Friday, May 18, 2012

የማህበረ ቅዱሳን የዋልድባ ሪፖርት

(አንድ አድርገን ግንቦት 11 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ማህበሩ ዝምታውን ሰብሯል ፤ የተጠናውን ሪፖርትም ለስለስ አድርጎ መፍትሄ በመሻት መልኩ አቅርቧል ፤ ይህም የህዝቡን ውዥንብር የቤተክህነቱንም ተቃርኖ ፤ ተገቢ ያልሆነ ደብዳቤ ምላሽ ይሆናል ብለው ያሰቡ ይመስላሉ ፤ መንግስትም ይህን አይቶ ከአቋሙ የመለሳለስ መንገድ ይሄዳል ብሎ አጥኚ ቡድኑ የሚያምን ይመስላል ፤ ሲጀመር ጥቂት ስለዋልድባ ገዳም አብያተክርስትያናት ነግረውናል ፤ ከገዳሙ ውጪ ያሉትንም አብያተክርስትያናት አስቃኝተውናል ፤  ግድቡ ይህን ያህል ርዝመት  ፤ ወርድ ፤  ቁመት እንዳለው ፤  የሚይዘው የውሀ መጠን  ፤ ውሀው የሚሞላበት ጊዜ ፤ ሸንኮራው የሚለማበት የካሬ መጠን ፤ ፋብሪካው በቀን ስንት ሸንኮራ እንደሚፈጭ ፤ በቀን ስንት ቶን ስኳር እንደሚመረት ፤ ተረፈ ምርቱ ለኢታኒል አገልግሎት እንደሚውልም ነግረውናል፡፡ ፤ ከዚያ ይሰራል ስለተባለው ፕሮጀክት ይዞታ ፤ ቦታው ላይ ይነሳሉ የተባሉት አብያተክርስትያናት በGoogle Earth በተገኝ ምስል አመላክተውናል ፤ የአጥኚ ቡድኑም እይታ ተካቶበታል ፤ ቀጥለውም የገዳሙ አባቶች ጥያቄ ላይ ያተኮሩ ይመስላል ፤ የሪፖርቱ የገጽ ብዛት 9 ሲሆን ስምንቱን ገጽ ከተለያዩ ሚዲያዎች የምናውቃቸውና   ጆሯችን ያስተናገደውን ደግመነው አንብበናል ፤ ግማሽ ገጽ የማህበሩን እይታ እና አስተያየት ይዟል ፤ አንድ ገጽ ደግሞ ማጠቃለያ ……  ይሁና ብለናል21 comments:

 1. Thank you M/K for your detailed report.

  ReplyDelete
 2. This is Mahibere Kidusan, reporting the facts against betekihenet's report and fabricated news. Ya let us speak the facts and dying.

  Bless you guys.

  ReplyDelete
 3. They did a detaled report as usual and thanks for that. But it dose not tell us what MK thinks about it,What their stand is? what is your sugession? you just gave us he siad, they siad etc.You gave the homework for the fathers and government that won't be done (open disccusion haaa i do no think so after 97)
  I just want to know what do u think as a mahiber.Do not you think it can be done other place or far from it.
  Did not get it at all my be i expected to read thier viwe and it is not included or they do not want to take the risk. Any way i know 'tirsun ke afetete anbesa gar megitem kebad new'

  ReplyDelete
 4. We thank MK very much for clear and reliable information to the people of Ethiopia. God bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 5. Thanks to GOD...egiziabehere kegnaga newe lemene enferalen?

  Yeferehaten menefese yasewegedelen!!!!!!

  negeme menafeqane ayetegnum!!!!!


  yesiole deje gene ayecheluatem tebelual bewengealu

  ReplyDelete
 6. ማኅበሩ ጊዜ ወስዶ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሮ መፍትሔ አምጪ በሆነ መልኩ ሪፖርት ማቅረቡ ያስመሰግነዋል። እኛ የምንፈልገው የማንነታችን መገለጫ የሆኑ ገዳማት እንዳይፈርሱ እና ስለኛ የሚጸልዩ አባቶች እና እናቶች እንዳይጉላሉ እና እንዳያዝኑ ነው። የማኅበሩ ሪፖርት ላይ የሚከተሉትን አላጎላም ወይም ይቀሩታል።

  1. ሪፖርቱ ዘግይቷል።
  2. ስለሚፈርሱት 3 አብያተክርስቲያናት ማኅበሩ ምንም ለማለት አልደፈረም።የጠራ አቋም ሊይዝ ወይም አቋሙን በጠራ መንገድ ማንጸባረቅ ነበረበት። ሥጋውና ደሙ የሚፈተትባትን አንዲት አጥቢያ መፍረስ ማኅበሩ በቀላል ይመለከተዋል ብዬ አላስብም ነበር፡፡ እንደአባል በማኅበሬ አፍሬያለሁ።
  3. ስለዐጽመ ቅዱሳን መነሳት ምንም አስተያየት የለውም? በቁጥር አለመስማማትን እንዲዘግብ አይደለም የምንጠብቀው።ስለአረፉት ቅዱሳን አጽም ያለውን አቋም እንዲያብራራ ነበር።
  በአጠቃላይ መፍትሔ አምጪ በሆነ መንገድ መዘገቡ ቢያስደስትም የጠራ አቋም አለመያዙ እና አንባቢን በ8 ገጾች መንደርደሪያ እና ቁንጽል የመፍትሔ ሃሳብ ማለቁ .....

  መንግስትም ልማት ከመገንባቱ በፊት ለሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥቶ አወያይቶ ወደ ግንባታ ቢገባ ጥሩ ይመስለኛል።

  ከማኅበሩ አባላት አንዱ።

  ReplyDelete
 7. ማኅበሩ ጊዜ ወስዶ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሮ መፍትሔ አምጪ በሆነ መልኩ ሪፖርት ማቅረቡ ያስመሰግነዋል። እኛ የምንፈልገው የማንነታችን መገለጫ የሆኑ ገዳማት እንዳይፈርሱ እና ስለኛ የሚጸልዩ አባቶች እና እናቶች እንዳይጉላሉ እና እንዳያዝኑ ነው። የማኅበሩ ሪፖርት ላይ የሚከተሉትን አላጎላም ወይም ይቀሩታል።

  1. ሪፖርቱ ዘግይቷል።
  2. ስለሚፈርሱት 3 አብያተክርስቲያናት ማኅበሩ ምንም ለማለት አልደፈረም።የጠራ አቋም ሊይዝ ወይም አቋሙን በጠራ መንገድ ማንጸባረቅ ነበረበት። ሥጋውና ደሙ የሚፈተትባትን አንዲት አጥቢያ መፍረስ ማኅበሩ በቀላል ይመለከተዋል ብዬ አላስብም ነበር፡፡ እንደአባል በማኅበሬ አፍሬያለሁ።
  3. ስለዐጽመ ቅዱሳን መነሳት ምንም አስተያየት የለውም? በቁጥር አለመስማማትን እንዲዘግብ አይደለም የምንጠብቀው።ስለአረፉት ቅዱሳን አጽም ያለውን አቋም እንዲያብራራ ነበር።
  በአጠቃላይ መፍትሔ አምጪ በሆነ መንገድ መዘገቡ ቢያስደስትም የጠራ አቋም አለመያዙ እና አንባቢን በ8 ገጾች መንደርደሪያ እና ቁንጽል የመፍትሔ ሃሳብ ማለቁ .....

  መንግስትም ልማት ከመገንባቱ በፊት ለሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥቶ አወያይቶ ወደ ግንባታ ቢገባ ጥሩ ይመስለኛል።

  ከማኅበሩ አባላት አንዱ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከአባባላችሁ የፓትርያርኩንና የጳጳሳቱን ግዴታ ሁሉ የማኀበረ ቅዱሳን ያደረጋችሁት ይመስላል ፡፡ የማኀበሩ ኃላፊነትና ግዴታ ፣ የተቋቋመበትስ ዓላማ ምን ስለሆነ ነው እንደምንፈልገው አልተወጠርክ ብለን የምንወቅሰው ፡፡ እንዲያውም ለቤተ ክርስቲያን ከሚገባው በላይ በመሄዱ ብዙ ተቀናቃኞችን አስነስቷል ፡፡ አባቶች ግዴታቸውን ቢወጡ ፣ የቤተ ክርስቲያንም ኃላፊዎች የሚመለከታቸውን አጥርተው ቢሰሩ ፣ አውደ ምሕረታቸውን ራሳቸው ቢቆጣጠሩና የሃይማኖት ግድፈትን በወቅቱ እንዲታረሙ ቢመክሩ ፣ ዛሬ ኘሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ወይም የቤተ ክርስቲያናችን ጠላት በየስርቻው መሰናክል እየደነቀረ ህልውናውን ለማጥፋት ባልተረባረበበት ነበር ፡፡
   ማኀበሩ ለቤተ ክርስቲያናትና ገዳማት ካለው ተቆርቋሪነት አኳያ እጅግ ብዙ ሥራ ሠርቷል ፡፡ ከዚህ የበለጠ ለመሥራት ደግሞ ሜዳው ገደል ፣ ቀኑም ጨለማ እየሆነ ስለሄደ ጥንቃቄም ማድረግ ደግ ነው ፡፡ የሰዎች አእምሮ የሚያስበውንና የሚመኘውን መለቅለቅ ቀላል ነበር ፡፡ ነገር ግን ጥያቄው መጀመሪያውንም ቢሆን የተነሳው ይኸው ከፖለቲከኞች ጐራ ለመሆኑ አቋሙ በቂ ማስረጃ አለን ብለው ለመቁጠርና ለመፈረጅ ፣ በአሥር ደቂቃም አዋጅ አሳውጀው ድርጅቱን በየትም ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ ስውር ዕድቅ ይመስል ነበርና በደፈና አትፍረዱ ፡፡

   Delete
  2. አስተያየቱ የተሰጠው ማኅበሩ የፓትርያርኩንና የጳጳሳቱን ግዴታ እንዲወጣ ተፈልጎም ወይም ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ለሰኮንድ በመዘንጋት አይደለም። ማኅበሩ አጥኚ የላከው በራሱ ነው። አጥኚ ልኮ ያየው በትክክል መዘገብ እና ለገዳሙ የሚጠቅመውን ምድራዊ ነገስታትን ፈርቶ በመልመጥመጥ ሳይሆን ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው እውነቱን እውነት ማለት አለበት። "ያየነውን እንናገራለን የሰማነውን እንመስክራለን" የሚለውን እንደመለያ የራሱ ህትመት ላይ መጻፉ መገለጫው ምንድን ነው? ማኅበሩ ዛሬ የደረሰው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ነገንም የሚሻገረው በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ በዲፕሎማሲ አይደለም።

   Delete
  3. እግዚአብሔር ክፉና ደጉን የምንለይበት አዕምሮ ፣ ቀናና ጠማማውን የምንለይበት ዓይን ፤ አርቆ የምናስተውልበትን አካል ፈጥሮልን ፣ በአግባቡ በመገልገል ሳንጓዝ ቀርተን ብንጐዳ ፣ እግዚአብሔርን ማማረር የለብንም ፤ ወይም እግዚአብሔር አልረዳንም ፣ አልፈቀደልንም ለማለት መንገድ ከፍተን ፣ አንገት ለመድፋት መቻኰል አይገባንም ፡፡ እሳትን በእሳት ማለት በጣም ቀላል ነው ፡፡ ነገር ግን መልሶ ራስንም መለብለቡ ስለማይቀር ፣ አንዳንዴ ትዕግሥተኛ መሆንም የአምላክ ፈቃድ ነውና በቸልታ ማለፍ መልካም ነው እላለሁ ፡፡ ለእኔ አጥኚ መላኩንም ያወቅሁት አሁን ሪፖርት ሲያቀርቡ ነው እንጅ አብሮ መጓዛቸውን እንኳን አልሰማሁም ነበር ፡፡

   እንዲያው ያሉትን ነባራዊ ሁኔታዎችን በሥርዓቱ ከተመለከትን እንዴት ነው በዚህ አጣብቂኝ ፈተና ውስጥ ይኸ ማኀበር ራሱን ማትረፍ የሚችለው በማለት ትንሽ ማሰላሰልና ማብላላት ያስፈልገናል ፡፡ ደረት በደረት ብሎ መሆን ነበረበት ? ለእኔ መልሱ አይደለም ነው ፡፡ ዛሬን ብልህ ሆኖ መትረፍና ፣ ለቀጣይ ሥራውም መገኘት የተሻለ ነው ፡፡ ማኀበሩ ያየውን ፣ የሰማውን ፣ ያሰበውን ፣ የተባለውን ጸያፍና ደግ ነገር ሁሉ ቢለቀልቅ ፣ ህልውናውን የሚያጣበትን ምክንያት ያበዛ እንደሁ እንጅ ለቤተ ክርስቲያንና ለገዳማቱ አንዳች ጥቅም አያስገኝም ነበር ፤ የጠየቁትም ዓላማቸው ስለከሸፈባቸው ነው ፤ ወጥመዱ እንዳልያዘ ስለተገነዘቡ ነው እንጅ ዜናው ለየት ያለ ጥቅም ይሰጣል ብለው አይደለም ፡፡ እንዴት ነው በሠፈራችን ዛሬ አላለፍክም ተብሎ የሚጠየቀው ፡፡ በሠፈራቸው ቢያልፍ ምን ይሆን ነበር ማለት ነው ፡፡ ብልጥ ለብልጥ ዓይን ፍጥጥ ፡፡

   ዛሬን ማለፍ ከቻለ ግን ነገም አውደ ምሕረት በሉተራውያን እንዳትወረር ይጠብቃል ፤ ገዳማቱም እንዳይዘጉ ይከራከራል ፤ ቢቃጠሉ ህዝብ ያስተባብራል ፤ ቤተ ክርስቲያንንም ከእምነት አገልግሎት መስጫነት አውጥተው የቱሪስት መናኸሪያ እንዳያደርጓት ይከራከራል ፤ የተዳከሙትን የአገልግሎት መስጫዎች አቅሙ በፈቀደ ይረዳል ፡፡ በፈጣሪ ዕርዳታና በአባቶች ምክርም በመታገዝ ሃይማኖት የምትስፋፋበትን ፣ ክርስትናችን የምታብብበትን ፣ ቤተ ክርስቲያንም ይበልጥ የምትደምቅበትን ፣ ወገን የሚተርፍበትን ትምርት ፣ ቅድስና የምናገኝበትን መንገድና ተግባር ለወገን ማስተላለፍ ይችላል ፡፡

   በግሌ ማኀበሩን ለማጥፋት ምክንያትን ሲፈልጉበት እያየን ፣ ችግሩን የኔ ብለን አለመረዳታችን ራሱ ትንሽ ያሳስበኛል ፡፡
   ማኅበሩ ከዛሬም የደረሰው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው። ነገንም የሚሻገረው በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ብሩህ አዕምሮአቸውንም እንዲጠቀሙበት ፈጥሮአልና ፤ በዚሁ መንገድ ከተረፉም እግዚአብሔር ስለ ሥራውና እገዛው ይመሰገናል ፡፡

   Delete
  4. ወንድም አባባልህ የትክክለኛነት መንፈስ ቢነበብበትም እየሆነ ያለውን ሁኔታ ግን የተገነዘብህ አይመስልም:: አየህ ወንድሜ ይህች የ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያን ጥንት አንድ ነበረች ዛሬ ግን በቤተክርስቲያኗ እራስ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብዙ ቤተ-እምነቶች ተፈጥረዋል:: ከ እነዚህ ቤተ እምነቶች ውስጥ ደግሞ ዛሬ ለ ቤተክርስቲያናችን አደገኛ ፈተና የሆነውና የማክበሩን ህልውና ለማዳከም ብሎም ለማጥፋት የሚታትረው የተሃድሶ አራማጆች ንቅናቄ ነው:: ታዲያ ማህበሩ ካለምንም ጥንቃቄ ሪፕኦርቱን ማውጣት አለበት ማለት የዚህ የተሃድሶ አራማጆች የሴራ ወጥመድ ውስጥ ዘው ብሎ መግባት አለበት እያልህ መሆኑን የዘነጋህ ይመስለኛ :: ሌላው ደግሞ ማህበረ ቅዱሳንን እንደ አንድ ግለሰብ ያየኸው ይመስለኛል አንድ ግለሰብ ቢሆን ኖሮ አዎ ባልኸው ነገር ሙሉ በሙሉ እስማማ ነበር ይሄ ግን ማህበር ነው ለ እይንዳንዱ እንቅስቃሴ ሁሉ ከ እ/ር ብቻ ሳይሆን ከ ቤተክህነት እና ከመንግስት ፈቃድ የሚያስፈልገው:: ይህ ማህበር እንደማህበር ሪፕኦርቱን ተዎያይቶበት ወደ ማህበሩ የተቀሰሩ ጦሮች ተዎርውረው እንዳይዎጉት እና ህልውናውን እንዳያጣ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት:: አዎ ከሳሾቹ ፈርጣማ ናቸው ቤተክህነት ከተሰገሰጉ ጥቂት ባለ ክህነት ሰዎች እስከ ቤተመንግስት ብሎም የፕሮቴስታንት እምነት አራማጆች እና ቤተክርስቲያኗን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሱ አክራሪ እስላሞች:: ትናንት የ እነዚህ ጸረ ማህበረ ቅዱሳን እንቅስቃሴ ውሃ እንደማያነሳ ገምተን ነበር ይሁንና መንግስት እንደ ተቋም በማህበሩ ላይ ያለውን ለዘብተኛ አቋም ወደ ጥላቻ አዘል እንዲቀየርና ማህበሩን በ አሸባሪነት እንዲዎነጅል አድርጎታል:: አየህ መንግስት እዚህ አቋም ላይ የደረሰው ማህበሩ የሚሰራቸውን መልካም ተግባራት እየተመለከተ ቢሆንም ለከሳሾቹ የፈጠራ ወሬ ግን በ አይኑ ከሚያየው የማህበሩ እንቅስቃሴ በላይ ዋጋ ሰጥቶታል ::ይህን እያየህ በዚህ እሳት ውስጥ ዘው ብሎ መግባት አለበት ማለትህ ገርሞኛል:: ክርስቲያንነታችን የሚለካው የ እ/ሄርን ቤት ጠብቀን በውስጧ እስከ እለተ ምጽዓት መቆየት ስንችል እንጂ እንደ እሳት እራት እሳቱን እናጠፋ ብለን ዘለን እሳቱ ውስጥ በመግባት አይደለም:: በመጨረሻም ማህበረ ቅዱሳን የአባቶቼንና የራሴን እምነት እንዳውቅ ስለረዳኝና እና በማንነት ቀውስ ውስጥ እንዳልኖር ስላደረገኝ በዚህ አጋጣሚ ከልብ ላመሰግነው እዎዳለሁ:: ይሄን ስል ግን በ እምነቴ እየኖርሁ ነው ማለቴ አይደለም እዉነቱን ለመናገር እናቴ ያሰረችልኝን ማትብ ከ አንገቴ ላይ ከማሰር የዘለለ እምነቱን እየኖርሁበት አይደለም ማለቴ ጾም አልጾምም ቤተክርቲያን እየሄድሁ አልሳለምም ጸሎት አልጸልይም የንስሃ አባት የለኝም ይህም የራሴ የስጋ ድክመቴ እንጂ የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ አምንበታለሁ:: በ እምነቴ ባልኖርበትም ለእምነቴ ቀናኢ ነኝ አዎ ያኔ ገና ከገጠር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንደገባሁ በገጠመኝ የእምነት ጥልፊያ ስዋከብ የፕሮቴስታንት እምነትን ሊሰብኩኝ ከቀረቡኝ ለሚነሱት ጥያቄዎች በሙሉ አርኪ የሆነ መልስ በመስጠትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እምነት እና ጥበብን በአንድ ላይ ይዛ የምትራመድ መሆኗን እንድገነዘብ ለረዳኝ ማህበረ ቅዱሳንና አባላቱ አክብሮት አለኝ:: ምን አልባት አንድ ቀን ብሎልኝ የስጋ ፈተናየን አሸንፌ እምነቴን መኖር ስጀምር የማህበረ ቅዱሳን አባል ሆኘ ማህበሩ ኦርቶዶክሳዊያንን ከ ነጣቂ ተኩላ ቤተክርስቲያንን ከ አጥፊዎቿ ለመታደግ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተሳታፊ በመሆን ለዚች እምነትን ጥበብ በተሞላበት አካሄድ ለምትራመደው ለ ጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጸንታ መኖር የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ ምኞቴ ነው::

   ይህን ጽሁፍ ለምታነቡ ሁሉ:- ከላይ ስለራሴ የጻፍሁት ማህበረ ቅዱሳን እንደሚባለው አክራሪ ሳይሆን የቤተክርስቲያኗን አስተምህሮ የሚያስተምር ስለመሆኑ ያለኝን ተሞክሮ እና ከተለያዩ ድረ-ገጾች የሚሰነዘሩ ትችቶች ማህበሩን ለመዎንጀል ሆን ተብሎ የሚሰነዘሩ አሉባልታዎች መሆናቸውን በመገንዘቤና አንዳንድ የዋህ ምዕመናን የማህበሩን እንቅስቃሴ ሳይረዱ ማህበሩ ላይ ጥላቻ እንዳያሳድሩ የ እኔንም ተሞክሮ ለማካፈል ስል ነው::

   በተረፈ እ/ር ይህቺን አምልኮቱ የሚፈጸምባት ቤተክርስቲያን ይጠብቅልን!!!!!!!!

   Delete
 8. Balanced social impact assessment! This is what is expected from experts.
  A3A

  ReplyDelete
 9. አባቶች ያልደረሱበትን እውነታ ከልጆች ማግኘት ቢያሳፍርም ፣ ሃቁን መቀበልና ከነሱ የሚጠበቀውን ኃላፊነት ለመወጣት ፣ ከእንግዲህ ቢሠሩ እንኳን ታላቅነት ነው ፡፡ እባካችሁ የዚህን ግልባጭ በቀጥታ እንዲደርሰው ለዛ ሰው ላኩለት ፡፡ መለከፍ ክፉ በሽታ ነውና ሰውየው ሳያነብ ተኝቶ ከርሞ ደግሞ ፣ ነገ ጠዋት ሌላ ማመልከቻ ፣ ወይም የይግባኝ ደብዳቤ እንዳይለቀልቅ ፡፡

  ሪፖርቱ ወገንተኝነትን ያላሳየ ፣ ሁሉንም በየመልኩ የተነተነና መፍትሄንም ያመላከተ ድንቅ ዘገባ ነው ፤ እግዚአብሔር ይስጣችሁ ፡፡ ለሃይማኖት መቆርቆር ብቻ ሳይሆን ለአገርም ሃሳቢ መሆናችሁ ይኸ በጣም ትንሹ ማመላከቻ ነው ፡፡

  ReplyDelete
 10. Mahbere Kidusan’s report is good but the conclusion is not appropriate. Even the monks and nuns in Waldba do not have the authority to suggest an exchange of 16.6 hectares of blessed land (blessed and trodden by the Christ and His Mother our Queen the Blessed Virgin Mary). Waldba is God’s own real-estate; not man’s. The report is also a little short on the environmental and urbanization threats Waldba encounters as a result of this invasion. It is, however, understandable that Mahber Kidusan is in an extremely difficult situation to report beyond what it already has given it is under such immense threats from the EPRDF.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰለፌ ጋር እያመሳሰሉ ታሪኩን ሲያበላሹ ፣ የሉተራውያን ቅጥረኞች ኘሮቴስታንታዊ ተሃድሶአውያን ማኀበሩን ህልውና አሳጥተው ለማፍረስ የማይቆፈረውን ሁሉ ሲቆፍሩ ፣ የተሰጠው መልስ የብልህና የአስተዋዮች ነው ፡፡ ስለ መሬት ከሆነ እግዚአብሔር ሲፈጥር ምድርን ሁላ ባርኳታል ፡፡ ያረከስናት ፣ ያጐደፍናት ሰዎች ነን ፤ ድንግል ማርያምና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድንበር አልከለሉልንም መላ ኢትዮጵያን ነው የቀደሱልን ፡፡ ነገር ግን አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ፣ ማኀበሩን ሌላ የመንግሥት አዋጅ እንዳይከተለው ጥሩ ሰላማዊ አካሄድ መዘገቡና ሃቁን ማሳወቁ ከቤተ ክርስቲያን ልጅነት አኳያ የሚጠበቅ ነው ፡፡ አመልካቾች የፈለጉት እኮ ሌላ ፖለቲከኛ ድርጅት የሚያስብል ዘገባ ነው ፡፡ የስኳር ልማቱ ለአገር የሚጠቅም ስለሆነ ፣ የዋልድባ ጉዳይ እንዳይነሳ ለማድረግና ጥያቄዎችን ለማዳፈን እንዲለፍፉ ነበር ፡፡ዋልድባ ቢጠፋም አገር ከለማች እንዲባል ነበር የተፈለገው ፡፡ እናም ትንሽ ሆዳችንን የሚያመን ቢሆንም አንዳንዴ እያስነጠሰን እንኳን ቢሆን የሚተርፍበትን መሥራቱ መልካም ነው ፡፡ የአካባቢን መልክአ ምድር መቀየሩ ብቻ ብዙ ለውጥ ፣ ብዙ ችግር እንደሚፈጥር የታወቀ ነው ፡፡ ግን ያሉን አባት ለሾማቸው ተገዥና አስገዥ የሆኑ ፣ የራሳቸው ምቾትና ጌጣ ጌጥና አልባሳት ላይ ያተኰሩ ፣ ታላቅ የሚባል ስምን የሚሹ አቡነ ጳውሎስ ናቸው

   Delete
  2. Well said. But God help us. It is very difficult for us to lose a monastery like WALDEBA. May God Speak the devil out of those who have thought about this all thing in the first place!! May God give consciousness to EPRDF leader,PM.MELES and Abune Paulos in all the devil they are doing to the Ethiopian people both Muslims and Christians.
   May God Help Us Speak and Live The Truth!!!

   Delete
 11. From the report I can see that the project crossed the boundary. But I don't think MK suggested the right thing at all. They seem very careful which more than they should be.
  At all I am not happy about what they suggested but I am happy that I got the right information.
  Now it is time that we pray strongly for our Monastery. It looks that we don't have anyone but God.

  ReplyDelete
 12. tiru new gin betilket alikerebem. yetedibesebesu negerocch alu.

  ReplyDelete
 13. Ewnetun mezegebachew tiru sihone neger gin akwamachew tiru aymeslegnim.

  ReplyDelete
 14. Thanks God! As I think the report tells us the right information. However, our Association seems frustrated for its further sevices. Living with frustration always may not sustain our association life but rather with the will of God. "Don't be dependant totally on your wisdom" said the bible. You should have been told us at least its social impact on monks life. This is what is expected from experts and sprituals. We all aside of You!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 15. sile reportu enameseginachihualen MK asteyayet sechiwoch yesetachihut asteyayet hulum tikil new kerasachi iyyita yemahiberu akkahed gin tibebawi yetemolabet silehone lamseginachihu ewodalehu yekesashochin /bete tekinetochin/afi yemiyazeganew new kezih behala yegna dirsha new yemikerew `medawum feresum` yehewu ...........wanawu neger betselot mebertat ena sile mebtachin menager yalebin egna nen hulunim akal yibeltun degmo bete tekinechin or bete tekulawochin hulunim sayihon tekulawochun

  ReplyDelete