Thursday, May 24, 2012

አባቶች ከባለፈ ስህተት የተማሩ ይመስላሉ

 (አንድ አድርገን ግንቦት 16 2004 ዓ.ም)፡-አባቶች ከባለፈ ስህተታቸው የተማሩ ይመስላሉ ፤ የባለፈው ዓመት የቃለ ጉባኤ ማጭበርበር ብዙዎችን አባቶች በጣም አበሳጭቶ ነበር ፤ ለቀናት የተነጋገሩበት ሳይሆን በሰዓታት በአቡነ ገሪማ አማካኝነት የተጻፈውን  መግለጫ ብዙዎችን አስከፍቶ ነበር ፤  በዚህ ጉባኤ ላይ ግን የባለፈው ሁኔታ ሊደገም አልቻለም ፤ ቃለ ጉባኤ የሚጽፉት አባቶች ያልተነጋገሩባቸውን 3 ነገሮች አካተው እንደባለፈው ሸፍጥ ለመስራ አስበው ነበር ፤ ከመፈራረማቸው በፊት እያንዳንዱ አጀንዳ ተነቦላቸው ያመኑበትን እና ያላመኑበትን ነገር ለይተው በማስቀመጥ ያልተነጋገሩባቸውን ጉዳይ  ቃለ ጉባኤው ላይ የተጨመሩትን ነገሮች በማስወጣት በከባድ ጥንቃቄ ቃለ ጉባኤውን ሊፈርሙ ችለዋል፡፡
 ይህ በእንዲህ እያለ የባለፈው ሲኖዶስ ወቅት በአቡነ ገሪማ አማካኝነት የተነጋገሩበት ሳይሆን ያልተነጋገሩበትን ጉዳይ ለጋዜጠኞች መግለጫ በአቡነ ጳውሎስ አማካኝነት ሊነበብ ችሎ ነበር ፡፡ አሁን ግን ይህን የመሰለ ሴራ ለመስራት አባቶች መንገድ ስላሰጧቸው ሴራቸውን መድገም አልቻሉም ፤ ጉባኤው ከተጠናቀቀ በኋላ ጋዜጠኞች ተጠርተው የቀናት ቆይታቸውን መግለጫ ለመስማት ብዙዎች መቅረጸ ድምጻቸውን በማስተካከል ሲጠባበቁ ነበር ፤ መግለጫ አርቃቂ ኮሚቴው የተነጋገሩባቸውን ጉዳዮች አንኳር አንኳሩን በመለየት ለሚዲያ በሚሆን መልኩ አዘጋጅቶ ሲያቀርብ አቡነ ጳውሎስ ማህበረ ቅዱሳንን የሚመለከተው አላነብም ብለው በማስቸገራቸው ፤ አባቶች ‹‹በቃ እርስዎ አያንብቡ ሌላ አንባቢ መርጠን እናስነብባለን ›› የሚል አቋም እንደያዙ አቡነ ጳውሎስ ሙሉው ለማንበብ መስማማታቸውን ገልጸዋል ፤ እርሳቸው ባይዋጥላቸውም የተጻፈውን አንድ ሳያስቀሩ ማንበብ ችለዋል ፤ ይህ ጉዳዬ ከሞላ ጎደል ከባለፉት ስብሰባዎች የአባቶች አንድነት የታየበት ፤ ተጽህኖ ማሳደር የቻሉበት ፤ መናፍቃን እና ተሀድሶያውያኑን በመሰል ትምህርታቸው ከቤተክርስትያን አንድነት ያወገዙበት ጉባኤ በመሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡

10 comments:

 1. በአባቶች ልቦና አድሮ ሥራውን የሠራው አንድ እግዚአብሔር ነው ፡፡ የአባ ሰላማ ድረ ገጽ አራት አባቶች የፈጸሙትና የወሰኑት አስመስሎ በገጹ መዳርና መኳል ጀምሯል ፡፡ በእናንተም እንደ እዛ አይሁን እንጅ የአቡነ ገሪማን ስም ጠቅሳችኋል ፡፡ ይኸ አያስፈልግም ፡፡ ይህችን ቤተ ክርስቲያን ከስንት ወረራ ለዘመናት ጠብቆ ያቆያት ፈጣሪ ለሁሉም እንደ ሥራው መስጠቱ ፣ የእጁንም ማስረከቡ ቢዘገይ እንጅ አይቀርም ፡፡ እናም ሁሎችንም አባቶች በቀና እንመልከት ፣ ቢቻለንም እናቅርባቸው ፤ ያልተረዱት ፣ ከእውነታውም የራቁበት ፣ በሌሎች የተነገራቸው ብዙ ጉዳይና ምክንያት ሊኖር ይችላል ፡፡ ጥርጣሬአቸውንና ውዥንብራቸውን ማስወገድ እንዲችሉ ፣ በፍቅርና በክብር እንቅረባቸው ፣ እናማክራቸው ፡፡ አንዳንዴም ባለማወቅና ባለመረዳት ስህተትን መፈጸም የተለመደ ነውና ፡፡ ካለፈው ሁሉም ቢማማር ፣ የወደፊቱ ጉዞአችን የተሻለና ቀና ይሆናል ፡፡ የስማችሁን ያህል ሁኑ ፤ አንድነትን ፍጠሩ ፤ መከፋፈልን ስበሩ ፤ ይኸ ለጠላት የውጊያ ሜዳ ማሳጣትም ይሆናልና ፡፡

  እግዚብሔር ለሁሉም ቀና አስተሳሰብ ይስጥልን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ደረጄ ከአ.አMay 26, 2012 at 11:08 AM

   እግዚአብሄር እንዲህ አደረገ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁን እያልኩ እባካችሁ አባሰላማዎች እንደሚነዙት የስም ማጥፋት የሚመስል ነገር ላለመክተት ቢሞከር ደህና ይመስለኛል ምክንያቱም ለእኛ እውነታው ብቻ ነው የሚጠቅመን ሰዎች በሰፈሩት ቁና እግዚአብሄር ይከፍላቸዋል ይህንንም በዕድሜያችን ያሳየናል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ደስ አሰኝቶናል፡፡ እናንተ ግን እባካችሁ በአባ ሰላማ ብሎግ የምናየው ሰውን/ግለሰቦችን የሚነካ ነገር በተቻለ መጠን ቢቀር እወዳለሁ፡፡ ክርስትናችን በዚህ ሳይሆን ለቤቱ እና ለቃሉ እንዲሁም ለፍጥረቱ ባለን ፍቅር ይለካልና፡፡
   ኢትዮጵያን / ቤተክርስቲያናችንን እና ሁላችንንም በቸርነቱ ይጠብቀን፡፡

   Delete
 2. Wud Andadregen lemerejachihu enamesegnalen. beahunu yeSinodos gubae Amlak yehizibun chinketina enba yayebet new. Abatoch yihinin yahil betigist ena betiniqaqe hulun betigat mesratachew biyasmesegnachewim gidetachewim new. ke'enersu yemitebekew yihew new. lelawinima titewit yele yealmun neger. ahunim beyetalka andand telkasha neger yemiyasib yemiyasera linor yichilal yinoralim ya malet ye'aganinit sira silehone abatochim saninik ena sanisadeb fetari endiyaswegdilachew mematsen new yemiyasifelgew. Habit nibret lemenekuse minu new maseb yalebin yihenin new lelije, lebetesebe awersalhu yemibal neger yele. endiya bayihonima behig tetebiqew beteseb mesritew menor yichilu neber silalhone new minkusinan yemeretut. engidih hulachinim lebetekrstianachin selamin, andinetin, tigatin, mastewalin, fikirin endiseten begara metseley alebin sile alemu hulu. Menafikanim eskahun yebetebetut, yamtatut, yachibereberut, yatalelut, yekefafelut ena kifu yasasebut hulu ende gum teno yitfabachew. betekrstianachin endemitastemirew yesewin tifat anfeligim benisiha temelisew (yehaset sayhon kenonachewin beagibabu)yemimelesu kehone semayawit eyerusalemin lemewres yabkan. yihe hulu dikam, rucha, fitigia ena hasab wede ewnetegnayitu bota lemegbat newina.

  ReplyDelete
 3. ይህን ያደረገው እግዚአብሄር ነው። ወደፊትም በአባቶቻችን አድሮ የሰራ እግዚአብሄር ወደፊትም ቤቱን እንዲጠብቅ አሳዳጆቹንም ከቤቱ እንዲያስወጣ እንለምነው። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ሁላችንንም ያጽናን ያበርታን አሜን።

  ReplyDelete
 4. ከሰደበኝ የደገመኝ እንዲሉ ፣ ይህን ጽሁፍ ብታወጡና ቃላቸውን እናንተም ብታስተጋቡት ፣ መልካም አይመስለኝም ፡፡ ምናልባት አንድ ቀን ህዝብ ማወቅ የሚገባው ማስረጃ ሊሆን ስለሚችል በማለት ብቻ ጽፌላችኋላሁ ፡፡

  የኘሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ጠበብቶች ስውር ሴራ ፣ በአንቀልባ ሸፋፍነው ያዘሉት ድብቅ ትምህርትና ዓላማ ፣ በብስጭት ምክንያት በራሳቸው ደጋፊ ገሃድ ወጣ ፡፡ በአባ ሰላማ ድረ ገጽ አንድ ብሶተኛ አስተያየት ሰጭ የክርስቶስ ቤትንም እንደ ፖለቲካው በጐጥና በጐሳ ለማድረግ አስበው እየተንቀሳቀሱ እንደነበር በሰጠው አስተያየት ገለጸ ፡፡ አዘጋጆቹም የሃሳቡ ተጋሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጠው ፣ እንዲህ ዓይነቱን ከፋፋይ ርዕስ ለህዝብ አቅርበው ማስነበባቸውና ፣ አብሮ እንዲነበብ እኔ የጻፍኩትን መልስ አፍነው መያዛቸው ነው ፡፡ ምን ያህል የቆሸሸ ሥራ እየሠሩ እንደነበር ፤ በምን ተጠምደውና በማን አለኝታ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ አንድ ማስረጃ ነው ፡፡ አባ እስጢፋኖስ ዘጉንዳጉንዲን እያወደሱ ፣ አንዴ አቡነ ተክለሃይማኖትን ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አፄ ዘርዓ ያዕቆብን እያወገዙ የሚጽፉት ሁሉ ከዚሁ የጎሣ እምነታቸው የተነሳ መሆኑን ዛሬ በንዴት ካወጡት ቃል ተረዳሁ ፡፡ በድረ ገጻቸው የተለጠፈው አስተያየት እንደሚከተለው ይነበባል፡፡

  "የተገፋው ወንጌል እንጂ ሰው አይደለም። የተጠላው እውነት እንጂ ተሀድሶ አይደለም። የተወገዘው ክርስቶስ እንጂ ሰባኪያን አይደሉም። የሻገተ እንጀራ ይሻለናል እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የነበራትን ንጹህ እንጀራ አንበላም ያሉት የሻገቱ ጳጳሳት ናቸው። የኔሮን ጳጳሳት ውግዘት ክርስትናን እንደሰደድ እሳት ከማቀጣጠል አያቆምም። የነዚህ ጳጳሳት ግዝት ዘበከንቱ አንድ ነገር አስተምሮናል። ቤተክርስቲያኒቱን ለአዲሱ የሸዋ መንግሥት ለማኅበረ ቅዱሳን ማስረከባቸውን። ይሁን እንጂ የወንጌል አገልጋዮች ለክርስቶስ መንግሥት መስፋትና ለቤተክርስቲያን ቀደምት አስተምህሮ መጠናከር የበለጠ መደራጀት፤ መሰባሰብ፤ ኅብረት መፍጠር፤ መትጋትና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መፋጠን እንደሚገባ መልእክት ያስተላለፈ ሆኗል።
  10 እና 15 ሰው በማውገዝ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የተቀጣጠለው የወንጌል እሳት አይቆምም። አንድ እውነት በማስቀመጥ ልቋጭ። የወንጌል ጠላት ማቅ ይወድቃል፤ ወንጌል ግን እንደእሳት ይስፋፋል።"

  ወዳጅ መሳይ ጠላትህን የምታዳምጠው አንድም ሲደሰት ወይም ሲበሳጭ አለበለዚያም ሲሰክር ነው ፤ ደብቆ የያዘውን ሁሉ ይዘረግፍልሃል ፡፡ "ቤተክርስቲያኒቱን ለአዲሱ የሸዋ መንግሥት ለማኅበረ ቅዱሳን ማስረከባቸውን" የሚለው ቃል መልዕክቱ ምንድር ነው ? አሁን ማን ይሙት የማኀበረ ቅዱሳን አባሎች በሙሉ የሸዋ ሰዎች ብቻ ሆነውባቸው ነው ወይስ የዘርዓ ያዕቆብ ዝርያ አድርገዋቸው ?

  ለኔ የቤተ ክርስቲያን በትረ መንግሥት ግልበጣ ተፈጽሞ መቆየቱንና ማኀበረ ቅዱሳንን ለማጥፋት የሚታገሉት በጎጥ ጭንብል ዓይናቸውን ሸፍነው እንደሆነ አላወቅሁም ነበር ፤ ዛሬ ተማርኩኝ ፡፡ እንደ እነሱ ሃይማኖትን በጎጥ የሚያምን ካለ እነሱኑ መከተል ይችላል ፤ ነገር ግን ይህን ተንኰላቸውን ሳያውቅ አብሮ የሚያጫፍር የኔ ብጤ ገልቱውን ግን እንዲገነዘብ ለማስተማር መንገዱ ሁሉ መቃኘት አለበት ፡፡ ሌላው የተደጋገመ ግድፈትም ክርስቲያን ነን እያሉ አባቶችን መዝለፋቸው ነው ፡፡ ይኸኛው የእምነት ጎደሎነት ብቻ ሳይሆን የአስተዳደግ በደልም ጭምር ነው ፡፡ የክርስትና ትምህርት በሰፈራቸው እንኳን ተሰብኮ የሚያውቅ አይመስለኝም እንኳንስ ክርስቲያን ሊሆኑና ሊባሉ ፡፡ ለወደፊቱ ይህን ዓይነቱንም ዓላማ ጭምር መዋጋት ያስፈልጋልና ከወዲሁ እንዲታሰብበት በማለት ተጻፈ ፡፡

  ReplyDelete
 5. "ክርስቲያን ነን እያሉ አባቶችን መዝለፋቸው ነው ፡፡ ይኸኛው የእምነት ጎደሎነት ብቻ ሳይሆን የአስተዳደግ በደልም ጭምር ነው ፡፡ የክርስትና ትምህርት በሰፈራቸው እንኳን ተሰብኮ የሚያውቅ አይመስለኝም እንኳንስ ክርስቲያን ሊሆኑና ሊባሉ ፡፡ ለወደፊቱ ይህን ዓይነቱንም ዓላማ ጭምር መዋጋት ያስፈልጋል"

  ReplyDelete
 6. "ሌላው የተደጋገመ ግድፈትም ክርስቲያን ነን እያሉ አባቶችን መዝለፋቸው ነው ፡፡ ይኸኛው የእምነት ጎደሎነት ብቻ ሳይሆን የአስተዳደግ በደልም ጭምር ነው ፡፡ የክርስትና ትምህርት በሰፈራቸው እንኳን ተሰብኮ የሚያውቅ አይመስለኝም እንኳንስ ክርስቲያን ሊሆኑና ሊባሉ ፡፡ ለወደፊቱ ይህን ዓይነቱንም ዓላማ ጭምር መዋጋት ያስፈልጋልና ከወዲሁ እንዲታሰብበት በማለት ተጻፈ ፡፡"
  መናፍቃኑ እኮ ለምን እምነታቸውን እንደአመኑበት ከሚመስሏቸው ጋር እንደማይከውኑት አይገባኝም:: ለነገሩ ጠላትነታቸው ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከልጇ እንድሁም የልጇን አምላክነት ባመኑት ላይ በመሆኑ ያቻሉትን ያክል ነፍስ እስኪያስከዱ ድረስ ድካማቸው ይቀጥላል:: የሚያሳዝነው በስጋ የኛው ወንድሞች የሆኑና ከአንድት የተዋህዶ እምነት አብረን የነበርን ያራሳችን የነበሩና ከእሷ ከተዋህዶ ተፈናጥረው ከወጡ በኋላ እኛም አንመለስባትም ሌላም አይከብርባትም አይነት ምቀኝነት ነው:: ሲፈልጉ በመሰላቸው በወንጌል አትሰብክም እርሱ ሳይሳካ ደግሞ በዘር እና በጎጥ በጣም ሲብስ ደግሞ በዘለፋ፣ በስድብ በሃሜት ሰውን መንደፍ ሆኗል ስራቸው:: እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጣቸው እንጅ ምን ይባላል:: የተዋሕዶ ልጆች የዋሕ ብቻ አትሁኑ ብልህም ጭምር እንጅ:: ሌላው በአባቶ ቻችን አድሮ ለቤተ ክርስቲያን መልካሙን ላደረገ ለርሱ ለፈጣሪ ክብር ምስጋና ይግባው::

  ReplyDelete
 7. Are you learning from your mistakes? If show us in practice

  ReplyDelete