- መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር አዲስ አበባ የሚኖሩ የደብረወርቅ ተወላጆችን “አቡነ ማርቆስ ደብረወርቅ ላይ ልማት በመጀመራቸው ተቃውመው ነው የመጡት” በማለት በርካታ ምእመናን በተሳሳተ አጀንዳ ቢያሰባስብም፣ ጉዳዩ ሃይማኖታዊ መሆኑን ስለተረዱ ይቅርታ ጠይቀው ተመልሰዋል።
- አቡነ ማርቆስ የቀረበባቸው ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ በደል ባሻገር በልማድ “ቅባት”ና ተዋህዶ በመባል ተከፋፍሎ የሚኖሩት የሀገረ ስብከቱ ምእመናን ርስበርሳቸው የሚያጋጩ ሥራዎች በመስራት ላይ መሆናቸው ጠቅላይ ቤተክህነትንና መንግስትን አሳስቧል።
- አቡነ ማርቆስ የገዟቸው ቤቶች (በአዲስ አበባ ሁለት፣ በግንደ ወይንና ሻሸመኔ) የሃብት ምንጫቸው የቤክህነቱን ትኩረት ስቧል።
- ምዕመኑ ከ116 ገጽ የድጋፍ ፊርማ ጋር አቤቱታውን አብሮ አቅርቧል
- ጠቅላይ ቤተክህነቱ አጣሪ ኮሜቴ ወደ አገረስብከቱ ይልካል።
ክፍል ሁለት
(አንድ አድርገን ታህሳስ 2 2005ዓ.ም) አቡነ ማርቆስ በሃገረስብቱ
ላይ ያደረሱትን በደል ባለፈው በክፍል አንድ (ክፍል አንድ ለማንበብ ይህን የጫኑ ) ጽሑፍ ማስነበባችን ይታወቃል። ይህን ተከትሎ ርቱዓነ ሃይማኖት የሆኑ የሃገረስብከቱ
ምዕመናን በቤተክረስቲያኗ መዋቅር የስልጣን ተዋረድ መሰረት ለጠቅላይ ቤተክህነቱን የአስተዳደር ዘርፍ ምክትል ሥራአስኪያጁን አቶ
ተስፋዬ ውብሸት ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ከም/ሥራ አስኪያጁ ጋር የምእመናን ተወካዮች ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ምንጮቻችን ዘግበዋል።
በውይይቱ ወቅት ም/ሥራ አስኪያጁ “ የቤተክርስቲያንን ማንነትና ክብር የሚያስጠብቅ እስከሆነ ድረስ ችግሩን የማንፈታበት ምክንያት
የለም” ማለታቸው ተሰምቷል። በቀጣይ አጣሪ ኮሚቴ ወደ ሀገረስብከቱ እንደሚላክና ያሉትን ማስረጃዎች ለአጣሪ ኮሚቴ እንዲያቀርቡ አሳስበዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸበር የደብረወርቅ
ተወላጅ የሆኑ በአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ በተለይ ደግሞ በታላቋ በደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም “ውሉደ አርከ ሥሉስ ዘደብረወርቅ የአብነት
ትምህርት ቤቶች ማጠናከሪያ ማኅበር” አባላትን በተሳሳተ አጀንዳ “ የመጡት እናንተ የጀመራችሁትን የልማት ሥራ ለመቃወም እና አባ
ማርቆስ ለደብረወርቅ ትኩረት ለምን ሰጡ?” ብለው ነው በሚል ሸውከኛነቱ በሚያሳጣ መልኩ ከምእመናን ተወካዮች ጋር ለማጋጨት የሞከረ
ቢሆንም በሁለቱም በኩል ባሉ በሳል ምእመናን አማካኝነት ውይይት በማድረግ ጉዳዩ የጋራቸው መሆኑን ተግባብተዋል። የተወሰኑትም “በሃገር
ልጅነት ብቻ” እና በተሳሰተ አጀንዳ አቡነ ማርቆስን እንዲደግፉ በመጠራታቸው አዝነው ወደ ስራ ቦታቸው መመለሳቸውና የቀሩት ደግሞ
ጥያቄውን ከምእመናን ተወካዮች ጋር ማቅረባቸው ታውቋል። ይህ መንፈሳዊ ማኅበር ቀናዒ አባት ካገኘ በደብረወርቅ ብሎም በሃገረስብከቱ
የሚገኙ አብነት ትምህርት ቤቶች ችግር መቅረፍ እንደሚችል ይታመናል።
ውሉደ አርከ ሥሉስ ዘደብረወርቅ የአብነት ትምህርት ቤቶች ማጠናከሪያ ማኅበር ካሰሩአቸው 19 የተማሪዎች ቤቶች መካከል
ከስብከተ ወንጌል መመሪያ ሃላፊነቱ በተጠረጠረበት ኑፋቄ የተወገደው አእመረ አሸብር በ1992 ዓ.ም በኑፋቄው ቅዱስ ሲኖዶስ
ቀኖና ሰጥቶት ከመቀሌ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ተባሮ እንደነበርና የሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ የነበሩት አቡነ ዘካርያስ “ቀኖናውን
ፈጽሟል” የሚል ደብዳቤ ለኮሌጁ በመጻፍ ያቋረጠውን ትምህርት ተመልሶ የጨረሰ ሲሆን በሃገረ ስብከቱ ታዋቂ የቅኔ መምህር የነበሩትን
መርጌታ አሥራትንና 24 ደቀመዛሙርቶቻቸውን እንዲሁም በቅዱስ ማርቆስ ይማሩ የነበሩ 12 ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ወደ መናፍቃን
ጎራ እንዲቀላቀሉ አድርጎአል። በአካባቢው ፕሮቴስታንቶች ዘንድ “የወንጌል ወታደሩ” በመባል ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት መናፍቅነቱን
አጋጣዊዎችን በመጠቀም በግልጥም በስውር እያራመደ እንደሚገኝ ማስረጃዎች ያሳያሉ።
መጋቤ ብሉይ አእመረ አሸብር
ምእመናኑ ያቀረቡት አቤቱታ ከጠቅላይ ቤተክህነት ምንጮቻችን ደርሶናል እንደሚከተለው እናቀርበዋልን
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ቀን፡- ኅዳር30/2005 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣
ከሁሉም በፊት የሀገረ ስብከቱን
ምእመናን አቤቱታ ለመስማት በመፍቀዳችሁ በእግዚአብሔር ስም እያመሰገንን እኛ በሀገረ ስብከቱ በተለይም በደብረ ማርቆስ ከተማና አካባቢው
የምንኖር የቤተክርስቲያን ልጆች በሀገረ ስብከቱ የተከሰቱትንና እየተከሰቱ ያሉትን ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ችግሮች ለመፍታት ከብፁዕነታቸው
ጋር የመንግስት ከፍተኛ የአመራር አካላትንም በመጨመር ተደጋጋሚ ውይይት ለማድረግ የሞከርን ቢሆንም ብፁዕነታቸው በሚያሳዩት አባታዊ
ያልሆኑ ንግግሮች ውጤታማ ሊሆን አልቻለም፡፡ እኛም የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ተሰባስበን በመወያየት የቤተክርስቲያኒቱን እሴት የሚያንኳስሱ
ክንዋኔዎች፤አሠራሮችና ሁኔታዎች ከዕለት ዕለት እየበዙ በመምጣታቸው ጉዳዩን ለቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል ለቅዱስ ሲኖድስ ሰላማዊና
ተቋማዊ መዋቅሩን በጠበቀ መልኩ ይኸው ዛሬ ለማቅረብ ተገደናል፡፡
ምክንያቱም፡-
í) በሀገረ ስብከታችን እየተከሰቱ ያሉ
አስተዳደራዊና ሃይማኖታዊ ችግሮችን ከምንጩ ለማስረዳት፤
î) አሁን የተከሰቱትና እየተከሰቱ ያሉት
ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ችግሮች ምንም መፍትሔ ሳይበጅላቸው በዚህ አካሄድ ከቀጠሉ ለሀገረ ስብከታችን እና ለመላ ቤተክርስቲያናችን
ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ሊያስከትል የሚችል በመሆኑ ከወዲሁ መፍትሔ እንዲፈለግበት፤
ï) ሀገረ ስብከታችን ልዩ ትኩረት የሚያስፈልገው
“ከቅባት” ጋር የተገናኙ ችግሮች ያሉበት በመሆኑ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችንና መላ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ልዩ ትኩረት እንዲሠጡት
ለማስገንዘብ ሲሆን ብፁዕነታቸው አቡነ ማርቆስም በተደጋጋሚ ራሳቸውን ከሁሉም የተለዩ ፣የማይገኙ ፣ የማይተኩ ፣ እሳቸው ያሉትን
የማይቀበል ያልዳነና ያልገባው መሆኑን በመግለጽ ካህናቱን በመሳደብ፣ ምእመኑን ወንጌል ያልገባው በደብተራ የተተበተበ እና ሌሎች
የንቀት፣ የስድብ እና የእርግማን ንግግሮችን በመናገር የበደሉን በመሆኑ ለችግሮች መፍትሔ ለማፈላለግ እንጂ አቤቱታችን ከጭፍን ጥላቻና
ነቀፌታ የነፃ ፍጹም ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ መፍትሄን በመሻት ነው፡፡
íኛ. አስተዳደራዊ ችግሮች
ብፁዕነታቸው አቡነ ማርቆስ ወደ
ምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እንደመጡ ብዙ ጉዳዮችን በትችት ሕዝቡንም በንቀት የተመለከቱ ሲሆን በመጡ በ3ኛ ወራቸው ጀምረው፡-
í) ከ41 በላይ ሹም ሽርና እገዳ ያካሄዱ ሲሆን አብዛኛዎቹ ሹም ሽሮችና እገዳዎች
ሕገ ቤተክርስቲያንን /ቃለ አዋዲውን/ ያልተከተሉ፤ተቋማዊ መዋቅሩን የጣሱ ይገኙባቸዋል፡፡
î) ቅድስት ቤተክርስቲያን በቅዱስ ሲኖዶስ
ፈቃድ በቃለ ዓዋዲው መሠረት የተቋቋሙትን ሰ/ት/ቤቶችን “ወንበዴዎች፤ሌቦችና
አሸባሪዎች” በማለት በሕዝብ ፊት ተሳድበው ለሰዳቢ ሠጥተዋል፡፡
ï በንጹሐን ምእመናን ላይ ሰብአዊ
ክብርንና ነፃነትን የሚጋፋ የስድብ፤ንቀትና እርግማን አካሄደዋል፡፡
ð ) ብፁዕነታቸው ከሦስት በላይ መኖሪያ
ቤቶች ያሏቸው ሲሆን ከእነዚህም መካከል ተወልደው ባደጉበት፣ በተማሩበትና ባስተማሩበት ጉንደወይን ከተማ /በ2004 ዓ.ም የተገዛ/
እና አዲስ አበባ / በ2000 ዓ.ም የተገዛ/ ያላቸው ሲሆን ከአዲስ አበባው መኖሪያ ቤት የግንባታ ውል ክፍያ ጋር በተያያዘ በብፁዕነታቸው
በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ላይ የተፈጸመው ክስና እስራት በሀገረ ስብከታችን ያሉትን ምእመናንን አንገት ሰብሯል፤ አዋርዷል፡፡ በዚህም ወቅት በሀገረ ስብከታችን አስተዳደር ውስጥ በሂሳብ ሹም፣
ገንዘብ ያዥና መዝገብ ቤት መካከል ሦስት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ
በአንድ ቀን የተደረጉ ለውጦችና ሰዎቹ ለብፁዕነታቸው ካላቸው ዝምድናና አካሄድ አንጻር ነገሩን ለሀገረ ስብከቱ ምእመናን ከጥቂት
ዓመታት በፊት በብፁዕነታቸው አቡነ ዘካርያስ ከተፈጸመብን በደል አንጻር እንቅስቃሴውን እንቆቅልሽ አድርጎብናል፡፡
îኛ.
ሃይማኖታዊ ችግሮች
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ወደ ሀገረ
ስብከታችን ከመጡበት ከኅዳር 2004 ዓ.ም ጀምሮ በካህናት፤በዲያቆናትና በሌሎች የቤተክርስቲያኒቱ ምእመናን ዘንድ ያልተለመዱ፤እንግዳ
ክንዋኔዎች እየተስተዋሉ ሲሆን ክንዋኔዎቹና አሠራሮቹም ምእመናንን ግራ ያጋቡ፤ለመናፍቃንም በር የከፈቱና የሚከፍቱ ናቸው፡፡
ከእነዚህም መካከል ፡-
1 ) ብፁዕነታቸው አቡነ ማርቆስ
ከመጡ ከሁለት ወራት በኋላ ጀምሮ የቅድስት ቤተክርስቲያናችን ቅዱሳን አበው ለመናፍቃን መልስ የሰጡበትና ለአማኞች ያስተማሩበት ሃይማኖተ
አበው መጽሐፍ ‹‹እኔ ልማታዊ ነኝ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም አለብን››
በሚል ተገቢ ያልሆነ ምክንያት ከቅዳሴ በኋላ እንዳይነበብ ተደርጓል፡፡
2) በአንዳንድ አድባራትና ገዳማት
በውል በታወቀ ምክንያት የቅዳሴ ጸሎት ሰዓቱ ቢቀየርም በፍትሐ ነገስት አንቀጽ 12 ላይ ‹‹ሕዝቡ ሳይሰበሰቡ የቅዳሴውን ጸሎት አይጀምሩ››
የሚለውን በመተው በሀገረ ስብከታችን ለብዙ ዘመናት ምቹ ከሆነው ንጋት የ12፡00 ሰዓት የቅዳሴው ጸሎት ያለ ምንም ተጨባጭ ምክንያት
‹‹ሰዓቱን ለወንጌል መጠቀም አለብን›› በሚል ምክንያት ወደ
11፡00 ሰዓት እንዲሆን ተደርጓል፡፡በዚህም እናቶች፤እህቶች፤ሕጻናትና አረጋዊያን ሌሊት 10፡00 ሰዓት ከቤታቸው እንዲወጡ በመገደዳቸው
መቸገራቸውን፤መማረራቸውንና በቅዳሴ ሰዓትም የምእመኑ ቁጥር መቀነሱን እንገልጻለን፡፡
3) በክብር ለቡራኬ በእጃችን በማድረግ
እንቀበለው የነበረውን የቅዳሴ ጸበል ያለ ምንም ምክንያትና ጥቅም ብፁዕነታቸው በጆግ በማደረግ በጅምላ ምዕመናንን መርጨት በማዘውተራቸው
ምእመናንም ሲጠይቋቸው ‹‹እንግዲያውስ አረቄና ጠላ ልርጫችሁ?››
በማለት የተዘባበቱና የመለሱ ሲሆን ነገና ከነገ ወዲያ ይህ አካሄድ ወደ ቅዱስ ቁርባኑ የማይሄድበት ምንም ተጨባጭ ምክንያት እንደማይኖር
እንገልጻለን፡፡
4) በቅዳሴ ጸሎት ጊዜ ታቦተ መንበሩን
ለምእመናን ግልጥ ሆኖ እንዲታይ በማስገደድ (ካህናቱ ሥጋውና ደሙን ሲፈትቱ እንዲታይ በማድረግ) በአካባቢው ሽማግሌዎች አበባል ‹‹የኢትዮጵያ ሙሽራ ዛሬ ተገለጠ ክፉ ቀን መጣ›› እስኪባል ድረስ
ብዙ ተቃውሞ ቢገጥማቸውም በቤተክርስቲያናችን ያልተለመደ የጸሎተ ቅዳሴ ሥርዓት እንድንከተል እየተገደድን እንገኛለን፡፡
5) በቅድስት ቤተክርስቲያናችን የሥርዓት
መጽሐፍት በሆነው በፍትሐ ነገስት መሠረት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጾሙን ወራት በሚታሰብበት በጾመ ኢየሱስ ወይም
ዐቢይ ጾም በአርምሞ፤በጾምና በጸሎት፤በንስሐና
ቅዱስ ቁርባን፤በሱባኤ የጌታን ሕማማተ መስቀል እያሰቡ ማዘን፤ማልቀስ የሚገባ በመሆኑ ከበሮ የማይመታ የማይጨበጨብ ቢሆንም ብፁዕነታቸው
ይህንን ሥርዓት በመተው ምእመናን “አልለመድንም ከበሮ አንመታም አናጨበጭብም”
ቢሉም ‹‹እኔ ሊቀ ጳጳሱ ተቀምጬ፤እኔ ፊታችሁ እያለሁ›› በማለት
በደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው ጽርሐ ጽዮን አብማ ማርያም ቤተክርስቲያን በተደረገ ጉባኤ ምእመኑ ሳይፈልግ በማስገደድ ከበሮ አስመትተዋል፤
አስጨብጭበዋል፡፡
6) ካህናት ምእመናንን በተለይም
የንስሐ ልጆቻቸውን በቅርብ መከታተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ መሰረት ካህናቱ በየንስሐ ልጆቻቸው ቤት በመዘዋወር ቡራኬ ይሰጣሉ፡፡
ብፁዕነታቸው ግን የሀገረ ስብከቱን ካህናት ክብርን በሚነካ መልኩና በጸበሉ ፈዋሽነት አለማመንን በሚያሳይ አነጋገር ‹‹ውኃ ግድግዳ ላይ ከመርጨት በቀር ወንጌል የማያውቁ›› በማለት
ተሳድበዋል፡፡ ጸበል ውኃ ብቻ ነውን? ካህናቱስ አይባርኩትምን? እርሱስ መጻጉዕ የተፈወሰበት ወንጌል አይሆንም? ካህናቱስ ሌላ አያውቁምን?
7) በፍትሐ ነገስት አንቀጽ 14
ላይ በተገለጸው መሠረት ሴት በወር አበባ(በወርኃ ጽጌ) ወቅትና አራስ ስትሆን ቤተክርስቲያን መግባትን የሚከለከል እንደሆነ ቢታወቅም
ብፁዕነታቸው መግባት እንደሚችሉ የፈቀዱ ሲሆን እርሳቸው በተገኙባቸው ጉባኤያት ላይ ‹‹እኔ አባታችሁ እያዘዝሁ፣እኔ ፈቅጄ፣ እኔ የቤተክርስቲያኒቱ ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያው እያለሁ›› በማለት
እንዲገቡ በማስገደዳቸው የተወሰኑት እናቶችና እህቶች ትዛዛቸውን አክብረው ሲገቡ ቀሪዎቹ ለቤተክርስቲያን ክብር ሲሉ ወደ ቤታቸው
ሲመለሱ ማየት የተለመደ ትርኢት ሆኗል፡፡
8) ብፁዕነታቸው ከላይ በተራ ቁጥር
ሁለት ከተጠቀሰው የቅዳሴ ጸሎት ሰዓቱን እንዲሻሻል ከማድረጋቸውም
በተጨማሪ በጸሎተ ቅዳሴ ጊዜ መውጣት እንጂ መግባት ይቻላል በማለት አባቶቻችንና ወላጆቻችን ያላስተማሩንን የማናውቀውን ሥርዓት እንድንከተል
እየተገደድን መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
9) ብፁዕነታቸው ነገረ ቅዱሳንን
በተመለከተ ግራ የሚያጋባ አቋም ያላቸው ሲሆን የሀገረ ስብከቱ ሰባኪያነ ወንጌልን በመንበረ ጵጵስና ሰብስበው ‹‹ክርስቶስን ስበኩ እንጂ አቡሀይ እሙሀይ አትበሉ›› በማለት ስለ
ቅዱሳን ያላቸውን አመለካከት ተናግረዋል፡፡
በአጠቃላይ በሀገረ ስብከታችን ብፅዕነታቸው ያደረሱብን ሃይማኖታዊና
አስተዳደራዊ በደል እኝህ ብቻ ሳይሆኑ የተጠቀሱት ማስረጃ ማቅረብ የሚቻልባቸው ሲሆኑ በዚህ ጹሑፍ ቢቀርቡ የቤተክርስቲያንና የአባቶቻችንን
ክብር የሚያስደፈሩ በመሆናቸው ያላቀረብናቸው ሲሆን እኛ በምስራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የምንገኝ የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጆች ከጥቂት
ዓመታት በፊት በብፁዕነታቸው አቡነ ዘካርያስ የደረሰብን በደል ከልባችን ሳይሽር ከኃሊናችን ሳይወጣ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ለችግራችን
መፍትሄ ለመፈለግና ምእመናንን ለመካስ ጥረት ቢያደርጉም ጥረታቸው በብፁዕነታቸው መቀጠል ሲገባውና የደረሰብንን በደል መካስ ሲገባቸው
ድጋሜ ዘርፈ ብዙና መሰረታዊ ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ ችግሮች በመከሰታቸው ምክንያት ይህን ችግር ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችንና
ለመላ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆች ጉዳዩን ለመግለጽ የተገደድን ሲሆን አስፈላጊውን ተቋማዊ መዋቅር ተከትለን ችግሩን ለመፍታት ጥረት
ብናደርግም ባለመሳካቱና ምላሽ ባለማግኘታችን መሆኑን እየገለጽን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አባቶቻችን ይህን ጉዳይ በጥልቀትና በስፋት
ተመልክተው መፍትሔ እንዲሰጡን ከዚህ ሸኝ ደብዳቤ ጋር ባያያዝነው 116 ገጽ የድጋፍ ፊርማ እየገለጽን እኛ የሀገረ ስብከቱ ምእመናን
በቅዱስ እግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ስም እንጠይቃለን፡፡
“ቡራኬያችሁና ጸሎታችሁ አይለየን”
የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ምእመናን
ተወካዮች
ግልባጭ
- ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል አቃቤ መንበረ ፓትርያርክ
- ለመንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት
- ለፓትሪያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት
- ለምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት
- ለምሥራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ዘርፍ ጽ/ቤት
Hi Blogger,
ReplyDeleteI also noticed bishop yeakob, bishop for entire africa is doing the same with this bishop. i.e. both of them disrespect liturgy, and tsebel. bishop yaekob always after liturgy he spreads tsebel into the face and head of people. my question is that do we have some logic on doing that? or do these guys have some common goals? please find out for us.
Thanks,
I like mahiber kidusan
ReplyDeleteእዚህ ሲያትል (WA) መጥተው የሰሩት ነገር እንዲሁ ተመሳሳይ ነበር::ለማንኛውም ተራው ምእመን ከጳጳስ የታሻለበት ዘመን ላይ ደርሰናል:: ይገርማል !!! ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው....... አለበለዚያ ፍርዱ ሚዛናዊ የሆነ ክርስቶስ ድሞዙን ይከፍለዋል::አይናችን ካልተጋረደ በግልጽ እያየንም ለው::
Deleteአባቶቻችንኮ ይህችን ቤተክርስትያን ዛሬ ለኛ ያስረከቡን እንዲሁ በዋዛ ሳይሆን እኔና እናንተ እንኩዋን ልንሸከመው ልንሰማው በማንችለው መከራና ስቃይ ውስጥ አልፈው ነው:: ዛሬ ግን ብዙዎች (ባባትነት ወንበር ላይ የትቀመጡ) .... ተቃራኒውን ሲፈጽሙ ማየት አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻው ሰዓት ላይ መሆናችንን የሚያስገነዝበንም ጭምር ነው::
ግንኮ ይህች ሃይማኖት የምትጥፋ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ሳይሆን ድሮ ነበር የምትጠፋው....ድሮ ድሮ:: ግና የሰራት እራሱ ባለቤቱ ስለሆነ ማንም አልቻለም ወደፊትም አይችልም::ባክቹ በውስጥም በውጭም ያላችሁ ቦጥቧጮች እጃችሁን ክቤ/ክ ላይ ሰብስቡልን ለራሳችሁም ጭምር ስትሉ!!!
See "Aba selama" blog they started insulting the our church as it is against the Gospel. It happened because of your unjustified article.
ReplyDeleteFor example # 7- women's monthly circle shouldn't be the reason for accusation. Please be smart how to challenge if there is a wrong teaching. Your reporting and the latter style made it the bishop sound pro Gospel and you and others against him because of that.
"AbaSelama blog" is protestant blog-- what were you doing there? protestants don't know the Gospel. They don't understand scripture because their teaches who translate it (these are white professors who are atheists) us hermeneutics to translate God's parables. They don't have the spiritual guidance that reveals the truth. For example, the example 7 you mentioned regards women's menses in the scriptures. The law that women do not enter the sanctuary during their menses was established before Adam and Even committed the original sin (read Metshafe Kufale). Tewahdo does not say it is Mergem. Hwho taught the protestants like "Abaselama blog" and Aba Woldetensae that God made the rule because there was no sanitation? Where did they find that explanation. the answer is - they invented it. That Sir'at was also affirmed again by the council of Nicea (the 318) which was later compiled in the Fitiha Negest. My friend, Tewahdo had many Tebebt Liqawunt that God gave unshakable faith, unparalleled wisdom and understanding. Don't ever doubt for a moment that they would be in error because everything they did was by the power of Menfes Kidus. No protestant had ever been spiritual and there is no truth without spirituality.
DeleteGod Bless you my friend. Yetewahedo Lejoch pleas do not read Abaselama blog.they are wax coated Protestants.
DeleteI know the bishop when i was there in GundeWayn .I think he always thought about Yenta Taye and Yenta Heinok .I saw the Gubaie held in Gundaweyin.Abune Markoes isnot from our church.
ReplyDeleteWhat is wrong with Aba Markos? I don't understand!
ReplyDeleteእዚህ ሲያትል (WA) መጥተው የሰሩት ነገር እንዲሁ ተመሳሳይ ነበር::ለማንኛውም ተራው ምእመን ከጳጳስ የታሻለበት ዘመን ላይ ደርሰናል:: ይገርማል !!! ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነው....... አለበለዚያ ፍርዱ ሚዛናዊ የሆነ ክርስቶስ ድሞዙን ይከፍለዋል::አይናችን ካልተጋረደ በግልጽ እያየንም ለው::
ReplyDeleteአባቶቻችንኮ ይህችን ቤተክርስትያን ዛሬ ለኛ ያስረከቡን እንዲሁ በዋዛ ሳይሆን እኔና እናንተ እንኩዋን ልንሸከመው ልንሰማው በማንችለው መከራና ስቃይ ውስጥ አልፈው ነው:: ዛሬ ግን ብዙዎች (ባባትነት ወንበር ላይ የትቀመጡ) .... ተቃራኒውን ሲፈጽሙ ማየት አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን የመጨረሻው ሰዓት ላይ መሆናችንን የሚያስገነዝበንም ጭምር ነው::
ግንኮ ይህች ሃይማኖት የምትጥፋ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ሳይሆን ድሮ ነበር የምትጠፋው....ድሮ ድሮ:: ግና የሰራት እራሱ ባለቤቱ ስለሆነ ማንም አልቻለም ወደፊትም አይችልም::ባክቹ በውስጥም በውጭም ያላችሁ ቦጥቧጮች እጃችሁን ክቤ/ክ ላይ ሰብስቡልን ለራሳችሁም ጭምር ስትሉ!!!
የነበሩበትም ደብር ብዙ ከዝህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ችግር ያለበት ነው
ReplyDelete