Tuesday, May 8, 2012

ሊቀ ስዩማን ኀ/ጊዮርጊስና አቡነ ፋኑኤል ሴራ ሪፖርታዥ(ክፍል ሁለት)

  •       የጆቢራዎቹን ህገወጥ ደብዳቤ ያከሸፉት ቆሞስ መላእከ ጽዮን አባ ሕሩይ ወንድይፍራው ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊነታቸው ተነስተው የማደራጃ መምሪያው ምክትል ሓላፊ የነበረው መምህር እንቁባህርይ ተከስተ በቦታው ተሹመዋል፡
  • ·         የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቀለምንጦስ “እኔ በማላውቅበት ኹኔታ የመምሪያው ሓላፊ ሊቀየሩ አይችሉም” በማለት ርምጃውን ተቃውመዋል፡፡
  • ·        ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለተሃድሶ መናፍቃን ከለላ መስጠቱን ቀጥለውበታል፡፡
  • ·        ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት የቤተክርሰቲያን ዋነኛ ችግር የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለህገ ቤተክርስቲያን ተገዥ አለመሆናቸው  ተናግረዋል


ዝርዝሩ እንደሚከተለው አቅርበነዋል
በክፍል አንድ ዘገባችን የጆቢራዎቹ ህገወጥ እንቅስቃሴ ቆሞስ መላእከ ጽዮን አባ ሕሩይ ወንድይፍራው ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃለፊ ያከሸፉት ቢሆንም እርሳቸው ላይ ተጽእኖ ለማሳደር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን፤ ባለፈው አርብ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የጨለማው ሲኖዶስ አባላት የፈጸሙትን ሸፍጥ ዝርዝሩን ለማቅረብ ቃል በገባነው ቃል መሰረት ይዘን ቀርበናል፡፡


መንግስት ከአክራሪ እስልምና ጋር በተያያዘ ሐሙስ ምሽት መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ እርሱንም ተከትሎ በአርሲ አካባቢ በተከሰተው ግጭት አማካኝነት ሙስሊሙ ማህበረሰበ ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ተጋጭቶ 4 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል ይህን ተከትሎ የአካባቢው እስልምና ምክር ቤት ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቶ ነበር ፤ ከሰሞነኛው የጠቅላይ ሚኒሰትሩ ንግግር መነሻ በማድረግ ማኅበረ ቅዱሳንን በማይወክለው  መንገድ ለመፈረጅ የተሃድሶ መናፍቃን ልሳን የሆኑ ድረ-ገጾች የገደል ማሚቱ ሆነው የጠቅላይ ሚኒስሩን ንግግር ሲያስተጋ ነበር፡፡ ለተሃድሶያውያኑ እና  መናፍቃኑ ሽፋን እየሰጡ ያሉት ቅዱስነታቸው አርብ ከሰዓት በኋላ ለርክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከየአህጉረ ስብከቶቻቸው ለስብሰባው አዲሰ አበባ የገቡትን ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት አስቸኳይ ጉዳይ ስላለ ለአርብ ከሰዓት በኋላ 9፡00 ላይ እንዲገኙ ጥሪ ጥሪ ተላልፎላቸው ነበር ፡፡ በጉዳዩ ላይ የፓትሪያሪኩ ቀኝ እጅ የሆኑት ብጹዕ አቡነ ገሪማ፣ ብጹዕ አቡነ ማርቆስ፣ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል እና ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ ከፓትሪያሪኩ ጋር ቀድመው ጉዳዩን መክረውበት እንደነበረ የደረሰን የውስጥ ምንጭ ይጠቁማል፡፡
 የጨለማው ሲኖዶስ ዋንኛ ሃሳቡን እውን ለማድረግ ስምምነት ላይ በመድረስ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ለማሳመን ተዘጅተው ነበር፡፡ የስብሰባው አጀንዳ ቅዱስነታቸው እንዲህ በማለት ነበር የገለጹት “መንግስት ትናንት ማታ አክራሪነትን በተመለከተ መግለጫ እንዳወጣ ሰምታችኋል? እኛም ጋር ችግር አለ ፤ ስለዚህ እኛም መግለጫ ማውጣት አለብን፡፡” በማለት ተናገሩ፡፡ ከዚህ በፊት  ማን ነበር “ቤተክህነቱ መንግስት ያሰበውን ብቻ ሳይሆን ወደ ፊት ሊያስበው ይችላል ብለው ያሰቡትን ለመፈጸም ይፋጠናሉ” ያለው? አቡነ ጳውሎስ ይህን ሲናገሩ ብጹአን ሊቃነ - ጳጳሳት “እኛ ጋር ያለው ችግር አላወቅነውም እርስዎ ይንገሩን?” ብለዋቸዋል፡፡ አስቀድመው ከቅዱስነታቸው ጋር የመከሩት አራቱ ሊቃነ ጳጳሳት (ብጹዕ አቡነ ገሪማ፣ ብጹዕ አቡነ ማርቆስ፣ ብጹዕ አቡነ ፋኑኤል፣ ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ) “ይህ እኮ የታወቀ ነው” አሉ ‹‹ሾላ በድፍኑ››› ነገሩን ሳይገልጡትና ሳያብራሩት:: ብጹዕ አቡነ ቀውስጦስና ብጹዕ አቡነ ህዝቅኤል “ ቅዱስ አባታችን እንኳን ከርስዎ መጣ እንጂ እኛ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ችግር እርስዎ ነዎት፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በአመት ሁለት ጊዜ ተሰብስበን እንወስናለን ነገር ግን አንዱም እንዳይተገበር እያደረጉ ያሉት እርስዎ ነዎት ፤ ውሳኔያችን አይተገበርም፡፡ ለህገ ቤተክርስቲያን  እየተገዙ አይደለም::” በማለት የቤተክርሰቲያን ዋነኛ ችግር የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለህገ-ቤተክርስቲያን ተገዥ አለመሆናቸው በግልጽ ተናግረዋቿል፡፡

አቡነ ጳውሎስ ከእዚህ በፊት እንደለመዱት  ይህን የመሰለ ከባድ ተቃውሞ ሲገጥማቸው  ለግማሽ ሰዓት ያህል አንዳች ሳይተነፍሱ በዝምታ ጊዜውን ያሳለፉ ሲሆን በዚህ ጊዜ ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት በጸሎት ዘግተው እንዲያሰናብቷቸው በትዕግስት ሲጠብቋቸው ተስተውለዋል ፡፡

ይህ ነገር አልሳካላቸው ሲላቸው አርብ ቀን አመሻሹ ላይ 11፡00 አካባቢ ደግሞ ሌላ ሸፍጥ ተጠነሰሰ፡፡ ለተሃድሶ መናፍቃንን ስውር አጀንዳ ላለመፈጸም ቤተክህነቱ ያጣውን በአላማ መቆምን ያሳዩትን ቆሞስ መላእከ ጽዮን አባ ሕሩይ ወንድይፍራው ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊነታቸው በማንሳት፤ ከተሃድሶ መናፍቃን ቅጥረኞች ጋር የጥቅም ትስስር ያለው የማደራጃ መምሪያው ምክትል ሓላፊ የነበረው መምህር እንቁ ባህርይ ተከስተን በቦታው ሹመዋል፡፡

ህገ ወጡን ደብዳቤ ከኃ/ጊየርጊስ ጋር በመሆኝ ሲያስፈጽም የነበረውን የመምሪያው ጸሐፊ የነበረውን መ/ር መኮንን ወልደ ትንሣኤ  የመምሪያው ምክትል ሓላፊ ሆኗል፡፡የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቀለምንጦስ “እኔ በማላውቅበት ኹኔታ የመምሪያው ሓላፊ ሊቀየሩ አይችሉም” በማለት የተወሰደውን ህገ ወጥ እርምጃ በሰዓቱ መቃወማቸውን ለማወቅ ችለናል ፡፡

ማህበረ ቅዱሳን ከአባ ሠረቀ ብርሐን ጋር በመሆን ላለፉት ሰባት ዓመታት የማህበሩን አገልግሎት ሲያደናቅፍ የነበረውን የማደራጃ መምሪያው ምክትል ሓላፊ የነበረው መምህር እንቁ ባህርይ ተከስተን ባለፈው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከኃላፊነት አንዲነሱ ጠይቆ እንደነበረ ይታወቃል ፤ በጊዜው የአባ ሠረቀ ብርሀን ጉዳይን ጫፍ አድርሶ  እልባት ያስገኝ ሲሆን የመምህር እንቁ ባህርይ ጉዳይ ግን  ተድበስብሶ በመቅረቱ በአሁኑ ሰዓት ማህበሩን  ዋጋ ሊያስከፍለው እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡ የጨለማው ሲኖዶስ አባላት ቤተክህነቱን በከፍተኛ ሁኔታ እያመሱት ይገኛሉ ፤ ይህን ህገ ወጥ ስራቸውንም አባቶች እና ምዕመኑ እንዲያውቁት የማድረግ ስራ ከማህበሩ ይጠበቃል ብለን እንገምታለን፡፡ በተለይ ኃ/ጊዮርጊስን በሚመለከት ያሉትን ማስረጃዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዲሁም ለምእመናን ይፋ እንዲያደርግ እየተጠየቀ ነው፡፡

እኛስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እይታ ግራ አጋብቶን ነበር ፤ አሁን ደግሞ የአቡነ ጳውሎስን ምን እንለዋለን ፤ አባቶች እሺ ቢሏቸው ምን ብለው ነው በሽብርተኝነት ላይ መግለጫ የሚሰጡት ? ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበሩ ላይ የተናገሩትን በመቃወም መግለጫ ያወጣሉ ወይስ በደንብ ያጠናክሩላቸዋል ? በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ፤ ባለፈው ሀሙስ የወጣው መግለጫ መንግስት ደረስኩባቸው ያላቸውን ነገሮች መሰረት በማድረግ ቢያወጣው ግማሽ እውነት ሊኖረው ይችላል ብለን እናምናለን ፤ ቤተክርስትያናችን ግን ነገሩን ከመቃወም የዘለለ ምን ልታደርግ ትችላለች ? ፤ ወይስ ይችን መልካም አጋጣሚ አድርገው በመጠቀም የአቡነ ፋኑኤልንና የኃ/ጊዮርጊስን የተንኮል ሀሳብ በመስማት  ሊያስመቱ ያሰቡት ይኖር ይሆን? እኛ ደብዳቤው ይፋ ሆኖ ሲወጣ የምናውቀው ነገር ይሆናል ፤ ግን መጠርጠሩ አይከፋም እንላለን፡፡ ‹‹ያልጠረጠረ ተመነጠረ ›› አይደል የሚባለው፡፡

የሲኖዶስ ስብሰባ በተካሄደ ቁጥር እስከ መቼ ነው የምንበጠበጠው ? ፤ እስከመቼስ ነው ህገወጦቹ እየተደገፉ ቤተክርስትያኒቱን በሀቅ ለማገልገል የቆሙት ሰዎች  እየተገፉ የምናየው? ፤ የሲኖዶስ አባቶች በጥቅምትና በግንቦት ላይ የሚሰበሰቡት የቤተክርስትያኒቱን ችግር ለመፍታት የተሰሩ ስራዎችን ለመነጋገር የወደፊት አቅጣጫም ለመጠቆም ይመስለናል ፤ አሁን ግን እየሆነ ያለው ትልቁን ጉዳይ በማስረሳት ጥቂት ሰዎች የሚያነሱት አቧራ ላይ ጊዜያቸውን እንዲያጠፉ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል ፤ የዋድባ ገዳም መናንያንን  አቤቱታ ለመስማት ያልተከፈተ በር ለተንኮልና ለሴራ  ከአሜሪካ ድረስ ለመጡትን ሰዎች ግን ወለል ብሎ መከፈቱ ያስገርማል ፤ የዋልድባ ገዳም እንዲህ የህዝብና የመንግስት በተጨማሪ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን  መነጋገሪያ በሆነበት ሰዓት አስቸኳይ ስብሰባ ያልጠሩት አባት ለተንኮልና ለሴራ ተግባር አላላውስ ያሏቸውን አባት ከኃላፊነት ለማንሳት አስቸኳይ ስብሰባ ጠሩ ፡፡  እነዚህ ሰዎች የትኛው መልካም ምግባራቸውና ስራቸው ነው ማህበረ ቅዱሳንን ለመውቀስ የሚያበቃቸው? በጀርባቸው የሰውን እንባ ይዘው የሚዞሩ ፤ በትከሻው ምንፍቅናን ለመዝራት ምዕመኑን ከቤተክርስትያን ለማውጣት ከአሜሪካ እስከ አዲስ አበባ ኔትወርክ ዘርግቶ በዋና ተዋናኝነት ታች ላይ በሚል ሰው እስከ መቼ ሰላማችንን እናጣለን ? ለማንኛውም እስኪ የሲኖዶስ ስብሰባ በሰላም ተጀምሮ እንዲፈጸም  ሁላችን እንጸልይ፡፡  

ቀጣይ ነገሮችን እየተከታተልን እናንተው ዘንድ ለማድረስ ቃል እንገባለን

7 comments:

  1. +++
    We believe in God who doesn't sleep, who keeps those who believe in Him. Evil starts from the devil who is the enemy of all the good our church is trying to do. Those people from highest to the lowest who are trying everythng for personal gain will be defeated at the end because truth always wins. We are tempted so much by what some fathers and church officials are doing against the church. We pray so that God defend for His church but we also fight against their ideas which are hurting our church so much!!! People please get conscientious and stand for truth!!!

    ReplyDelete
  2. just keep on telling the truth!!!

    ReplyDelete
  3. እምዬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ፤
    የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ፡፡

    ReplyDelete
  4. "Ye'asa gimatu kechinqilatu new" We have to remove the cancer cell of the church and that is "Beyonce's Guider". And we know what caused the cancer, his past unpleasant behavior. He is being threatened by ELIZABET.

    ReplyDelete
  5. Egziabhere Yebarkachu Andadregen

    It is very sad news , It is clear Abune Paulos is the one who makes all this stirring, The daughter and sons of True Ethiopian Tewahedo all around the world from America , Europe, Asia, Australia, New zealand knows. We all are ready to do our best to look after and pray for our beloved church, GOD IS WITH US.

    ReplyDelete
  6. Dear andadrigen!

    Thanks for the info!

    i heard that this guy (Haile Giorgis...) had been working in US embassy and a friend of mine told me that when he left from that embassy, many more corespondenses that he mad with some tehadisso groups such as the so called haimanot abew was found on his table.........

    I think all needful info shall be disclosed to holy sinod by concerned groups

    Egziabher ke enant gar yihun

    ReplyDelete
  7. Its such as you learn my thoughts! You seem to grasp a lot approximately this, like you wrote the book in it or something.
    I think that you can do with a few p.c. to drive the message home a little bit, however other
    than that, this is wonderful blog. An excellent read.
    I will certainly be back.
    Take a look at my blog :: GFI Norte

    ReplyDelete