(አንድ አድርገን ሚያዚያ 26 2004ዓ.ም)፡- ትላንትና ማታ ኢቲቪ ላይ መንግስት የሰጠው መግለጫ በጣም አስገርሞኛል
፤ ይህ የሀይማኖት ጉዳይ ይህን ያህል መግለጫ የሚስወጣ ነገር ላይ ይደርሳል ብዬ አለመገመቴ ይሆናል ፤ ይህን የመሰለ መግለጫ የሰማሁን
በ97 ነበር ፤ መግለጫው በጣም በርካታ ነገሮችን ያካተተ በመሆኑ የ20 ደቂቃ ቆይታን ወስዷል ፤ መግለጫው ተሰጠው ዶ/ር ሽፈራው
ከሚመሩት ፌደራል ጉዳዮች ነበር ፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚሄድበት መስመር ያደረገውን ነገር በዝርዝር ያስቀመጠም መግለጫ ነበር
‹‹ትእግስታችንን ከፍርሀት አትቁጠሩብን›› በማለት አበክሮ መንግስት ተንፍሷል ፤ በተለያዩ መስኪዶች የሚደረገውን ነገር ቀን በመጥቀስም
ለማቅረብ ሞክሯል ፤ ከ2 ቀን በፊት ‹‹በሃይማኖት ጉዳይ ላይ የለዘበ አቋም እንዳታሳዩ›› የሚል መመሪያ ከመንግስት መውረዱን ጽፈን
ነበር ፤ በልደታ ፍርድ ቤትም ከ19 አቃቢ ህጎችና ዳኞች መሀከል 13ቱ በቅዳሜ ቀን ህገወጥ ስብሰባ ሲያደርጉ መደረሱንም ገልጸን
ነበር ፤ ትላንትና ግን በጣም የጠነከረ መግለጫ ተሰጥቷል ፤ በፌስቡክ እና በፓልቶክ የሚዶለቱትን ነገር እንደ ምሳሌ አንስቷል ፤
ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለተየቀው ጥያቄ መንግስት መልስ መሰጠቱን አሳስቧል
፤ ነገር ግን ሌላ አላማ ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ተጠንቀቁ በማለት
መልእክት አስተላልፏል ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አክራሪ ብሎ ከፈረጃቸው ድርጅቶች ጋርም ሚደረግን ግንኙነት እንዲያቋርጡ ጠቁሞ
አልፏል ፤ ማህበረሰቡ መስኪድ ሄዶ ጸሎት አስርጎ መመለስ የማይችልበት ደረጃም መድረሱን ጠቁሟ ፤ ሰዎች በየመስኪዱ ከኢማሞች ማይክራፎን
እስከመቀማት ደርሰዋል ብሏል ፤ የፖሊስ ኋይል ላይም አካላዊ ጉዳት አድርሰዋል በማለት ያትታል ፤ መንግስትና ሀይማኖት የተለያዩ
ነገሮች መሆናቸውን አትቷል ፤ መንግስት ለማንኛውን የእምነት ተቋም እንደማያደላም ያስቀምጣል ፤ መንግስት ከህገ መንግስቱ ጎን መቆሙንም
ጠቁሟል ፤ ከቀናት በፊት በአርሲ በአርብ ቀን 4 ሰዎች መገደላቸውን
ለማወቅ ችለናል ፤ በአወሊያ አካባቢም 2 ሰዎች መሞታቸውን የመገናኛ ብዙሃን ጠቅሰዋል ፤
ሀገር ሰላም ስትሆን ነው ሰው ወጥቶ መግባት የሚችለው ፤ የእነርሱ ሰላም ማጣት በተዘዋዋሪ እኛንም ሰላም እንዳያሳጣን
እሰጋለው ፤ ለእነርሱ የተሰነዘረው ሆን ብሎም ይሁን በአጋጣሚ እኛ ላይም እንዳያርፍ ስጋት አለኝ ፤ እኔ መግለጫው ያስገረመኝ ውስጡ
የያዘውን ነጥብ ሳስበው ብቻ ነው ፤ ነገሩ ምን ያህል የመንገስት ራስ ምታትም እንደሆነ ለማወቅ ችያለሁ ፤ ጥያቄዎች ሁሉ በጊዜው መፍትሄ ቢሰጣቸው ለዚህም ባልተደረሰ ነበር ፤ አሁንም የእኛን የዋልድባ ጉዳይ መሰረታዊ የሆነ
መፍትሄ መንግስት ካልሰጠ ህዝቡ ማንጎራጎሩን አያቆምም ፤ በአሁኑ ሰዓት ወደ ዋልድባ የተመመው ህዝብ እግሩን ወደ ኋላ አይልም ፤
ይህ ጉዳይ ከባድ ነው ፤ መልሱን ከመመለስ በፊት ስህተትን ማመን ግድ ይላል ፤ መንግስት ቱግ ብሎ በመቆጣት እና ያልሆነ መግለጫ ማውጣትና እርምጃም መውሰድ
የለበት ፤ እንደ መንግስት ‹‹ሆደ ሰፊ›› መሆን አለበት ብለን እናምናለን ፤ አይደለም ሀገር ቤተሰብ ማስተዳደር ራሱ ከባድ መሆኑን
እናውቃለን ፤ መንግስት ሆደ ሰፊ ካልሆነ መንግስትንና ህዝብ ያላቸው ግንኙነት ሆድና ጀርባ ስለሚሆን ስለሚያደርጋቸው ነገሮች ጠንቅቆ ሊያስብባቸው ይገባል እንላለን ፤ ህዝብ ሁል
ጊዜ ጥያቄ ማቅረቡንም ወደ ኋላ አይልም ፤ ለምን ጠየክም አይባልም ፤ ጥያቄዎች ሁላ ተገቢ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ፤ የምዕመኑን ጥያቄ
መደፍጠጥ ግን ህዝቡን ሌላ ነገር እንዲያስብ ቂም እንዲይዝ እና አላስፈላጊ ነገር ውስጥ እንዲገባ መንገዱን ይከፍትለታል ፤ በዚያን
ጊዜ የሚደረግ ነገር ለማንም የሚጠቅም አይሆንም ፤ እኛ ሀገራችን ያላትን አንጻራዊ ሰላም ይዛ እንድትቀጥል ጽኑ ምኞታችን ነው ፡፡
ትንሽ ጊዜ ወስደው ቢመለከቱን ከመግለጫው ይልቅ የተሸለ ሀሳብ ይቀርባልም ብለን እናስባለን ፤ ይባስ ነገሮች እንዳይከሩ መንገዳቸውም እንዳይሰፋ ስጋት አለን ፤ አሁን ያለንበት ዘመን ነገሮችን ተነጋግሮ መፍታት የሚቻልበት ወቅት ነው ብለን ስለምናምንም ሊሆን ይችላል ፤ መንግስት ሲናገር ሚሊዮኖች ይሰማሉ ፤ጊዜውና ሁኔታውም ያስፈራቸዋል፤ ሚሊዮኖችም ራሳቸውን ፍርሀት ላይ ይጥላሉ ::
ትንሽ ጊዜ ወስደው ቢመለከቱን ከመግለጫው ይልቅ የተሸለ ሀሳብ ይቀርባልም ብለን እናስባለን ፤ ይባስ ነገሮች እንዳይከሩ መንገዳቸውም እንዳይሰፋ ስጋት አለን ፤ አሁን ያለንበት ዘመን ነገሮችን ተነጋግሮ መፍታት የሚቻልበት ወቅት ነው ብለን ስለምናምንም ሊሆን ይችላል ፤ መንግስት ሲናገር ሚሊዮኖች ይሰማሉ ፤ጊዜውና ሁኔታውም ያስፈራቸዋል፤ ሚሊዮኖችም ራሳቸውን ፍርሀት ላይ ይጥላሉ ::
ከጠቅላይ ሚኒስትራችን የፓርላማ ንግግር በፊት ይች መግለጫ ታስቦባታል ፤ ነገር ግን ማህበረሱ ድንገተኛ እንዳይሆንበት
ስለ ወቅቱ በሀይማኖት ዙሪያ ያለው ሁኔታ በሰፊው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዳሰሳ ሰጥተውበታል ፤ በመሀሉም የማህበረ ቅዱሳንን ስም አንስተው
አልፈዋል ፤ ይህ ነገር በሆነ ከ15 ቀናት በኋላ ይህን መግለጫ ሰምተናል ፤ ቀጣዩን ለጊዜው መገመት አንችልም ፡፡
'ወዳጅህ ሲታማ ለእኔ ብለህ ስማ' አለ የሀገሬ ሰዉ።
ReplyDeleteየሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጥያቄ መጅሊሳችንን እኛ እንምረጥ ኃይማኖታችንን የማይገልጽ ትምህርት አንፈልግም ማለት መሆኑን ራሳቸው ነግረውናል ሌላ አላማምየለንም ብለዋል ታዲያ የመንግስትን አንድምታ ምን ይሉታል የነሱ ጥያቄ እኮ ወቅታዊ ነው የኛ ዝምታ ብቻ ነው የሚገርመኝ:: በኛስ ቤት የማናውቃቸው ጳጳሳት አልተሾሙብንም ወይ፣ በኛስ ሙሉ ወንጌሎች በቤታችን እመቤታችንን እስኪሳደቡ፣ ቅዱሳንን እስኪያቃልዱ በሃይማኖታችን ላይ ሲሸፍጡብን እያየን አይደለም ወይ ታዲያ አባ ጳውሎስ ይህን ክፋት ጥበቃ እያሰጡ ይህን የተቃወሙትን እያስገላመጡ በኃይልም እያስቀጡ አይደለምን:: ሊቃውንቱ ተጥለው ዳዊትን እንኳ በቅጡ ያልተማሩት አልነገሱባትምን:: ያለምንም ሎተሪ አሸናፊነት ሚሊየነሮችና ባለ ሚሊዮ ን ቪላ ቤት ያላቸው መነኮሳት እና ጳጳሳት የሉምን:: በቤታችን እኮ እጃችንን ከሙዳየ ምጽዋት ላይ እናንሳ ያሉት የሚገፉባት በመቶዎቹ ቺዎች የዘረፉት የበለጥ በጀት ወዳለባቸውና አነስተኛ ቁጥጥር ወዳለባቸው ክፍሎች ያለፈ የመቶ ሺዎቹን ዝርፊያ ልምድ ወደሚሊዮን ከፍ እንዲያደርጉት የሚመደቡባት መናፍቃኑ ከመምሪያ የሚንሳፈፉባት ኑፋቄአቸው እንደ ነውር መሆኑ የቀረበትና የበለጥ ተደማጭነት የሚፈቀድባት አይደለችምን:: ታዲያ በዚህ ጊዜ እኛስ ፍትሃ ነገስቱ እንደሚያዘው መሪዎቻችንን መምረጥ የለብንም በቤተ ክርስቲያናችንስ ጉዳይ እስከመቼ አያገባንም እያልን በጠራራ ጸሃይ ዝንዘርፍ እንኖራለን በቃ በቃ እንበል ከዚህ በላይ ምን እንደምንፈራ አይገባኝም:: ፍርሃትን ራሱን እንደፈራን መሞታችን እኮ ነው::
ReplyDelete