- የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጆች ለጥያቄ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አልቀረቡም፡
- የጽሑፎቹን ይዘት ከሕግ እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ ሰባት አባላት ያሉት ከሚቴ ተቋቁሟል፡፡
(አንድ አድርገን ግንቦት
8 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በትናንት ዘገባችን የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጆች ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ፣ ም/ዋና አዘጋጅ ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር፣ የህዝብ ግኙነት ዋና ሓላፊው እስክንድር ገብረ ክርስቶስና ከድቡብ ወሎ ሃገረስብከት ተባሮ የመጣው የህዝብ ግኙነት ዋና ም/ሓላፊው ሣህሉ ለዛሬ ጠዋት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው ማን እንደጻፈው? እንዲያስረዱ መወሰኑ ገልጸን ነበር፡፡
ትናንት ማክሰኞ ጠዋት አዘጋጆች ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም አዘጋጆች አልቀረቡም፡፡ የአቡነ ጳውሎስ እጅ እንዳለበት እየተነገረ ነው፡፡ ፓትሪያሪኩ አዘጋጆች ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንዳይቀረቡ እንዳግባቡአቸው እየተነገረ ነው፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አባላትም በአዘጋጆቹ መቅረብ ዙሪያ ሁለት የተለያየ ሃሳብ እንደ ነበራቸው ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ የመጀመሪያው ሀሳብ በተለይ ዋና አዘጋጁ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ ቢቀርብም ትክክለኛ የጽሀፉን አዘጋጅና ተባባሪዎች ስለሚያጋለጥ ይቅረብና ያስረዳ የሚል ሃሳብ የቀረበ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የፓትሪያሪኩ ምንደኛ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ም/ዋና አዘጋጅ ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር፣ የህዝብ ግኙነት ዋና ሓላፊው እስክንድር ገብረ ክርስቶስና የህዝብ ግኙነት ዋና ም/ሓላፊው ሣህሉ ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት ከመዝለፍ ያለፈ ጠቃሚ ነገር ስለማይናገሩ(እንዳይናገሩ ስለተመከሩ) በጋዜው ላይ ያለው ጽሁፍ ተመርምሮ ውሳኔ እንስጥ የሚል ነበር፡፡
ምልዓተ ጉባኤው የጽሑፎቹን ይዘት ከሕግ እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ የሚያቀርብ ሰባት አባላት ያሉት ከሚቴ አቋቁሟል፡፡ኮሚቴው አባላት ኾነው የተመረጡት ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡- ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ ሲሆኑ የሕግ ባለሙያዎቹና ምሁራኑ ደግሞ ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ፣ ዶ/ር ተክለ ሃይማኖት አንተነህ፣ ዲያቆን ፊልጶስ ዓይናለም እና አቶ በፍርዱ መሠረት ናቸው፡፡
ከቀትር በኋላ ምልዓተ ጉባኤው የጋዜጣው ጽሁፎች በንባብ የሰማ ሲሆን ሁሉም ሊቃነጳጳሳት በጉዳዩ ላይ አስተያየት በየተራ ሰጥተዋል፡፡ አባቶችን ለመከፋፈል በጨለማ ቡድኑ አባላት የተሴረው ሴራ አባቶችን ይበለጥ በአንድነት እንዲቆሙ፤ የቤተክርስቲያኒቱ ዋነኛ የችግርቿ ማጠንጠኛ የሆኑትን ፓትሪያሪኩን እንዲቃወሙ እድል ፈጥሮላቸዋል፡፡ፓትሪያሪኩ አጋጣሚው ከተመቻቸላቸው ለብጹዓን ሊቃነጳጳሳት ክብርና ደህንነት፣ የቤተክርስቲያን ሰላምና አንድነት እንዳማይገዳቸው የዜና ቤተክርስቲያን ጽሁፍ ግልጽ እንደሚያደርገው አስተያየት እየተሰጠበት ነው፡፡
o
በዚህ ጉባኤ ላይ ከ20 የማያንሱ አጀንዳዎችን ቀርጾ ለመነጋገር ያሰበው ቅዱስ ሲኖዶስ እስከ
አሁን ይህ ነው የሚባል አጀንዳ ላይ ተነጋግሮ ውሳኔ ማስቀመጥ አልቻለም ፤ ይህም የሆነበት ምክንያት የሲኖዶሱ ስብሰባ ከመጀመሩ
ከቀናት በፊት ከምድረ አሜሪካ በመጡ ሁለቱ ሰዎች አማካኝነት እና እዚያው በዓላማ የሚጋሯው የቤተክህነት አስተዳዳሪዎች አማካኝነት
በተጠነሰሰው ሴራ ስብሰባውን አባቶች እንዳሰቡት እንዳይካሄድ እንቅፋት የሆኑ ስራዎችን እየሰሩ ስለሚገኝ ነው ፤ ዋናው አላማቸው
አባቶች በአንድነት ስለ ቤተክርስትያን በአንድነት ሆነው እንዳይቆሙ ፤ በደራሽ ነገር ተተምደው ዋናውን ጉዳይ ላይ መዋያየት እንዳይችሉ
፤ አጀንዳዎቹ ለቀጣይ ጥቅምት ጉባኤ እንዲተላለፉ ሲሆን እስከ አሁን እኛም በተመለከትነው መሰረት ሀሳባቸው የሚሳካላቸው ይመስላል
፤ ነገር ግን አባቶች በጽንዓት በመቆም የሚመጣውን ፈተና በመቋቋም ቤተክርስትያኒቱ የጣለችባቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ እምነታችን
ነው፡፡
o
ቸር ወሬ ያሰማን
ዋናው አላማቸው አባቶች በአንድነት ስለ ቤተክርስትያን በአንድነት ሆነው እንዳይቆሙ ፤ በደራሽ ነገር ተተምደው ዋናውን ጉዳይ ላይ መዋያየት እንዳይችሉ ፤ አጀንዳዎቹ ለቀጣይ ጥቅምት ጉባኤ እንዲተላለፉ ሲሆን እስከ አሁን እኛም በተመለከትነው መሰረት ሀሳባቸው የሚሳካላቸው ይመስላል ፤ ነገር ግን አባቶች በጽንዓት በመቆም የሚመጣውን ፈተና በመቋቋም ቤተክርስትያኒቱ የጣለችባቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ እምነታችን ነው፡፡
ReplyDeletechere wore yaseman
ReplyDeletemazenagiyawene tolo wesenen adendawen bigemere ....
ReplyDeleteብዕሩ ዘ-አትላንታsaid...
ReplyDelete"ባለጌዉ ጳጳስ"በኢትዮጵያ ምድር የትኛዉ መሪ ነዉ የሚወቀሰዉ? የቤተ መንግሥቱ ወይስ የቤተ ክህነቱ? መቼም ጌታዉን ያመነ በቅሎ ነዉ ጭራዉን ከዉጭ የሚያሳድረዉ። "በቅሎ" ያልኩበት በግ የሚለዉ ቃል ጠፍቶኝ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ። በግማ በግ ናት የጥሩ ነገር ምሳሌ፤ በቅሎ ተራጋጭ የማትወልድ ናትና ስለ ልጅ ፍቅር ይግባት አይጋባት ለማወቅ ይቸግራል። ዲቃላም ትመስላለች አባቷ አህያ እናቷ ፈረስ ናቸዉና። እና ጌታዋን ተማምና ጭራዋን ዉጭ ብታሳድር አይደንቅም። ዛሬ ልባቸዉ ዉጭ ሥጋቸዉ ዉስጥ የሆኑ እነ አባ ጳዉሎስና ግብረ አበሮቻቸዉ የእናታቸዉን ጀርባ እየተራገጡ ይገኛሉ። አንተ ባለጌ እንዴት እንዲህ ትናገራለህ የሚለኝ ካለ አዎ ብልግናዉ እያየለ በረት ቤተ ክርስቲያን በባለጌዎች ስለተደፈረች እኔም ብባልግ አያስኮንንም ለማለት ነዉ። ባለጌ ልጅ እርግጫ የሚጀምረዉ ከእናቱ ጀርባ ነዉ እንዲሉ አኒህ ሰዉ እርግጫ የጀመሩት ከእናት ቤተ ክርስቲያን ጀርባ በመሆኑ እንደርሳቸዉ ተራጋጭ የሆኑ ልጆች አፍርተዋል። እኒህ ሰዉ እርግጫ የጀመሩት ከቅዱስ ሲኖዱሱ ጀርባ በመሆኑ ለቅዱስ ሲኖዶስ የማይተዘዝ ወዳጅ አፍርተዋል። እኒህ ሰዉ ምንኩስናቸዉን ዘንግተዉ ለገንዘብ ያደሩ ሙሰኛ በመሆናቸዉ የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ የሚቦጠቦጡ ብልና አይጦች አፍርተዋል። ከዚህ የዘለለ ባለጌ ከዬት ይምጣ። ልባቸዉ ሲቆፈር የአበዉ የሃይማኖት ደንብ የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ሳይሆን መዥገርና ዓልቅት ነዉ የሚያበቅለዉ። ባለጌ ከዚያም የዘለለ ሌላም። እርግና የተጫናቸዉን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳቱን አስደበደቡ፣ በአንዲት የቆሎ ትምህርት ቤት ተምረዉ እንዳላደጉ፤ በእንተ ስማ ለማርያም ከዉሻ ታግለዉ ለክብር እንዳልበቁ ከከሀዲያን ጋር ጮማ እየቆረጡ ዉስኪ እየተራጩ መስቀሉን አስኬማዉን ዘንግተዉ የቤተ ክርስቲያንን የወንጌል ገበታ አጎደፉ። ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን መልካም ተስፋ ሰንቀዉ በአህያ ጀርባ እየተጓዙ በቁርጥ ስሜት ደፋ ቀና ብለዉ የሚያገለግሉትን አባቶችን በግፍ አስገደሉ። "አባ ጳዉሎስ" በምእመኑ ሕይወት ተሳለቁ። ብዙዎችን ምሰኪን የቤተ ክርስቲያን ልጆች በግፍ አሳሰሩ አሳደዱ። ዛሬም የተጸናወታቸዉ ይህ ርኩስ መንፈስ እዉነት ሳይሆን ሸፍጥን፣አንድነትን ሳይሆን መለያየትን፣ፍቅርን ሳይሆን ጥላቻን፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ክብርን ሳይሆን ዉርደትን በመዝራት ላይ የገኛሉ። እረ አንቱ ሆዬ! አንቱ እያሉ ስድብ ትሉኝ ይሆናል እንደ እርሳቸዉማ ሥራ አንቱ መባል ባይገባቸዉም አድሜ ለንስሀ ታድሏቸዉ ሰባት ዐሥርት ዓመታት በደፈናዉ እንደ ቃዬን ሲቅበዘቡ ኖረዉ የሌ ባይጠቀሙበት ዕድሜ ክቡር ነዉና አንቱ ይገባቸዋል። "ጅብ እየበላ ይገድላል" እንዲሉ አባ ጳዉሎስ ቤተ ክርስቲያንዋን ዉስጥ ዉስጡን እየበሉ ገደሏት። እግዚአብሔር የእጃቸዉን ይስጣቸዉ። እየተበላ የሚሞትን ሰዉ ልብ በሉ... ህመሙ እንዴት እንዲሰማ... ለእኔም የተሰማኝ ህመም ይህ ነዉ። በቃ እዉነት እላችኋለሁ ባለጌ ናቸዉ። ዕዩማ ተስፋ የቁረጠ ሰዉ። የእናቱን ገዳይ የማይበቀል ልጅ ያለ አይምሰላቸሁ። አባ ፋኑኤል፣ ዕንቁ ባህርይ፣አባ ሰረቀ ለዕቅዳችሁ ተፈጻሚነት የጀርባ አጥንት የሆነ መንግሥታችሁ ይታደጋችሁ እንደሆነ አያለሁ... እኔ ስል ብቻዬን እንዳይመስላችሁ እናንተ ስትባልጉ እንደ እኔ ያልባለጉ ትዕግሥት የገዘታቸዉ በቁርጡ ቀን ግን ለአሞራ እንኳ ሥጋችሁ እንዳይተርፍ የሚዘለዝሏችሁ የተዋህዶ አርበኞች እንዳሉ እወቁ። ጨዋ ነበር ያሳደገኝ ባለጌ ዓይቼ ባለግሁ ይቅርታ!!! ብዕሩ ዘ-አትላንታ
selam lenante andadirigenoch endet nachihu berekete egziabher yideribachihu eyalihu blogu ethiopia aynebebim tezegitual ena hack eyaderegin new minanebew bizu sew gin eyanebebe aydelelm siletezega ena bichalachihu lela address bitiserulet elalehu yezewetir anibabi negn YEDINIGIL MARIAM AMALAGINET YEMELIKT TIBEKA YESEMAETAT TELOT KEGNA YIHUN....
ReplyDelete