጥለው ደብዳቤ መውጣቱ ታውቋል፡፡ 
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ባሉበት
ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ
የተጻፈው ደብዳቤ በአጭሩ…
ቅዱስነትዎ አራተኛው ፓትርያርክ ሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መሾሞ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን በወቅቱ በተከሰተው ሁኔታ ምክንያት ቅዱስነትዎ ከሀገር መውጣት ምክንያት እና በምትኩም ፓትርያርክ ተሹሞ መቆየቱ ግልጽ ሆኖ ሳለ  በምትኩ የተሾሙት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል ፡፡  ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ህልፈተ ህይወት ቀጥሎ ስለ ፓትርያርክ መሾም በተመለከተ ጉዳዩ ተነስቶ የሀገር ሽማግሌዎችና የእምነት ተከታዮች “ለቤተክርስቲያኒቱ አንድነት ሲባል ሌላ ፓትርያርክ መሾም የለበትም ፤ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ መንበራቸው ከሙሉ ክብራቸውጋር መመለስ አለባቸው ፡፡ ተከፋፍሎ የነበረውም ቅዱስ ሲኖዶስ ወደ አንድነት መምጣት አለበት” ተብሎ በቀረበው የሀገር ውስጥ ሽማግሌዎች ሀሳብ መሰረት እኛ ሀሳቡን ሙሉ ለሙሉ ተቀብለነዋል ፡፡  ቅዱስነትዎ ይህን ሃሳብ ተቀብለው ልዩነቱን በማጥበብ በቤተክርስቲያናችን አንድነትና ሰላም እንዲሰፍን በቅዱስነትዎ የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ ይዘው ወደ ሀገርዎ እና ወደ ቤተክርስቲያንዎ እንዲገቡ ይህን ደብዳቤ ጽፈናል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
ፕሬዝዳትን ግርማ ወ/ጊዮርጊስ
የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት
ፊርማ እና ማህተብ
እንዲያውቁት
  • ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ
  •  ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
  •  ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር
  •  ለሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር
ግልባጭ
  •     ለኢንጂነር አራጋው ጥሩነህ የሚመራው የሽማግሌዎች ቡድን
        አዲስ አበባ
የአርበኛ አባቶች ማህበር መሪ ሊቀ ትጉሃን አስታጥቄ እና ኢንጂነር አራጋው ጥሩነህ እና ሌሎች የሽማግሌ ቡድን የሚመራው አካል ፕሬዝዳንቱ ጋር በመቅረብ የቀድሞ ፓትርያርክ በአቶ ታምራት ላይኔ ሴራ አማካኝነት ከሀገር እንደተሰደዱ እና በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስቲያኒቱ በሁለት ሲኖዶስ እንደምትመራ በመወያየት ይህም አግባብ አለመሆኑን በመናገር ይህን ደብዳቤ ከፕሬዝዳንቱ ስልጣን ውጪ እንዲጻፍ አድርገዋል፡፡ ክቡር ፕሬዝዳንት አቶ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለቪኦኤ የአማርኛው ድምጽ በመጀመሪያ ደብዳቤው ከእሳቸው ቢሮ በእሳቸው ማህተብ እንደወጣ እና በኋላ ግን የተሰጣቸው ስልጣን ይህን ለማድረግ እንደማይፈቅድላቸው ሲገነዘቡት እንደገና ደብዳቤው ከተበተነበት እንዲሰበሰብ እንዳደረጉ ተናግረዋል ፡፡
ከፕሬዝዳንት ግርማ አንደበት
“ያ ደብዳቤ ስህተት ሆኖ ስለተገኝ እንዲመለስ ብለናል ፤ የሆነ ሆኖ ይህ የመንግስት ትዕዛዝ አይደለም የግለሰብ ሀሳብ ነው ፤ በእኔ በኩል Contradict አድርጌዋለሁ ፤ ከስልጣኔ ውጪ ነው ያደረኩት ፤ በችኮላ የተሰራ ስራ ስለሆነ ትቼዋለሁ ፤ በስሜትና በችኮላ የሆነ ነገር ነው ፤ በሰዎች ሀሳብ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ደብዳቤ ነው ፤ ሌላ ችግር እንደሚያመጣ አላገናዘብኩኝም    በመጀመሪያ አቡነ ናትናኤል ናቸው የተቃወሙት ፤ አቡነ ናትናኤል “ይህ የእናንተ ጉዳይ አይደለም አያገባችሁም” አሉን ፤ አቡነ ናትናኤልን በስልክ አግኝቻቸው ነበር እና “ይቅርታ አድርጌልሀለሁ” ብለውኛል” በማለት ለቪኦኤ ጋዜጠኛ ለአቶ አዲስ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡

የአንድ አድርገን ሃሳብ
እስከ አሁን ያሳለፍነው ጊዜ ማብቂያው በተቃረበበት ወቅት የምንሰጣቸውን አስተያየቶች የምንጽፋቸውን ሃሳቦች እርቀ ሰላሙ ላይ የሚያመጣውን እንቅፋት እንዳይኖር ልንጠነቀቅ ይገባል ፡፡ ይህ እርቀ ሰላም እንዲሳካ የሚፈልጉ በርካታ ምዕመናን እንዳሉ ሁሉ እኛን ከማይመስሉ ከወዲያ ግድም የቆሙ እርቀ ሰላሙ ቢፈጸም ጥቅማቸውን የሚነካባቸው ሰዎች እርቀ ሰላሙ በሰላም እንዳያልቅ የበኩላቸውን የማሰናከያ ጥረት እንደሚያደርጉ ልንዘነጋ አይገባም ፡፡  ከሽማግሌ ነን ባዮች ጀርባ ማን እንዳለም ለመገመት ያስቸግራል ፤ ለህዝበ ክርስቲያንና ለቤተክርስቲያን በማይጠቅም አካሄድ  ፓትርያርክ ለማስቀመጥም ውስጥ ውስጡን የሚሰሩ ስራዎች እንዳሉም እናውቃለን ፡፡ በማወቅም ሆነ  ባለማወቅ የሚደረጉ እንቅፋቶችን ቀድመን ልንከላከል ያስፈልጋል ፡፡ 
አሁን ይህ ደብዳቤ ከቤተመንግስቱ ራሳቸውን የሽማግሌዎች የሰላም አፈላላጊ ኮሚቴ ብለው በመሰየም ትልቅ እይታ ለማግኝት በፕሬዝዳንቱ በኩል ደብዳቤ ሲያጽፉ በመጀመሪያ የተቃወሙት እና “እናንተ ይህ ጉዳይ አያገባችሁም” ብለው ቀጥተኛ ምላሽ የሰጡት አቃቢ መንበር አቡነ ናትናኤል መሆናቸው ደስ ያሰኛል፡፡ በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያን ስለ ውጫዊ ተፅህኖ በፊት ለፊት የሚጋፈጥ አባት ያስፈልጋታል፡፡ በጉዳዩ የማያገባውን አካል በግልጽ “አያገባህም” ተብሎ ሊነገረው ይገባል፡፡  የዛሬ 20 ዓመት መንግሥት ያን ሁሉ ሴራ ቤተክርስቲያን ላይ ሲዶልት እና ሲሰራ እንደ አቡነ ናትናኤል “አያገባህም” ብሎ የሚናገረው አባት በግልጽ ቢኖር ኖሮ እኛም 20 የችግር ፤ የጎጠኝነት ፤ የዘረኝነት ፤ ያለመግባባት ፤ የመከፋፋል ፤ የሁለት ፓትርያርክና  የሁለት ሲኖዶስ ጊዜ ባላሳለፍን ነበር፡፡ ጊዜ ቢወስድም አንድ መሆናችን እንደማይቀር እናምናለን ፤ አሁንም ቢሆን አባቶች ይህን እግዚአብሔር ቤተክርስቲያኒቱ አንድ እንርትሆን ያመጣውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መንግሥት በማንኛውም ሰዓት ስለ ቤተክርስቲያን ፤ ስለ ቀጣይ ፓትርያርክ እና መሰል የማያገባው ጉዳይ ላይ ገብቼ አስታራቂ ሃሳብ ልስጥ ቢል ሲኖዶሱ በአንድ ድምጽ እንደ አቃቢ መንበር አቡነ ናትናኤል “አያገባህም” ብለው መናገር መቻል አለባቸው ፡፡ 
አቃቢ መንበሩ እንደ አንድ የሃይማኖት አባት ከፕሬዝዳንት ግርማ ጋር ስለተጻፈው ደብዳቤ በመወያየት ያደረጉላቸው ይቅርታ እጅጉን ደስ የሚያሰኝ ነገር ሆኖ አግኝተነዋል ፡፡ ፕሬዝዳንቱም የሰሩት ስራ አግባብ አለመሆኑን ተረድተው ስህተታቸውን አሜን ብለው መቀበላቸውም ጥሩ ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ግርማ ቀኝ ግራውን ባለማስተዋል የ20 ዓመቱን ታሪክ ወደ ኋላ ሄዶ ባለመቃኝት  በሰዎች ገፋፊነት የ20 ዓመትን ክፍተት በትንሽ ደቂቃ ንግግር ለመፍታት የጻፉት ደብዳቤ  እርቁ ላይ ሌላ ጥላ ሳያጠላ በአስቸኳይ እንዲሰበሰብ ማድረጋቸው  መልካም ነው ፡፡ ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት ይህ የአንድ ሰው ሃሳብ እንጂ የመንግሥት አለመሆኑን ተናግረዋል ፤ መንግሥትም ለሕገ-መንግሥቱ ተግባራዊነት በተጀመረው እርቀ ሰላም ዙሪያ እጁን ባያስገባ ለህዝብ ፤ ለቤተክርስቲያን ፤ ለሀገርና ለመጪው ትውልድ ፍጹም ሰላም ጥሩ ነው የሚል አስተያየት አለን፡፡

በአሜሪካ በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል የተጀመረውን እርቀ ሰላም ጫፍ ያደርስልን ዘንድ የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ይሁንልን፡፡
ቸር ሰንብቱ   



“አንድ አድርገን”

7 comments:

  1. I will see this news from two sides.

    1) our president is one of the officials in the current government. Whether he retract his words back or not, it shows the interest of the "Government" to make changes of the old philosophy (or at least agree that there was some mistake in the past). I wish the government can clearly say one thing: "The government accepts the decisions by the Synod in Addis Ababa, i.e whether Abune Merkorios or new patriach"


    2) Evenif our president's view is very nice (which I always wanted it to happen), but going further and telling us, there are no fathers who deserve the place, bla bla is nonsense. For me, people should stop judging at this moment. The fathers will elect a new father if that is the last decision, following spritual steps.

    The news is already out there, can we just use this for the better of the peace and reconcillation process not for "ፀጉር ስንጠቃ". May GOD be with us in the whole process.

    ReplyDelete
  2. በእውነት አባታችን አቡነ ናትናኤል እንደዚያ ብለው ከሆን በጣም ያስደስታል ነገር ግን ይህ የፖለቲካ ፍጆታ እንዳይሆን እፈራለሁ ምክንያቱም መንግስት ጣልቃ እየገባ ነው እየተባለ ስለሆነ "ጣልቃ እንግባ ብንል እንኳን ማድረግ አንችልም ቤትክርስቲያን ትከለክለናለች" ብሎ ለማስመሰል የተጠነሰሰ ሊሆን ይችላላ:: ሰዎቹ ለመሆኑ በሀገር ላይ ማድረግ የፈለጉትን ማንን ፈርተው ይተዋሉና አቅም ካላጡ በቀር:: እግዚአብሔር መልካሙን ሁሉ ያድርግልን አሜን!

    ReplyDelete
  3. GoD bless you our president you are not only ethiopian president but also the ethiopian orthodox church president just like his majesty.

    ReplyDelete
  4. The presidents decision to write to Abune Merkorios emanates from his innocent
    heart that bleeds for two decades.What is in the presidents head and heart is clear.he has shown us his stance in clear terms.Similarily ,I appreciate Abune
    Natnaels advice telling him that case belongs to the church.we should learn to say others if they appear in the forthcoming.God Himself will never leave us
    alone at this messed up days and poisoned environment.He will do His part.We
    should do our part.May God send His mighty hands to help us.

    ReplyDelete
  5. Sewyew Argitewal Pirezdant Girma Malete new Negerun Yeserut Leke Tiguhan Astatsike Yetebalut Gondere Nachew Adenkachewalehu Yigermal Yidenkal Lemhonu Sinodosu Sayawk Abune Merkorewos Yigibu Malet Min Malet New ? Abune Natnaeil Ahun tikikil nachew Degimo Abune Merkorewos Digam Mewedader Yichilalu Bilo Yetenagerew Asefa kerto yeman Miemen New ? Alawaki Sami ----Yilekelkal

    ReplyDelete
  6. አቡነ መርቆሬዎስ በህይዎት አሉ፤ መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸው ስልጣን ነው፤ ከሃገር የወጡት ተገፍተው ነው፤ ሕዝባቸውን በሙያቸው እያገለገሉ ናቸው።
    ታድያ ለምን ሌላ ፓትርያርክ መምረጥ አስፈለገ? እግዚአብሔር ያረመውን እኛ እንዳናበላሽ እናስተውል።
    አቡነ መርቆሬዎስ ፈቃደኛ ከሆኑና በቀራቸው የእድሜ ዘመን መንጋውን ለመጠበቅ ፈቃደኛ ከሆኑ:-
    ፩ ወደ ኢትዮጵያ ይግቡ፣
    ፪ ማእረጋቸው ፬ኛው ፓትርያርክ እንደሆነ ይጠበቅ፣
    ፫ አሜሪካ ከ፬ ባላነሰ አህጉረ ስብከት ትከለል፣
    ፬ ቃለ አዋዲ በመላው የውጭ አገር ላሉ የኢኦተቤክ ባስቸኳይ ይሰራጭ፣
    ፭ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ከሙስናና ከዘረኝነት ባስቸኳይ ትንጻ፣
    ፮ ስራችን ሁሉ ክርስቶስን ይምሰል፤ ቅድስትና ብጽእት ማርያምን እናስብ፥ የመላይክትን አገልጋይነት እንይ፥ ጻድቃንና ሰማእታት ትተውልን እንዳለፉ ጠብቀን እናስተላልፍ።

    ReplyDelete
  7. Negeru Melkam Nebere Abune Merkorewos Wede Botachew Yimelesu ( Gonder Tesebisibo Yigiba )1 Abune Melketsedek 2 Abba Weide tisae 3 Mr Lieule Kal 4 Kesis Melaku Baweke Yemesaselut Menafikan Abirew Megibatachew New Malet new ? Ahun Diridiru yeleyelet Ayimesilim Menafikan Simelesu Mesitekakel yalebet neger yelem wey ?

    ReplyDelete