Sunday, May 20, 2012

ማህበረ ቅዱሳንን በመንግስት የማስመታቱ ሴራ


ኢሳት ስለ ቤተክህነቱ ደብዳቤ የዘገበው

ግንቦት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ማህበረ ቅዱሳን በሚያሳትማቸው ልሳኖቹ በዋልድባ በሚገነባው የስኳር ፐወሮጀክት ዙሪያ መንግስትን የሚደግፍ ዘገባ ያላተመበትን ምክንያት እንዲያስረዳ  በጠቅላይ ቤተ-ክህነት ተጠየቀ።
በቤተ- ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምርያ ለማህበሩ በፃፈው ክስ አዘል ደብዳቤ፦ “በዋልባ ገዳም አካባቢ የሚካሄደውን ግዙፍ የስኳር ልማት ፕሮጀክት በተመለከተ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያወጣው መግለጫ በማኅበሩ ልሳናት ላይ ለምን እንዳልተዘገበ  ማህበሩ  በጽሁፍ መልስ ይሰጥበት ዘንድ ጠይቋል።

ከስኳር ኮርፖሬሽን ሚኒስትሩ ከ አቶ አባይ ፀሀዬ ጋር ወደ ዋልድባ ሄደው የነበሩት የቤተ-ክህነት ተወካዮች ከጉዟቸው መልስ በ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው በሰጡት መግለጫ፤ እየተካሄደ ያለው የስኳር ፕሮጀክት የዋልድባን ገዳም ይዞታ እንደማይነካ፤ ይልቁንም የፕሮጀክቱ ግንባታ ለመነኮሳቱ ጠቀሜታ እንዳለው መግለፃቸው ይታወሳል።
በወቅቱ ለተለያዩ ሚዲያዎች ፍጆታ እንዲውል በማለት በጽሁፍ የበተኑትም ጋዜጣዊ መግለጫ በቴሌቪዥን ቀርበው የተናገሩትን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።
የገዳሙ መነኮሳት እና የ አካባቢው ነዋሪዎች  የ አቶ አባይ ፀሀዬም ሆነ የቤተ-ክህነት ተወካዮቹ መግለጫ ውሸት እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣሉ።
የቤተ-ክህነት ወኪሎች ወደ ዋልድባ ባቀኑበት ወቅት የማህበረ-ቅዱሳን ጋዜጠኞችም  ሁኔታውን ተከታትለው  ለመዘገብ ወደ ስፍራው ያመሩ ሲሆን፤ ከጉዟቸው መልስ ግን  “የቤተ-ክህነት ሰዎች ስለሰጡት መግለጫም “ሆነ  “ራሳቸው በአካል ስላዩት እውነታ” ከመፃፍ ተቆጥበዋል።
የማህበሩ ልሳናት ጋዜጠኞች ስላዩት እውነታ ከመዘገብ የተቆጠቡት፤ጋዜጠኞቹ ያረጋገጡት ነገር የመንግስት ባለውልጣናት እና የቤተ-ክህነቱ ተወካዮች ከሰጡት መግለጫ ጋር የሚጋጭ ነው።የቤተ-ክህነቱ ተወካዮች የሰጡት መግለጫ በውሸት የታጀለ ነው። የስኳር ፕሮጀክቱ ጠቀሜታው ባይስተባበልም፤ የገዳሙን ህልውና አጠያያቂ አድርጎታል።የተረጋገጠው እውነታ ይኸው ነው።ልሳናቱ  ቢዘግቡ ይህን ነበር የሚዘግቡት። ይህን ከመዘገብ የተቆጠቡት መንግስትና አንዳንድ የማህበሩ ፀሮች ማህበሩን በፖለቲካ ጠምዝዞ ለመጣል እያደረጉት ላለው ሴራ በር ላለመክፈት ነው” ብሏል-አንድ ስሙን መግለጽ ያልፈለገ የማህበሩ አባል ለኢሳት በሰጠው አስተያዬት።
”…ይሁንና ይህን ያህል ጥንቃቄ ቢደረግም ይባስ ብሎ የሀሰት መግለጫ ለምን አልተዘገበም?” የሚል ክስ አዘል ጥያቄ መቅረቡ አስገራሚ ነው”ያለው ይኸው የማህበሩ አባል፤ “ማህበሩ በነሱ ሥልጣን ስር ስለሆነ በሚያትማቸው ጋዜጦች የነሱ ሀሰብ ግዴታ መውጣት እንዳለበት ማሰባቸውም፤እጅግ አደገኛ የአፋኞች አስተሣሰብ ነው”ብሏል።
ሌላው አስገራሚው  በጠቅላይ ቤተ-ክህነት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሃላፊ በመምህር ዕንቁ-ባህርይ ተከስተ  ስም እና ፊርማ  ለማህበረ-ቅዱሳን ጽህፈት ቤት የተፃፈው ክስ አዘል ደብዳቤ ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከፓትርያርኩ ጽህፈት ቤቶች በተጨማሪ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ግልባጭ መደረጉ ነው።
ቀደም ሰል የህወሀቱ መስራች አቦይ ስብሀት ነጋ እና የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ አባይ ፀሀዬ የማህበረ ቅዱሳንን አመራሮች ቢሯቸው ድረስ ጠርተው ማስፈራራታቸው፤ በቅርቡ ደግሞ አቶ መለስ ዜናዊ በፓርላ ሪፖርት ሲያቀርቡ ማህበሩን የአክራሪዎች ስብስብ እንደሆነ አስመስለው መዝለፋቸው ይታወሳል።

6 comments:

  1. ይህን ነበር እፈራ የነበረው ፡፡ እንኳንም ተነቃቃን ፤ ጥንቃቄ ለማድረግ በእጅጉ ይጠቅማል ፡፡

    ReplyDelete
  2. እኔ የማህበሩ አባል አይደለሁም ይሁንና የተቋቋመበትን አላማና ከፈጸማቸው በጎ ስራዎች አኳያ ግን ደጋፊው ስሆን አንዳንድ አባላቱ በስሜትና ባለመብሰል እያደረጉት ያለው ጥፋት ግን ያሳዝነኛል። በእርግጥ እኔ ለቤተክርስቲያኔ ባለኝ ቅርበት በዚህ ዘመን በተሀድሶዎች በኩል እየተደረገ ያለውን በቤተክርስቲያን ላይ የተቃጣውን የጥፋት ርብርቦሽ ስለምረዳ የማህበሩን የጭንቀት ምንጭም በደንብ ይገባኛል። በአሁኑ ሰአት በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚታየው ትርምስ ከማህበሩም/የጥበቃ/ ይምጣ ከተሃድሶዎች/የማፍረስ/ ወይም ከእበላ ባይ ሆዳሞች: መነሻና በር ከፋቹ ግን የቤተክርስቲያናችን የበላይ የአስተዳደር አካል የከፈተው ክፍተት ነው። በቤተክርስቲያኗ ሊኖር የሚገባው ሆኔታዎችን ያገናዘበ አስተዳደራዊ ለውጥ አለመኖር፣ በእምነት ጉዳይ እርግጠኛ ያልሆኑ ሰዎች አለቦታቸው መቀመጣቸው፣ በተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ሚከሰቱ ያፈጻጸም ችግሮችና ሌሎችም ሲሆኑ በተለይ አባቶች በተለይ በተለይ ፓትርያርኩ ውስጣቸው ያለው ቤተክርስቲያኗን በሆነ መልክ ለመቀየር የመፈለግ እምነት ባይኖራቸው ኖሮና የጸናውን አጽንቶ በመያዝ የሚያምኑ ቢሆን ያለፈው 20 አመት ታሪካችን ሌላ ይሆን ነበረ። አሁንም መፍትሄው የአባቶች አንድ ልብ መሆን ቀዳሚው ሲሆን ቀጣዩ ዘመኑን የዋጀ ተገቢውን አስተዳደራዊ ለውጥ ማምጣት ነው። ያኔ የተሃድሶዎችን የጥፋት እርምጃ ባንድ ድምጽ መግታት ይቻላል፣ የአንዳንድ ስሜታውያን ትርምስንም ማስቆም ቦታ መንሳት ይቻላል ጎበዝ ቤተክርስቲያኗ ድሃ ሆና እኮ አይደለም ከከተሞች ወጣ ስንል አድባራት ተዘግተው የምናያቸው ያለው አሰራር ሰንካላ መሆን እንጂ። አሰራሩ እንከን የለሽ ቢሆን ሌላ በጎን የተዘጉትን እናስከፍት፣ ምንፍቅናን እንከላከል፣ ሊቃውንቱን እንርዳ.....የሚል ሃሳብ ይዘው ማህበራት ስጋት እስኪመስሉ ድረስ ይደራጁ ነበር? ለማንኛውም የጸናውን የተዋህዶ እምነቴን እንዲነካብኝ የማልፈልግ የተዋህዶ ልጅ ስሆን ማንኛውን የእምነትም ሆነ በሲኖዶስ ጸድቆ ከወጣው የቤተክርስቲያን ስርአት ውጭ ምንም አይነት ተሃድሶን የምጠየፍ፣ በአንዳንድ በማህበረ ቅዱሳን እንጭጭ አባላት ጭፍንተኝነት ምክንያት በየቦታው እየተፈጠሩ ያሉ ልዩነቶች የሚያሳዝኑኝም ነኝ። በመጨረሻ ቀን እኪወጣ የቅዱሳን አምላክ የተሃድሶነት መንፈስን ያስታግስልን በቡድንተኝነት ስሜት እየተፈጠሩ ያሉትን ልዩነቶች ያስቁምልን እያልኩ/ አንዳንድ ስሜታውያን የማህበሩ ልጆች ሆይ በከንቱ የማህበር ፍቅር ተይዛችሁ የናንተ ቡድን አባል ካልሆንን የተዋህዶ ልጆች ጋር እየተለያያችሁ ስለሆነ እባካችሁ ቆም በሉ/ ይህንን የምለው ተሃድሶና መናፍቅ ከጎዳን በላይ መላያየታችን የበለጠ ስለሚጎዳን ነው ትልቁ ማህበራችን በተዋህዶ ልጅነት መጠለላችን ነውና የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች አንሁን ባካችሁ። ማህበሩን ስንደግፍ ስለእከሌ ወይም ስለእከሊት ሳይሆን ያኔ በዛ ዘመን የሚመጣውን ክፉ ዘመን አስቦ በታላቁ አባትና በቀናኢ የቤተክርስቲን ልጆች ላይ አድሮ ስራን የሰራ የጌታን መንፈስ መሆን አለበትና ድንበር በሌለው ልብና ኩላሊትን በሚመረምር አምላክ ፊት ነገራችን ሁሉ በእምነት፣ በማስተዋልና በፍቅር ይሁን።

    ReplyDelete
  3. No matter what, the out come is the truth that will set you free. so i hope this government has to stop playing Childish Game this is not about politics this is about religion. which many fathers and mothers gave their life for this religion. i hope they are not stupid enough to continue their dictator leadership to destroy spiritual brothers and sister around the country. the result won't be good in both side.

    ReplyDelete
  4. lemenafik yikirta ayasfeligim.

    ReplyDelete
  5. Lemenafik Temekiro Laltemelese yikirta ayasfeligim!!!

    ReplyDelete
  6. AMILAK YITEBIKEN LE AYIMANOTU INDE MUSE YEMIKOM SEWU AMILAK YANSALIN MACEM HULUM NEGER LEBEGO NEWU HULACHINIM LETSELOT INNINESSA NIQU!!!OF HAA BARRU WAAQAYYOONIS HAA BARRU JIREENYA KEENYA ISA HAA GODHANNU, YEROONSA GA'EERA HUNDUMTUU DAMMAQA HAMMA YOONAA RAFNERRA OBBOLANKOO BARRI DHUMAA GA'EERA

    ReplyDelete