በኢንተርኔት ችግር መረጃ
በጊዜው ባለማውጣታችን ይቅርታ እጠይቃለን
አርእስተ ጉዳይ
- የተሃድሶ መናፍቃን መሪዎችና አስተባባበሪ የሆኑትን ግለሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ አወገዘ፡፡
- ቃለውግዘቱ ከመደበኛው የሲኖዶስ ቃለጉባዔ በተለየ መልኩ በመገናኛ ብዙኅን እንዲነገር የውግዘቱን ጽሑፍ የሚያዘጋጁ አራት ሊቀነጳጳሰት ተመርጠዋል፡፡
- በጋሻው ደሳለኝ ኮሚቴው አጣርቶ ያቀረባቸው ሁለት መረጃዎች የሚያስወግዙት ቢሆንም፣ ለገቢያ ያዋላቸው ስምንቱ የስብከት ካሴቶች፣ በአውደ ምህረት ያሰተማራቸው ትምህርቶች የድምጽወምስል መረጃዎች ኮሚቴው አብሮ አይቶ እንዲያቀርባቸውና የጥቅምቱ ሲኖዶስ ላይ በጋሻው ከነትምህርቱ እንዲወገዝ ተወስኗል፡፡ ኮሚቴ ወደ አስር የሚጠጉትን የድምጽወምስል መረጃዎች ያላያቸው በፓትሪያሪኩና በእጅግአየሁ በየነ ተጽእኖ ስለተደረገበት መሆኑን ተነግሯል፡፡
- ለሊቃውንት ጉባዔ ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት መናፍቃኑ ላስተማሩት ኑፋቄ በቃልም በጽሁፍ መልስ እንዲሰጥ ታዟል፡፡
(አንድ አድርገን ግንቦት
15 ፤ 2004ዓ.ም )፡- ቅዱስ ሲኖዶስ ማክሰኞ በጠዋቱ ውሎ የተሃድሶ አራማጅ ድርጅቶችን በተመለከተ በማሕበረቅዱሳን በኩል መረጃዎች ቀርበው፣ የሊቃውንት ጉባኤ አጣርቶ፣ ለሊቃነ ጳጳሳት ኮሜቴ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበራቱን አውግዟል፡፡በህግ እንዲጠየቁም ትእዛዝ ማስተላለፉን ገልጸን ነበር፡፡
ከቀትር በኋላ ደግሞ በቀረበለት መረጃ መሰረት ሰባት የተሃድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ መናፍቃንን አውግዟል፡፡ከዛሬ ጀምሮ ሥልጣነ ክህነታቸውና ማዕገ ስማቸው ተገፎ አቶ እንዲባሉ፤ በማንኛውም የቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዳይሳተፉ ወስኗል፡፡
የተወገዙት መናፍቃን ስም
1. አቶ ጽጌ ስጦታው
2. አቶ አሸናፊ መኰንን
3. አቶ ደረጀ ገዙ
4. አቶ በዛ ስፍርህ
5. አቶ ግርማ በቀለ
6. አቶ አግዛቸው ተፈራ
7. አቶ ሰሎሞን ጥበቡ ናቸው፡፡
ከዚህ በተያያዘ በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በአባ ሠረቀ እና ጌታቸው ዶኒ ላይ ባቀረቧቸው ማስረጃዎች የግለሰቦቹ የሃይማኖት ሕጸጽ ተምርምሮ በቀረበው ሪፖርት መሰረት አባ ሰረቀ “የፓትሪያሪኩ፣ የአባቶች እምነት የእኔም ነው፡፡” በማለት ራሳቸውን ገለልተኛ ማድረጋቸውን፤እንዲሁም ጌታቸው ዶኒ ስላቋቀመው የቅን ልቡና የመንፈሳዊና የፈውስ አገልግሎት የእምነት ተቋም ሲጠየቅ ‹‹ልጆቼን የማበላው ተቸግሬ ነው፡፡› በማለት መመለሳቸውን ይታወሳል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ አባ ሠረቀ ስለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ንጽሐ ባሕርይ የሚያመነው በጽሑፍ እንዲያቀርብ፣ እውነትና ንጋት ብሎ ለጻፈው መጽሐፍ መሰል ጥራዝ ማስተባበያ መጽሐፍ እንዲጽፍ፤ ይህን ካላደረገ በጥቅምቱ ሲኖዶስ እንዲወገዝ ወስኗል፡፡
ጌታቸው ዶኒ የቀረበበት ማስረጃ የሃይማኖት ሕጸፅ ያለበት መሆኑን የሚያረጋግጥ ቢሆንም በአሁኑ ሠዓት የሚያምነውን ሃይማኖት በፅሑፍ እንዲያቀርብና ቐኖና እንዲሰጠው ወስኗል፡፡
ቃለውግዘቱ ከመደበኛው የሲኖዶስ ቃለጉባዔ በተለየ መልኩ በመገናኛ ብዙኅን እንዲነገር የውግዘቱን ጽሑፍ የሚያዘጋጁ አራት ሊቀነጳጳሰት ያካተተ ኮሚቴ ሰይሟል፡፡ ብጹዕ አቡነ አብርሃም፣ ብጹዕ አቡነ ገሪማ፣ ብጹዕ አቡነ እስጢፋኖስና ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል አዘጋጅተው ረቡዕ ጧት ለምልዓተ ጉበኤ ያቀርባሉ፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን!
ፈተና ብበዛም እግዚአብሔር አምላክ በአባቶቻችን አድሮ መልካም ውሳኔዎችን እያስወሰነልን ነው::
ReplyDeleteስለተደረገልን ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር አምላካችን ስም ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በፍጥረቱ ሁሉ የተመሰገነ ይሁን::
የእግዚአብሔር ቸርነቱ የእመ አምላክ አማላጅነቱዋ የቅዱሳን ጸሎትና ተራዳእነት ከእኛ ስላልተለየ ነው ይህ የተደረገልን::
ግን አሁንም በዚህ እግዚአብሔርን ከማመሰገን ባለፈ ብዙ በመደሰት መዘናጋት የለብንም:: ማስተዋል ያለብን ቤተክርስቲያናችን ኢጥሙቃንን በማጥመቅ ከበረቱዋ የወጡትን በመመለስ ለመናፍቃን የሐሰት ትምህርት መልስ በመሰጠትና ለሕዝቡ ተደራሽ በማድረግ ዕርቃኑን በማስቀረት በሕዝቡ በማኅበራዊ ሕይወት በሰፊው በመሳተፍ በኢኮኖሚ ችግርና በተለያየ ምክንያት በሞራሉ እየላሸቀ ያለውን ኅብረተሰብእ በመታደግ ወዘተርፈ መገስገስ ስገባት በአስተዳደር ችግርና አንቀዋት በያዙአት የተሐዲሶ መናፍቃን ሴራ እስካሁን በተከላካይ መስመር ላይ መሆኑዋን ነው:: ተከላካይ ደግሞ ብበዛ ግብ እንዳይገባበት ቢያደርግ እንጂ የማግባት እድል የለውም:: ሙከራው ስደጋገምም መግባቱ አይቀርም:: መናፍቃን የምዕራባውያን ባህል አሕዛብ በተቁዋሙዋና በምእመናኑዋ በተደጋጋሚ ጥቃት ብፈጽሙም ተቅዋሙዋ ከውስጥ ባለባት ችግር ምክንያት ዘመኑን የዋጀ ተመጣጣኝ ምለሽ ለመስጠት አለተነሳችም::
እኛ ምእመናን እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ቸርነቱ ሳይለየን ይህን በመሰለ ፈተና ውስጥ በአባቶቻችን አድሮ ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ውሳኔ ካስወሰነልን በፈቃደ እግዚአብሔር በምክረ ካህን በመኖር በአካን ምክንያት ወደ እስራኤል ጉባዔ የገባውን ርኩሰት ኢያሱ እንዳራቀ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ወጭ እንዲንኖር የሚያደርጉንን ነገሮች ማስወገድ ይገባናል :: ያን ጊዜ እኛ ዝም እንላለን ::በአጽራረ ቤተክርስቲያን አድሮ እረፍት የሚነሳትን ዲያብሎስን እግዚአብሔር ያስታገስልናል ፡እኛንም በጸጋ በምሕረት ይጎበኘናል ፡፡በቤቱ ለማገልገልም ጸጋችንን በትክክል እንረዳለን አገልግሎታችንም ፍሬያማ ይሆናል፡፡
ቤተክርስቲያናችን በደራሽ ጉዳዮች ከመወጠር በረጅም ጊዜ እቅድ እንድትጉዋዝ ወደ ቀደመ ክብሩዋ እንድትመለስ የኛ የምእመናን ተሳትፎ ወሳኝ ነው ፡፡
የአሁኑም ሆነ የወደፊት ዋነኛ የቤተክርስቲያናችን ፈተና የተሐዲሶ መናፍቃን ናቸው፡፡ ተሐዲሶ ቤተክርስቲያንን ለመክፈልና ይዞታዎቹዋን ለመናፍቃን ለማስረከብ በሚያደርገው ሴራ ከውስጥ ጳጳስ ቄስ ዲያቆን ለመምሰል ስሠራ ወጥኑን ስጨርስ ለመክፈል ከማናፍቃን እንኩዋን በሰበካ ጉባኤ ከማሰመዝገብ ወደ ኋላ አይልም፡፡ አያምጠውና ፍርድ ቤት ብንቆም እንኩዋን መናፍቃንን አግበስብሶ አምጥቶ ይህን ያህል ተከታዮች አሉኝ ከማለት ወደ ኋላ አይልም ፡፡ይህንንመ በባለፈው የጥቅምት ስኖዶስ የበጋሻው ደጋፊ ነን እያሉ በአንገታቸው ማተብ እንድታይ አድርገው ከሀዋሳ ከመጡት መናፍቃን መረዳት ይቻላል፡፡ለተሐዲሶ መናፍቃን ዘላቂ መፍትሔው ከላይ እንደተጠቀሰው ከእኛ የሃይማኖት ጽናት ከምግባር ቅናት በተጨማሪ ቤተክርስቲያንን ማወቅ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንን ማወቅ ሲባል ሕጉዋን ሥርዓቱዋን አስተምህሮዋን ትውፊቱዋን ማወቅ ፡ማንንም ብሆን ከዚህ ከቤተክርስቲያን ሥርዓት ሕግ ትውፊት አስተምህሮ አንጻር መመዘን የምንችልበት ደረጃ መድረስ እኔ… የኤገሌ ነኝ ከማለት እኔ የቤተክርስቲያን ነኝ ለቤተክርስቲያን የሚበጅ ሥራ እየሠራ ያለው ማን ነው ማለት መቻል ቅዱስ ስኖዶስ በየጊዜው የሚወስናቸው ውሳኔዎች ተግባራዊ እንደሆኑ መከታተል ከሰበካ ጉባዔ አባልነት በተጨማሪ በምደረጉ ምርጫዎች ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ወዘተርፈ፡፡
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ እስራኤል ወይትባረክ ስመ ስብሐትሁ ቅዱስ ወይምላዕ ስብሐትሁ ኩሎ ምድረ ለይኩን ለይኩን፡፡ ወያርእየነ ትንሣኤሃ ለቤተክርስቲያን ወለሀገሪትነ ኢትዮጵያ::
thangk GOD bewinu le EGZIABHER yemisanew neger alene?
ReplyDeleteGood job ande aderegenoche!!
ReplyDeletehoping more good news to come !
በዚህ መዘናጋት የለብንም !
we have a lot to do.
ስላደረገልንና ስለሚያደርገው ሁሉ እግዚብሔርን እናመስግነው ፡፡ ይኸ የእሱ ውጊያ ድምዳሜው ነው ፡፡ የወደፊቱን ግን ቀላል አድርገን በመገመት ሞኝ እንዳንሆን ከወዲሁ ይታሰብበት ፡፡ የሚጸድቁበት ስለሚመስላቸው ገና ብዙ እንደሚጓዙ እጠብቃለሁ ፡፡ ልቦናቸውን እርሱ ራሱ እያቀና ቢመልሳቸው እጸልያለሁ ፡፡
ReplyDeleteለዚህ ድል ላደረስከን ፈጣሪአችን
ክብር ሁሉ ላንተ ይሁን
አሜን
Hale luya...God is great....I am very happy on the decisions. Our church separated the "tekulas" from sheep. But I have one big questions i.e. what are those guys doing inside our church while their mind and thoughts is with protestants.
ReplyDelete