Thursday, December 27, 2012

የአቶ ስብሀት ነጋ ቅዥት





  • “ስብሓት ነጋ ቤተ ክርስቲያን ልትበታተን እንደምትችል አስጠንቀቁ!!”  ሀራዘተዋህዶ


(አንድ አድርገን ታህሳስ 18 2005 ዓ.ም)፡- “ስብሀት ነጋ ቤተክርስቲያን እንደምትበታተን አስጠነቀቁ” በማለት አንድ ጽሁፍ ሀራ ዘተዋህዶ ላይ አነበብን ፤ አቦይ ስብሀት  ቤተክርስቲያኒቱ ሃገራዊ ግዴታዋን ስትወጣ የነበረች፣ ለወደፊቱ ታላቅ ሚና ሊኖራት የሚችል ስለኾነች አሁን የት አለች ብለን እናስብ በማለት የአቡነ ጳውሎስ ሞት በኋላ በቤተክህነት አዳራሽ በተቀመጠው ደብተር ላይ ጽፈዋል ፤ ሰውየው አንዳንድ ጊዜ እንደ ነብይ ያደርጋቸዋል ፤ አንዳንዴ ደግሞ በትህምክት ባህር ውስጥ የሰመጡ ትህምክተኛ ሆነው ሳለ “ትምክተኞች” ብለው መናገር ይዳዳቸዋል ፤ አንዳንዴም አይምሮውን ያጣ ሰው ይመስል የሚናገሩትን ነገር አያውቁትም ፤ ሌላም ጊዜ ደግሞ አንደበታቸው ከጭንቅላታቸው የቀደመ አዛውንት ሆነው ያገኙቸዋል ፤ አልፎ አልፎም ፕሮፈሰር መስፍን እንዳሉት “ቂል የያዘው ሰይፍ” አይነት ሃሳብ በማንሳት የማህበረሰብ መነጋገሪያ ሆነው ያገኟቸዋል፡፡ ትልቅ አዛውንት ብለው እንዳያከብሯቸው የወረደ እና የዘቀጠ በ21ኛው ክፍለ ዘመን መነሳት የሌለበት ሃሳብ ሲያነሱ ያገኟቸዋል ፤ ቀላል ብለው እንዳይንቋቸው ደግሞ አምላክ እድሜ ሰጥቶ ሁለት ጸጉር እንዲያወጡ አድርጓቸዋል ፤ ታዲያ እኝን ሰው ምን እንበላቸው ?
የዛሬ ዓመት ግድም በቤተክርስትያናችን አባቶች ላይ የከፈቱት የስም ማጥፋት ዘመቻ የምናስታውሰው ነው፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ፍቃድ ሰጥቶት በተሰጠው ፍቃድ የሚንቀሳቀስን መንፈሳዊ ማኅበር ሲሳደቡ ለሰማቸውና ጽሁፋቸውንም ላነበበ ሰው እኝ ሰውዬ ምን እየሰሩ ? ጤነኛ ናቸውን ? ነው ብሎ መጠየቁ አይቀርም፡፡ አሁን ደግሞ ብለው ብለው የወደፊት እጣ ክፍላችንን ሊነግሩን ይዳዳቸዋል ፡፡ ሰውየው ኢሕአዴግ ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ አዲስ አበባ የገባበትን ግንቦት 20 ሲያከብር ልጆቻቸውን `FREE ERITREA` የሚል ቲሸርት ህዝቡን ለማናደድ ሆን ብለው ለብሰው በአደባባይ እንዲወጡ ያደረጉ ሰው ናቸው፡፡ ይህ አይነት ድርጊት ከጤነኛ ሰው መጠበቅ የሚከብድ ይመስለናል ፤  ሰውየው በትጥቅ ትግሉ ከፍተኛ ቦታ ያላቸው የኢህአዲግ የፖለቲካ መሀንዲስ እስከ መባል የደረሱ ሰው ናቸው ፤ በቅርቡ የሞቱት ጓዳቸው መሀንዲስነቱን ቢወስዱባቸውም ፤  አሁን ደግሞ ብለው ብለው ስለ ቤተክርስቲያን መጻኢ እድል ሊነግሩን ይፈልጋሉ ፤ “ቤተክርስቲያን ከአቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ ልትበታተን ትችላለች” በማለት ሃሳባቸውን አስፍረዋል ፤ ይህን ሀሳባቸውንም ሀራ ዘተዋህዶ ብሎግ ላይ ሰፍሮ ተመልክተናል ፤ ራሱን በ70 እና በዚያም በዘለለ እድሜ ላይ የሚገኝ የሚናገረውንና የሚሰራውን ስራ በአግባቡ የማያውቅ ሰው ስለ ቤተክርስቲያን ቀጣይ እጣ ክፍሏ አፉን ሞልቶ መናገር አይችልም ፡፡

እሳቸውን የመሰሉ የጫካ አጋሮቻቸው ከ20 ዓመት በፊት በቤተክርስቲያናችን ላይ ሸፍጥ ታጥቀው ነገ አልታይ ብሏቸው እጃቸውን በእኛ ጉዳይ ባያስገቡ ኖሮ የዛሬ ችግሮቻችን ባልተፈጠሩ ነበር ፡፡ የዛሬው 20 ዓመት የለኮሱት መከለፋፈል አልበቃ ብሏቸው አሁንም ቤተክርስቲያኒቱን ወደ ሌላ የማያባራ ክፍፍል ውስጥ ለመክተት የራሳቸውን ሰዎች በመመደብ ስራቸውን እየሰሩ እንደሚገኙ እናውቃለን ፤ አብዮታው ዲሞክራሲን የተጠመቀ ጳጳስ የእነሱን መስፈርት የሚያሟላ ጳጳስ መንፈስ ቅዱስ በሚመራው በቅዱስ ሲኖዶስ የሚታጨው በአንድ አምላክ የሚመረጠው ፓትርያርክ ራሳቸው ለመሾም ስራ እየሰሩ እደሆነ መናገር የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል ፡፡ ታዲያ በየትኛው መለኪያ ነው አቦይ ስብሃት የእኛን እጣ ክፍል የሚነግሩን ? ፡፡ ሀገርኛ ብሂል “ከሰደበኝ የነገረኝ” እንደሚባለው ሁላ እሳቸው እንዲህ ማለታቸው ሳያንስ እንዲህ አሉ ብሎ በብሎግ ላይ ሚዛን የማይደፋ ውሀ የማያነሳ ወሬ ማንሳት ተገቢ አይደለም፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት “ማህበረ ቅዱሳን አቋሙን ለወጠ” አሉን ዛሬ ደግሞ…..እንዲህ ይሉናል፡፡ 

ብዙዎች ከአንድነት ይልቅ ክፍፍሉ ፤ ከብርሐን ይልቅ ጨለማው  ቀድሞ የሚታያቸው የአመለካከትም ሆነ የእይታ ችግር ያለባቸው ሰዎች አሉ፡፡ “መንገዱ ሳስበው ሳስበው ደከመኝ” ብለው ሳይጀምሩት ባሉበት ቁጭ ብለው ያልዘሩትንና ያልደከሙበትን ማጨድ የሚፈልጉም አሉ፡፡  እኛ ግን ተስፋ እናደርጋለን ፤ አሁን ያለው ሁለት ሲኖዶስ በቅርብም ይሁን በሩቅ አምላክ በፈቀደ ጊዜ አንድ እንደሚሆን ፤ ተስፋችንን በአምላካችን ላይ በማድረስ አንድነትን ከላይ እንጠብቃለን ፤ አባቶቻችን ምዕመኑ እና ቤተክርስቲያኒቱ የቆመችበትን ቦታ በማስተዋል ለሁሉም የሚጠቅመውን እርቅ ያስቀድማሉ ብለን እንገምታለን፡፡ ትውልድ ስማቸውን በጥሩ ያነሳቸው ዘንድ የተበላሸን ታሪካችንን ያስተካክላሉ ብለንም ተስፋ እናደርጋለን ፡፡  አሁን ብዙ ቦታ የሚከፋፍል ሀሳብ ሳይሆን የሚያስፈልገው አንድ የሚያደርግ ፤ ክፍተትን የሚያጠብ ፤ ጉድለትን የሚሞላ ሃሳብ ብቻ ነው፡፡ እንደ አቦይ ስብሀት ህልም አይሉት ቅዥት ዝም ብሎ መናገርም ሆነ በብሎግ ላይ መፃፍ  ዋጋ የለውም ፤ እኛንም አንድ አያደርገንም፡፡ 

ኩርሲዎች “የእናት ሞት እያደር ይቆረቁራል” ይላሉ ፡፡ እኛም የቤተክርስቲያናችን ሁለት ቦታ ሆና ወደፊት እያደር እንዳይቆረቁረን በማሰብ ይህን አጋጣሚ መጠቀም ግድ ይለናል፡፡ የሚጠቅም ሀሳብ በማንሸራሸር የማይሆነውን ደግሞ ወደ ኋላ በማለት ለአንድነታችን እንትጋ፡፡


“አመልህን በጉያ ስንቅህ በአህያ” ብለው የድሮ አባቻችን በአንዲት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ፤ በአንዲት  እምነታቸው በተዋህዶ ላይ የመጣባቸውን ነገር ለመመለስ “ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት” በማለት አንድነታቸውን ያሳዩ ነበር ፤ ሰአሁን እኛም የሚያስፈልገን ነገር የውስጥ ችግሮቻችንን ወደ የሚፈቱበትን ወቅ በማሻገር  የውጭውንና ዋናው የአንድነት ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ሃሳቦች እንጂ ከዚህም ከዚያም የተለቃቀሙ ወሬዎች መሆን መቻል የለባቸውም ፤ ስለዚህ ትልቁ ነጥብ ላይ ጥላቸው እስካላጠሉ ድረስ ትንንሾቹን የምታገስበት አካሄድ መከተል መቻል አለብን
  
አመልህን በጉያ ስንቅህ በአህያ” ብለው የድሮ አባቻችን በአንዲት ሀገራቸው ኢትዮጵያ ፤ በአንዲት  እምነታቸው በተዋህዶ ላይ የመጣባቸውን ነገር ለመመለስ “ክተት ሰራዊት ምታ ነጋሪት” በማለት አንድነታቸውን ያሳዩ ነበር ፤አሁን እኛም የሚያስፈልገን ነገር የውስጥ ችግሮቻችንን ወደ የሚፈቱበትን ወቅ በማሻገር  ዋናው የአንድነት ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ሃሳቦች እንጂ ከዚህም ከዚያም የተለቃቀሙ ወሬዎች መሆን መቻል የለባቸውም ፤ ስለዚህ ትልቁ ነጥብ ላይ ጥላቸው እስካላጠሉ ድረስ ትንንሾቹን የምታገስበት አካሄድ መከተል መቻል አለብን
 

በመጨረሻም አንድ የጋሞ ተወላጅ የአቦይ ስብሃትን ጽሁፍ አንብቦ ከጨረሰ በኋላ በባህላችን አንድ አባባል አለ  “ቱሌይ ካሴ ኤሪያይስ ዩጤሽ” ፡፡ ምን ማለት ነው? ብዬ ስጠይቀው፡፡ “መሀይም ሁሌም የሚያውቀውን ይዘፍናል” እንደ ማለት ነው አለኝ፡፡ 




ቸር ሰንብቱ

8 comments:

  1. We know Sebhat nega very well.Please do not raise
    him up as if he is a man of principle.when we talk
    about him we are giving him importance.We have seen
    him that he does not act his age.We lack words to explain his deep-rooted ignorance.On top of that he
    is not normal.he is very sick.He is insulting our
    religion.Our church taught him Amaric alphabet.he
    does what devil is doing.Leave him

    ReplyDelete
  2. ብዕሩ ዘ-አትላንታDecember 27, 2012 at 7:32 PM

    “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን”
    መቼም ዶሮ ስታልም ያየ ህልሟንም የነገረችዉ ሰዉ የለም። ህልሟንም የፈታላት ሰዉ እንዳለ ተነግሮ አይታወቅም። መስሎ መናገር ነገርን ለማጽናት ይጠቅማልና አበዉ ተናገሩ። ድመቷን ዉሮ ምን ታልሚያለሽ ቢሏት ሳንባ እንዳለችዉ እንደማለት። አቶ ስብሐትም ምን ያልማሉ ቢባሉ መበታተን ቢሉ መቸም አይገርምም። አቶ ስብሐት ነጋም እንደ ዶሮዋ ህልም ተረት ቢወሰዱ የተሻለ ነዉ። እርሳቸዉ የጫካ ዉስጥ ንግርታቸዉ የለቀቃቸዉ አይመስልም። ከተማም ገብተዉ መሰልጠን ያልቻሉ የዕድሜ ባለጸጋ ማስተዋል የጎደላቸዉ የአእምሮ ደሃ ስለመሆናቸዉ በተገኘዉ አጋጣሚ በሚደሰኩሩት ረብ የለሽ ንግግራቸዉ ይታወቃሉ። ሽበትማ ድንጋይም ይሸብታል። ኢትዮጵያን የመሰለች ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገር ለመበታተን በብሔር ቋንቋ ነግደዉ ባይሞላላቸዉ ኢትዮጵያዊነትን በምላት የያዘችዉን ተቋም ለመበተን ሃያ ዓመታት በመሀል ሀገር፣ አሥራ ሰባት ዓመታት በጫካ ፤በጥቅሉ ለሰላሳ ሰባት ዓመታት የተደከመበትን ህልም ዛሬ ቢናገሩ የሚደንቅ የሚገርም አይሆንም። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እኮ እንደርሳቸዉና መሰሎቻቸዉ እቅድማ ቢሆን ኖሮ አባ መርቆሪዮስ ተሰደዉ አባ ጳዉሎስ በተተኩ ማግስት ጉዳዩ ተሳክቶ ነበር። የሚያሳዝነዉ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ርስቱ ግዛቱ እንደሆነች አለማወቃቸዉ ነዉ።
    ለሰዉ ልጅ ዕድሜ ተቋም ነዉ ብዙ ይማሩበታል። በዕድሜ ካካበቱት ልምድ ተምረዉ ያስተምሩበታል። ታዲ ያ አቶ ስብሐትን ምን ነክቷቸዉ እንዲህ በአደባባይ ማበድ የጀመሩት። “እብድ ቢጨምት እስከ እኩለ ቀን ነዉ” እንዲሉ በነፍጥ የጨመቱ ስልጡን ባይ ድስኩረኛ እየተደፋፈሩ ያሉት አርባ ሚሊዮን ምእመን በያዘች ተቋም ላይ መሆኑን ለአፍታም አለመገንዘባቸዉ ነዉ። ቤተ ክርስቲያናችን በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኮራ እምነትን ከታሪክና ከኢትዮጵያዊነት ጋር እንዳስረከበችን ልብ ሊሉ ይገባል። እርሷን ስናጣ ሀገራችንን እንደምናጣ የምናወቅ የቁርጥ ቀን ዘጎች ስላለን እጆቻቸዉን ቢሰበስቡ የተሻለ ነዉ። ከብዕሩ ዘ-አትላንታ

    ReplyDelete
    Replies
    1. አቶ ብዕሩ ዘ-አትላንታ ፍጹም ኢትዮጵያዊ ለሆነ አስተያየትዎ የተዋህዶ እራስ የባህርይ ሊቀ ካህናት መድህን አለም ክርስቶስ ጸጋውን ያብዛሎት:: ለማለት የፈለኩትን በሙሉ ስላሉት ከርሶ ጽሁፍ አንድ ነገር ብቻ መድገም ፈልጋለሁ::
      **ቤተ ክርስቲያናችን በኢትዮጵያዊነታችን እንድንኮራ እምነትን ከታሪክና ከኢትዮጵያዊነት ጋር እንዳስረከበችን ልብ ሊሉ ይገባል። እርሷን ስናጣ ሀገራችንን እንደምናጣ የምናወቅ የቁርጥ ቀን ዘንጎች ስላለን እጆቻቸዉን ቢሰበስቡ የተሻለ ነዉ።**
      ውሃምኮ እሳት ሲበዛበት ድስት ይከፍታልና.... የስከዛሬው ዝምታ ብዚያው ይቀጥላል ብለው አስበው ከሆነ ተሳስተዋል:: የሚነሳው ማዕበል ጠራርጎ ቀይ ባህር ነው የሚከታቹ:: ለዚህም ትምክህታችን በዘመናዊ ጦር በታንክና አውሮፕላን ተደራጅቶ የመጣውን ግዙፍ የጣሊያንን ጦር በጦርና በጎራዴ በቻ መክተው እንዲመልሱት የረዳቸው እራሱ ባለቤቱ ነውና, ቆም ብለው ቢያስቡበት የተሻለ ነው:: እባካቹ እጃችሁን ከቤተክርስትያን ላይ አንሱልን ::::::
      ተዋህዶ ለዘለዓለም ትኑር:: ይነጋል ምሽቱ - ከሲያትል ዋሽንግተን::

      Delete
  3. Qiletam werada shimagile new!!!

    ReplyDelete
  4. አሁን ፍንትው ብሎ እየታየ የመጣው ነገር
    ፩ኛ በወያኔ ጦስ የደጋፊያቸው ጥጋብ መታገሻው
    ፪ኛ በቆብ ዘረኝነት የናወዙት መነኮሳት ባልዋሉበትና ምንኩስና እና በማያከብሯት ቤተ ክርስቲያን ላይ እንደንጉስ ተጀንነው የሚኖሩበት ጊዜ ማብቃቱን ነው::
    አገራችን በሚጠሏት ቤተ ክርስቲያናችን በሚያናንቋት ሁለቱም ጠላቶቻቸው ከላይ ፊቅ፣ ቁጢጥ ብለው በሚገዙአቸው ጠላቶቻቸው እየደረሰባቸው ያለው ግፍና መከራ ከመስፈሪያው በላይ በመሆኑ ግፉ ተትረፍርፎ በልጆቿ ላይ ኃዘኑና ለቅሶው በዝቷል:: ለቤተ ክርስቲያን ከሚያለቅሱላት መካከል በዱር በገደሉ መከራውን ታግሰው የሚኖሩት ጋዳማውያንና የቤተ ክርስቲያኒቱን የወደፊት አካሄድያሳሰባቸው ጥቂት አረጋውያን ጳጳሳት እና መነኮሳት ጭምር እንደሆኑ ልብ እንላለን:: ይሁን እንጅ ቤተ ክርስቲያንን የሌባ ዋሻ ያደርጓት አባ ጳውሎስ ከሞታቸው በኋላ እንኳ ቤተ ክርስቲያን ቀን እንዳይወጣላት ከሳቸው በባሰ ፈተናዋን አብዝተው አዘጋጅተውላት አልፈዋል:: በሳቸው የተሾሙትም ወይ አብነቱ ወይ ዘመናዊ ትምርቱ የለ እንዳው በብልጠት አመሷት:: አሁን ግን ቤተ ክርስቲያን የመነኮሳት መቀለጃ የሆነችበት ቀን የተቃረበ ይመስለኛል:: ምንኩስናንም የምናስከብርበት ጊዜ ላይ የተቃረብን ይመስለኛል:: ምንኩስናም ሕጉንና ደንቡን ፈጽሞ ይፈጸማል ሳይማሩ ዓለቃ መሆን ዝምብሎ አባት ነኝ እያሉ ባልወለዱት ህዝብ ላይ መቀለድ መብቃት ያለበት ጊዜ ላይ ነን:: ላልወለዱት ልጅ አባት ለመሆን እኮ መብሰል ያስፈልጋል የልጁን አለመወለድ ምክንያት አድርጎ ከሚመጣም ፈተና ለመዳን ማወቅ ማስተዋል ያስፈልጋል ለዚህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶ ች የድሮዎቹን አብነት ማድረግ ስለሚያስፈልግ ያልተማረ መነኩሴና ካህን ከመሾም ሁሉ ልንድን ነው:: ጠላታችን ድንቁርና በኛው ሰዎች ተጭኖ ከመሃላችን ገብቶ እያጠፋን ነው ይልቅስ እንዋጋው አለማወቅ ያጠፋናል:: የተማሩት እና የተመሰከረካቸው መነኮሳትና ካህናት ደግሞ የሚገባቸውን ቦ ታ ይሰጣቸው እንበል::

    ReplyDelete
  5. ውድ አንድ አድርገን። ሕዝቡ ሌላ ሌላውን ትቶ እግዚአብሔር በዕጣ ይምረጥልን ቢል የሚያስማማ አሳብ ይመስለኛል። አሁን የተያዘው ብዙውን ሰው ግራ ስላጋባ የሚጠቀመው ክፍል በሕግ ሆነ ያለሕግ ከመንግሥት አጀንዳ ጋር የተስማማው ክፍል ነው። ሰሞኑን ይህን አስፈንጣሪ አግኝቼ ላክሁላችሁ። በርቱ። አዚ ነኝ ከዳላስ። http://www.ethiopianchurch.org/essay1/150-%E1%8D%93%E1%89%B5%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%AD%E1%8A%AD-%E1%89%A0%E1%8B%95%E1%8C%A3.html

    ReplyDelete
  6. im going to pray that everything would work out!!!!

    ReplyDelete
  7. enantem ke poletics wetu!!ande adregen belachu yemetawerut selemekefafel new!

    ReplyDelete