• (ሰበር ዜና) ማኅበረቅዱሳን ከሠንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መመረያ ሰር መመራቱ ቀርቶ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ቤተክህነቱ ሥራአስኪያጅ እንዲሆን ተወሰነ፡፡
• የተሃድሶ አራማጅ ድርጅቶች ተወገዙ፡፡በህግም ይጠየቃሉ፡፡
• መ/ር እንቁ ባህርይ ተከስተ ጉዳይ እንደባለፈው ጥቅምቱ ሲኖዶስ ተደባብሶ ታለፈ፡፡
(አንድ አድርገን ግንቦት
15 ፤ 2004ዓ.ም )፡- በዛሬ ጠዋት በትናንቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በተወሰነው መሰረት በማኅረቅዱሳንና በማደራጃ መምሪያው ስለተፈጠረው ችግር መላእከ ጽዮን ቆሞስ አባ ሕሩይ ወንድይፍራውና የማኅበሩ አመራሮች ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው እንደሚያስረዱ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም ምልዓተ ጉባኤው የማኅበሩን አገልግሎት እያደናቀፈው ያለው የመምሪያው ማኅበሩን የመምራት አቅም ማነስ በመሆኑ ማህበሩ ለጠቅላይ ሥራአስከያጁ ተጠሪ እንዲሆን ወስኗል፡፡
የተሃድሶ አራማጅ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በተመለከተ በማሕበረቅዱሳን በኩል መረጃዎች ቀርበው፣ የሊቃውንት ጉባኤ አጣርቶ፣ ለሊቃነ ጳጳሳት ኮሜቴ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት ቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበራቱን አውግዟል፡፡በህግ እንዲጠየቁም ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡
የማኀበራቱ ስም
1. የእውነት ቃል አገልግሎት
2. የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር
3. አንቀጸ ብርሃን
4. የምሥራች አገልግሎት
5. ማኅበረ በኵር
6. ማኅበረ ሰላማ
በግለሰቦቹም ላይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተመሳሳይ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን!
AMEN
ReplyDelete