(አንድ አድርገን
ግንቦት 22 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የየባቦጋያ ምስራቀፀሐይ መድሀኒዓለም የመሬት ጉዳይ አሁን አሁን ድራማ እያስተናገደ ይገኛል ፤ እነ ጌታቸው
ዶኒ ህዝብ የወከላቸውን የአካባቢው ክርስትያኖችን ነጣጥሎ የማዳከም ስራቸውን ተያይዘውታል ፤ ፍርድ ቤቱ ቦታው ያለ አግባብ ለሪዞርት
ባለቤቱ እንደተሰጠ በመቃወም ላቀረቡት ጥያቄ “ቤተክርስትያኒቱ ራሷ ትጠይቅ ፤ እናንተ የቤተክርስትያን ህጋዊ ወኪል አይደላችሁም” የሚል ድፍን ያለ መልስ ከፍርድ ቤት በጊዜው እንደተሰጣቸው
ገልጸን ነበር ፡፡ ይህ ጉዳዩ ፍርድ ቤቱ እንዲህ ቢልም ክርስትያኖቹ እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ በህገወጥ መንገድ የተወሰደውን ከ10ሺህ ካሬ
በላይ የመድሀኒዓለምን ቦታ ለማስመለስ የቻሉትን ያህል እየጣሩ መሆኑን
ለማወቅ ችለናል፡፡
አቶ ጌታቸው
ዶኒ የመሬቱን ጉዳይ ወጥረው የያዙትን የቤተክርስትያን የቁርጥ ቀን ልጆች ላይ ከአዲሱ የቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ጋር በመመሳጠር
“አስፈራርተው ዛቻ አድርሰውብናል ፤ ለህይወታችን እንሰጋለን እና ሙዳየ ምጽዋት ገልብጠው ዘርፈዋል” በሚል የሀሰት ክስ አቅርበውባቸው
ነበር ፤ የባቦጋያ መድሀኒአለም ጉዳይ ላይ “አስፈራተው ሙዳይ ምጽዋት ዘርፈዋል” የተባሉትን ግለሰቦች ፍርድ ቤት
16/09/2004 ዓ.ም ቀርበው ነበር ፤ አንደኛ ምስክር ሆነ የቀረቡት አዲሱ ቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን ፤ ሁለተኛ
ምስክር አቶ ጌታቸው ዶኒ ፤ ሶስተኛ ምስክር የደብሩ ሰበካ ወንጌል ፤ ሲሆን አራተኛ ምስክር ደግሞ በብር የተገዛና አቶ ጌታቸው
ዶኒ የመከረው ሰው ነበር፡፡
አንደኛ ምስክር
ሆነው የቀረቡት አዲሱ የቤተክርስትያ አስተዳደሪ ቀሲስ መስፍን ፍርድ ቤት ውስጥ የአቃቢ ህጉንና የዳኛውን መስቀለኛ ጥያቄ በማድመጥ
ከመስካሪው(የሰባኪውን ምስክርነት) ቃል ጋር በማመሳሰል ውጭ ላለው በብር ለተገዛው ምስክር ቃላቸውን አንድ አይነት እንዲሆን ሲናገሩ
በቦታው በነበረች ፖሊስ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው ለ24 ሰዓት አስር ቤት አሳድረዋለቸው ፤ በ2000 ሺህ ብር ዋስ በቀጣይ ቀን ሊለቀቁ ችለዋል፡፡ በተጨማሪ አቶ ጌታቸው
ዶኒ በሀሰት ሊመሰክር ችሎት ላይ እንደቀረበ “ማስፈራራቱ የደረሰበት ቀን እና ሰዓቱን በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሆነ አስረዳ” በሚባልበት
ጊዜ አንደበቱ ተያይዞ መናገር ባለመቻሉ አቃቢ ህጉ ጥያቄውን መመለስ አለመቻሉን በማስተዋል ነጥቡ እንዲያዝለት ለዳኛው አመልክቷል
፤
ሌላኛው የአቶ
ጌታቸው ምስክር ሰባኪ ወንጌል ሲሆን በጊዜው የተፈጠረው ነገር ብዙዎችን አስገርሟል ፤ በመሰረቱ አንድ ሰው ሊመሰክር ፍርድ ቤት
ሲቀርብ ክርስትያን ከሆነ በመጽሀፍ ቅዱስ ፤ ሙስሊም ከሆነ በቁርአን መጽሀፍ ፤ እምነት ከሌለው ደግሞ ዳኛው የሚለውን ቃል ደግሞ
እያለ ምስክርነት እንደሚሰጥ ህጉ ያስገድዳል ፤ ይህ ሰባኪ ወንጌል የተባለ ምስክር በውሸት ለመመስከር እጁን መጽሀፍ ቅዱስ ላይ
አስቀምጧል ፤ የመሀላው ስነስርዓት እንዲፈጸም ዳኛው አዘዋል ፤ በችሎቱ ላይ እውነት እንደሚመሰክር በአስማይው አማካኝነት ስርዓቱን
ተከትሎ ማለ ፤ ከመሀላው በኋላ እውነቱን ሳይሆን ጌታቸው ዶኒ እና የባቦጋያ ሪዞርት ባለቤት የመከሩትን ነገር በሀሰት ሽምጥጥ አድርጎ
ቃሉ ሰጥቶ አበቃ ፤ ይህን የተመለከቱ ሰዎች ክፉኛ አዝነውበት ችሎቱን መከታተል ጀመሩ ፤ ከደቂቃዎች በኋላ በሀሰት የመሰከረው ሰባኪ
ወንጌል ችሎት ውስጥ ብቻውን እንዳበደ ሰው ሲስቅ ፤ ሰውነቱን መቆጣጠር
አቅቶት ሲንዘፈዘፍ መመልከት ተችሏል ፤ ሰውነቱ ከመንቀጥቀጡ የተነሳ አጠገቡ የተቀመጠ ሰው በሁኔታው በመገረም ከአጠገቡ መቀመጥ
ስላቃተው ቦታ ሊቀይር ችሏል፡፡ በስተመጨረሻ ከችሎቱ ሲወጣ ፊቱን ላብ አጥምቆት በጣም በተደናገጠ መንፈስ “ሙስሊም መሆን ይሻል
ነበር” ሲል ተደምጧል፡፡ እንዴት ከባድ ነው የእግዚአብሔር ቃል ላይ እጅን አስቀምጦ መማል ? “በስሜም በሐሰት አትማሉ፥ የአምላካችሁንም
ስም አታርክሱ እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ኦሪት ዘሌዋውያን 19፤12 ይህ ሰባኪ ባለፈው እሁድ “ሙስሊም መሆን ይሻል ነበር” ባለ አንደበቱ ከቅዳሴ በኋላ አውደምህረት ላይ በመቆም
ትምህር ሊያስተምር ሲል በጊዜው የነበረው ምዕመን “ውረድ አንተ ልታስተምረን አይገባም ፤ ያላየህውን እና ያልሰማህውን የምትመሰክር ሰው የእግዚአብሔርን
ቃል መስበክ አትችልም” ብለው ከአውደ ምህረቱ ዞር እንዲል አድርገውታል፡፡
ይህ ሰው መጽሀፍ
ቅዱሱን ያውቀዋል ፤ መጽሀፍ ቅዱስ ላይ እጅን አስቀምጦ ውሸት መናገር
ያልሆነውንና ያልተደረገውን መመስከር ምን ማለት እንደሆነ ተረድቶታል ፤ የእርሱ የሀሰት ምስክርነት ግን ወደፊት ቤተክርስትያኒቱ ላይ ምን እንደሚያመጣ
ያስተዋለ አይመስልም ፤ ህሊናው ችሎት ላይ ሊያስቀምጠው ስላልቻለ ከጤነኛ ሰው የማይጠበቅ ምግባር እዚያው በተቀመጠበት ሲያሳይ ተስተውሏል ፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ ማለትም ይህን የመሰለ የሸፍጥ ስራ
የሚሰራ ሰው ነው ፤ ችሎቱን የተከታተሉ ሰዎች ግማሹ “አይ የእግዚአብሔር
ስራ አራት ምላስ አድርጎ አናገራቸው” ሲሉ ግማሹ ደግሞ በሁኔታው በመገረም ዝምታን የመረጡ ምዕመናን ነበሩ ፤ ይህን ምን ይሉታል ?
“የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል ” የሐዋሪያት ስራ 9 ፤5 ሰው ላይ በሀሰት ቆመን ሊሆን ይችላል በቤተክርስትያን ላይ በሀሰት እንዳንቆምባት እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
“ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ
አይቀርም በሐሰትም የሚናገር ይጠፋል።” ይላል መጽሐፈ ምሳሌ 19፤9 የትም ቢሆን በሀሰት መመስከር ከህሊና ተጠያቂነት አያድንም
፤ “ምስክርነታቸውም እንዲሁ እንኳ አልተሰማማም።” የማርቆስ ወንጌል 14፤59 ፤ “በሐሰት አትመስክር፥” ማቴዎስ ወንጌል 19 ፤ 18 ይላል የወንጌል ቃሉ
፤ አቶ ጌታቸው ዶኒ የመድሀኒዓለምን ቦታ በብር ለመቀየር ከሪዞርቱ
ባለቤት ጋር በመሆን የገዛቸው ምስክሮች አንድ አይነት ቃል በችሎት ፊት ሊናገሩለት አልቻሉም፤ ይህን በመሰለ ትያትር ችሎቱ ወደ
ሌላ ቀን ሊዛወር ችሏል፡፡ በድብቅ በህገወጥ መንገድ ተደብቃችሁ የሸጣችሁትን የመድሀኒዓለምን ታቦት ማደሪያ ቦታ በገሀድ ስራችሁን
እያጋለጠ ቦታውን ትመልሳላችሁ ፡፡
አቶ ጌታቸው ዶኒ ሲጀመር ኦርቶዶክስ አይደለም ፤ የቀረበበት መረጃዎች ሰውየውን ነጻ የሚያወጡት አይደሉም ፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ
የሰጠው መልስ ሰውየውን ነጻ የሚያወጣው አይደለም ፤ አሁንም ይህ ሰው አንድ ካልተባለ ቤተክርስትያንን ከማፈራረስ ወደ ኋላ የሚል አይደለም ፤ እርሱ ምን ያድርግ በተዘዋዋሪ ህጋዊ አድርጋ ደብዳቤ
ሰጥታ የቤተክርስትያኑን ቦታ ሽጥ ብሎ የአቡነ ጳውሎስ ፊርማ ያለበት ደብዳቤ የሰጠው ቤተክህነት እያለ ፤ አይዞ በርታ የሚሉት አባት
እያሉ ……………
የዚህ የቦታ
ጉዳይ ወደ ፌደራል መንግስትና የሚመለከታቸው ከፍተኛ የመንግስት አካላት ከነ ሙሉ ማስረጃዎች ጋር ስለተላከ የደረሰበትን ነገረ ወደፊት
እናሳውቃለን፡፡
Oh God What Kind of Ugly generation is this??
ReplyDeleteBetam yasazinal...yabesachal...endih yetechemaleke zemen wust deresin. Gin yibelen, abatoch bezih yikochu yihon? balefew tewegizo biley noro yihin hulu anisemam neber. Getachew Menafik mehonu tsehay yemokew guday new!!!!
ReplyDeleteway medhane alem yihuna ante yewededikew engideh min yideregal
ReplyDeleteንጉሥ ዳዊት ከመንገሱ በፊት በንጉሡ በሳዖል በደረሰበት መከራ ወቅት ምን እንዳለ ማሰብና ፍጻሜውን መመልከት ለዚህ ጥፋት መልስ አይሰጥም ትላላችሁ፡፡ ዳዊት ያለው "እግዚአብሔር ይህንን በደል ይየው ይመልከተውም" ነበር፡፡ የዳዊት ልመና ተሰምቶ ሳዖል በክፉ መከራ ተይዞ በኣጋንንት ሲሰቃይ እንደነበረና መጨረሻ ላይም ለመራራ ሞት መዳረጉን ልብ ይሏል፡፡አሁንም እግዚአብሔር ይህንን ነገር ይየው ይመልከተውም፡፡ ፍርዱንም ያሳየን፡፡ Amen!!!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteEgziabher yesirahin yistih getachew
ReplyDeleteyehi lenate bereket newe esikemechereshawe e/r yerdachihu erasu medhanialem kenatega newe (hulachinm betechrestiyanen entebike)
ReplyDeleteZegabachihu Melkam Neber Kahinun Gin Ato Malet Menafikinet new Kihinetin Akibiru Sewyewn Besirachw Tenageru
ReplyDeleteዘመንኛ ሰባኪዎች ቅዱስ መጽሃፍ ላይ እጅ ጭነው መቀለድ ጀመሩ?! መልካም ነው! ሆዳቸው አምላካቸው ክብራቸው በነውራቸው ሲሆን ምን ይባላል?! አዬ "አባ" ጳውሎስ አምላክ የእጅዎን ይክፈልዎ ፣ በእውነት የቤተ ክርስቲያን የቅዱሳኑ አምላክ ይጠይቅዎ ! መዥገር ይመስል ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ተጣብቀው ንጽህናዋን ለሆዳሞች አሳልፈው ሰተዋልና አምላክ ይፍረድ....
ReplyDeleteGetachew! Egizer yayihal....firdhin tebek. Lenegeru ante min taderge yelakehn Paulos eyale. You are not Ortodox and that is why you are siding with investor and challenging the church. There is no spirituality on you face...you looks a merderer and short sighted. Mekeberiyahin felege!!
ReplyDeleteለማንኛውም አምላክ ልቦናችሁንይመልሰው
Delete