ባለፈው ዓርብ ሁለት የውጭ ዜጎች ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደመጡበት እንዲመለሱ መደረጉን መንግሥት አስታወቀ
ከሪፖርተር የተወሰደ
በእስልምና ሃይማኖት ሽፋን ከትናንትና በስቲያ በተለይ በአዲስ አበባ በሚገኙ መስጊዶች ሊደረግ የነበረው ብጥብጥ የመፍጠር ቅስቀሳ፣ መንግሥት ሚያዝያ 25 ቀን 2004 ዓ.ም. ባስተላለፈው ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ምክንያት መክሸፉን የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ወርቁ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ላለፉት 11 ሳምንታት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኙ መስጊዶች፣ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የተለያዩ ረብሻዎችን ሲያደርጉ የነበሩ አንዳንድ ግለሰቦች፣ ከትናንትና በስቲያም በአንዳንድ መስጊዶች ላይ ረብሻ ለመፍጠር የሞከሩ ቢኖሩም፣ የሃይማኖቱ ተከታዮች ያለምንም ችግር ፀሎታቸውን አድርሰው ወደየመጡበት ተመልሰዋል፡፡
ከትናንትና በስቲያ በተለይ በአንዋር መስጊድ ለፀሎት ተሰባስበው በነበሩበት ወቅት የሃይማኖቱ ተከታዮች ‹‹አላህው አክበር፣ የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት አንፈልግም፣ በምክር ቤቱ ምርጫ አያገባውም፤›› እና ሌሎችን መፈክሮች በማሰማት በመስጊዱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲዟዟሩ እንደነበር በስፍራው የነበሩ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡
መንግሥት ሚያዝያ 25 ቀን 2004 ዓ.ም. በሰጠው የማስጠንቀቂያ መግለጫ፣ አንዳንድ ግለሰቦች ሃይማኖታዊ ተቋማትን በመጠጋት ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጥያቄዎች ያነሱ እንደነበር አስታውቋል፡፡ ግለሰቦቹ በአወሊያና በሌሎቹም መስጊዶች ሰላማዊ ሙስሊሞች ፀሎት እንዳያደርሱ፣ ዘመን አመጣሽ ማኅበራዊ ድረ ገጾችን በመጠቀም ለከፍተኛ ረብሻና ጥፋት ይዘጋጁ እንደነበር ጠቁሟል፡፡ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት በሰላምና በፍቅር ይኖር የነበረውን የሃይማኖት ተከታይ፣ በሕገ መንግሥቱ የተሰጠውን መብት የሚያሳጣ እንቅስቃሴ ያደርጉ እንደነበርም አስታውሷል፡፡
በሃይማኖት ስም ያልሆነ እንቅስቃሴ እያካሄዱ የሚገኙት ቀደም ባሉት ዓመታት በአንዋር መስጊድ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ለበርካታ ዜጐች ሕይወት መጥፋት ምክንያት በመሆናቸው፣ ፍርድ ቤት የወሰነባቸውን ቅጣት ጨርሰው የወጡ አንዳንድ ግለሰቦችም እንደሚገኙበት መንግሥት በመግለጫው አስታውቋል፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው አብረዋቸው እየተንቀሳቀሱ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
አወሊያ ትምህርት ቤትንና የእስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ምርጫን በሚመለከት ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ ቢሰጣቸውም፣ ለጥያቄያቸው ምላሽ እንዳልተሰጠ በማድረግ ሰፊ አፍራሽ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ማካሄዳቸውን የመንግሥት መግለጫ ያትታል፡፡
ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የሚንቀሳቀሱት ግለሰቦች እየፈጸሙ ያለው መንግሥትን የማጥላላት ድርጊታቸው መረን እየለቀቀ መምጣቱን ያስታወቀው የመንግሥት መግለጫ፣ ግለሰቦቹ ጅሀድ (የሃይማኖት ጦርነት) እስከማወጅ መድረሳቸውን ጠቁሟል፡፡
በፀጥታ ኃይሎች ላይ ድብደባና የተለያዩ የማስፈራሪያ ዛቻዎችን የሚያደርሱት እነዚሁ ወገኖች፣ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በምዕራብ አርሲ ዞን በገደባ አሳሳ ወረዳ አሳሳ ከተማው ውስጥ ባነሱት ብጥብጥ ንፁኅን ዜጎች መጐዳታቸውን መግለጫ አስታውሷል፡፡
ሚያዝያ 12 ቀን 2004 ዓ.ም. በአንዋር መስጊድ አካባቢ በፀጥታ ማስከበር ሥራ ላይ የነበረን ፖሊስ በመደብደብ ጉዳት እንዳደረሱበት፣ አወሊያ ትምህርት ቤት አካባቢ በተደጋጋሚ መንገድ በመዝጋትና ለፀሎት በሚመጡት ላይ ድንጋይ በመወርወር የተለያዩ የብጥብጥ መፍጠሪያ ስልቶችን ሲጠቀሙ እንደነበር አመልክቷል፡፡
በተለያዩ መስጊዶች በመገኘት የፀሎት ሥነ ሥርዓት የሚመሩ ኢማሞችንና የሃይማኖት አባቶችን የድምፅ ማጉያ በመንጠቅ የፀሎት ሥርዓቱ እንዳይካሄድ ያደርጉ እንደነበር መግለጫው አስታውሶ፣ በቅርቡ ከአማራ፣ ከትግራይና ከኦሮሚያ የተመለመሉና ለሕገወጥ ተግባር የተላኩ 13 ግለሰቦች ቄሌም ወለጋ ዞን ውስጥ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አብራርቷል፡፡
መንግሥት የንቅናቄው መሪ መሆናቸውን ከሚናገሩት ጋር በተደጋጋሚ ውይይት በማድረግ የተጀመረው አካሄድ እንደማያዋጣቸው ቢመክራቸውም፣ ከውይይቱ በኋላ የመንግሥትን ስም ማጥላላት መጀመራቸውን ገልጿል፡፡ ነገር ግን ማወቅ ያለባቸው ነገር ‹‹መንግሥት መሻገር የማይችሉት ቀይ መስመር እንዳለው ነው›› በማለት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ባለፈው ዓርብ ሁለት የውጭ ዜጎች ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደመጡበት እንዲመለሱ መደረጉን መንግሥት አስታወቀ፡፡ በደፈናው ከመካከለኛው ምሥራቅ መጥተዋል የተባሉት ሁለቱ የውጭ ዜጎች ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ወደ አንዋር መስጊድ በመሄድ የያዙትን ጽሑፍ ሊበትኑ ሲዘጋጁ እንደተደረሰባቸው መንግሥት ያወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
Koy enante yemitasemut yebetekristean dimtsi new woys mindinew? I just don't understand why you talk about muslim religion in this blog?
ReplyDeletekewuch yemetu huletu sewoc lemin lefir alkerebum?yewuch hager gazetegochin sayqer mengsit eyasere aydelem?lemehonu mesgid tesebsibo allahu akber yemilew hulu new chidir fetari?yemengist mastenqeqiya lemin asfelege?tiyakewn beagbabu memeles ayshalim neber?
ReplyDeleteany way yehulumhaymanot yikeber zend entagel
AnonymousMay 7, 2012 05:45 AM
ReplyDeleteI think we have to be fair at this point. They are our brothers and sisters, there suffering is our suffering. If possible we should create an organisation which will make us collaborate to remove the current government who says Religious freedom but in reality no at all.
የ መንግስት ዋና ኣላማው ሙስሊም እና ክርስትያን ማጋጨት ነው ለሁሉም ነገር ማስተዋል ያስፈልጋል
ReplyDelete