Wednesday, May 9, 2012

ተድባብ ማርያም ሞት ነገሰ፤

(አንድ አድርገን ግንቦት ልደታ 2004ዓ.ም)፡- ከአዲስ አበባ በ600 ኪሎሜትርና ከሳይንት አጅባር በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝው የተድባብ ማርያም ገዳም የዛሬዋን ቀን የቅድስተ ቅዱሳን፣ ንጽሂተ ንጹሃን የእመቤታችንን ልደት ለማክበር በጉዞ ላይ ከነበሩት 17ቱ በመኪና አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት ወረዳ በምትገኝው እና ግንቦት 1 ቀን ርእሰ አድባራ ተድባብ ማርያም ገዳም ለንግስ በመጓዝ ላይ የነበሩ  ሰዎች በደረሰባቸው የመኪና የመገልበጥ አደጋ በእለተ ሰኞ በ29/08/2004ዓ.ም   17ቱ ህይወታቸው ማለፉን ለማወቅ ችለናል፤

በ29/08/2004ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን በደረሰው አደጋ ወዲያውኑ 17 ምዕመናን ህይወታቸው ማለፉን ሁለት ምዕመናን ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውን ፤ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ሳይንት አጅባር ህዳር 11 ሆስፒታል መግባታቸውን ፤ አንድ ምዕመን ደግሞ አጅባር ጤና ጣብያ እርዳታ እየተደረገለት መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሞቱት ምእመናን ውስጥ አስሩ ተድባብ ማርያም ገዳም ማክሰኞ በ30/08/2004ዓ.ም  የቀብር ስርአታቸው  ተፈጽሟል ፤ የቀሪዎቹ ምዕመናን አስከሬን ወደመጡበት አካባቢ ተሸኝቷ፡፡ ገዳሙ ጋር ሊደርሱ ጥቂት ኪሎ ሜትስ ሲቀራቸው አንድ መነኩሴ እና ሁለት ወጣቶች መኪናው እንዲያቆምላቸውና የተቀረውን መንገድ በእግራቸው እንደሚሄዱ ተነጋግረው መንገድ ከጀመሩ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ አደጋው መከሰቱን 3ቱ በዚህ አይነት ሁኔታ መትረፋቸውን ለማወቅ ችለናል ፡፡በቅርብ ከምናውቃቸው ከፈረንሳይ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስትያን አባ እንዳላማው እና የሰንበት ትምህርት ቤቱ አንጋፋ አባል የነበረው መጋቢ ስርዓት ሀይሌ የአደጋው ሰለባ ሆነዋል ፡፡

በመኪና አደጋ ህይወታቸው ላለፈውና ቀብራቸው እዚያው በገዳሙ ለተፈጸመው ምዕመናን ብጹእ አቡነ ገብርኤል በተገኙበት በፈረንሳይ አቦ ቤተክርስትያን በ30/08/2004ዓ.ም አመሻሹ ላይ ጸሎተ ፍትሀት ተደርጓል፡፡





‹‹አንድ አድርገን›› ፡- ‹‹ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ቸሩ እግዚአብሔር መጽናናቱን ያድላቸው  ፤ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሎች የሚገኙትን እህትና ወንድሞቻችንን ወደ ቀደመ ጤንነታቸው ይመልሳቸው›› አምላክ ነፍሳቸውን ከአብርሀም እና ከይስሀቅ ከያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን በማለት የሀዘናችሁ ተካፋይ መሆናችንን ለመግለፅ እንወዳለን  ፡፡

9 comments:

  1. sad!!
    በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ቸሩ እግዚአብሔር መጽናናቱን ያድላቸው ፤ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሎች የሚገኙትን እህትና ወንድሞቻችንን ወደ ቀደመ ጤንነታቸው ይመልሳቸው›› አምላክ ነፍሳቸውን ከአብርሀም እና ከይስሀቅ ከያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን

    ReplyDelete
    Replies
    1. በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ቸሩ እግዚአብሔር መጽናናቱን ያድላቸው ፤ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሎች የሚገኙትን እህትና ወንድሞቻችንን ወደ ቀደመ ጤንነታቸው ይመልሳቸው›› አምላክ ነፍሳቸውን ከአብርሀም እና ከይስሀቅ ከያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን

      Delete
  2. በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ቸሩ እግዚአብሔር መጽናናቱን ያድላቸው ፤ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሎች የሚገኙትን እህትና ወንድሞቻችንን ወደ ቀደመ ጤንነታቸው ይመልሳቸው›› አምላክ ነፍሳቸውን ከአብርሀም እና ከይስሀቅ ከያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን በማለት የሀዘናችሁ ተካፋይ መሆናችንን ለመግለፅ እንወዳለን ፡፡

    ReplyDelete
  3. ayi Ante Amlak , Ebakih lazenut Metsinanatin sitilin.

    ReplyDelete
  4. K kedereje weynye gar yetegazu nachew wyenis ke mahibere kidusan gar

    ReplyDelete
  5. EGZIABHER nefsachewun yimar kedegagochu kidusan abatochachin gar yidemirlin!!!

    ReplyDelete
  6. አምላክ ከናንተ ጋር ይሁን

    ReplyDelete
  7. Egziabher nefs yimar!

    ReplyDelete
  8. አምላክ ነፍሳቸውን ከአብርሀም እና ከይስሀቅ ከያዕቆብ አጠገብ ያኑርልን ቸሩ እግዚአብሔር መጽናናቱን ያድላቸው::

    ReplyDelete